TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት አጽድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአቶ ተመስገንን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማጽደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / etv ዘግቧል። …
#NewsAlert
አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ሹመት አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።
@tikvahethiopia

ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመትን አጽድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል።

Photo
#Update
" ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል
በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት ግቢ እንዲቀይርላቸው ጠይቀዋል።
በኮሌጁ የጸጥታ ችግር አለ የሚል መረጃ ደርሶናል እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የኮሌጁ ሁነኛ አካል ፣ " ተማሪዎቹ የነገሯችሁ #እውነት ነው። ችግሩ ተፈጠረ፣ ግቢው ተደበደበ። ተማሪዎች ወጡ " ሲሉ አረጋግጠዋል።
በተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፤ " ተማሪዎች ላይ የደረሰ #ጉዳት የለም። ከግቢው ገቡ፣ ከዚያ ተኩስ ተጀመረ፣ ከዚያ #ቦምብ አፈነዱ፣ ጥይት ተተኮሰ " ሲሉ አስረድተው፣ " ‘ተማሪዎች መውጣት አለባችሁ የሚል ነገር ተናገሩ እነርሱ (ታጣቂዎቹ) " ብለዋል።
ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ከግቢ መውጣት እንዳለባቸው ይህን ካላደረጉ ግን በቀጥይ እርምጃ እንደሚወስዱ እንዳስጠነቀቁ ገልጸዋል።
የሴቶች ብሎክ 1 እና 3 ሕንጻ የተወሰነ በታጣቂዎች መመታቱን የገለፁ ሲሆን " ተማሪ ግን #አልጎዱም " ብለዋል።
" ተማሪዎች ላይ ታርጌት አላደረጉም ሕንጻውን ነው የደበደቡት። ቦምቡ ደግሞ ከተማሪዎች ወደ ካፌ መሄጃ በኩል እዚያው ከግቢው ውስጥ ፈንድቷል። የፈነዳበት ቦታ ይታወቃል " ሲሉ አክለዋል።
ተኩስ የከፈቱት ታጣቂዎች ፍላጎታቸው ምንድን ነው ? ለሚለው ጥያቄ እኚሁ ግለሰብ " ‘ዩኒቨርሲቲ በቃችሁ፣ ከመጀመሪያውስ ለምን መጣችሁ?’ እያሉ ሲናገሩ ነበር " ያሉ ሲሆን " ‘አሁንም ግቢውን ለቃችሁ ውጡ። ዛሬ አንጎዳችሁም። ቀጣይ ግን ስንመጣ ብናገኛችሁ ቀጥታ እርምጃ እንወስዳለን’ የሚል እንድምታ ነበር ብለዋል።
በግቢው አጠቃላይ ከ1,500 እስከ 2,000 ተማሪ የሚገኝበት ሲሆን ከትላንት ጠዋት ጀምሮ #አብዛኞቹ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ተናግረዋል።
" ወደ ቤት የሚሄዱ አሉ (ምክንያቱም በጣም ጭንቅ ነበር በተለይ ሴቶች፣ ሌሊትም #ሲያለቅሱ ነበር) ዘመድ ጋ ወደ ከተማ የሚጠጉም አሉ። #ሆቴል ይዘው ያደሩ ልጆችም አሉ። ቤተሰብ ሩቅ የሆነባቸው፣ ገንዘብ የሌላቸው ተማሪዎች አሉ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለው በጭንቀት " ሲሉ የሁኔታውን አሳሳቢነት አስረድተዋል።
ታጣቂዎቹ ወደ ካምፓሱ ሲገቡ ጥበቃዎች አልነበሩም ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ ፣ " የእኛ ካምፓስ አዲስ ስለሆነ አጥር የለውም። በዙሪያው ጥበቃዎች አሉ። ግን ጥበቃዎች በኮማንድ ፓስቱ ምክንያት መሣሪያ አይዙም። መሣሪያ ቢይዙም የመጣው ኃይል በጣም ብዙ ነው " ብለዋል።
የተማሪዎቹ ፍላጎትስ ምንድነው ? ለሚለው ጥያቄም፣ " ተማሪዎች መማር ይፈልጋሉ። ምክንያቱም በኮሮና ጊዜ፣ በጦርነት ምክንያት አማራ ክልል ላይ ብዙ ታሹ። አብዛኛው ተማሪ መማር ይፈልጋል፣ ግን ደግሞ ከሕይወት የሚበልጥ ነገር የለም " የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።
የካምፓሱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በጉዳዩ ዙሪያ ረቡዕ ጥር 29 ቀን 2016 ዓ/ም አስቸኳይ ስብሰባ እንደነበራቸው፣ በዚህም " በጥበቃ (በመከላከያ) ተጠብቀው ይማሩ ወይስ ሌላ ግቢ እናመቻችላቸው ? " በሚለው ጉዳይ እንደተወያዩና ውሳኔው ግን እንዳልታወቀ ተመላክቷል።
መረጃው የተዘጋጀው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#ETHIOPIA
ላለፉት 12 ዓመታ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ባገለገሉት አቶ ደመቀ መኮንን ምትክ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ዛሬ ተሹመዋል።
ጎጃም ብቸና ተወልደው ያደጉት አቶ ተመስገን በርካታ ዓመታትን በደህንነት እና ወታደራዊ ዘርፎች ውስጥ ሰርተዋል።
አቶ ደመቀ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታንም ደርበው ይዘው የነበረ ሲሆን በዚህም ቦታ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
አምባሳደር ታዬ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ኢትዮጵያን ወክለው ያገለገሉ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ከሚባሉ በዘርፉ የረጅም ጊዜ የስራ ልምድ ካላቸውና ስመጥር ከሆኑ ዲፕሎማት አንዱ ናቸው።
የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸው ተሸኝተዋል።

#NewsAlert ዶክተር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ። 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ15ኛ መደበኛ ስብሰባው የዶክተር መቅደስ ዳባ ሹመትን አጽድቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶክተር መቅደስ ዳባን የሥራ ልምድ ዘርዝረው ለምክር ቤቱ ባቀረቡት መሰረት ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ሹመቱን ማፅደቁን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ዘግቧል። …
#DrMekdesDaba
ዛሬ ዶ/ር ሊያ ታደሰን በመተካት የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶክተር መቅደስ ዳባ እ.ኤ.አ በ2021 በማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ዘርፍ ባደረጉት ምርምር እና አስተዋጽዖ በሴቶች ዘርፍ በዓለም የጽንስና የማኅፀን ፌዴሬሽን ከመላ ዓለም ከተመረጡት ሃኪሞች አንዷ በመሆን የ #FIGO አዋርድ / ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ትውልድ እና እድገታቸው በአዲስ አበባ ሲሆን የተወለዱት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ ነው።
የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን (ከነርሰሪ እስከ 12ኛ ክፍል) በአዲስ አበባ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት ነው የተከታተሉት።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ፤ ልክ እንደጨረሱ በዛው ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አገልግለዋል።
የህብረተሰብ ጤና ማስተርስ ትምህርታቸውንም እዛው ዩኒቨርሲቲ ተምረዋል።
የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተከታትለዋል።
ዶክተር መቅደስ ዳባ በስራው ዓለም በዓለም የጤና ድርጅት (WHO) የምክትል ዳይሬክተር ረዳት ፣ የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዝዳንት ፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በጽንስና ማህጸን ትምህርት ክፍል ውስጥም ሰርተዋል።
ዛሬ በይፋ የኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ቦታ በመተካት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይረክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተሹመዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የዛሬው ሹመት እስኪሰጣቸው ድረስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሆነው እየሰሩ የነበረ ሲሆን ከኢህአዴግ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በስልጣን ላይ የሚገኙ ጉምቱ ባለስልጣን ናቸው።
በሌላ በኩል፤ ትዕግስት ሃሚድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይረክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይጠገብ የመዝናኛ አማራጭ ከዴኤስቲቪ!
ፓኬጅዎን ያሳድጉ የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋቾችን የሻምፕየንስ ሊግ ፍልሚያ እና አዳዲስ ፊልሞችና ሾዎች በዲኤስቲቪ ቻናሎች ይከታተሉ
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia

#Update " ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት…
#Update
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ " ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል " የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንድ ስማቸውን እንዲገለፅ ላልፈለጉ የዩኒቨርስቲው አካል ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
እኚህ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ በትላንት በስቲያ ምሽቱ ተኩስ ተማሪ ላይ ያተኮረ / ተማሪ ላይ ታርጌት ያደረገ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጸዋል።
" ተማሪዎች እንጠራ ብለው በተደጋጋሚ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀዋል። ትምህርት ሚኒስቴርም ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ነው ዩንቨርሲቲው ሊጠራ የቻለው " ሲሉ አስታውሰዋል።
" ዩንቨርሲቲው አሁን ላይ እያስተማረ ነው። ተማሪዎችም ትምህርት ጀምረዋል። በርከት ያሉ ተማሪዎች መጥተዋል። በዚህ መንገድ ደግሞ ተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ነገሮች አሉ። ዩንቨርሲቲው አቅም እስከፈቀደለት ድርስ ትምህርቱን ይቀጥላል። በመካከል ተማሪዎች ለራሳቸው የሚፈሩት፣ የሚሰጉት ነገር ካለ አይገደዱም " ሲሉም አክለዋል።
" ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማንም አይገምትም። ማንም ለማንም ዋስትና መሆን አይችልም። By theway በዚህ ጊዜ ላይ ከባድ ነውና ሁሉም ተማሪ ለራሱ ዲሳይድ ማድርግ መቻል አለበት " ያሉት እኚሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ " ሲመጡም ያንን ተገቢ ግምት ውስጥ ያስገባሉ ተብሎ ነው የሚታሰበው። ተማሪዎች መማር አለብን ብሎ የሚያስብ ከሆነ ማስቀጠል እስከተቻለ ድረስ ይማራሉ " ብለዋል።
አክለውም " ይህንን ዓመት Withdraw ማድልግ እፈልጋለሁ የሚል (ተማሪ) አይከለከልም። ተማሪ በራሱ አምኖበት የሚያደርገው ስለሆነ በዩኒቨርስቲ በኩልም አይጠየቅም " ያሉ ሲሆን " ሁኔታው ግን እስከመቼ እንደዚህ ይቀጥላል ? የሚለው ነገር እንዲህ ነው ብዬ ማለት አልችልም/አላውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።
" የጸጥታው ሁኔታ አጠቃላይ በአገሪቱም፣ በክልሉ አግሪቬት እያደረገ በሄደ ቁጥር ዩኒቨርሲቲዎች ሴንተር ሊሆኑ ይችላሉ። እከባለፉት ዓመታት ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ካየነው ሁኔታ አንጻር፣ ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰቡ ነፀብራቅ ስለሆኑ እዚያ (ውጭ ላይ) የተፈጠረው ነገር እዚህም (ዩኒቨርሲቲ ውስጥ) ይፈጠራል " ብለዋል።
የሁኔታውን አሳሳቢነት በተመለከተ በሰጡት ቃልም፣ " Risk free የሆነ Environment የለንም። ምንም ስጋት የሌለበት ሁኔታ የለም። አሁን ከሚታዩት ነገሮችም አንጻርም፣ ከዚህ በኋላም ማለቴ ነው ፤ Risk free zone ስለሌለን ተማሪዎች መወሰን አለባቸው " ብለዋል።
ተማሪዎች በበኩላቸው " የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ውይይት እያደረጉ ነበር " ቢባልም የመፍትሄ ሀሳብ እንዳልተነገራቸው፣ ቢያንስ ሰላም ወዳለበት ካምፓስ እንዲያዘዋውሯቸው ጠይቀዋል።
ይህን ተከትሎም ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርጋችሁ ? ሲል ጠይቋል።
" እንኳን እንዲህ አይነት ነገር ተፈጥሮ ሁሌም አስቸኳይ ስብሰባ አለ " ሲሉ ገልጸው፣ " ችግር ተፈጥሮ በጉዳዩ ዙሪያ ሳይወራ አይቀርም። ካምፓስ ተቀይሮ የሚመጣ ለውጥ አለ ወይ? Through time long run ምን ይፈጠራል ? የሚለውን analaysis ሲሰራ ካምፓስ መቀየር ዘላቂ የሆነ Problem solve mechanism ነው ? የሚለው ነገር ላይ ያጠራጥራል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለው፣ " እስከመቼ ድረስ ቀይረህ ትችለዋለህ ? ደግሞስ ካምፓስ ተቀይሮ ምን ያህል ይችላል ? አንድ ካምፓስ ምን ያህል ይችላል ? የሚሉት ጉዳዮች አሉ በዚያው ልክ። ለተማሪዎቹ imidate የሆነ መፍትሄ እየተፈለገ ነው። ግን ዘላቂያዊነቱ ላይ ነው ትንሽ ጥያቄ ያለው " ሲሉ አስረድተዋል።
#TikvahFamilyAA

#CRRSA
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፤ በጥር ወር አገልግሎትን በገንዘብ በመሸጥ እንዲሁም ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ኤጀንሲው ፥ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ እንዲሁም ላልተገባ ግለሰብ በገንዘብ አገልግሎት የሰጠ የተቋሙ ሰራተኛ እና ተገልጋዮችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ነው ገለጸው።
ኤጀንሲው በሰጠን ማብራሪያ ፤ የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት #ሰራተኛ የሆነ ተጠርጣሪ 30 ሺህ ብር በመቀበል በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ እና የጋብቻ ሰርትፍኬት ማዘጋጀቱ ተደርሶበር በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የመሸኛ ማስረጃ /Clearance / በ10 ሺ ብር ያዘጋጀውን ግለሰብ ከየካ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በየካ ወረዳ 10 አካባቢ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎታል።
ኤጀንሲው፤ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እና አዲስ ከተማ ወረዳ 9 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆኑ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ በመስጠታቸው በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዚህ ጥር ወር በኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት በተመራው ክትትል እና ኦፕሬሽን ፦
- ሰባት በተቋሙ ስም የተሰሩ ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ ግለሰቦች፣
- ሶስት የተቋሙ ሰራተኞች ፣
- አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ እና አንድ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማሩ በድምሩ 12 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ መቻሉን አሳውቋል።
ኤጀንሲው ፤ " በመዋቅሬ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል በማድረግ ከሌብነት የፀዳ ተቋም ለመገንባት ጥረት እያደረኩ ነው " ያለ ሲሆን ህብረተሰቡ በተቋሙ ስም ከሚያጭበረብሩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
" በተቋሙ ጥቂት ሰራተኞች የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራት በቅንነት እና ታማኝነት የሚያገለግሉ ሰራተኞችንም አይወክልም " ብሎ " በህዝብ የሚታመን አገልጋይ ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ነዋሪው አጋዥ እንዲሆን " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

#Update በትግራይ ክልል የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ከሰዓት በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን ታሪካዊውን የ " አል ነጃሺ መስጂድ "ን ጎብኝተዋል። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም ፤ " ነጃሺ ያለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም ነው፤ የሚለማው ታሪኩም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው " ብለዋል። የፌዴራል መጅሊሱ…
#Update
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመካከል የነበራቸውን ችግር #በይቅርታ ከፈቱ በኃላ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት መልሰዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችም ወደ ትግራይ ተጉዘው በጦርነት የተጎዳውን የአልነጃሺ መስጂድን ጉብኝተው በጦርነት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ላሉ እና በድርቅ ለተጎዳው ህዝብ ድጋፍ ሰጥተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።
የተደረገው ድጋፍ የጥሬ ገንዘብ፣ የመድሃኒትና የእህል ሲሆን የርክክብ ስነ-ሰርዓቱ ዛሬ በመቐለ ከተማ ተከናውነዋል።
ድጋፉ በዝርዝር ምን ይመስላል ?
1ኛ. እህል ➡ 5,700 ኩንታል በቆሎ/እህል ብር 24 ሚልዮን የሚያወጣ።
2ኛ. መድሐኒት ➡ 1 ኮንተይነር 40 ፊት መድሐኒት ብር 40,200,000 ብር የሚያወጣ።
3ኛ. ለአልነጃሺ ትራንስፎርመር ➡ 3 ሚልዮን ብር
4ኛ. ለሌሎች ➡ 1.2 ሚልዮን ብር
ጠቅላላ ብር 67 ነጥብ 2 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለትግራይ ህዝብ መደረጉ ተነግሯል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
ፎቶ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት