TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የበዓል መዋያ ስጦታ ተበረከተ

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በዋናው መስሪያ ቤት የበዓል መዋያ ስጦታ አበርክቷል፡፡

ስጦታው የተበረከተላቸው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ ሰባት የሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋውያን እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ባንኩ ላደረገላቸው የበዓል መዋያ ስጦታ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ “ለጋራ ስኬታችን” በሚል መሪ ቃል የዛሬውን ጨምሮ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ምንጭ፡ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቴሌግራም ገፅ

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጰያ 
ለጋራ ስከታችን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #BankInEthiopia #Bank #gena #genaholiday
👏31362😭17😢10🕊8😡7🥰5🙏5😱2
የገናን በዓል ፏ እያልን በአብሮነት እናሳልፍ። መልካም የገና በዓል ይሁንልን!
151🙏25😡15🕊10👏3😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ #የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ (MOU) ይዘት ምን ይላል ? አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦ - #ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ስታደርግ እንደነበረው፤ ከሶማሌላንድም ጋር ከዚህ በፊት እንደነበረው አይነት ስምምነቶችን ያነሳና ይሄ ስምምነት ወደተሟላ ደረጃ መድረስ እንዳለበት ያስቀምጣል። - ኢትዮጵያ አሁን ያለባትን ስጋት እንድትቀርፍ የህዝብ እድገቷን ፣ የኢኮኖሚ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው የመግባቢያ ስምምነት አደጋ ይዞ ይመጣል ?

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ያለ አንዳች ግጭት፣ ውጊያ ከባለቤቶቹ ተደርጓል ያሉት የመግባቢያ ስምምነት አደጋ እንደማያመጣ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦

" ኢትዮጵያ የባህር በር የላትም፤ እድገቷ በጣም ጨምሯል። በዙሪያዋ የሚተናኮሳት ፤ እሷን መተናኮስ ባይፈልግም እርስ በእርስ ሲተናኮስ ፍንጣሪው የሚደርስበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

እጇን አጣጥፋ ተቀመጠች እንበል ... በቃ ጅቡቲ ብቻ ምንም እንዳትሆን እንፀልይ ፣ የጅቡቲ መንገድም ምንም እንዳይሆን እንፀልይ ብሎ መንግሥት ቢቀመጥ የኢትዮጵያን ዋስትና ያረጋግጥ ነበር ወይ ብሎ መከራከር አለባቸው ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች።

ወይም ኢትዮጵያ በዚህ መንገድ ሳይሆን ከዚህ በተሻለ ሌላ አማራጭ ልታገኝ ይገባ ነበር ብለው ማምጣት አለባቸው።

የአንዳንድ ሰዎችን ንግግር እየታዘብኩት ያለው የዛሬ ስንት ዓመት የሆነ መንግሥትን ወቅሰው የኢትዮጵያን የባህር በር አሳጣ ብለው ፤ የሆነ አካልን ወቅሰው በዚህ ምክንያት ' ግማሽ ትውልድ ቢያልቅም መዋጋት አለብን ' ይሉ የነበሩ ሰዎች አሁን ደግሞ ያለ ውጊያ በንግድ ሂሳብ ያለንን ሰጥተን የሌለንን ለማግኘት የሚደረግ ስምምነትን አደጋ ያመጣል ይላሉ።

' ግማሽ ትውልድ ቢያልቅም ችግር የለም ልዋጋ ' የሚል ሰው እንዴት ብሎ ነው ያለ ውጊያ በጋራ የመግባቢያ ሰነድ ፣ ከባለቤቶቹ ጋር በሚደረግ ትብብር የሚደረግ ፊርማ ኢትዮጵያ ላይ አደጋ የሚያመጣው ?

የህዳሴ ግድብን ስንገነባ አደጋ ያመጣል፣ ያጋጨናል፣ ያዋጋናል፣ ስለዚህ ምናለ ትንንሽ ወንዞችን ብናለማ ያሉ ሰዎች አሁን ከለማ በኃላ አደጋ አልመጣም። እንደውም ተጨማሪ አደጋ መከላከል የምትችልበትን አቅም ነው የፈጠረችው።

የባህር በር ቢኖረን ተጨማሪ ጉዳት ሊደርስብን የማይችልበትን አቅም ነው የሚፈጥረው። ሁለት ሶስት አራት አምስት እራሳችን የምናለማው ወደብ ቢኖረን ቤዝ ቢኖረን እራሳችን የምንቆጣጠረው እራሳችን ኢንቨስት ያደረግንበት ቢኖረን የተሻለ አማራጭ ነው የሚኖረን። የተሻለ የመከላከል ፣ የተሻለ በቀላል ዋጋ ንግዳችንን የማሳለጥ ፣ በቀላሉ አቅማችንን የማጎልበት እድል ነው የሚፈጠረው።

እኛስ ጎረቤቶችን ነን የቀጠናው ባለቤቶች ነን፤ ከበርካታ ሺህ ኪሎሜትሮች መጥቶ ቤዝ ያለው ሀገር ነገር ፍለጋ አይደለም የመጣው ግን ጥቅሙን ለማስከበር ነው የመጣው እኛ ባለቤቶቹ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥና ሌሎች እስኪወስኑ ድረስ ለእነሱ እንፀልይ የሚል ትውልድና ግለሰብ ስለኢትዮጵያ ጥቅም፣ በአጠቃላይ ስለ ብሄራዊ ጥቅም ተገቢ ግንዛቤ፣ ተገቢ ቁርጠኝነትና ይሁንታ ኖሮት ነው የሚናገረው ማለት ይከብዳል። "

@tikvahethiopia
👏761😡170140🙏24🕊23🥰10😱8😭8😢5
#EOTC

በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ #ወጣት የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በዝማሬ እና በፀሎት አክብሮ ውሏል።

" ጃንደረባው ትውልድ " በተሰኘ ማህበር አዘጋጅነት በተዘጋጀ " የአእላፋት ዝማሬ " የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሃ ግብር እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን አብዛኛው #ወጣት በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በልዩ #በሃማኖታዊ ስነስርዓት ተቀብሏል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም  የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ሌሎች ብፁዓን አባቶች ተገኝተው ነበር።

" የጃንደረባው ትውልድ ማኅበር " በቅርቡ በመንበረ ፓተርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የማኅበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ የእውቅና ምሥክር ወረቀት ማግኘቱ ተነግሯል።

ፎቶ፦ TMC / ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
5.29K🙏236👏102🥰96🕊76😡47😱17😭17😢3
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC በአዲስ አበባ ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦርቶዶክሳዊ #ወጣት የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማን በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በዝማሬ እና በፀሎት አክብሮ ውሏል። " ጃንደረባው ትውልድ " በተሰኘ ማህበር አዘጋጅነት በተዘጋጀ " የአእላፋት ዝማሬ " የሚል ስያሜ በተሰጠው መርሃ ግብር እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን አብዛኛው #ወጣት በቤተክርስቲያን ተገኝቶ የኢየሱስ…
" እስከዛሬ ድረስ ልጆቻችን በዓልን ምክንያት በማድረግ የማይገባ ቦታ እያከበሩ ነበር " - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ በአዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል በነበረ የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋዜማ " የአእላፋት ዝማሬ " የተሰኘ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር።

በንግግራቸውም ፤ " እስከዛሬ ድረስ #በልደት#በትንሳኤ ምክንያት እየተደረገ ልጆቻችን ወደማይገባ ቦታ እያከበሩ ነበር " ብለዋል።

በመሆኑም የልደት በዓልን ወደ ቤተክርስቲያን በመምጣት አምልኮ እየተፈፀመ፣ በዝማሬ ፣ በምስጋና እንዲከበር " ልደትን በልደት ቦታችን ቤተክርስቲያን ይከበር " በማለት መምህር ሄኖክ ያደረጉትን ጥሪ በመስማት ምዕመናን በስፍራው መገኘታቸውን ገልጸዋል።

መምህሩ ላደረጉት ተግባርም ብፁዕነታቸው ምስጋና አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ፤ መርሀግብሩ በመስቀል አደባባይ እና በጃንሜዳ ሊደረግ ታስቦ እንደነበር ነገር ግን ከወቅቱ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከመንግሥት ጋር በመቀራረብ ንግግርና ውይይት ተደርጎ ለዚህ ዓመት በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል እንዲከበር መደረጉን ብፁዕነታቸው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
4.87K🙏296👏80🥰77🕊77😡37😭17😱10😢8
#TikvahEthiopia

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት አደረሳችሁ ! መልካም በዓል !

Baga Guyyaa Ayyaana Dhaloota Iyyasuus Kiristoosin Ishin gahe ! AYYAANA GAARII !

እንኳዕ ንባዓል ልደተ ክርስቶስ ብሰላም ኣብፀሐኩም ! ርሑስ በዓል ልደት !

@tikvahethiopia
437🙏64😡20🕊10😢4🥰3😭3😱2
#መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፦

" . . . ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ፍትሕ ይጐድላል፣ ፍትሕ ከጐደለ ብሶት ይፈጠራል፣ ብሶት ካለ ሰላም ሊኖር አይችልም።

በሁሉም የዓለማችን ክፍል ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚብሔር እየተዘነጋ በመሄዱ ቀውሱ ተባብሶ ይታያል፤ የሰው ልጅ ኑሮ በየትም ይሁን በየት በስጋት የተሞላ ሆኖአል፤ የሚወራው ሁሉ ስለ ግጭት ስለአየር ብክለት ስለ ረኃብና እልቂት ሆኖአል።

ዓለም የጉልበተኞችና የባለ ሀብቶች ብቻ እንድትሆን የተፈጠረች እስክትመስል ድረስ ከባድ የፍትሕ መዛባት አጋጥሞአታል፤ የዝቅተኛው ማኅበረ ሰብ ሰብአዊ መብት ተዘንግቶአል፤ ከዚህ አኳያ ዓለም በዚህ እስከ ቀጠለች ድረስ ሰላም የማግኘቷ ዕድል በጣም አጠራጣሪ ነው።

የክርስቶስ ልደት ያስተማረን ግን እንደዚህ አልነበረም፤ ጌታችን የተወለደው በተዋበና ምቹ በሆነ የሀብታም ቤት ሳይሆን #በከብቶች_በረት ነበረ፤ የተገለጠውም ለባለሥልጣኖች ሳይሆን ዝቅተኞች ለሚባሉ እረኞች ነበረ፤ ልዑላኑ ሰማያውያንና ትሑታኑ ምድራውያን በአንድነት አገናኝቶ ስለ #ሰላም በጋራ እንዲዘምሩ አደረገ፤ አሳዳጅ ሳይሆን ተሳዳጅ ሆኖ በግብጽ አገር በመንከራተት አደገ፤ ይህን ሁሉ ያደረገው እኛ እሱን እያየን እንደ ሰንደቅ ዓላማ እንድንከተለው ነበር።

ጌታችን ከባለሥልጣናቱና ከባለሀብቶቹ ይልቅ በድሆቹ ደረጃ የተወለደው ለድሆቹና ለዝቅተኞቹ ትኩረት እንድንሰጥ ለማስተማር ነው። የእኛ ድርጊት ግን #ግልባጩ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ብሎ፣ በስመ እግዚአብሔር ተሰይሞ፣ መስቀልን በአንገቱ ተሸክሞ የእሱ መሰል በሆነው ወይም መስቀል በተሸከመው ወንድሙ እና እኅቱ እንዲሁም በመሰል ፍጡር ላይ ያለ ርኅራኄ ሲጨክን መታየቱ ነው፤ እንዲህ እየሆነ እንዴት ሰላም ይምጣ? እግዚአብሔርስ እንዴት በረከቱ ይሰጣል? ይህ እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን  ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከእንዲህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የሞራል ዝቅጠት በአስቸኳይ መውጣት አለብን፤ ጠቡ፣ መለያየቱ፣ መጨካከኑ፣ ለኔ ለኔ መባባሉ ከረምንበት፤ ሆኖም ያመጣልን ነገር ቢኖር ሁለንተና ውድመት ብቻ ነው። ያስገኘልን ትርፍ ይህ መሆኑ እያወቅን በዚሁ ልንቀጥል አይገባም።

ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል ? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጐዳ ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን ?  ሦስት ሺሕ ዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦች እንዴት ችግራቸውን በጠባይና በብልሐት ማስወገድ አቃታቸው ? ይህ ከቶ ሊሆን አይገባም።

ሁላችንም ሰከን ብለን እናስብ፤ ለሁሉም የማሰቢያና የመመካከሪያ ጊዜ ፈጥረን ችግሩን በስፍሐ አእምሮ እንፍታው፤ችግርን በምክክርና በይቅርታ መፍታት አማራጭ የሌለው ጥበብ ነው። የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ልኂቃን በዚህ ተግተን ልንሰራ ይገባል፤ መንግሥትና የፓለቲካ ፓርቲዎችም ለዚህ የበኩላቸውን ድጋፍ ያድርጉ፤ በዚህም ሰላማችንን እንመልስ፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
1.9K🕊90🙏63😡35👏32🥰9😢3😭3