TIKVAH-ETHIOPIA
#ግብፅ #ሱማሊያ በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል። ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል። የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች። ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት…
የግብፁ መሪ ምን አሉ ?
የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል።
" ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር አትፈቅድም " ሲሉ የተናገሩት አልሲሲ ፤ " የግብፅ ሃያልነት ወንድማማች የሆነ ሀገሮች ላይ ስጋት በመፍጠር መሞከር የለበትም ፤ አትፈታተኑን " ብለዋል።
" ግብፅን አትሞክሩ ፤ የግብፅ ወንድሞች የሆኑ ሀገራት ላይም ስጋት ለመሆን አትሞክሩ " ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ጥያቄ ከቀረበልን ጣልቃ እንገባለን ሲሉ ተናግረዋል።
የግብፁ ፕሬዜዳንት ፤ " በተለይ ወንድማማች ሀገሮች ከጎናቸው እንድንቆም በሚጠይቁን ጊዜ ለመቆም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " ግብፅ በአንዱ አረብ አገር ላይ ጥቃት ቢሰነዘርበት ለመደገፍ ዝግጁ ነች " ሲሉ ተደምጠዋል።
ፕሬዝዳንት በንግግራቸው #የኢትዮጵያንም 🇪🇹 ስምን አንስተው ሲናገሩ ነበር።
አልሲሲ ፤ " ለኢትዮጵያ ያለኝ መልዕክት የሶማሊያን አንድን መሬት ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት አይሳካም በዚህ የሚስማማም የለም " ብለዋል።
የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነት በግብፅም በሶማሊያም ዘንድ ተቀባይነት የለውም ፤ ጣልቃ እንድንገባ ከተጠየቅን ደግሞ በሶማሊያ ላይ የሚፈጸም የሉዓላዊነት እና ግዛት አንድነት ጥቃትን ለመመከት ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል።
ግብፅ ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ እድል ይፈጥራል የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌላንድ ጋር በፈረመች በማግስቱ ነው ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ በማለት ተቃውሞ ማሰማት የጀመረችው።
_________
" ግብፅ እና አረብ ሊግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው "
ኢትዮጵያ ከሰሞኑን አረብ ሊግ ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ምላሽ በሰጠችበት ወቅት ፤ " ግብፅ እና አረብ ሊግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው " ስትል ነው የገለፀችው።
" ይህ ድርጅት በማን እንደሚዘወር ይታወቃል " ያለችው ኢትዮጵያ የወጣው መግለጫ ተቋሙንም አባል ሀገራቱንም የሚመጥን እንዳልሆነና የማን ድርጅት እንደሆነም እንደሚታወቅ ገልጻለች።
በግብፅ እና አረብ ሊግ መካከል ያለው ግንኙነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ተደርጎ እንደሚወሰድና ምንም ልዩነት እንደሌለው በግልፅ መናገር እንደሚያስፈልግ ይሄን ደግሞ ወጣቱ ትውልድም እንዲያውቀው መደረግ እንዳለበት አስገንዝባለች።
ከሰሞኑን የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር " ኢትዮጵያ ለቀጠናው ያለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " ብለው ለተናገሩት ንግግር በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተሰጠ ምላሽ ፤ ኢትዮጵያ ለአካባቢው የመረጋጋት መንስኤ እንደሆነችና ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ #ቧልት / የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ እንደሚችል መገለፁ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

" የባሕር በር ጉዳይ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው " - ኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? " ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ከዓላማው ውጪ የሆኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ተሰራጭተዋል። የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን…
#ኢትዮጵያ🇪🇹
" ... ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ #አንዳንድ_ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ?
- ኢትዮጵያ ለሶማሊያ #ሰላም እና #ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ #ደም እና #ላብ በግልፅ አሳይታለች።
- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድንበር ተጋርተው የሚኖሩ ጎረቤቶች ብቻ ሳይሆኑ የጋራ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል እና ህዝብ የሚጋሩ ወንድማማች ሀገራት ናቸው።
- ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የሚያስተሳስሩ ጉዳዮች ጠንካራ ናቸው ፤ እጣ ፈንታችን የማይነጣጠል ነው።
- ከሶማሌላንድ ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ለኢትዮጵያ የንግድ ግንኙነት የሚሆን የባህር አገልግሎት የሚሰጥ የትብብር እና አጋርነት ስምምነት ነው። ስምምነቱ በየትኛውም ሀገር ላይ ሉዓላዊነትን የሚጥስ / የሚገዳደር / በግዳጅ የየትኛውንም ሀገር ሉዓላዊነት የሚረግጥ አይደለም።
- እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ አንዳንድ ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ያነሳሳቸው ለሶማሊያ ያላቸው ወዳጅነት ሳይሆን #ለኢትዮጵያ_ያላቸው_ጥላቻ / የጠላትነት ስሜት መሆኑ ግልጽ ነው።
- እነዚህ ተዋናዮች አጀንዳቸው የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ፣ መረጋጋት እና ደህንነት አይደለም። ሊዘሩ የፈለጉት #አለመግባባት እና #ትርምስን ነው። እየታየ ያለው ነገር ውጥረት የሚያባብስ እንዲሁም ደግሞ አጋጣሚውን ለመጠቀም ለሚፈልጉ የውጭ ተዋናዮች ፍላጎት ብቻ የሚያገለግል ነው።
- ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመስረተ ሁሉን አቀፍ ቀጠናዊ ትስስርን ለመፍጠር ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር በትብብር መንፈስ ለመስራት እየጣረች ነው።
- ኢትዮጵያ ውጥረትን ከሚፈጥሩና ከሚያባብሱ መግለጫዎች፣ ንግግሮች እና ትርክቶች ይልቅ ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ በጽኑ ታምናለች።
#AmbassadorRedwanHussien #X

Tecno Spark 20 Pro +
በአዲስ ዲዛይን ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ በመሆን የቀረበውን ‘ Spark 20 Pro + ’ ስልክ ቀድመው የራሶ ያድርጉ!
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia
በአዲስ ዲዛይን ለአያያዝ እና አጠቃቀም ምቹ በመሆን የቀረበውን ‘ Spark 20 Pro + ’ ስልክ ቀድመው የራሶ ያድርጉ!
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስርዓተ ቀብርን ክብሩን በጠበቀ ደረጃ እንዲፈፀም ለማድረግ ኮሚቴ እንደተቋቋመ አሳውቋል። ኮሚቴው ይፋዊ መግለጫ ይሰጣልም ተብሏል። ከሚሰጠው መግለጫ በኃላ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስክሬን ወደ ሀገር ቤት መጥቶ የቀብር ስነስርዓቱ እንደሚፈፀም የቴሌቪዥን ጣቢያው አሳውቋል። የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ የጋዜጠኛ አስፋው አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን…
#UPDATE : የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስርዓተ ቀብር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ይፈፀማል።
ዛሬ ጥዋት የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስክሬን ለህክምና ሄዶ ህይወቱ ካለፈበት አሜሪካ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።
ስርዓተ ቀብሩ የሚፈፀመው በመንበረ ጸባኦት ቅ/ሥላሴ ካቴድራል መሆኑ ተነግሯል።
ከስርዓተ ቀብሩ ቀደም ብሎ ቤተሰቦቹ፣ አድናቂዎቹ፣ ወዳጆቹ በተገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ የስንብት መርሐግብር ይካሄዳል ተብሏል።
ከዚህ መርሐ ግብር በኃለ ከ7፡30 እስከ 9:00 ሰዓት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፍትሃት እና የቀብር ስነ ስርዓት ይፈጸማል።
የፎቶ ባለቤት ፦ EBC

#ኢትዮጵያ🇪🇹 " ... ለሶማሊያ በችግር ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ #አንዳንድ_ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ አድርገው ለማሳየት እየሞከሩ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ምን አሉ ? - ኢትዮጵያ ለሶማሊያ #ሰላም እና #ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በውድ ልጆቿ #ደም እና #ላብ በግልፅ አሳይታለች። - ኢትዮጵያ…
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
" ... ለሶማሊያ #በችግሯ_ጊዜ ብዙ ድጋፍ ያላደረጉ አንዳንድ ተዋናዮች ራሳቸውን እንደ እውነተኛ ወዳጆቿ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ያነሳሳቸው ለሶማሊያ ያላቸው ወዳጅነት ሳይሆን #ለኢትዮጵያ_ያላቸው_ጥላቻ መሆኑ ግልጽ ነው። "

ፎቶ/ቪድዮ ፦ በኬንያ፣ ናይሮቢ በአፄ ኃይለስላሴ ስም የተሰየመ የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ቅዳሜ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል።
እንደ ኬንያ መገናኛ ብዙሃን መረጃ ፤ በ " ናይሮቢ ፈጣን መንገድ " ላይ የተገነባው የፈጣን መንገድ መውጫ ፕላዛ ከባለፈው ዓመት ሃምሌ 2023 አንስቶ በቻይና እና ኬንያ ተቋራጮች ሲገነባ የቆየ ሲሆን በአካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ ፍሰትን ያቀላጥፋል ፤ ወደ #ናይኖቢ_ከተማ ማዕከል ለመግባትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ተብሏል።
ይኸው የኃይለስላሴ የፈጣን መንገድ መውጫ 5 መስመሮች እንዳሉት ተጠቁሟል።
አፄ ኃይለስላሴ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ለረጅም አመታት በንጉሰ ነገስትነት የመሩና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት - OAU / የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት - AU እንዲመሰረት ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ መሪ ነበሩ።

#ትግራይ
ዛሬ ጥር 13/2016 ዓ.ም በትግራይ በርካታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተሰምቷል።
ሰልፎቹን ያካሄዱት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ናቸው ተብሏል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የተደረጉት ፦
* በሸራሮ
* በሽረ
* በአክሱም
* በዓድዋ
* በተምቤን
* በዓዲግራት
* በጉሎመኸዳ
* በኢሮብ
* በመቐለና ልሎች ከተሞች ሰሆን ከጠዋት ጀምሮ በተካሄደ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮች ሲሰሙ ነበር።
በተለይ ከምዕራባዊ ትግራይ ሙሉ በሙሉ ፣ ከተወሰኑ ሰሜናዊ ምዕራብ ፣ ማእከላይ ፣ ምስራቃዊና ደቡባዊ ዞኖች መፈናቀላቸው የሚናገሩት ሰልፈኞቹ " ወደ ቤታችን መልሱን " ብለዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ፦
➡ የፕሪቶሪያው ውል ሙሉ በሙሉ በአስቸኳይ ይተግበር !
➡ የፌደራልና የጊዜያዊ መንግስቱ አስተዳደሮች ሃላፊነታቸው ይወጡ !
➡ ሰርተን ለፍተን እንድንኖር ወደ ቤታችን መልሱን !
➡ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !
➡ በምግብና በመድሃኒት እጦት እየተገረገፍን ነው !
➡ ከጥይት የተረፍን ድምፅ በሌለው ጥቃት እያለቅን ነው !
➡ ሰብአዊ እርዳታ ይሰጠን !
የሚሉና ሎች መፈክሮችን በመያዝ የየከተሞቹን አደባባዮች በመዞር ድምፃቸው አሰምተዋል።
በሰልፎቹ ከህፃን እስከ አዛውንት የሚገኙባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይች መሳተፋቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ከተለያዩ የትግራይ ከተሞች ያሰባሰባቸው መረጃዎች ያመለክታሉ።
በሽረ እንዳስላሰ ከተማ በተካሄደው ስልፍ የተሳተፉ አንዲት ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን የተፈናቀሉት እናት ፤ " የእንጀራ መሰቦቻችን ባዶ ናቸው ፤ የሚበላ የሚጠጣ ስጡን ፤ መንግስት ለአይኑ ጠልቶናል ፤ ያስጠለሉን ለራሳቸው ስለተራቡ ለእኛ መስጠት ማካፈል አቆቶችዋል ፤ አድኑን ! " ብለዋል።
በሽረ ከተማ የተካሄደው ስልፍ ተሳታፊዎች ለምግባረ ሰናይ ድርጅቶች ፣ ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ለትግራይ ዳያስፓራ ማህበረሰብ ፣ ለፌደራል መንግስትና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በሚል ርእስ ባሰራጬት ፅሑፍ ማጠቃለያ " የፕሪቶሪያ ውል ሙሉ በሙሉ ይተግበር ! በምዕራባዊ ዞን ህዝብ ላይ በመካሄድ ያለው ድምፅ የሌለው እልቂት ይቁም ! " ብለዋል።
ይህ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ ሰልፎኞቹን ተቀብሎ ያነጋገረ የመንግስት ሃላፊና ተወካይ እንደሌለ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።