TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዜዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የልኡካን ቡድን ዛሬ ትግራይ ክልል፣ መቐለ ገብቷል።

የልኡካን ቡድኑ ፦
- በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች፤
- በትግራይ እስልምና ጉዳይ አመራሮች
- በመቐለ ከተማ ሙስሊም ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎለታል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ ቤት እና በትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት መካከል የነበረውና በጦርነት ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት በቅርቡ በይቅርታ ወደነበረበት እንዲመለስ መደረጉ ይታወሳል።

Photo Credit፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#StockMarket (የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮችን በቅርበት በሚከታተሉት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በአንድ ወቅት ለቢቢሲ ድረገፅ ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ) ስቶክ ገበያ ምንድነው ? ለስቶክ ማርኬት ‘ የድርሻ ገበያ ’ የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ልንሰጠው እንችላለን። ኩባንያዎች የኩባንያውን የባለቤትነት ድርሻ ለገበያ ያቀርባሉ። ሰዎች ይህን ድርሻ ከገዙ በኋላ ኩባንያው ትርፋማ በሆነ መጠን…
#CapitalMarket #Ethiopia

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 ስራ ላይ ውሎ ይገኛል።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን #ሰኞ ጀምሮ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቋል።

በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው አካላት በመመሪያው የተቀመጡትን የፈቃድ መስፈርቶችን በማሟላት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚባል ደረጃ የ " ኢንቨስትመንት ባንክ " ፍቃድ መስጠት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አሳውቋል።

በዚህ ላይ መሰማራት የሚፈልግ መስፈርቶችን የሚያሟላ አካል ቢሮ ድረስ በመሄድ ማመልከቻ ማስገባት ይችላል ተብሏል።

በተጨማሪም ፦

- የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪ ምን ማለት ነው ?

- ማመልከት የሚችለው ማነው ?

- የአገልግሎት ሰጪ ፈቃድ ለማግኘት ዋና ዋና መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

- የማመልከቻ አቀራረብ ሂደቱ ምን ይመስላል ? የሚሉትን ጉዳዮች ከላይ በተያያዘው አጭር ማብራሪያ መመልከት ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢትዮጵያ የካፓታል ገበያ ባለስልጣን ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ይቀላቀሉ »»» https://bit.ly/3RBi8kH

#ግሎባል_ባንክ_ኢትዮጵያ
TIKVAH-ETHIOPIA
የሹፌሮች ጉዳይ . . . " በ2 ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ " - ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር በጅማና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ‘አስጎሪ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲያሽከረክሩ በነበሩ ሹፌሮችና ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ጥቃት ማድረሳቸውን ስሜ ከመጠቀስ ይቆይ ያሉ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ…
#አሽከርካሪዎች 

“ ታጣቂዎች ሌመን አካባቢ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። መረጃው እውነት ነው ”- የዓይን እማኝና ባለስልጣን

“ በ3 ዓመታት ውስጥ 100 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች በወንበዴ ጥይት ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፣ ንብረት በየሜዳው ሲነድ፣ ገዳይን አሳደው ለሕግ ሲያቀርቡ አላየንም ” - የሹፌሮች አንደበት

በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሲከሰት ቢስተዋልም በተለይ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች አማካኝነት “ የገበያ ዕቀባ ” የሚል የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በመግታት፣ በሚንቀሳቀሱ ሹፌሮችና ተጓዦች ግድያ፣ የተሽከርካሪዎች ቃጠሎ በስፋት እየተፈጸመ መሆኑን ባለስልጣን፣ የዓይን እማኝና ሹፌሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

“ ሰሞኑን ከአዲስ አዲስ አበባ ወደ ወላይታ ሶዶ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ የሸኔ ታጣቂዎች ሌመን አካባቢ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ሬሳቸውም ወደ ወላይታ ሶዶ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ተወስዷል ” ሲሉ አንድ የዓይን እማኝ ገልጸውልናል።

የተገደሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንዲያስረዱ ሲጠየቁም፣ “ ታጣቂዎቹ ‘የገበያ ዕቀባ’ በሚል ሰሞኑን ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ አግደው ስለነበር ነው ” ብለዋል።

“ ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ ” መባሉ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሟቾቹ የሚኖሩበት ወረዳ አንድ ባለስልጣን “ ልክ ነው። መረጃው እውነት ነው ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

“ ታጣቂዎች ናቸው የገደሏቸው ” የሚል መረጃ ደርሶናል ይህስ እውነት ነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ “ አዎ በታጣቂዎች ነው። እውነት ነው ” ብለዋል።

አንድ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ሹፌር በበኩላቸው፣ “ መንግሥት የትራንስፖርት አገልግሎት ስጡ ይላል። ታጣቂዎች በገሀድ መንገድ በመዝጋት ሹፌሮችን ይገድላሉ። እዚህ አገር አዛዡ ማነው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ “ ሹፌሮች በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ሆኖባቸዋል። በርካቶች እንወጡ እየቀሩ ነው። መንግሥት ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ የማይሰጠው ለምን ይሆን ? ምን ሰርተንስ ቤተሰብ እናስተዳድር ? ” የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

የአሽከርካሪዎችን ሁኔታ በየወቅቱ በመከታተል የሚታወቀው የሹፌሮች አንደበት በበኩሉ፣ “ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአገሪቱ በ3 አመታት ጊዜ ውስጥ 100 የሚደርሱ አሽከርካሪዎች በወንበዴ ጥይት ሕይወታቸው ሲቀጠፍ፣ ንብረት በየሜዳው ሲነድ፣ ገዳይን አሳደው ለሕግ ሲያቀርቡ አላየንም ” ሲል ወቅሷል።

አክሎም፣ “ ወንበዴን አሳዶ መያዝ፣ አድኖ መቅጣት ያልቻለ ኃይል እና አካል የእንቅስቃሴ እቀባን ተግብረው ከተማ የሚቆሙትን ‘ውጡ’ በማለት አስገድደው ልከው እንዲቃጠሉ አድርገዋል። ሶስት (3) የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸው መረጃ ደርሶናል ” ብሏል።

ለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ያደረገው ሙከራ ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ባይሳካም፣ ኃላፊው ጉዳዩን በተመለከተ ሰሞኑን ለኢፕድ በሰጡት ማብራሪያ፣ “ አሸባሪው ሸኔ የጠራው የገበያ አድማ በሕዝብና መንግሥት የተቀናጀ ሥራ ማክሸፍ ተችሏል ” ብለዋል።

መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በትግራይ ክልል የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ከሰዓት በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን ታሪካዊውን የ " አል ነጃሺ መስጂድ "ን ጎብኝተዋል።

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም ፤ " ነጃሺ ያለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም ነው፤ የሚለማው ታሪኩም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው " ብለዋል።

የፌዴራል መጅሊሱ ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሂም ፤ " ነጃሺ ታሪካችን ብቻ ሳይሆን ምልክታችን ነው እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደቀደመ ቁመናው እንመልሰዋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው ከሀሩን ሚዲያ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#CapitalMarket #Ethiopia በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016 ስራ ላይ ውሎ ይገኛል። በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን #ሰኞ ጀምሮ ለካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ማመልከቻዎችን መቀበል እንደሚጀምር አሳውቋል። በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው አካላት በመመሪያው የተቀመጡትን የፈቃድ መስፈርቶችን…
የኢንቨስትመንት ባንክ ምንድነው ? ከሌሎች ባንኮች በምን ይለያል ?

የንግድ ባንኮች የሚባሉት ፦ በብሔራዊ ባንክ ስር የሚተዳደሩ ፤ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ተሰጥቷቸው የሚተዳደሩ ናቸው።

ኢንቨስትመንት ባንክ ፦ በካፒታል ገበያ አዋጅ መሰረት የሚቋቋም፣ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድ የሚሰጠው ነው። ከግለሰቦች ተቀማጭ የሚወስድ ከሆነ የኢንቨስትመንት ባንክ መሆን አይችልም።

የኢንቨስትመንት ባንኪግ ስራ ምንድነው ?

ዋና ስራው ወደ ካፒታል ገበያ የሚመጡትን ኩባንያዎች፣ ድርጅቶች ፣ መንግስት ፣ ከተሞች ሊሆኑ ይችላሉ ቦንድ መሸጥ ሲፈልጉ ፣ አክሲዮን መሸጥ ሲፈልጉ ፦
* አክሲዮኑ ምን ይመስላል ?
* አክሲዮኑ በምን ያህል ዋጋ ይሸጥ ?
* መቼና ለማን ይሸጥ ? የሚለውን የፋይናንስ ስትራተጂ ላይ የምክር አገልግሎት የሚሰጡና የሚያገናኙ በካፒታል ገበያ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚጫወቱ ናቸው።

ለምሳሌ ፦ አንድ በግል የተያዘ ድርጅት ፤ ወደ ህዝብ ድርጅት ነው መቀየር የምፈልገው ፣ የሼር ኩባንያ ነው መሆን የምፈልገው ብሎ ሼሩን የካፒታል ማርኬት ላይ መሸጥ ቢፈልግ ድርጅቱ ምን ያህል ነው ዋጋው ? ለአብነት ወደ 2000 ሼር ቀይሬ 2 ሺህ ሼር ለገበያው ሸጣለሁ ቢል እያንዳንዱ ሼር ዋጋው ምን ያህል ነው የሚለውን አጠቃላይ ስራ የሚሰራው ኢንቨስትመንት ባንክ ነው።

በተጨማሪ ኢንቨስትመንት ባንክ ፦

* price discovery / ገበያው ላይ ኩባንያዎች ያላቸው እውነተኛ ዋጋቸው ምንድነው የሚለውን ያጣራል።
* የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ያማክራል።
* የካፒታል ብክነት እንዳይኖርና ካፒታል ወደአስፈላጊው ቦታ እንዲሄድ ያደርጋል።

ኢንቨስትመንት ባንኮች እንደ ሌሎች የንግድ ባንኮች ከሰዎች ላይ ተቀማጭ ገንዘብ / deposit አይወስዱም።

የኢንቨስትመንት ባንኮች የማማከር ስራን የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ ኩባንያዎች የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ለመግባት ሲወስኑ ኩባንያውን ማዛጋጀት፣ ሼሩ ምን ያህል ነው የሚለውን መለየት ፣ ምን ያህል ሼር ለምን ያህል ሰው የሚለውን መለየት ስራዎችን ይሰራሉ።

የካፒታል ገበያውን የሚቆጣጠረው አካል ፤ በካፒታል ገበያው ለሚሳተፉ አካላት ፍቃድ ከመስጠት እና ሂደቱን ከመቆጣጠር ባለፈ ኢንቬስተሮች በየትኛው ዘርፍ መሳተፍ አለባቸው የሚለውን አይወስንም ሃሳብም አይሰጥም ፤ ይህን የሚያደርጉት የአዋጭነት ትንተናዎችን በመስራት የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።

ማማከር፣ ኢንቬስተሮችን እና ተፈላጊ የፋይናንስ ሃብት ማገናኘት የኢንቨስትመንት ባንኮች ስራ ይሆናል። የካፒታል ገበያ ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶችን ወክለው ከሰነደ መዋዕለ ነዋይ ገበያው ሆነ ከተቆጣጣሪ መ/ቤቱ ጋር በመሆን ብዙ ስራዎች ይሰራሉ።

ለኢንቨስትመንት ባንክ መስረታ የሚጠየቀው ካፒታል ለንግድ ባንኮች ከሚጠየቀው #ያነሰ ነው።

የንግድ ባንኮች በዚህ ላይ መሳተፍ ይችላሉ ?

አሁን በኢትዮጵያ ስራ ላይ ያሉ የንግድ ባንኮች ጎን ለጎን የኢንቨስትመንት ባንክ ተሳትፎ የሚያደርጉበት እድል አላቸው።

እንደ ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን መረጃ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መስፈርቱን ለሚያሟሉ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ መስጠት የሚጀምር ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ያሉና ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ባንኮችም የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠብቅ ተስፋ ተደርጓል።

Credit ፦
#DrBirukTaye (ECMA Director)
#SirakSolomon (ECMA Senior Legal Advisor)
#YohanessArega (ECMA Senior Advisor)
#WuberstTessema (Journalist , FBC)

ዝግጅት ፦ #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
" ወይ የሆነ መፍትሄ ተወስዶ እንዲቆዩ አልተደረጉ ፤ ከሄዱ ደግሞ በስነሥርዓት እንዲሸኙ ማድርግ ይገባ ነበር " - ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ዶክተር (በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሌክቸረር)

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፤ ትላንት ምሽት 2:45 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው እንደነበር አንድ በተቋሙ ውስጥ በመምህርነት የሚሰራና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ዶክተር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

" ከሰሞኑን በዩኒቨርሲቲው ጥሪ ተማሪዎች ገብተው ነበር " ያለው ይኸው ዶክተር ፤ ትላንት ምሽት በተማሪዎች ዶርም አካባቢ ታጣቂዎች ገብተው ከባድ ተኩስ ከፍተው ነበር ብሏል።

" የተማሪዎች ዶርም አካባቢ ነው ከባድ ተኩስ እና ፍንዳታ የነበረው ፤ እኔ በወቅቱ ለሪሰርች ስራ ላይብረሪ ነበርኩ ፤ ተኩሱና ፍንዳታው የተሰማበት ትክክለኛ ሰዓት ደግሞ ምሽት 2:45 ላይ ነው " ሲል ገልጿል።

" በኃላ ላይ ስንጠይቅ ታጣቂዎቹ ተማሪዎቹን ' እኛ እናተን ልንጎዳ አይደለም ግን ከነገ ጀምሮ ግቢውን ለቃችሁ እንድትወጡ ስለምንፈልግ ነው ' ብለዋቸዋል " ያለው ዶክተሩ ፤ " የነበረው ተኩስ ከ10 ደቂቃ በኃላ ከቆመ በኃላ እኛም ከላይብረሪ ወጥተን ወደየቤታችን ገባን " በማለት የትላንት ምሽቱን ሁኔታ አስረድቷል።

" ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ ተማሪዎች ሲሄዱ ነበር ፤ ይሄን መረጃ ለእናተ በምሰጥበት ወቅት (ከሰዓት ላይ) ብዙ ተማሪ ሻንጣውን ጭኖ ፣ እየጎተተ እየወጣ ነው " ሲል የገለፀው ዶክተሩ ፤ " እኔ እንዳየሁት አስተዳደር አካባቢ ያሉ ሰዎችም አላነጋገሯቸውም ፤ ተማሪዎቹ ሰብሰብ ብለው ነው በራሳቸው ሲሄዱ የነበሩት፤ ከስንት ጊዜ በኃላ እድሜያቸው እንዳይሄድ ብለው ለመማር የመጡ ተማሪዎች ወይ የሆነ መፍትሄ ተወስዶ እንዲቆዩ አልተደረጉ ፤ ከሄዱ ደግሞ በስነሥርዓት እንዲሸኙ ማደርግ ይገባ ነበር " ብሏል።

" ተማሪዎች በዚህ መንገድ ከግቢ መውጣታቸው በጣም ስላሳሰበኝ ነው ይሄን ለናተ የምናገረው ፤ ትላንት ማታ ላይብረሪ ውስጥ የነበሩበት ሁኔታ አሳዛኝ ነበር ፣ ሲያልቅሱ ነበር ፤ አንዳንዶቹ ድምፅም ሰምተው የሚያውቁ አይደሉም ብቻ ያሳዝናል " ሲል ገልጿል።

በህክምና ኮሌጁ ሌክቸረር የሆኑት እኚህ ዶክተር ፤ " ለተማሪዎች ስነልቦና የሚያነጋግራቸው አካል ሊኖር ይገባ ነበር ፣ ተረጋጉ የሚላቸው አካልም መኖር ነበረበት ፤ ከጥዋት ጀምሮ ይሄን መረጅ እስከሰጠሁበት ሰዓት ያነጋገራቸው አካል የለም ፤ የግቢ ጥበቃዎችም መሳሪያ ተነጥቀናል ምንም ማድረግ አልቻልንም ነው የሚሉት ፤ ብቻ ተማሪዎቹ መፍትሄ ቢፈልጋላቸው " ሲሉ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዩኒቨርሲቲው በኩል ስለጉዳዩ ምን አይነት ምላሽ እንዳለ ለማወቅ ጥረት አድርጓል፤ ነገ ጥዋት ይቀርባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ከስራ የታገድኩበትን የኢየሱስ ይመጣል ስብከት ወደፊት በስፋት የምሰራበት ጊዜ ይመጣል ፤ አሁን ግን ጊዜው ህዝብን የማገልገያ ነው " - ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ

ከወራት በፊት የደንብ ልብስ በመልበስና የፖሊስ መኪና በመያዝ  " ኢየሱስ ይመጣል !! " በሚል ሃይማኖታዊ ቅስቀሳ እና ስብከት በማካሄዳቸው ከስራ የታገዱት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ እግዱ ተነስቶላቸው ወደስራዉ መመለሳቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ዛሬ ምሽቱን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኢንስፔክተር ተሰፋዬ ደምሴ ፤ አሁን ላይ ፍጹም ደስታ ውስጥ መሆናቸዉን በመግለጽ ባሳለፏቸዉ ጊዜያት በጸሎት እና በተለያየ መልኩ ከጎናቸዉ ለነበሩት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢንስፔክተሩ " የክልሉ አመራር መክሮ እና ይቅርታዬን ተቀብሎ ወደስራ ስላስገባኝ አመሰግናለሁ " ያሉ ሲሆን " ሙስሊም ክርስቲያን ሳልል በቅንነትና በትጋት ለማገልገል ዝግጁ ነኝ " ብለዋል።

" ከስራ የታገድኩበትን የኢየሱስ ይመጣል ስብከት ወደፊት በስፋት የምሰራበት ጊዜ ይመጣል " ያሉት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ " አሁን ግን ጊዜው ህዝብን የማገልገያ ነው " ብለዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ  ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አሜሪካ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸው።

ማክሰኞ ጥር 28 / 2016 ዓ/ም በአሜሪካ የነበራቸውን አገልግሎት አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱም በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከደረሱ በኃላ ወደ #ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው ዛሬ ወደ አሜሪካ ለመመለስ ተገደዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከተው የመንግስት አካል የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ  የሥራ ኃላፊና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ  መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ አገር እንዲገቡ  እንዲፈቀድላቸው እንዲያደርግ ብትጠይቅም የመፍትሄ ምላሽ ባለመገኘቱ ወደ መጡበት አሜሪካ ተመልሰዋል።

መንግሥት እስካሁን ስለጉዳዩ የሰጠው ማብራሪያ የሌለ ሲሆን በቀጣይ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia