TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በተለይ ሀሰተኛ የሰነድ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል " ብለዋል።

" ኦዲት በማድረግ ሂደት ውስጥ የጎደሉ ካርዶች መኖራቸውን፣ ብዙ ካርድ ባይሆንም አንድ ባለሙያ ሦስት፣ አራት ካርዶች ሲጎድሉበት አይተናል” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ይሄ ከፍተኛ የሆነ ከባድ ጥፋት ነው። ወደ ወንጀል የሚያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ " ሌላው ደግሞ በኦዲት ግኝት ውስጥ ‘የዲጂታል መታወቂያ ኦዲት አይደረግም’ የሚል አስተሳሰብ ነው ያለው። ነገር ግን በእኛ ተቋም ዲጂታል መታወቂያ ኦዲት ይደረጋል። ዘጠኝ የሚሆኑ ባለሙያዎች የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ለግለሰቦች ለመስጠት ባደረጉት ጥረት ነው ኦዲት ግኝቱ ይዞ የወጣው " ብለዋል።

" ከዚያ ባሻገር የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና የሥራ ክፍል ደግሞ በርካታ ሥራዎች ይሰራሉ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ያስረዱት አቶ ዮናስ፣ " አገልግሎቱን በገንዘብ ለመሸጥ ሲደራደሩ የነበሩ ባለሙያዎችን፣ ደላሎችን በቁጥጥር ስር አውለናል። በተለይ ሀሰተኛ የሰነድ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል " ነው ያሉት።

ተቋሙ ሀሰተኛ መረጃን ለመለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም ገልጸው፣ " በዚያ ሂደት ውስጥ ባደረግናቸው ክትትሎች፣ በሰራናቸው ኦፕሬሽኖች ሰዎቹን ለመያዝ ችለናል። ስለዚህ በወንጀል የሚጠየቁት የኦዲት ግኝት የተገኘባቸው፣ ካርዶች የጎደሉባቸው፣ ከአሰራሩ ውጪ አገልግሎት የሰጡ ናቸው " ብለዋል።

አክለውም፣ " ከዚያ ባሻገር አመራርም ደግሞ እኛ ጋ በተቋም ግንባታችን ውስጥ መጠየቅ አለበት የሚል አቋም አለን። በዚህ መሠረት ሥራቸውን በአግባቡ ያልመሩ አመራሮች ወደ 10 የሚሆኑ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን። በፓለቲካ አድሚኒስትሬሽን ውሳኔ ነው የሚሆነው " ሲሉ አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ከላይ ያሉትን ማብራሪያዎች የሰጡት ተቋሙ የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ የላኩትን መረጃ ተከትሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ነው።

ዋና ዳይሬክተሩ የተቋሙን የ6 ወራት አፈጻጸም በተመለከተ በላኩት መረጃ መሠረት፦
 
*የኦዲት ክትትል የተደረጉት ዋና መስርያ ቤትን ጨምሮ 11 ክ/ከተማ እና 22 የወረዳ ጽ/ቤቶች ነው።

*ተጠያቂነቱ በ2015 ዓ.ም በተሰጠው አገልግሎት ላይ የተሰራጩ የካርዶችና ሰርተፍኬቶች የቤት ለቤት አገልግሎትን ጨምሮና የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባለመከተል፣ አሰራርን በመጣስ ፣ ጉድለት በመፍጠር፣ ስራን በአግባቡ ባለመምራት እና ጉድለት በመፍጠር ላይ ያተኮረ ነው። 

*ተጠያቂ የሆኑ በጠቅላላው 63 ሰዎች ናቸው። 12 በወንጀል እና 41 በዲሲፕሊን የተጠየቁ ናቸው። ቀሪ 10 የጽ/ቤት አመራሮች ስራን በአግባቡ ባለመምራት ተጠያቂ የሚሆኑ ይሆናል። 

*አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ከ47 ባለሙያዎች መካከል 34 በከባድ እና ቀላል ዲሲፕሊን፣ 9 ባለሙያዎች በወንጀል ተከሰዋል። ከዚህ ውስጥ 6 ሰራተኞች የሌላ ተቋም ሰራተኛ የሆኑ ሠራተኞችን ጨምሮ እስከ 25 ሺህ ብር ጉቦ ለመጠየቅ ሲሞክሩ በተሰራ የተቀናጀ ኦፕሬሽን እጅ ከፍንጅ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

*አንድ ግለሰብ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሀሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ሲያደርግ ከሚያዘጋጅበት መሳርያዎች ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል። 

*4 በወረዳ ጽ/ቤት፣ 34 በኤጀንሲው ዋና መስርያ ቤት በድምሩ 36 ሃሰተኛ ሰነድ ይዘው የተገኙ ተገልጋዮች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል። ከዚህም ውስጥ 3ቱ ፍርድ ተሰጥቷቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል #ጫና ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ። አምባሳደር ሬድዋን፤ " የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣  ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ዓይነት ጫና…
#ኢትዮጵያ

" ስለ ስምምነቱ ቀድሞውኑ የሚመለከታቸው ሀገራት እና ተቋማት እውቅናው ነበራቸው ፤ ግን አላዋቂ ለመምሰል ጥረት እያደረጉ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር በተያያዘ ዕድል ያላት የሚመስለው ከሰሜን በኩል ነበር።

ሁሉም ሰው ስለ ባህር በር ሲወራ ቀይ ባህር ነው፤ ስለ ባህር ሲወራ ኤርትራ ነው ፤ ስለ ባህር ከተወራ አሰብ ነው። ይሄን አሁን ለመገልበጥ የሚያችል አዲስ አቅጣጫ ነው የወሰድነው።

ኢትዮጵያ ዙሪያዋ እድሎች አሏት፣ ዙሪያዋ ያሉ እድሎችን መጠቀም የሚያስችል አቅምም አላት፤ መጋራት የሚያስችል በጎ ፍላጎትም መነሻም አላት።

በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ አንድ የሆነ የባህር በር ሊኖራት ይገባል በሆነ መንገድ የሚለው ብዙዎች እየገዙት የመጣ ነው።

አትጋጩ፣ ችግር አትፍጠሩ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚመጣበትን መንገድ በትዕግስት ሂዱ ነው እንጂ የሚለው ኢትዮጵያ unfair የሆነ ነገር እየፈለገች ነው የሚል ብዙ ምልከታ የለም።

ኢትዮጵያ ፍላጎቷን፣ ያላት concern ትክክል ነው፣ የህዝብ እግደቷም ትክክል ነው፣ ኢኮኖሚዋም ትክክል ነው ፣ የቀጠናው ችግር ትክክል ነው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በአውንታዊነት ሚና ልጫወት ማለቷ ተገቢ ነው የሚለውን አጀንዳ ማድረግ ተችሏል።

... ይሄንን ፊርማ (ከሶማሌላንድ ጋር) እስክንፈርም ድረስ በUN ተቋማትም፣ በአንዳድን ትላልቅ ሀገሮች መረጃዎችም ፣ በእኛ Think tank በሚባሉ NGOዎችም ይሰራ የነበረው ጥናት የኢትዮጵያ መንግሥት ወይ ኤርትራን ይወራል፣ ወይ ደግሞ ሶማሌላንድን በአውዳል ግዛት በኩል ረብሻ ፈጥሮ ቀጠናውን ያተራምሳል የሚል ጥናት ነበር ሲሰራ የነበረው።

በዚህ ላይ draft ቀርቦ የቀረበው draft official ከመሆኑ በፊት የተመለሰ draft እናውቃለን። ይሄንን እነማን እንደሚሰሩት እናውቃለን፣ እሱ ውስጥ #ኢትዮጵያውያን እንዳሉበትም እናውቃለን። ስለዚህ ትላልቆቹ ሀገራት የሳቱት ነገር ፤ እኛም ባገኘናቸው ቁጥር ጦርነት አንፈልግም ውጊያ አንፈልግም ሲባል ' አይ መዋጋታችሁማ አይቀርም አናምናችሁም ' የሚባል ነው ጭቅጭቁ ከዋሽንግተን እስከ ሌሎቹ ድረስ ፤ ስለዚህ በዚህ ሊዋጉ ነው ብለው ሲገምቱ በዚህ በኩል በሰላም መጣን አልተገመትንም ግን ያልተገመትነው ለበጎ ነው።

... መንግሥት ፍላጎቱን ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለጎረቤት ሀገሮች ፣ በአጠቃላይ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ከአንዴም ሁለት ጊዜ envoy ተልኳል። የማያውቁት ነገር ቢኖር ሙሳቤሂ መቼ እንደሚመጣ (ወደ አዲስ አበባ) እና እዚህ ውስጥ የሼር ጉዳይና የእውቅና ጉዳይ MoU ውስጥ እንደሚካተት አያውቁም። ስለዚህ ከሞላ ጎደል አሰብ አካባቢ የምንከራተት አድርገው ስለወሰዱ ይሄን ጉዳይ ትርጉም አልሰጡትም።

አሁን አፍጥ ሲመጣ ነው ሰው የደነገጠው እንጂ የአብዛኛው ሰው ፍርሃት #በአሰብ በኩል ችግር ትፈጥራላችሁ ፣ ስለዚህ እጃችን ላይ በቂ ችግር አለ የዩክሬን አለ የጋዛ አለ፣ ከምትጨምሩብን በሰላማዊ መንገድ አድርጉትና በሰከነ መንገድ እኛም እናግዛችኃለን የሚል ነውና የpredictability deficit የተነሳበት angle ትክክል አይመስለኝም።

ስለ ጉዳዩ ለእያንዳንዱ ለሚመለከተው መንግሥት አስረድተናል። "

#AmbassadorRedwanHussien #etv

@tikvahethiopia
🤩የአፍሪካን ምርጦችን በአፍሪካ ዋንጫ🏆

🔥ከጥር 4 - የካቲት 3 2016 ድረስ  የሚካሄደው  34ተኛ የአፍሪካ ዋንጫ ሁሉንም 52 ጨዋታዎች በላቀ ጥራት በቀጥታ በዲኤስቲቪ  ሱፐርስፖርት ቻናሎች በቀጥታ በሁሉም ፓኬጆች ይመልከቱ!

👉አንድም ደቂቃ እንዳያመልጥዎ ፈጥነው የዲኤስቲቪ ዲኮደር ይግዙ!

👉የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

#AFCONonDStv #AFCON2023#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#ዜና_ዕረፍት

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ጋዜጠኛው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሀገር ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተነግሯል።

ጋዜጠኛው ቀድሞ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ህይወቱ እስካለፈበት ሰዓት ድረስ ደግሞ የEBS ቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ በመሆን ሰርቷል።

በተለይ በEBS ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው " ኑሮ በአሜሪካ " ፕሮግራም እና " እሁድን በEBS " ፕሮግራም በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሎ ነበር።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሸ ባደረበት ህመም ምክንያት ህክምና ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።

ለወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን!

Via @TikvahethMagazine
#CBE
በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
===========
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም  App Store በማውረድ  አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

***  
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!  
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh  
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
#ጥናት

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጥራታቸው ተጠብቆ ባለመገንባታቸው፣ በዕጣ የቤት ባለቤት የሆኑ ዕድለኞች ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን የአፍሪካ ከተሞች የምርምር ጥምረት (ACRC) እና ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (FSS) በጋራ ባደረጉት ጥናት ማረጋገጥ መቻላቸውን አስታውቀዋል።

ሁለቱ ተቋማት ጥናቱን ለአንድ ዓመት ያህል ነው ያደረጉት።

በጥናቱ ከ6 በላይ ከፍተኛ ተመራማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በኢኮኖሚ፣ በመዋቅራዊ ሽግግርና በወጣቶች አቅም ግንባታና በመኖሪያ ቤቶች ላይ የተደረገ ነው።

ጥናቱ ምን ይላል ?

- በአዲስ አበባ ከተማ ከመነሻውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ አይደሉም፡፡

- መንግሥት 40/60 ወይም የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በዕጣ ለደረሳቸው ሲያቀርብ ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ ስለማይገነቡ፣ ዕድለኞች መልሰው አፍርሶ ለመሥራት ይገደዳሉ ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ፦
* ለኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ፣
* የሲራሚክ ንጣፍ፣
* ለመፀዳጃ ቤት መስመር፣
* ግድግዳ እንደገና ለመሥራትና ሌሎች የጎደሉ ነገሮች ለማሟላት ለከፍተኛ ወጪ ይዳረጋሉ።

- እነዚህ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልጉ በመሆናቸው፣ መንግሥት ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብዓት ጀምሮ እስከ ባለሙያ ድረስ ጥራታቸውን በመጠበቅ ማቅረብ ይኖርበታል።

በተጨማሪ ...

በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ተስማሚ የሆኑ ነገሮች እንደሌላቸው ታይቷል። ወጣቶች በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ፣ በኢመደበኛ ዘርፍና በጤና ላይ ያላቸውን በጎ ተግባራትና ያሉባቸው ችግሮች ተለይተው በጥናቱ ተካተዋል።

በኢትዮጵያ ከዚህ በፊት አብዛኛውን የቤት አቅርቦት ተፈጻሚ የሚሆነው በመንግሥት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ቤት አልሚ ድርጅቶች ተቋቁመው የማኅበረሰቡን የቤት ጥያቄ እየመለሱ መሆናቸው የሚበረታታ ነው።

በቤት አቅርቦት ላይ ለውጦች እየመጡ ቢሆንም አሁንም የመሬት አቅርቦት፣ እንዲሁም በዝቅተኛና በመካከለኛ ገቢ ላይ የሚገኙ ሰዎች ቤት ለመሥራት ቢፈልጉ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ነው።

👉 በአጠቃላይ ጥናት የተደረገባቸው ጉዳዮች ላይ ያሉትን ችግሮች ለመፍታትና በጥናቱ የቀረቡ ግኝቶች መሬት ወርደው ተግባራዊ እንዲሆኑ፣ ለፖሊሲ አውጪዎች የሚቀርቡ ይቀርባሉ ተብሏል።

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#መቐለ
 
ከመቐለ ከተማ ተሰርቃ ልትሰወር የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በፀጥታ ኃይሎች ርብርብ ማትረፍ ተችሏል።

ዘረፋው አመሻሽ የተፈፀመ ሲሆን ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በፓሊስ እርምጃ መመከን ችሏል።

ስርቆቱ እንዴት ተፈፀመ ?

መኪናዋ RAVA-4 ስትሆን በ " 03532 ኮድ-2 ትግ " የሰሌዳ ቁጥር የምትታወቅና ባለቤትነትዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሃይለ ገ/መስቀል የተባሉ ግለሰብ ናት።

እስካሁን በፓሊስ ቁጥጥር ስር #ያልዋሉት ተጠርጣሪዎች መኪናዋ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቴድሮስ ከተባለ የመኪናዋ ባለቤት ልጅ #አፍነው በመቀማት ይዘዋት መሰወራቸው የተረዱ ባለቤቶች ወድያውኑ ወደ ፓሊስ ስልክ ደወሉ።

ፓሊስ ጊዜ ሳያጠፋ ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች በማሰማራት ከመቐለ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚያወጡ መንገዶች #እንዲዘጉ አደረገ።

ይህንን የተቀናጀና የተናበበ የፓሊስ የፀጥታ እንቅስቃሴ የተረዱ የሚመሰሉት መንታፊዎች መኪናዋን በአስፋልት መንገድ ጥለው ሸሽተዋል።

ፓሊስም መኪናዋን ከጥር 4 ወደ ጥር 5 /2016 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 8:00  በቁጥጥር ስር አውሏታል።

የሚሊዮኖች ብር ዋጋ ያላት መኪና ስርቀው ጥለዋት የጠፉት ተጠርጣሪዎች አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በከፍተኛ ጥረት ላይ እንደሆነ የገለፀው የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፤ ባለቤቶች ንብረቶቻቸው በጥንቃቄ እንዲይዙ መክሯል።

ተጠርጣሪዎች በህግ ስር ውለው ቅጣታቸው እንዲቀበሉ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግ መጠየቁ መቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድርግ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧን።

Photo Credit - FM መቐለ
                                     
@tikvahethiopia            
#ሶማሌ

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ።

ዛሬ ከሰዓት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ፤ ሸበሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።

አደጋው የደረሰው ከጅግጅጋ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ " ሚኒባስ " ተሽከርካሪ እና ከሸበሌ አቅጣጫ ሲመጣ በነበረ " ሲኖ ትራክ " እየተባለ በሚጠራው ተሽከርካሪ መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው።

ፖሊስ የአደጋውን ምክንያት እያጣራ ሲሆን የሚደርስበትን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ በትራፊክ አደጋው ምክንያት በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ለቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከክልሉ ቴሌቪዥን (ኤስአርቲቪ ሶማልኛ) ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
የሳፋሪኮምን ያልተገደበ ኢንተርኔት ጥቅልን በቅናሽ በM-PESA ሳፋሪኮም App ላይ ብቻ  ያገኙታል::
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስርዓተ ቀብርን ክብሩን በጠበቀ ደረጃ እንዲፈፀም ለማድረግ ኮሚቴ እንደተቋቋመ አሳውቋል።

ኮሚቴው ይፋዊ መግለጫ ይሰጣልም ተብሏል።

ከሚሰጠው መግለጫ በኃላ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስክሬን ወደ ሀገር ቤት መጥቶ የቀብር ስነስርዓቱ እንደሚፈፀም የቴሌቪዥን ጣቢያው አሳውቋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ የጋዜጠኛ አስፋው አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ቤተሰቦቹ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሥንብት ሥነስርዓት ይካሄዳል ብሏል።

ሃሙስ ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሜሪላንድ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የፍትሃት ሥርዓት እንደሚከናወንለትና ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል።

በአዲስ አበባም ሊካሄደው የቀብር ሥነስርዓቱ የተዋቀረው ኮሚቴ ደግሞ የቀብሩን ቀንና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በይፋ ይሰጣል ብሏል።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ሀገር ዲሲ የጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከወራት በፊት ስትሮክ አጋጥሞት ለተጨመሪ ህክምና ወደ አሜሪካ ሄዶ የነበረ ሲሆን ተደጋጋሚ ምርመራ ተደርጎለት የጭንቅላት ካንሰር እንዳለበት ተነግሮት ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እና ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia