TIKVAH-ETHIOPIA
#JigjigaUniversity “ ፈተና አልፈን ቴምፖ እየጠበቅን ባለንበት ድጋሚ በሰኔ ትፈተናላችሁ ተባልን በሰላሚዊ ሰልፍ ስንጠይቅ። የተመታ ተማሪ አለ ” - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን 🔴 “ የኛም የመጀመሪያ ጥያቄያችን ነው። እየተከራከርን ነው ” - የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ➡️ “ ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር…
#Update
" ታፍሰው የተወሰዱ አሉ። 20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል ፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም " - የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች
የመውጫ ፈተና ተፈትነው አልፈው ቴምፖራሪ ሲጠባበቁ እንደነበሩ የገለጹ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች፣ በድጋሚ ገና በሰኔ ላይ 'ትፈተናላችሁ' በመባላቸው ዛሬም መብታቸውን ሊጠይቁ በተዘጋጁበት በጸጥታ አካላት ድብደባና አፈሳ እንደደረሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬስ ምን አሉ ?
አንዱ ምሩቅ በሰጡን ቃል፣ " ተማሪ ሲያልፍ እንዴት እንዲህ ተብሎ ይጠየቃል ? ብለን ሀሳብ ልናቀርብ በተሰለፍንበት ወቅት (50 እናሆናለን)፤ 20 ተማሪዎች በፓትሮል ተጭነው ተወስደዋል፤ የት እንዳደረሷቸው አናውቅም። ስልካቸው አይሰራም። የቀሩትም ተደብድበው ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሉ " ሲል ተናግሯል።
ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ ተመራቂ፣ " ፈተናችን ታግዶ ከቆዬ ሰነባብቷል። በዚህም የግቢው አስተዳደር አካላትን ምላሽ ለመጠየቅ እየሞከርን ነበር። ሊያናግሩን ፈቃደኞች አይደሉም። ትላንት ልንጠይቅ ስሄድ አባረሩን፤ ዛሬ ልጠይቅ ስንሄድ ደግሞ በርካታ የጸጥታ አካላት ተጭነው መጥተው ተማሪዎች ተደብድበዋል። ሌሎችም በፓትሮል ተጭነው ወደ ማረሚያ ቤት ሂደዋል " ብሏል።
ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢ፣ " የመወጫ ፈተና በድጋሜ ከጥር 25 እስከ 30 2017 ዓ/ም እንደወሰድን ይታወቃል። እንዳለፍን፣ ውጤት እንደመጣ ተልኮልናል። ፎቶ ተነሱ ተብለን ዶክሜት ልንሰጥ ፎቶ ተነስተን አስገብተን ክሊራስ የመውጫ ሞልተን ጨርሰን በሳምንቱ ውጤታችሁ ታግዷል ተባልን " ሲል ገልጿል።
" ምንድነው ? አልን ' ትምህርት ሚኒስቴር ነው ያገደው ' ተባልን ስንጠብቅ ቆየን ነገር ግን እስከዛሬ የተሰማ ነገር የለም። የድሀ ልጆች ነን። ቤት ተከራይተን ለምግብ እያስላክን ነው። እኔ 25 ሺሕ ብር ወጪ አድርጌያለሁ። ዩኒቨርሲቲው ከግቢው አሶጥቶናል የሚሰጠን ሰርቪስ የለም ” ሲል ገልጿል።
ሌላኛዋ ተመራቂ ተማሪ፣ “ ተሰብስበን ጥያቄ ልንጠይቅ ነበር። እዚሁ እኛ ፊት ነው የደበደቧቸው። ወደ 20 ሴቶችም ወንዶችም የታሰሩ አሉ። የጸጥታ አካላት ሙሉ ግቢውን አጥለቅልቆት ነበረ ገና ማውራትና መጠየቅ ሳንጀምር " ብላለች።
" ምንም ብጥብጥ አልፈጠርንም፤ ያወክነው ነገርም የለም፤ መብታችን እንዲከበርልን እሱም ኢ - ፍትሃዊ የሆነ ነገር ተደርጎብናል ፍትህ እንፈልጋለን ባልንበት ሁኔታ ነው " ይህ ሁሉ የተደረገው ብላለች።
" ገና እየተሰባሰብን ባለበት መሳሪያ ታጥቀው ዱላ ይዘው የመጡ የጸጥታ ኃይሎች ሰበሰቡንና ተማሪዎቹን በግፍ እየደበደቡ ነበረ። አወላላ ሜዳ ላይ ታፍሰው የተወሰዱ አሉ ወደ 20። ስንደውልም ስልካቸው አያነሱም የት እዳሉ አናቅም። አይተናል እዛነበርን በመኪና ጭነው ነው የወሰዷቸው ” ስትል ተናግራለች።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ በመጨረሻም፣ ለጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ያሳሰቡ ሲሆን፣ ለቅሬታቸው ምላሽ ለማግኘት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ ዩኒቨርሲቲውና ትምህርት ሚኒስቴር ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው ስልክ አልተነሳም።
የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በሽር አብዱላሂ (ዶ/ር)፣ የተማሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ትላንት በጠየቅናቸው ወቅት ስለጉዳዩ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልጸው ነበር።
ፕሬዜዳንቱ በወቅቱ ሁነቱን ሲያስረዱም፣ "ጉዳዩ ‘ፈተና በሁለተኛ ጊዜ የተቀመጡት ተማሪዎች ውጤታቸው ‘#ችቲግ’ ምልክት አለው’ በመባሉ ትምህርት ሚኒስቴር ሆልድ ስላደረገ ነው/" ነበር ያሉት።
(ጉዳዩን የምንከታተለው ይሆናል)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

Photo
#Update
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምን ምላሽ ሰጠ ?
" ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ የተሳሳተ መረጃ ነው " - ክፍለ ከተማው
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፤ በቅድሚያ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በኃላም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት " ጨለማን ተገን በማድረግ ፈርሷል " ስላሉት የተባረክ መስጂድ አጥር ጉዳይ አሁን ለሊት መግለጫ አውጥቷል።
ክፍለ ከተማው ፤ " በዛሬው እለት እሁድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ሜክሲኮ አካባቢ የመንግስት አካላት የመስጂድ አጥርን አፈረሱ የሚል መረጃ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘዋወር መዋሉ ይታወቃል " ብሏል።
ማንኛውም የመንግስትና የህዝብ ጥቅምን የሚጎዱ ህገወጥ ድርጊቶች ሲፈፀሙ በህግ አግባብና ህጋዊ ውሳኔን መነሻ በማድረግ ሲከላከል መቆየቱን ወደፊትም የሚተገብረው ትልቁ ኃላፊነቱ መሆኑን አንስቷል።
" በዛሬው እለት በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የዋለው መረጃ ቤተ እምነትን ሽፋን በማድረግ መንግስት ዉሳኔ ያልሰጠበት መሬትን ያለአግባብ ከህግ ዉጪ ለመያዝ የተደረገ ተግባራዊ እንቅስቃሴን ለመከላከልና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተወሰደ እርምጃ ነው " ብሎታል።
" ጉዳዩን በተሳሳተ መንገድ መተርጎም በምንም ዓይነት ተቀባይነት ያለው ድርጊት አይሆንም ፤ ህዝባችንም እጅግ አስተዋይ ህዝብ በመሆኑ ጉዳዩን በሚዛኑ የሚረዳ እንደሚሆን እናምናለን " ብሏል።
" ተባረክ መስጂድ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ከመስጂዱ አባቶችና ምዕመናኑ ጋር በቅርበት አብሮ ከሚሰራቸው፣ ወደፊትም አብሮነቱን ከሚያጠናክራቸው የእምነት ተቋማት መካከል አንዱ ነው " ያለው ክ/ከተማው ፥ " ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የመስጂዱ አስተዳደር ከህጋዊ ይዞታዉ ዉጪ ያለ መሬት ላይ የማስፋፊያ ጥያቄ ለአስተዳደሩ አቅርቧል በሚል ሰበብ ለሀገራዊ ፕሮጀክት ሲባል በቦታዉ የነበሩ ነዋሪዎችና የፌደራል ፖሊስ ካምፕን ወደ ሌላ ቦታ በማዛወር የፀዳ ቦታን የመስጂድ ይዞታ እንደነበረ አስመስሎ ማቅረብ የተሳሳተ መረጃ ነው " ሲል አሳውቋል።
" ቦታው ከዚህ በፊት የፌደራል ፖሊስ ካምፕና የነዋሪዎች የነበረ ሲሆን ቦታውን በማፅዳት ሀገራዊ ፋይዳ ላለዉ ፕሮጀክት በሀገራዊ ፕሮጀክት ኮንትራክተሩ አማካኝነት ሙሉ ባዶ ቦታዉ በኤጋ ቆርቆሮ እንዲታጠር ተደርጎ የቆየ ነው " ብሏል።
" ነገር ግን ይህ እውነት ሆኖ ሳለ አሁን ግን ቦታውን ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱ እንደሆነ በማስመሰል በመንግስት የታጠረዉን ቦታ ያለምንም ህጋዊ ፍቃድ የመስጂዱን ታፔላ እና በር በመስራት የመስጂዱ አካል በማስመስል ህገ ወጥ ተግባር ከመፈጸሙም በተጨማሪ በመስጂዱ ይዞታ ስር ያልነበረ ቦታ ' መንግስት አፈረሰዉ ' በሚል እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች ፍፁም ህጋዊ መሰረት የሌላቸዉ መሆኑን የእምነቱ አባቶችና ተከታዮች በሚገባ ልትረዱት ይገባል " ሲል አስገንዝቧል።
" ያለአግባብ በተዛባ መረጃ ላይ ተመስርታችሁ ያልተገባ እንቅስቃሴ የምታደርጉ አካላትም ከድርጊታችሁ መታቀብና ቀረብ ብሎ መረጃና ማስረጃ አጣርቶ መረዳትን እንድታስቀድሙ " ሲል በመግለጫው አሳስቧል።
ክፍለ ከተማው ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልግ ለማንኛውም አካል መረጃ ለመስጠት በሩ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ ሪኤግዛም ተፈትነው ቢያልፉም ” ቴምፖ ማግኘት እንዳልቻሉ፣ በመጨረሻም በድጋሚ ትፈተናላችሁ እንደተባሉ፣ አሰራሩም ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ በድጋሚ መፍትሄ ጠየቁ።
ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በድጋሚ ባሰሙት ቅሬታ ፥ “ ኤግዚት ኤግዛም አምና ብንወድቅም ዘንድሮ ለስድስት ወራት ተዘጋጅተን ነው ለፈተና የቀረብነው። ተፈትነን ውጤታችንን አይተናል፤ የመውጫ ፎርምም ጨርሰናል። ዶክሜንት ስጡን ስንላቸው ግን ‘ታግዷል’ አሉን " ሲሉ ገልጸዋል።
" ስንጠይቅም ‘ትምህርት ሚኒስቴር በሰኔ ትፈተናላችሁ ብሏችኋል’ አሉን። አምና ተማሪዎች ወደቁ ሲባል ለምን ? ብሎ ያልጠየቀ አካል ዘንድሮ ለምንድን ነው ተማሪዎች ያለፉት ብሎ እንዴት ሞራላችንን ያቆሽሻል ? " ብለዋል።
ተማሪዎቹ ችግር ካለ ሀሳባቸውን በነፃነት የሚገልጹበት መድረክ እንዲዘጋጅ ቢጠይቁም እንዳልተቻለ አመልክተዋል።
" ሰሞኑን ተማሪ ከተማ ቤት ከተከራየበት በልዩ ኃይል እየተፈለገ እየታፈሰ እየታሰረ ነው። ከ7 እስከ 8 ተማሪዎች ሆነን ነው ቤት የተከራየነው " ብለዋል።
አብረዋቸው የተፈተኑት ዶክሜንት እንደተሰጣቸው የነሱ የታገደበት ምክንያቱን እንዳላወቁ ግን ሰኔ ወር ላይ ድጋሚ መፈተን እንዳለባቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
" ማለፊያ ውጤት አምጥተን እያለ ሰኔ ላይ ድጋሚ የምንፈተንበት አሳማኝ ምክንያት ምንድን ነው ? ብሎ ጥያቄ ማቅረብ ቀርቶ ከግቢው አካባቢ፣ ከከተማውም አይዲ ይዘን ከተገኘን የ2012 እና 2013 ባች ተማሪዎች ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ነው የሚወሰዱት " ብለዋል።
" የመብታችንን ጥያቄ ልጠይቅ ባልንበት ወቅት ከ20 በላይ ተማሪዎች ታስረው የደረሱበት ያልታወቀበት፣ ከከተማም እየታፈሱ ተማሪዎች እየታሰሩ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። ተማሪዎች ወዳልተፈለገ ፓለቲካ እየገቡ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ለጊዜው አልተሳካም።
ስለጉዳዩ የጠየቅነው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኅብረት የቀረበውን ቅሬታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደተጋገረ ገልጾ፣ " ከትምህርት ሚኒስቴር ‘ታንጄብል የሆነ ነገር ስለያዝን ፈተናው ይደገማል’ በሚል ነው ይዘውት ያሉት " ብሏል።
አክሎ፣ " እኛም ታንጄብሉ ነገር ምን አይነት ነው? በሚለው እየተነጋገርን ነው ያለነው እንጂ እንዲደገም ተነግሯቸዋል " ነው ያለው።
ታዲያ የሚፈተኑ ከሆነ ዩኒቨርሲቲው የዶርም አገልገሎት እንኳ ሊሰጣቸው አይገባም ነበር ወይ ? ስንል ላቀረብንለት ጥያቄ በሰጠው ምላሽም፣ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው ጋር እንደሚወያይ፣ የታሰሩ ተማሪዎች ስለመኖራቸው ግን እንዳልሰማ ገልጿል።

#Update " ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች ➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች 🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ…
#Update
#የጤናባለሙያዎችድምጽ
" የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ 14 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች ከስራ ቦታቸዉ ተወስደው ታስረዋል " - የሀንጣጤ ሆስፒታል ባለሙያዎች
" ' ለሚዲያ መረጃ ስለሰጣችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል ' የሚሉ አመራሮችም አሉ ! "
በሲዳማ ክልል፤ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፊያ ባለመከፈሉ ለሎካ አባያ ወረዳ፣ ለማዕከላዊ ሲዳማ ዞንና ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆማቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ማሳወቃቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ስለ ጉዳዩ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ ፥ የሠራተኛዉ ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀዉ ክፍያዉ እንዲፈፀም ከክልሉ መንግስት ብድር መጠየቃቸዉንና በቅርቡ እንደሚከፈላቸዉ ገልፀዉ የነበረ ሲሆን " የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ " ሲሉ ገልጸውም ነበር።
ትላንት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት " ሁሉም ሰራተኛ በአንድነት ተፈራርሞ ባስገባዉ ደብዳቤ መሰረት ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ያቆሙ ቢሆንም የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክር እና 7 የማኔጀመንት አካላትን ጨምሮ 14 የሚሆኑ የሆስፒታሉ ባለሙያዎችን ፖሊስ ከስራ ቦታቸዉ ጭምር ወስዶ አስሯቸዋል " ብለዋል።
" ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆሙ ሰበብ ተደርጎ በመደበኛ ስራዉ ላይ እንከን እንዳይፈለግበትና ላለመከሰስ የስራ ሰዓቱን በአግባቡ እየተጠቀመ ነዉ " የሚሉት ሠራተኞቹ " ትላንት ጠዋት በድንገት 2 ዶክተሮች፣ 7 ነርሶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን 'ትፈለጋላችሁ' በሚል ያለ ፍርድ ቤት መጥሪያ ከነ ጋዎናቸዉ ጭምር ወደ ሀንጣጤ ፖሊስ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።
" ሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብንሄድም ' ከበላይ አካላት ታዘን ነዉ ' የሚል ምላሽ ነዉ የተሰጠን " ብለዋል።
ሠራተኞቹ ቀኑን ሙሉ እዛዉ ለመሆን መወሰናቸዉንና ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ የተወሰኑ አመራሮች ወደ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ቢሆንም የታሰሩት ሳይፈቱ ወደ ' ቤታችሁ ሂዱ ' ተብለው እስኪጨላልም እዛዉ የቀሩ ባለሙያዎች እንደነበሩ አስረድተዋል።
" የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካልተከፈለን ብለን ስራ አላቆምን " የሚሉት የጤና ባለሙያዎቹ " አይደለም መደበኛ ስራ ለማቆም ምንም ሳይከፈለን በብዙ ችግሮች ዉስጥ ሆነን እራሳችንን እየጎዳን ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓቱን ስራ ጭምር ስንሰራ ቆይተናል ነገሮች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ በደብዳቤ አሳዉቀን የትርፍ ሰዓቱን ስራ ለማቆም ተገደናል " ብለዋል።
ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ባቆመበት ሁኔታ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ የማኔጅመንት አባላትንና የተወሰኑ ሠራተኞችን ለይቶ የማሰሩ ጉዳይ ተገብነት የሌለው እና የሚመለከታቸዉ አካላት በአፋጣኝ እልባት ሊሰጡበት የሚገባ ጉዳይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
" ' ሚዲያ ላይ ስለከሰሳችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል' የሚሉ አመራሮች ነበሩ " ያሉን ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ሜዲካል ዳይሬክተሩንና ማኔጅመንቱን ' ለምን ሠራተኛ ታሳምፃላችሁ፣ ከወረዳዉና ከዞኑ መንግስት የሚተላለፍላችሁን መመሪያ ለምን አታስፈፅሙም ' ብለዉ የሚያስፈራሩም ነበሩ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የከፍተኛ አመራሮችን ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጓል።
ከዚህ ቀደም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በስልክ መረጃ የሰጡን ቢሆንም አሁን ላይ " ወደ ቦታዉ በአካል ካልመጣችሁ መረጃ መስጠት አልችልም " በማለታቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።
ፈቃደኛ ሲሆኑ ምላሻቸዉን የምናካትት ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

" በቀጣይ 10 ቀናት እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ➡️ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል " - ኮሚቴው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማይናማር በአስከፊ ሁኔታ የሚገኙ ወደ 700 የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገለጸ። የሚኒስቴሩ…
#Update : በማይናማር ' ዲኬቢኤ ' ካምፕ የነበሩ 252 ኢትዮጵያውያን ትላንት ለታይላንድ የቀረበች በማይናማር በምትገኝ ማይዋዲ ወደምትባል ከተማ መሻገራቸውን፣ ይህም ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችላቸው አንድ እርምጃ መሆኑን የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዚህም፣ ኢትዮጵያውያኑንና የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 276 ወጣቶችን የዲሞክራቲክ ካረን ጦር ወደ ማይዋዲ እንደላከ ኮሚቴው ነግሮናል።
ኢትዮጵያውኑ በማይናማር በሚገኘው የዲሞክራቲክ ካረን ጦር (ዲኬቢኤ) ሥር የነበሩ፣ በመጀመሪያ ወደ ታይላንድ እንዲያሻግራቸው፣ ከዚያ ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው የመንግስትን ምላሽ ደጋግመው ሲጠይቁ የነበሩ ናቸው።
ኮሚቴው " አሁንም ገና መንግስት ወደ ቦታው ወኪል መላክ አለበት። ‘ለኤንጂኦ ውክልና ሰጥተናል’ ነው ያሉት ግን በኤንጂኦ ውክልና ብቻ ተላልፈው ወደ ኢትዮጵያ መተላለፍ አይችሉም። ለዚህ ጉዳይ የመንግስት ደሊጌሽን ያስፈልጋል " ብሏል።
" በተጨማሪም፣ በማይናማር ቢጄኤፍ ካምፕ ስክሪን አውት ተደርገው፣ ፓስፓርት ተሰጥቷቸው የተቀመጡ ወደ 495 ኢትዮጵያውያን አሉ። እንዲሁም የመንግስትን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሦስት ልጆች በስቃይ ናቸው የዛሬዎቹ ልጆቻቸን ከወጡበት አካባቢ ያሉ ማለት ነው " ሲል አክሏል።
" ከዚህ ቀደም ልጆቻችን በአንድ ወቅት ከካምፕ ባመለጡበት ወቅት በፓሊስ ታግተው የተመለሱ ወደ 26፣ በቢጂኤፍ ካምፕ አካባቢም ሌሎች 14 ልጆቻችን በስቃይ ላይ ናቸው። የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው ያሉት " ብለዋል።
" ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቀናል። ልጆቹን ከነሙሉ ስማቸውና ከነፓስፓርት ቁጥራቸው አስተላልፈናል። ‘ለሁለቱም ኤምባሲዎች እናሳውቃለን’ ብለውናል " ሲል ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

#EOTC ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመላው የሮማ ካቶሊካዊ መሪዎች እና በመላው ዓለም ላሉ ምእመናን እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ገልጸዋል።…
#Update
በዓለም ላይ ከ1.4 ቢሊየን በላይ ተከታዮች ያላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በትናንው ዕለት 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕይወታቸው ማለፉን ማስታወቋ ይታወሳል።
ቫቲካግ ዛሬ እንዳስታወቀችው የፖፕ ፍራንሲስ ሞት ምክንያት በስትሮክ እና የልብ ህመም ነው።
የስርአተ ቀብራቸውን ቀን ለመወሰንም ካርዲናሎች በቫቲካን ተሰብስበው ነበር።
በዚህም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ እንደሚፈጸም ቫቲካን አስታውቋል።
በሌላ በኩል ፥ እንደ ቤተክርስቲያኒቱ ሕግ የአዲሱ ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ምርጫ ከ15 እስከ 20 ቀን ውስጥ ይጀመራል።
አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስኪመረጥ ድረስ ቤተክርስቲያኒቱ በካርዲናሎች ቡድን ትመራለች። ቀጣዩን ሊቀ ጳጳስም የሚመርጠውም ይኸው የካርዲናሎች ቡድን ነው።
የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን 252 ካርዲናሎች ያሏት ሲሆን እንደ ቫቲካን ከሆነ በሊቀ ጳጳስ ምርጫው ላይ ድምፅ መስጠት የሚችሉት 138ቱ ካርዳናሎች ብቻ ናቸው።
ከ1975 ጀምሮ በሊቀ ጳጳስ ምርጫው ላይ ድምፅ መስጠት የሚችሉት ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በታች የሆኑ ካርዲናሎች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጓል።
ካርዲናሎቹ በእነዚህ ጊዜያት ከውጪው ዓለም ጋር መገናኘት የማይችሉ ሲሆን የምርጫው ሂደትም በጣም ሚስጥራዊ ነው።
ካርዲናሎቹ አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስኪመርጡ ድረስ ይቆያሉ። ረጅሙ የቆይታ ጊዜ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ሊቀ ጳጳስ ለመምረጥ 3 አመት የቆዩበት ነው።
በ2013 ፖፕ ፍራንሲስ ሲመረጡ ከአንድ ቀን ብዙም ያልተሻገረ ነበር።
መረጃው የቫቲካንን እና ዩኤስ ቱዴይ ነው።

" ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ " - የጤና ባለሙያዎች
" የ4 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ተከፍሎን ስራ ጀምረናል፤ በወረዳዉ ስራ ሲዘጋ መክፈል የተለመደ ነው !! "
ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ሥራ ማቆማቸውንና 14 ሰዎች መታሰራቸውን በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ የሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።
ጤና ባለሙያዎቹ ዛራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ካልተከፈለዉ የ9 ወራት ዉዝፍ ዉስጥ የ4 ወራት ክፊያ መፈጸሙን ተከትሎ ሥራ መጀመራቸውን የገለጹት ባለሞያዎቹ " የትርፍ ሰዓት ስራ ከቆመ በኋላ ክፍያ መፈፀም በወረዳዉ የተለመደ ጉዳይ ነዉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከታሰሩ 5ኛ ቀናቸዉን የያዙት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች " እንዲፈቱ በተደጋጋሚ እየጠየቅን ነዉ ያሉት ሰራተኞቹ እስካሁን ግን ግልፅ ምክንያት አልተነገረንም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪና ፖሊስ አዛዥን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

#EOTOC ዛሬ ማለዳ ቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በዚህም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፎኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል። በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለረቡዕ ሚያዝያ…
#Update
ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታገደ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያን መሰረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብሮ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ እንዲያከናውን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን ፍቃድ መሰጠቱ ይታወሳል።
ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት " ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም " በሚል ርእስ የተላለፈው ትምህርት ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው መታገዱን የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዛሬ አሳውቋል።
በሌላ በኩል የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ በጻፈው ደብዳቤ " ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን ' እመቤታችን ቤዛ አይደለችም ' የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን ተመልክተናል " ሲል ገልጿል።
በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ እንዲሁም ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።
#EOTC #FenoteTsidk

ኢትዮ ቴሌኮም ስለ አክሲዮን ሽያጩ ምን አለ ?
- ኢትዮ ቴሌኮም ለ121 ቀናት የ10% ድርሻ አክሲዮን ሲሸጥ ቆይቷል።
- አጠቃላይ 47,377 ኢንቨስተሮች ተሳትፈዋል ፤ ሼሮችን ገዝተዋል።
- አጠቃላይ 10.7 ሚሊዮን ሼር ተሸጧል።
- አጠቃላይ 3.2 ቢሊዮን ብር አሴት/ value ተፈጥሯል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፍራንቼስኮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅድስት መንበር የቅድስት ማርያም ባዚሊካ ተፈጽሟል።
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገራት መሪዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች ተገኝተው ነበር።
Photo Credit - CNN