#መልዕክት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፦
" . . . ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ፍትሕ ይጐድላል፣ ፍትሕ ከጐደለ ብሶት ይፈጠራል፣ ብሶት ካለ ሰላም ሊኖር አይችልም።
በሁሉም የዓለማችን ክፍል ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚብሔር እየተዘነጋ በመሄዱ ቀውሱ ተባብሶ ይታያል፤ የሰው ልጅ ኑሮ በየትም ይሁን በየት በስጋት የተሞላ ሆኖአል፤ የሚወራው ሁሉ ስለ ግጭት ስለአየር ብክለት ስለ ረኃብና እልቂት ሆኖአል።
ዓለም የጉልበተኞችና የባለ ሀብቶች ብቻ እንድትሆን የተፈጠረች እስክትመስል ድረስ ከባድ የፍትሕ መዛባት አጋጥሞአታል፤ የዝቅተኛው ማኅበረ ሰብ ሰብአዊ መብት ተዘንግቶአል፤ ከዚህ አኳያ ዓለም በዚህ እስከ ቀጠለች ድረስ ሰላም የማግኘቷ ዕድል በጣም አጠራጣሪ ነው።
የክርስቶስ ልደት ያስተማረን ግን እንደዚህ አልነበረም፤ ጌታችን የተወለደው በተዋበና ምቹ በሆነ የሀብታም ቤት ሳይሆን #በከብቶች_በረት ነበረ፤ የተገለጠውም ለባለሥልጣኖች ሳይሆን ዝቅተኞች ለሚባሉ እረኞች ነበረ፤ ልዑላኑ ሰማያውያንና ትሑታኑ ምድራውያን በአንድነት አገናኝቶ ስለ #ሰላም በጋራ እንዲዘምሩ አደረገ፤ አሳዳጅ ሳይሆን ተሳዳጅ ሆኖ በግብጽ አገር በመንከራተት አደገ፤ ይህን ሁሉ ያደረገው እኛ እሱን እያየን እንደ ሰንደቅ ዓላማ እንድንከተለው ነበር።
ጌታችን ከባለሥልጣናቱና ከባለሀብቶቹ ይልቅ በድሆቹ ደረጃ የተወለደው ለድሆቹና ለዝቅተኞቹ ትኩረት እንድንሰጥ ለማስተማር ነው። የእኛ ድርጊት ግን #ግልባጩ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡
እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ብሎ፣ በስመ እግዚአብሔር ተሰይሞ፣ መስቀልን በአንገቱ ተሸክሞ የእሱ መሰል በሆነው ወይም መስቀል በተሸከመው ወንድሙ እና እኅቱ እንዲሁም በመሰል ፍጡር ላይ ያለ ርኅራኄ ሲጨክን መታየቱ ነው፤ እንዲህ እየሆነ እንዴት ሰላም ይምጣ? እግዚአብሔርስ እንዴት በረከቱ ይሰጣል? ይህ እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
እኛ ኢትዮጵያውያን ከእንዲህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የሞራል ዝቅጠት በአስቸኳይ መውጣት አለብን፤ ጠቡ፣ መለያየቱ፣ መጨካከኑ፣ ለኔ ለኔ መባባሉ ከረምንበት፤ ሆኖም ያመጣልን ነገር ቢኖር ሁለንተና ውድመት ብቻ ነው። ያስገኘልን ትርፍ ይህ መሆኑ እያወቅን በዚሁ ልንቀጥል አይገባም።
ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል ? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጐዳ ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን ? ሦስት ሺሕ ዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦች እንዴት ችግራቸውን በጠባይና በብልሐት ማስወገድ አቃታቸው ? ይህ ከቶ ሊሆን አይገባም።
ሁላችንም ሰከን ብለን እናስብ፤ ለሁሉም የማሰቢያና የመመካከሪያ ጊዜ ፈጥረን ችግሩን በስፍሐ አእምሮ እንፍታው፤ችግርን በምክክርና በይቅርታ መፍታት አማራጭ የሌለው ጥበብ ነው። የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ልኂቃን በዚህ ተግተን ልንሰራ ይገባል፤ መንግሥትና የፓለቲካ ፓርቲዎችም ለዚህ የበኩላቸውን ድጋፍ ያድርጉ፤ በዚህም ሰላማችንን እንመልስ፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ፦
" . . . የክርስቶስን መወለድ በአግባቡ ለማክበር ለሰው ልጆች ሕይወት፣ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንና ለእርሱ ቅዱስ ስፍራዎች ክብርን እንስጥ፡፡
ከራስ ወዳድነት መንፈስ እንውጣ በመላው አገራችን #ሞት_ይብቃ፣ #ሰላም_ይስፋፋ፡፡
የተራቡ ፣ የተጠሙ ፣ የታረዙ ፣ የተበደሉ፣ የታመሙና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን እናስታውስ፡፡
ከጎናቸው እንሁን እንርዳቸው እናጽናናቸው፡፡ ለኛ ምን ይደረግልን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ምን እናድርግ እንበል፤ መጠጊያ ለሌላቸው መሸሸጊያ እንሁንላቸው፡፡
የሚገለሉ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው እናድርግ፡፡ ዘመዳቸው እንሁን፡፡ ምክንያቱም የልደት በዓል ክርስቶስ ዘመዳችን እንደሆነ የሚያበሥረን በዓል ነውና፡፡
በልደት ምስጢር ማንም እንግዳ ሊሆን አይገባውም፡፡
እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ በግብጽ ባርነት ሳላችሁ በመገለል፣ በመማረር ኖራችኋል፡፡ ስለሆነም እንግዳ እንዳታማርሩ ይላል፡፡ ይህ ትልቅ የፈጣሪ ትዕዛዝ ነው፡፡ ሁላችንም ልናቀርበው የሚገባው ጥያቄ የሚከተለው ነው፡፡
‹‹እንግዳ አባርሬ ይሆን››? እንግዳን ከሚያዋርድ ሐሳብ፣ ትምህርት፣ መልዕክት ጋር ተባብሬ ይሆን? የእኔ ባሕል ሙሉ ስለሆነ ሌላውን መጫን፣ ማግለል አለብኝ ብዬ ይሆን ? ይህ ዓይነት ሐሳብ ከእግዚአብሔር ቃል እንደሚርቅ ተረድቼ ይሆን? ከእንደዚህ ዓይነት ሐሳብ ለመውጣትስ ምን ማድረግ ይገባኛል ልበል፡፡
ከዚህ ሐሳብና ይህ ዓይነት ሐሳብ ከሚገለጥባቸው ተግባራት ነፃ መውጣት የምንችለው ወደ ገና በዓልና ወደ ትንሣኤ ምስጢር ስንቀርብ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ሰማይና ምድር ከእኛ ጋር አብረው ለታላቁ ጌታ ታላቅ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ "

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዜዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ፦
" . . . በዓለማችን #የሰላም ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በራሱና በሰው ልጆች መካከል፤ እንዲሁም በሰው ልጆች መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ ሰላምን ለማውረድ ያደረገውን ማሰብ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ምሳሌነት ለመከተል መወሰንን ይጨምራል፡፡
በተለይም በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የሚታዩት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተወግደው ሰላም እንዲሰፍንና አገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ መላው የአገራችን ሕዝቦችና ሕዝበ ምዕመኑ እንደወትሮው የእግዚአብሔር አምላካችንን ጣልቃ ገብነት ተግተው መለመንና አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች ለሚነሱ አዳዲስ ግጭቶችም ሆነ ለሰነበቱት አለመግባባቶች ዋነኛ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው #በሰላማዊ_መንገድ ተቀራርቦ መመካከርና መነጋገር ብቻ እንደሆነና የትጥቅ ፍልሚያ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ታምናለች፡፡
የሰው ልጆች አብረው በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ የሰላም ወንጌልን ትሰብካለች፡፡ ከሰላም እጦት የተነሳ የሚፈጠረውን ሞትና እንግልት ትቃወማለች፤ በበኩልዋም ችግሮች ሲፈጠሩ ለእርቅና ለሰላም ጥረቶች የምትጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆንዋንም በየጊዜው ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም ራስዋ በየጊዜው በተለያዩ ታጣቂ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ቀጥታ ተጠቂ የሆነችባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡
ለዚህም በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ ንጹሐን ምዕመናኖቻችን ላይ የደረሰው የጅምላ ግድያ በማሳያነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ በጊዜው ድርጊቱን ከመቃወምና ከማውገዝ ባሻገር ሁኔታውን አስመልክቶ ክትትል እንዲደረግና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ጥሪ ማድረግዋ የሚታወስ ነው፡፡
አያይዛም እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ የትጥቅ ፊልሚያዎችን አቁሞ ለሰላማዊ ምክክር ዕድል መስጠት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነም አስታውሳለች፡፡
አሁንም ይህንኑ ጥሪ ደግማ ደጋግማ ማሰማትዋን ትቀጥላለች፤ ምዕመናንዋንም በዚሁ መስመር በጸሎት በማትጋት ላይ ትገኛለች፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም፤ እርሱ የምህረት ፊቱን ይመልስልናል፤ ሰላሙንም በእርግጥ ይሰጠናል፡፡ "

ቪድዮ፦ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ ላይ ሳለ #መስኮቱ_መገንጠሉን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከበረራ አግዶታል።
የአሜሪካው አላስካ አየር መንገድ በቁጥር 65 የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖቹን አግዷል።
እገዳው በበረራ ወቅት የአንደኛው አውሮፕላን መስኮት ተገንጥሎ አውሮፕላኑ በአስቸኳይ ለማረፍ ከተገደደ በኋላ ነው።
አርብ ዕለት በኦሬጎን ግዛት ከፖርትላንድ ከተማ ተነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የገጠመውን አደጋ ተከትሎ ከ35 ደቂቃዎች በረራ በኋላ በመነሻው ለማረፍ ተገዷል።
አየር መንገዱ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩት 177 ተሳፋሪዎች እና ሠራተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው አውሮፕላኑ #በሰላም አርፏል ብሏል።
የአደጋው መንስዔ እስኪጣራ ድረስ ሁሉንም 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከበረራ እንዳገደ አየር መንገዱ አስታውቋል።
ይህ ቦይንግ ሰራሹ አውሮፕላን ባለፉት ዓመታት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
ከአምስት ዓመት በፊት #በኢትዮጵያ እና #ኢንዶኔዢያ ባጋጠመ አደጋ ምክንያት ከበረራ ታግዶ የነበረው ይህ ማክስ 737 ዝርያ መሆኑ ይታወቃል። #BBC

#AddisAbaba
ሸይኽ አብዱ ያሲን በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ተገደሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 " አስኮ አዲስ ሰፈር " የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ትላንት ምሽት ላይ ከዒሻ ሰላት በኃላ " ባልታወቁ ሰዎች " በተተኮሰባቸው ጥይት የራስ ቅላቸውን ተመተው ህይወታቸው አልፏል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፤ መንግስትና ባለድርሻ አካላት አስቸኳይ የማጣራት ተግባር በማድረግ የኢማሙን ገዳይ ለሕግ እንዲያቀርቡ እንዲሁም ህብረተሰቡ የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ምርመራ አጋዥ ሊሆን የሚችል መረጃ በማቀበል የኢማሙ ገዳዮች እንዲታወቁ ለህግ እንዲቀርቡ የበከሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፏል።
ምክር ቤቱ አሳዛኝ እና አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ኢማም ሼይኽ አብዱ ያሲን አላህ እንዲምራቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ እንዲያደርግላቸው፣ የሸሂድነትን ማዕረግም እንዲያጎናፅፋቸው እንዲሁም ለቤተሰባቸውና ለመላው ሙስሊም ማህበረስሰብ መፅናናትን እንዲሰጥ አላህን ተማፅኗል።
የስርዓተ ቀብር ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ ይፋዊ መረጃ ይሰጣል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ሸይኽ አብዱ ያሲን በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ተገደሉ። በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 " አስኮ አዲስ ሰፈር " የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ትላንት ምሽት ላይ ከዒሻ ሰላት በኃላ " ባልታወቁ ሰዎች " በተተኮሰባቸው ጥይት የራስ ቅላቸውን ተመተው ህይወታቸው አልፏል።…
#Update
ትናንት ምሽት ከዒሻ ሶላት በኋላ አስኮ አዲስ ሰፈር ከሚገኘው በድር መስጂድ ወደ ቤታቸው እያመሩ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ከጀርባ ጭንቅላታቸውን ተመተው የተገደሉት የመስጂዱ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ስርዓተ ቀብራቸው በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ይፈፀማል።
ዙህር ላይ ሲያስተምሩበት በነበረው በበድር መስጅድ ሶላተልጀናዛ ተሰግዶባቸው የቀብር ስነ ስርዓታቸው ከዙህር በኋላ ነው የሚፈፀመው።
ምዕመናን በቦታው በመገኘት በሸይኽ አብዱ ያሲን ሽኝት ላይ እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።
የሸይኽ አብዱ ያሲንን ግድያ እጅግ " በጣም አሳዛኝ እና አስደንጋጭ " ሲል የገለፀው የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፤ መንግስትና ባለድርሻ አካላት አስቸኳይ የማጣራት ተግባር በማድረግ ገዳዩን ለሕግ እንዲያቀርቡ አሳስቧል።
ህብረተሰቡም የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ምርመራ አጋዥ ሊሆን የሚችል መረጃ በማቀበል የኢማሙ ገዳዮች እንዲታወቁና ለህግ እንዲቀርቡ የበከሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፏል።

#Update ትናንት ምሽት ከዒሻ ሶላት በኋላ አስኮ አዲስ ሰፈር ከሚገኘው በድር መስጂድ ወደ ቤታቸው እያመሩ ማንነቱ ባልታወቀ አካል ከጀርባ ጭንቅላታቸውን ተመተው የተገደሉት የመስጂዱ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ስርዓተ ቀብራቸው በኮልፌ የሙስሊም መቃብር ይፈፀማል። ዙህር ላይ ሲያስተምሩበት በነበረው በበድር መስጅድ ሶላተልጀናዛ ተሰግዶባቸው…
" ፖሊስ ምርመራ ላይ ነው " - የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ምክር ቤት
የበድር መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ ሸይኽ አብዱ ያሲንን የግድያ ሁኔታ በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በምርመራ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገልጿል።
ወንጀል የፈፀመውን አካል በማፈላለግ ረገድ ፖሊስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማህበረሰቡ በንቃት ጉዳዩን እንዲከታተል እና ጥቆማዎችን በማድረስ አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ እንዲያደርግ ጥሪ ተላልፏል።
ም/ቤቱ ፤ ወንጀለኛውን ለማጋለጥ እና ለህግ ለማቅረብ ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ እንደሚሰራ አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፤ ሸይኽ አብዱ ያሲንን ስርዓተ ቀብር በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ተፈፅሟል።
በስርዓተ ቀብር ወቅት በተላለፈ መልዕክት ትክክለኛው የግድያው ምክንያት ሳይጣራ ያልተረጋገጡና የምርመራ ሂደቱን የሚያበላሹ መረጃዎችን ከማሰራጨት መቆጠብ ይገባል ተብሏል።
በተጨማሪ ፤ ሼይኽ አብዱ ያሲን የቲም ልጆች አሳዳጊ የነበሩና ከመሞታቸው በፊት እዳ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን ህዝበ ሙስሊሙ ዕዳቸውን በመክፈል እና ከየቲም ልጆቻቸው ጎን እንዲቆም ጥሪ ቀርቧል።
Photo Credit - Harun Media