TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ ዛሬ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ለሶስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር።

ሰልፈኞቹ በጋራ ከሚኖሩበት ሰፈር በሰልፍ በመውጣትና በመቐለ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ፦
- የተገባልን ቃል ይተግበር !!
- አጉል ተስፋ ይብቃን!!
- ከአግባብ ውጪ ከወርሃዊ ራሽናችን መቁረጥ ይቁም !
- በሰውነታችን ውስጥ ያለው ብረት አውጡልን ! የሚሉ መፈክሮች አሰምተዋል።

የጦርነት አካል ጉዳተኞች ዛሬ በመቐለ ከተማ ያካሄዱት ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት መልስ እንዲሰጡ የመቐለ 104.4 ኤፍኤም ሬድዮ ጣብያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ናስር መምሑር ፤ " የጦርነት አካል ጉዳተኞቹ ያቀረቡት ጥያቄ በዝርዝር ለመስማትና ችግሮቻቸው በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ ያለው ስራ በማስመልከት ለመወያየት ኮሚሽኑ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ነገ ወደ መኖሪያ ካምፓቸው እንሄዳለን " ብለዋል።

" የአካል ጉዳተኞቹን ጥያቄዎች በስፋትና በጥልቀት በማድመጥ መፍትሄ እናስቀምጣለን " ሲሉ አክልዋል።

መረጃውን የመቐለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከው።

ፎቶ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ
                
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Haile

" ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " - ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ

ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በጸጥታ ችግር ስለወደመው ሆቴል ሁኔታ እና በጎንደር  ከተማ በሚገኘው ሪዞርት በኩል በጸጥታ ችግር የገጠማቸውን የገቢ መቀዛቀዝን በተመለከተ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሆቴል ምረቃ መርሀ ግብር በተገኙበት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ክልል በጸጥታ ችግር የወደመባቸውን ሆቴል በተመለከተ ባደረጉት ገለጻ፣ እስካሁን መንግሥት መንግሥት ካሳ እንዳልከፈለና አሁንም ይከፍላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ነው የተናገሩት።

" ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " ያሉት ሻለቃ ኃይሌ፣  የሻሸመኔው ሆቴልም በቀጣይ ከሚመረቁት ሆቴሎችና ሪዞሮቶች መካከል አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።

ከሻሸመኔው ሆቴል ውድመት ባሻገር በመከላከያና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየወቅቱ የጸጥታ ችግር በሚስተዋልበት አማራ ክልል ጎንደር ከተማ ሪዞርታቸው ሲያገኝ የነበረው የገቢ ምንጭ መቀዛቀዙን ገልጸዋል።

ሻለቃ ኃይሌ፣ ከጎንደር ከተማ ሪዞርት በዓመት ከሚገኘው ግማሽ ያህሉ ገቢ በጥምቀት ወቅት ይሰራ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የገቢ መቀዛቀዝ እንዳጋጠመ ሲገልጹ ተደምጠዋል። 

መረጀውን የላከው በመርሀ ግብሩ የተገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#StateofEmergency

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ልዩ ስብሰባ ይቀመጣል።

በዚህም ስብሰባው በዋነኝነት በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱም በመላው ሀገሪቱ እንዲፈፀም ለ6 ወራት ታውጆ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

የምክር ቤት አባላት ዛሬ ከመሸ ለነገው ልዩ ስብሰባ " አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማረዘም " የሚለውን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች እንደተላከላቸው ተነግሯል።

የተወካዮች ምክር ቤት በዋነኛነት በአማራ ክልል ተፈጻሚ እንዲሆን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያጸደቀው ነሐሴ 8/2015 ነበር።

ለ6 ወራት የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቀነ ገደብ በዛሬው ዕለት በመጠናቀቁ ነገ ም/ቤቱ በ " ልዩ ስብሰባ " አዋጁን ያራዝመዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህን መረጃ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የምክር ቤት አባላትን ዋቢ በማድረግ ነው ያሰራጨው።

@tikvahethiopia
“ ኑሮ ከብዷት ነው ! ”

ኑሮ ከብዷቸው ራሳቸውን ለማጥፋት ትልቁ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ የወጡ አንዲት እናት በሕይወት ተረፉ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጫው ካሬ ቀበሌ ወይሶ ሰፈር ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም፣ ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት  ወ/ሮ ሂሩት በቀለ “ራሳቸውን ለማጥፋት” ረጅሙ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ታወር ጫፍ ላይ ወጥተው እንደነበር ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከወረዳው ባለስልጣን ማረጋገጥ ችሏል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት በክልሉ ወላይታ ሶዶ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን አስራት ፣ “ ማክሰኞ ዕለት (ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም) የመብራት ፖል ጫፍ ላይ ወጥታ፣ አውቶማቲክ ስለሆነ በራሱ ጊዜ ዘጋና ጠቆማ ሰጠን (ሰው ወደ ላይ እየወጣ እንደሆነ)፣ ከዚያ ከወረዳ ቲም ተዋቅሮ ፓሊስ፣ የወረዳው አመራርና የቀበሌ አመራር አንድ ላይ በመሆን ወደ ስፍራው ደርሰው ሴትዮዋ ጋ ሲደርሱ ጫፍ  ላይ ወጥታ ነበር ” ብለዋል።

“ አንድ ላይ በመሆን እንድትወርድ ሰዎች ለምነው ነበረ፣ ‘አልወርድም’ ብላ በጣም አስቸግራ ነበር” ያሉት አቶ ተመስገን፣ “ሌሎቹ ሰዎች ተደብቀው ፓሊስ፣ የሴትዮዋ እናትና አባት አንድ ላይ ሆነው በመለመን ወረደች ” ሲሉ አስረድተዋል።

ወ/ሮ ሂሩት እንዲህ ያደረጉት ለምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ተመስገን፣ “ ኑሮ ከብዷት ነው። የሁለት ልጆች እናት ናት። ኑሮ ከብዷት ከባለቤቷ ሁሉ ተጣልታ ከቤተሰቦቿ ጋ ነች። እናትና አባቷ ጋ ሆና ነው ይሄ ክስተት የተፈጠረው ” ብለዋል።

ሴትዮዋ ሕመምተኛ ስለሆኑ ከወረዱ በኋላም ሶዶ ኦተና ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው ለጊዜው በወላይታ ሶዶ የሚገኘው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

አፖሎ ካለ "ኢንተርኔት ተቋርጦ ገንዘብ መላክም መቀበልም አልቻልኩ" ማለት የለም።
*685# በመደወል አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#AddisMayaPlayschool

We are registering!
1 to 4 years
Tel: 0906929258 / 0906839358
Email: [email protected] website:https://www.addis-maya.com/

Address : Bisrate Gebriel , Around Ireland Embassy (Residence)
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር : -

1ኛ. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣

2ኛ. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣

3ኛ. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን በፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ መሰረት መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ ማዘጋጀቱን ጠቁሟል።

በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት መስጠት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተራዘመ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አንደኛ ልዩ ስብሰባው በአማራ ክልል የታወጀውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ አራት ወራት  አራዝሞታል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሁለት ተቃውሞ በሶሰት ድምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ለአራት ወራት የተራዘመው።

@tikvahethiopia
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
Forwarded from Ethio telecom
ድንገተኛ ወጪ አጋጥምዎት፣ ገንዘብ አስፈልግዎታል?

ቴሌብር አለ!

ከጓደኞችዎ እና ከቤተሰብዎ ወዲያውኑ በቀላሉ ገንዘብ በቴሌብር ይጠይቁ እና ይቀበሉ።

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
“ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” - የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ጤና ባለሞያዎች ወደሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

“ የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲልም አመልክቷል።

የቢሮ የፈውስና ተሃድሶ ዋና የሥራ ሂደት ስምኦን ገ/ፃዲቅ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ የጤና ባለሙያዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እየፈለሱ ነው ” ብለዋል።

አሁን ‘ሁሉም ነገር ወደነበረበት ተመልሷል’ በሚባልበት ሁኔታ መቋቋም እንኳ ስላልቻሉ የፈለሱ የጤና ባለሙያዎችን በቁጥር ለመግለጽ ለጊዜው ባይቻልም አዲስ አበባን ጨምሮ የተሻለ ክፍያ ወዳለባቸው ሌሎች የውጪ አገራት ጭምር እየፈለሱ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ስምኦን (ዶ/ር)፣ ለሠራተኞች ፍልሰት ምክንያቱ ፦
* የ17 ወራት ደመወዝ፣
* የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ መሆኑን ገልጸው፣ “ደመወዝ አልተከፈላቸውም ማለት የዕለት ተዕለት ወጪ መሸፈኛ የቤትን ኪራይን ጨምሮ ሲቆይባቸው ነው የቆየው ” ብለዋል።

“ሌላውን ትተን የቤት ኪራይ እንኳ መክፈል አልቻሉም። አሁን የተበጣጠሰ የደመወዝ ክፍያ ቢኖርም በተጨማሪ ደግሞ የትርፍ ሰዓት ክፍያ የላቸውም” ያሉት የሥራ ሂደት ተተኪው፣ “የጤና ተቋማት የሥራ ማስኬጃ በጀት ይመደብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ይሄ የለም ” ሲሉ የሁነቱን አሳሳቢነት አስረድተዋል።

“ ጤና ቢሮ፣ የክልል መንግሥትም ከፌደራል መንግሥት በሚያገኘው የደመወዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ ብቻ ሳይሆን የጤና ተቋማት የመድኃኒት መግዣና የሌላ ሥራ ማስኬጃ በጀት ይመድብላቸው ነበር በአሁኑ ሰዓት ይሄ የለም” ብለዋል።

ዶ/ር ስምኦን አክለውም፣ “መበጀት የነበረበት ያለፈው የ17 ወራት ደመወዝና ጥቅማጥቅም፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳለ ሆኖ ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ደመወዝ መከፈል ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ ያለውም የተበጀተ በጀት የለም” ነው ያሉት።

በመሆኑም ከፌደራል መንግሥት ጀምሮ ያለው ሁሉም የሚመለከታቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ሁሉ እየፈለሱ ያሉት የጤና ባለሙያዎች በቦታቸው እንዲቆዩ ለማድረግ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚጠባ ተጠይቋል።
 
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከምን ደረሰ ?

" ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ መንገድ ይጠርጋል " የተባለው የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌለንድ ጋር ከተፈረመ ትላንት 1 ወር አልፎታል።

የመግባቢያ ስምምነቱ እኤአ ጥር 1 ነበር የተፈረመው።

ይህ ስምምነት በተፈረመበት ወቅት በመንግሥት ባለስልጣናት በኩል በተሰጡ ገለፃዎች ፦

* በ1 ወር ውስጥ የስምምነቱ ዝርዝር ይፋ እንደሚደረግ፤

* ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ እንደሚገባ ተነግሮ ነበር።

እስካሁን ቀጣይ የስምምነቱን ምዕራፎች በተመለከተ / ሂደቱ ምን ላይ እንደደረሰ በይፋ የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

ከጥቂት ቀናት በፊት በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ ተወካይ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ጉዳዩን ለማጠናቀቅ ከሁለቱም ወገኖች የቴክኒክ ኮሚቴ በማዋቀር ላይ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።

የስምምነት ፊርማውን ትከትሎም ግንኙነቶች እንደነበሩ፤  የሶማሌላንድ የውጭ ጉዳይ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትርም ጉዳዩን ለማሳለጥና መሰረት ለማስያዝ ኢትዮጵያ ቆይተው መመላሳቸውን ተናግረው ነበር።

የሶማሌላንድ ተወካዩ አምባሳደር አብዱላሂ ሞሀመድ ፤ ይዋል ይደር እንጂ ሁለቱ ኮሚቴዎች ወደ ስራ እንዲገቡ እንደሚደረግ ፤ ይህ በጣም በቅርቡ እንደሚከናወን አመልክተው ነበር።

ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የዛሬ 1 ወር ኢትዮጵያን የባህር በር እንድታገኝ የሚያስችል ፤ ሶማሌላንድ ደግሞ ሉዓላዊ ሀገር እንደሆነች እውቅና ልታገኝ የምትችልበትን ዕድል ይፈጥራል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው እንደነበር ይታወሳል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ የሰነበተ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል መቃቃርን ፈጥሯል ይህ መቃቃር እስካሁን ያልተፈታ ሲሆን በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ በኩል የስምምነቱ ቀጣይ ሂደት በ1 ወር ውስጥ ያልቃል ፣ ዝርዝሩ ይፋ ይደረጋል ቢባልም እስካሁን ስለጉዳዩ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia