TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC " ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው " - ብፁዕነታቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምን አሉ ? - የማይደፈር ሲደፈር አይተናል፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም። - " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም…
#ጥምቀት

" በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን አይወክሉም " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልእክቶች የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮሩ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በተለያዩ ቋንቋዎች ለተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቃለ መጠይቅና ምላሽ እንዲሰጡ ለተመረጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰጡት አባታዊ መመሪያ የቅድስት ቤተክርስቲያን መልእክት የሚተላለፈው በማእከል በመሆኑ የማእከሉን መልእክት ብቻ እንዲያስተላልፉ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ከግል አስተያየት መቆጠብ እንደሚገባም አበክረው አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያኗ የሰላም ሰባኪ እንደመሆኗ መጠን የቤተክርስቲያን መልእክት ሲተላለፍ ሰላም ላይ ማተኮርና በዓል ለማክበር የሚወጡ ምእመናን በዓሉ በሰላም አክብረው እንዲመለሱ መልእክት ማስተላለፍ እንደሚገባ ግልጽ መመሪያ ሰጥተዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ሁሉም ሃይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ይህ በዓል የሚከበርባቸውን ቦታዎች ለማጽዳትና ሥርዓት ለማስከበር ጥረት እያደረጉ ያሉ የሌሎች ሃይማኖት አባላትን በአባትነት ያመሰገኑት ብፁዕነታቸው ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች የሚገኙ የሌሎች ቤተ እምነቶችን ማክበር እንደሚገባ ለሁሉም ካህናትና ምእመናን አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን የማይወክሉና ቤተክርስቲያናችን በዓሉን በሰላም ለማክበር ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እያደረገች ያለውን ጥረት ከግንዛቤ ያላስገባ መሆኑን ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia
#MoE

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም #አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ላሉ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል ብሏል።

በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትነው ያላለፉ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የሚያካሂዱት የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የሚመርጡት በዚህ ማስፈንጠሪያ (Link)
(https://exam.ethernet.edu.et)  ነው።

ስለሆነ ከጥር 08 እስከ ጥር 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በ " ቴሌ ብር " ብቻ በመክፈል መመዝገብ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል [email protected] በኩል ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የሚፈቱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚያካሂዱትና  እና የአገልግሎት ክፍያ የሚፈፅሙት በተቋማቸው በኩል መሆኑን ገልጾ አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አመልክቷል።

@tikvahethiopia
Forwarded from Ethio telecom
ባህር ማዶ ካለ ወዳጅ ዘመድ የሞባይል ጥቅል ሲላክልዎ እስከ 20% ቅናሽ ማድረጋችንን በደስታ እንገልጻለን !

እነዚህን ከመደበኛ ጥቅል እስከ 20 % ቅናሽ የተደረገባቸውን ጥቅሎች ሲሞሉልዎ እስከ 100 % የሚደርስ ተጨማሪ ስጦታ ይበረከትልዎታል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#ተመስገን_ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ጥር 7 ቀን 2016 ዓ/ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰሚ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፣ “ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን” ያሏቸውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ጠይቀዋል።

ጋዜጠኛው ይህን ጥያቄ ያቀረቡት ዛሬ ቀጠሮ ተሰጥቶበት የነበረው ጉዳያቸው ከመታየቱ በፊት የሚያቀርቡት አቤቱታ እንዳላቸው ለዕለቱ ዳኞች ጥያቄ በማቅረብ ነው።

ስለሚያቀርቡት አቤቱታ ችሎቱ ለጋዜጠኛ ተመስገን አቤቱታቸውን እንዲገልጹ ከፈቀደላቸው በኋላ፣ “የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ አሕመድ መሐመድ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ምክንቻቶቼን አቀርባለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ይህን ከገለጹ በኋላ የቀኝና የመሀል ዳኛ የለሆሳስ ንግግር አድርገው አቤቱታቸውን በፅሑፍ እንዲያቀርቡ ማሳሰቢያ የሰጡ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ተመስገንም ፈቃድ ካገኙ በኋላ፣ “በእዚህ ችሎት በርካታ ጋዜጠኞች ስላሉ አቤቱታዬን በንባብ እንዳሰማ ሊፈቀድልኝ ይገባል” ብለውሸ ሲገልጹ፣ ፅሑፉን ባጭሩ እንዲያቀርቡ ማሳሰቢያ ተሰጥተዋል።

አሳጥረው እንዲያቀርቡ ዳኞች በፈቀዱላቸው መሠረት ያነበቡት ፅሑፉ በዝርዝር ምን ይላል?

“ዐቃቤ ሕግ ጥቅምት 1/2015 ዓ.ም ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ 2ኛ ክስን በሚመለከት 3ኛ እና 4ኛ ፍሬ ነገሮች፤ እንዲሁም 3ኛ ክስን የይግባኝ ቅሬታ ያላቀረበበት መሆኑን ጠቅሶ ወደፊት፦ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ውጤቱን ተመልክቶ የይግባኝ ቅሬታ እንደሚያቀርብበት በይግባኝ ማመልከቻው ላይ በግልጽ አመላክቶ እያለ፣ 

* ታህሳስ 17/2015 ዓ/ም መልስ ሰጪን ያስቀርባል በሚል ትዕዛዝ ከሰጡት ዳኞች መካከል አቶ መሐመድ አሕመድ የሚገኙበት መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡በችሎቱ የተሰጠው ትዕዛዝም ዐቃቤ ሕግ በ2ኛ ክስ ቅሬታ ያላቀረበባቸውን 3ኛ እና 4ኛ ፍሬ ነገሮችን በመጨመር፤ 

* እንዲሁም 3ኛ ክስን በማካተት በ1ኛ እና 2ኛ ክሶች መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት፣ 3ኛ ክስን በሚመለከት ክስ የቀረበበት ድንጋጌ ወደ ጥላቻ ንግግር ወይም የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከለከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 በመለወጥ እንዲከላከል በአብላጫ ድምጽ የተሰጠውን ብይን፤ 

*እንዲሁም የተጠቀሰውን አዋጅ ለጉዳዩ ያለውን አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑን ስለታመነበት መልስ ሰጪ ይቅረብ ብለናል በሚል ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡” የሚል ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን ያነበቡትና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ይኼው ሰነድ አክሎም፣ “ይህ ትዕዛዝ ዐቃቢ ህግ በይግባኝ አቤቱታው ከጠየቀው ዳኝነት በማለፍ የተሰጠ ትዕዛዝ መሆኑን መረዳት የሚቻል ከመሆኑም በላይ የመልስ ሰጪን መብት በብርቱ የሚጎዳ አድራጎት ነው” ይላል።

በተጨማሪ ፣ “ከላይ ስማቸውን የጠቀስኩት ዳኛ በዚህ ጉዳይ ከችሎት ሳይነሱ ይቀጥሉ ቢባል ጉዳዩ ፓለቲካዊ ይዘት ያለው እንደመሆኑ መጠን በመዝገቡ ላይ ትክክለኛ ፍትህ ይሰጣሉ ብዬ የማላምንና ወደ ፊትም የሚሰጠው ፍርድ ነጻና ገለልተኛ ይሆናል ብዬ ስለማላምን በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 33/1/ሠ መሠረት የግራ ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ መሐመድ አሕመድ በዚህ ጉዳይ ከችሎቱ እንዲነሱልኝ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ” ሲል ያትታል።

በመጨረሻም፣ የጋዜጠኛውን አቤቱታ ካደመጠ በኋላ ችሎቱ፣ የዳኛውን ከችሎት መነሳትና አለመነሳት ጥያቄን በተመለከተ ለመወሰን፣ እንዲሁም ጋዜጠኛ ተመስገን በዋናው ክሳቸው ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀውን መለስ ለመቀበል ለጥር 28 ቀን 2016 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት  #ነዳጅ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ በተደርገ ማሻሻያ ቀደም ሲል ሲሰጥ ከነበረው የድጎማ መጠን ዝቅ አንዲል መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፦
- በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣
- የከተማ አውቶብሶች
- ፐብሊክ ባስ
- ሚዲባስ፣ ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በየ6 ወሩ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች የድጎማ መጠን ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ለሚቀጥሉት 6 ወራት ፦

* ለቤንዚን ተጠቃሚ አገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች እና ፐብሊክ ባስ ብር 22.36 በሊትር ሲሰጥ የነበረውን ድጎማ ወደ 19.16 በሊትር ዝቅ እንዲል፣

* ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲሰጥ የነበረው ብር 23.21 በሊትር ድጎማ በሊትር 19.89 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ሚዲባስ፣ ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር የሚሰጠው ድጎማ በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ፦

* ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ ለቤንዚን ተጠቃሚዎች ሲስጥ የነበረው ብር 12.78 በሊትር ድጎማ ወደ 6.39 በሊትር፣

* ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲስጥ የበነረው የብር 13.27 ድጎማ ወደ ብር 6.63 በሊትር ተቀናሽ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መረጃው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ #ኢትዮጵያ የአየር ክልሏን ከማንኛውም ጥቃት ሊከላከሉ የሚችሉ ዘመናዊ የውጊያ ትጥቆችን እየታጠቀች መሆኑና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዛሬ እጅግ ዘመናዊ የሆነውን የsu-30 ተዋጊ ጀቶችንና የስትራቴጂክ ሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን በመረከብ መታጠቁን ገልጿል።

ይህ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን ሌሎች በሂደት እንደሚገቡ ተነግሯል።

ዛሬ የአየር ኃይሉ የታጠቃቸው የsu-30 እና የስትራቴጂክ ሰው አልባ አውሮፕሎች እጅግ ዘመናዊ፣ የ5ኛው ትውልድ አካል የሆኑ በሀገር ላይ ሊቃጡ የሚሞከሩ ጥቃቶችን ለማክሸፍ ወሳኝ የሆኑ ናቸው ተብሏል።

@tikvahethiopia