TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኢትዮጵያ #ሰላም
#ሰላም_ከሌለ_ሁሉ_ነገር_የለም!
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦
" ... በምድር ላይ ሰላም ካልነገሰ በቀርን መቼም ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ሰላም ዓለምን የሚገዛ ነው ፤ ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም። ሰላም ካለ ሁሉ ነገር አለ።
ለሰላም የሚሆን ዋጋ በዓለም ላይ አይገኝም። ብርም ይሁን ፣ ወርቅም ይሁን አልማዝም ይሁን #አይመጥነውም። ለሰላም የሚሆን ዋጋ አይመጥነውም ይሄ ሁሉ።
ሰላሙን የምናመጣው እኛው ነን ፣ የምናባርረውም እኛው ነን።
ሰላም በምድር መንገስ አለበት። ሰላም በምድር ካለ ሁሉም ነገር አለ ፦
- ሀብት አለ
- ትምህርት አለ
- ስልጣኔ አለ
- ድሃ በጉልበቱ፣ ሃብታም በሀብቱ ፣ የተማረም በእውቀቱ ሀገርን ያቀናል እራሱም ይኖራል።
ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው።
ስለ ሰላም #መጸለይ ምንጊዜም አስፈላጊ ነው። ሰላም በሶስት ፊደል የተወሰነች ብትሆንም ዓለምን #የምትገዛ ሰላም ናት። ሰላም ዓለምን ይገዛል ምክንያቱም ሁሉም ነገር የሚስተካከለው በሰላም ስለሆነ።
ስለ ሰላም ምንጊዜም ቢሆን #ሁሉም_ኢትዮጵያዊ በያለበት ጸሎት ማድረግ አለበት፤ በጸሎት ሁሉም ነገር ይገኛልና። "
የፎቶ ባለቤት፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው + ኢጃት (አዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል - ' የአእላፋት ዝማሬ ' - በኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ)
@tikvahethiopia

ℹ️ ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው #ከሁለት_ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል። የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች ፦ -…
ℹ ዛሬ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት " በሚል ወደ ኤርትራ፣ አስመራ መጓዛቸው ተሰምቷል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " በሁለቱ ወንድማማች አገራት " የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመምክር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ብሏል።
በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።
ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር ማግኘት መንገድ ይጠርጋል የተባለውን የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲይ ፕሬዝዳንቱ ወደ ተተለያዩ ሀገራት መሪዎች የስልክ በመደወል ውይይት ሲያደርጉ መሰንበታቸው ተሰምቷል።
ከማንም በፊት በቅድሚያ የደወሉላቸው ለግብፁ መሪ አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሲሆን ከዛ በኃላ ከኳታር ኤሚር፣ ከኡጋንዳው መሪ ፣ ከቱርክ እንዱሁም ከአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ እና የደኅንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጋር መክረዋል።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ባደረገችው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ማንም የሚጎዳ አካልና #ሀገር ፤ የተጣሰ ህግና የተሰበረም እምነት እንደሌለ አሳውቃለች።
እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር፣ የቆዳ ስፋት እና እድገት ኖሯት የባህር በር አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ፣ ያለ አንዳች ግጭት እና ጦርነት በሰጥቶ መቀበል መርህ ጥቅሟን ለማስከበር እንደምትሰራ በተደጋጋሚ ገልጻለች።
ሀገራት ከበርካታ ሺህ ኪሎሜትሮች መጥተው በዚሁ ቀጠና ቤዝ ሲመሰርቱ ጥቅማቸው ለማስከበር መሆኑን የገለፀችው ኢትዮጵያ የቀጠናው ባለቤት የሆና እጆቿን አጣጥፋ የምትቀመጥበት ምክንያት እንደሌለ ገልጻለች።

" ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው " - የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ምክር ቤት የበድር መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ ሸይኽ አብዱ ያሲንን የግድያ ሁኔታ በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በምርመራ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገልጿል። ወንጀል የፈፀመውን አካል በማፈላለግ ረገድ ፖሊስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማህበረሰቡ በንቃት ጉዳዩን እንዲከታተል እና…
#ይፈለጋል #Wanted
" ... ሟች ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ፤ ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው የተባለ ግለሰብ መሆኑን ገልጿል።
ግለሰቡ #እጁን_እንዲሰጥም ፖሊስ አሳስቧል።
ፖሊስ ተጠርጣረው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አስተላልፏል።
የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ " የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበረ ሟቹ ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል። " ሲል አሳውቋል።
መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅ ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
በወንጀል የተጠረጠረ ግለሠብን መደበቅ ሆነ እንዲያመልጥ መተባበር የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስጠንቅቋል።

ℹ ዛሬ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት " በሚል ወደ ኤርትራ፣ አስመራ መጓዛቸው ተሰምቷል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ሐሰን ሼይክ ሞሐሙድ " በሁለቱ ወንድማማች አገራት " የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ለመምክር ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ብሏል። በቆይታቸውም ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ይመክራሉ ተብሏል። ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር…
ℹ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ሶማሌላንድ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈፀም መብትን የሚደግፍ እና የሶማሊያን መንግሥት ጣልቃ ገብነትን ውድቅ የሚያደርግ ውሳኔ አሳልፏል።
ሶማሌላንድን የራሴ አካል ናት የምትለውን ሶማሊያ እያቀረበች ያለውን የይገባኛል ጥያቄ #ውድቅ በማድረግም "የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ሉዓላዊነትና ነጻነቷ የተረጋገጠ ነው " ብሏል።
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ የመግባቢያ ስምምነትን ውድቅ የሚያደርግ ሕግ ፈርመው አፅድቀዋል። ፕሬዜዳንቱ ሕጉ " አንድነታችንን እና ሉዓላዊነታችንን እንዲሁም የግዛት አንድነታችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነው " ማለታቸው ተነግሯል።
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ግን የሶማሊያ መንግሥት እንቅስቃሴዎችን ውድቅ በማድረግ ሉዓላዊት ሀገር መሆኗን እየገለፀች ትገኛለች።
ሶማሊያ እያቀረበች ያለው ይገባኛል ሀሰት መሆኑን ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት አመታት መቆጠራቸውን፣ የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዬጵያ ጋር የተደረገው ስምምነት (MoU) ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲተረጎም የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለው እያሳወቀች ነው።
በሌላ መረጃ ፤ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ኤርትራ፣ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተቀብለዋቸዋል። ሁለቱ አካላት በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ተነግሯል።

ፎቶ ፦ #የኢትዮጵያ እና #የሶማሌላንድ ወታደራዊ አመራሮች ውይይት አደረጉ።
ዛሬ በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተገኝቶ ውይይት አድርጎ ነበር።
በውይይቱም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ #አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
Photo Credit - FDRE Defense Force

#MPESASafaricom
የመጀመሪያ የተረክ በM-PESA አሸናፊዎቻችን የባጃጅ እና የስልክ ሽልማታቸውን ተረክበዋል! ለአሸናፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላቹ!
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether