TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ከተራ2016
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በቤተክርስቲያኗ ሥርዓት እና ትውፊት መሰረት የ2016 ዓ/ም የጥምቀት ከተራ በዓልን በመላው ሀገሪቱ አክብረዋል።
በተለይ በአዲስ አበባ ከተራ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሯል።
ታቦታት ከየአብያተክርስቲያናቱ ወጥተው ወደ የማደሪያቸው ባህረ-ጥምቀት ገብተዋል።
በነገው ዕለት በመላው ሀገሪቱ የጥምቀት በዓል ይከበራል።
@tikvahethiopia

Tecno Spark 20 pro +
የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል አዲሱ ምርት የሆነውን ስፓርክ 20 ፕሮ ፕላስ (Spark 20 Pro+) የተሰኘ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ፣ እጅግ ከፍተኛ የካሜራ ጥራትና የፕሮሰሰር አቅም፣ ለረጅም ጊዜ መቆየት የሚችል ባትሪ፣ ማራኪ ቅርጽ እና ውበት ያለው የመጨረሻው የቴክኖሎጂ ውጤት የያዘውን እንዲሁም ደንበኞች የላቀ የአገልግሎት ተሞክሮ እንዲኖራቸው የሚያስችለውን የስማርት ሞባይል ስልክ ሞዴል በአዲስ አበባ ፍሬንድሽፕ ፓርክ ልዩ እና ደማቅ በሆነ ዝግጅት አስተዋወቀ።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#ሳፋሪኮም
እንኳን ሽክ ብላችሁ ለምትውሉበት የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ!
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ትክክለኛ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ቀጥሎ በሚገኙት ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
Facebook: https://www.facebook.com/SafaricomET
Telegram: https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia
Twitter:
https://x.com/SafaricomET?t=y2XAHAhPNvFeZqXa2YE6aQ&s=08
Instagram: https://www.instagram.com/safaricomet?igsh=MWJtcjJrMzNhMzVsNg==
YouTube: https://youtube.com/@safaricomethiopia2751?si=w2o8uz61oHeZM9gm
#በአብሮነት_ወደፊት
#SafaricomEthiopia

ፎቶ ፦ የ2016 ዓ/ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ስነ-ስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።
ዛሬ ጥዋት የእምነቱ ተከታዮች በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ በዓለ ጥምቀቱን በማህሌት ፣ በቅዳሴ፣ በመንፈሳዊ መዝሙሮች እና በተለያዩ የወጣቶችና ሕፃናት መርሃ ግብሮች አክብረዋል።
© Pax Catholic TV / EPA

#Photo
የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ፤ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የጥምቀተ ባህር ስፍራዎች ቀሳውስት እና ሊቃውንት ለምዕመናን ትምሕርት ሰጥተው፣ ጸሎት ተደርጎ እና ጥምቀተ ባሕሩ ተባርኮ ሥርዓተ ጥምቀቱ ተካሂዷል።
አሁን ላይ በዛሬው ዕለት የሚገቡ ታቦታትን የማስገባት ስነስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ያለውን ገፅታ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ከተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች በማሰባሰብ ልከንላችኃል።
ፎቶዎቹ ከአዲስ አበባ ፣ ጎንደር ፣ መቐለ ፣ ኣክሱም ፣ ላሊበላ፣ ደሴ ፣ ወልድያ ፣ ሀዋሳ ፣ ሐረር ፣ ድሬዳዋ ፣ አሶሳ ፣ ጋምቤላ ፣ ቡሌሆራ ...ከሌሎችም ከተሞች የተሰባሰቡ ናቸው።
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-20
© ሁሉም ፎቶዎች #ምንጫቸው የተገለፀበት ነው።

Telegraph
Tikvah Ethiopia
የጥምቀት በዓል አከባበር (በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን) ፦ አዲስ አበባ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Photo የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ ፤ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የጥምቀተ ባህር ስፍራዎች ቀሳውስት እና ሊቃውንት ለምዕመናን ትምሕርት ሰጥተው፣ ጸሎት ተደርጎ እና ጥምቀተ ባሕሩ ተባርኮ ሥርዓተ ጥምቀቱ ተካሂዷል። አሁን ላይ በዛሬው ዕለት የሚገቡ ታቦታትን የማስገባት ስነስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን…
ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?
ዛሬ በአዲስ አበባ ' ጃንሜዳ ' ባሕረ ጥምቀት በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መልዕክት አስተላልፈው ነበር።
ከቅዱስነታቸው መልዕክት መካከል የሚከተለው ይገኝበታል ፦
" ... እኛን የላከ እግዚአብሔርም ሆነ፣ ከሱ የተላክን እኛ ለሰው ልጆች ሁሉ የምናስተላልፈው መልእክት “ንስሐ ግቡ” የሚለው ነው፡፡
በእውነት ንስሐ ከገባን ጠቡ፣ ግድያው፣ ዘረፋው፣ መለያየቱ ይቆማል ፤ በምትኩ ደግሞ ፍቅር፣ አንድነትና ወንድማማችነት ይሰፍናል፤ መከባበር፣ መተማመን፣ መስማማትና ይቅር ባይነት የበላይነቱን ያገኛል፤ ውጤቱም ሰላምና ዕድገት ይሆናል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የምትሰማ ነፍስ ካለች እኛ የምንነግራት ይኼና ይኼ ብቻ ነው።
ከንስሐና ከፍቅር ውጭ በእግዚአብሔር ስም የሚናገር መልእክተኛ ካለ እሱ የእግዚአብሔር መልእክተኛ አይደለም፤ እባካችሁ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች የእግዚአብሔርን ቃል በሰላምና በሰላም ብቻ ለሕዝቡ እናድርስ፤ ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል በትክክል ሰምቶ ለሰላም ይታዘዝ፡፡
ሌላው የጥምቀት በዓል ዋና መልእክት “ያለው ለሌለው ያካፍል” የሚለው ትእዛዘ እግዚአብሔር ነው፡፡ ዛሬ ብዙ ወገኖቻችን ሕፃናት፣ እናቶች፣ እኅቶችና አረጋውያን በረኃብ ተቈራምደው ዕለተ ሞታቸውን ሲጠብቁ እያየን ነው፡፡
ወገኖቻችን በረኃብ እንዲህ እየሞቱ #እንደባዕድ ዝም ብለን የምናይ ከሆነ ክርስቲያንነቱ ጥያቄ ውስጥ አይገባምን ? ስለሆነም ኢትዮጵያውያንም ሆን የዓለም ማኅበረ ሰብ በሙሉ በጽኑ ረኃብ ለተጠቃው ሕዝባችን እጃቸውን እንዲዘረጉ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥያቄያችንን እናስተላልፋለን፡፡
እግዚአብሔር በዚሁ ዕለት እኛን ለመቀበል ሰማያዊ በሩን እንደከፈትልን እኛ ኢትዮጵያውያንም አእምሮአችንን ከፍተን ለመረዳዳት ለሰላም፣ ለፍቅር ለይቅርታ ለአንድነትና ለእኩልነት ተጠቃሚነት በርትተን እንድንሰራ ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላፋለን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡
የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ፊዚክስ፣
➡ ኬሚስትሪ፣
➡ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት
የማኅበራዊ ሣይንስ፦
➡ እንግሊዝኛ፣
➡ ሒሳብ፣
➡ ታሪክ፣
➡ ጂኦግራፊ፣
➡ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት
ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።
በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።
ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።
የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ?
የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።
ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር።
ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ #ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ #በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ።
ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።
የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር።
የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ እንደሚሄድ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት መግለፃቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ አይዘነጋም።
#ምንጭ ፦ @tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)
#ድብዳቤው ፦ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች የተገኘ ነው።

#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ ➡ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ ➡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#Update
ከቀናት በፊት ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ጋር ግኙነት እንዳቋረጠ የገለፀው በጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን መንግሥት ዛሬ ከኢጋድ አባልነት መውጣቱን አሳውቋል።
የሱዳንን ብሔራዊ ጦር የሚመራው የሱዳን መንግሥት ኢጋድ በኡጋንዳ ኢንቴቤ አድርጎት በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ የተፋላሚውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በስብሰባው እንዲሳተፉ መጋበዙ ‘የሃገሪቱን ሉላዊነት ጥሷል’ በማለት ከኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጦ ነበር።
ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ባወጣው መግለጫ ከኢጋድ አባልነት ሀገሪቱ መውጣቷን ይፋ አድርጓል።
ምንጭ ፦ አልጀዚራ

#ግብፅ #ሱማሊያ
በግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ግብዣ የተደረገላቸው የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል።
ሁለቱ ፕሬዜዳንቶች በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።
የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግሥት " ከሶማሊያ ጎን እቆማለሁ " ብላ በስምምነቱ ላይ ተቃውሞ ያሰማቸው ግብፅ ነበረች።
ከዚህም ባለፈ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በስምምነቱ ተቃውሞ ዙሪያ ቀደመው ስልክ ከደወሉላቸው መሪዎች አንደኛው ፕሬዜዳንት አልሲሲ እንደነበሩ አይዘነጋም።
ፕሬዜዳንት አልሲሲም ከቀናት በኃላ ፕሬዜዳንቱ ወደ ኤርትራ ባቀኑበት ወቅት ግብፅን እንዲጎበኙ ጥሪ አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በዚሁ ጥሪ መሰረት ለሁለት ቀን ጉብኝት ትላንት ምሽት ካይሮ ገብተዋል።
ግብፅ ፤ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 የባህር በር እንዲኖራት እድልን ይሰጣል ከተባለውና ከሶማሌላንድ ጋር ከተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ወዲህ ኢትዮጵያን የሚወነጅሉ አስተያየቶችን ስትሰጥ የነበረ ሲሆን ከሰሞኑን " ኢትዮጵያን በአካባቢው የአለመረጋጋት ምንጭ እየሆነች ነው " የሚል ንግግር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ተናግራለች።
ኢትዮጵያም ግብፅ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለተናገረችው ንግግር በአምባሳደር መለስ አለም በኩል ፤ " ኢትዮጵያን በአለመረጋጋት መንስኤነት መክሰስ በአንድ ቃል ለመግለፅ #ቧልት ነው፤ የዘመኑ ቀልድ ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል። " በሚል የመልስ ምት ሰጥታታለች።