TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከሌላ አከባቢ መጥቶ በከተማው ስልፍ አደርጋለሁ ማለት ህልም ነው " - የመቐለ ከተማ አስተዳደር

የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ "ለእሁድ ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም የተፈቀደ ይሁን የሚካሄድ የምናውቀው ሠልፍ የለም " ሲል አስታወቀ።

የመቐለ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካህሳይ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ ለታህሳስ 21 /2016 ዓ.ም በከተማው የተፈቀደ ይሁን እንዲካሄድ የታቀደ የምናውቀው ሰልፍ የለም ብለዋል። 

" ህዝብ እንደ ወትሮ በመበደኛ ስራውና ጉዳዩ መዋል አለበት " ያሉት ምክትል ከንቲባው ፤ " የከተማው አስተዳደር ቃል ጥሶ ያልታወቀና ያልተፈቀደ ጉዳይ (ሰልፍ) አካሂዳለሁ በሚል ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ምክትል ከንቲባው አክለው ፤ " የተባለውን የማያከብር ማንኛውም አካል እንደማንታገስ ማሳወቅ እንፈልጋለን " ብለዋል።

ውሳኔው የአስተዳደሩ ኮሚቴ መሆኑ የገለፁት አቶ ኤልያስ ፤ ከሌላ አከባቢ መጥቶ ሰልፍ የሚያደርገውን አካል ስምና ማንነቱ ባይጠቅሱም " ከሌላ አከባቢ መጥቶ በከተማው ስልፍ አደርጋለሁ ማለት ህልም ነው " ብለዋል።

" በተለያዩ ሚድያዎች እየቀረቡ የተዛቡ መረጃ ይሰጣሉ " ላሏቸው አካላት ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ ያስጠነቀቁት ምክትል ከንቲባው ፤ " ህዝቡ ካልተረጋገጡ አሉባልታ ወሬዎች በመራቅ ስራው ማከናወን አለበት " ብለዋል። 

መረጀውን የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የላከልን።

@tikvahethiopia            
@samcomptech

አሁንም አዳዲስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ብዛትም ጥራትም በአንድ ቦታ እኩል የተገናኙበት የላፕቶፕ መደብር አለን። ሁሉንም አይነት የላፕቶፕ  ይዘን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ታላቅ ቅናሽ አዘጋጅነት እየጠበቅንዎ ነው።

ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች፣ ለጌመሮች፣ ለቪዲዮ፣ ኤዲተሮች ፣ ለግራፊክስ ሰሪዎች፣ ለዲዛይነሮች አዳዲስ ላፕቶፕች እና ስልኮች በቅናሽ ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይዘን ቀርበናል። @samcomptech

በሚገርም ፍጥነት ፣ ቅለት እና ከ 10 ሰሀት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖች አሉን ፦

ቴሌግራም 👉https://t.iss.one/samcomptech

☎️ 0928442662/ 0940141114
@sww2844
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የፊታችን ቅዳሜ (ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ/ም) ለመንግስት ሰራተኞች ፈተና ይሰጣል። ይኸው ፈተና የስነ ምግባርና የክህሎት ክፍተቶችን ለመለየት የሚካሄድ የምዘና አካል እንደሆነ የከተማው አስተዳደር ገልጿል። የቅዳሜው የምዘና ፈተና #ከዳይሬክተር እስከ #ፈጻሚ ሰራተኞች ያሉትን እንደሚያካትት ተመላክቷል። በተሰማሩባቸው ስራዎች ተገቢውን እውቀት፣ ክህሎትና ስነምግባር…
" 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተና ወስደዋል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

የመንግስት ሰራተኞች የብቃይ ምዘና ፈተና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ፈተናውን 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተናቸውን ወስደዋል።

ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው መሆኑን ያስታወሰው ቢሮው ፈተናው በቀጥታ ከተቋማት ሪፎርም ጋር የተያያዘ መሆኑን አመልክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

• " ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ ተከስቷል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

• " በትግራይ ክልል የተከሰተዉ ድርቅ ' በ1977 ተከስቶ ከነበረው ድርቅ ጋር ወደሚስተካከል ደረጃ እየደረሰ ነው ' በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ የፌዴራል መንግሥቱና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ ለመግታት እጃቸውን እንዲዘረጉ በይፋ ጠይቀዋል።

አቶ ጌታቸው ባሰራጩት መግለጫ በክልሉ ያለው ድርቅ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ጠቅሰዋል።

" በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው "  ያሉት ፕሬዝደንቱ ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ ድርቅ መከሰቱን ተናግረዋል።

አሁን የተከሰተው ድርቅና ረሃብ በትግራይ የነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ተደማምረው ከፍተኛ አደጋ ሊያደርሱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የትግራይ ኢኮኖሚ መቃወስ፤ የክልሉ መሠረት ልማቶች በተለይ የጤና ተቋማት መውደማቸው እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው የትግራይ ክልል ነዋሪዎችን ለከፍ ችግር ማጋለጡን አስሀንዝበዋል።

" ስለዚህ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌዴራል መንግሥትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በትግራይ እያንዣበበ ያለውን ረሃብና ሞት ለመታደግ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል " ብለዋል።

" ረሃብ ድምፅ አልባ ገዳይ መሣሪያ ነው " ያለቱ አቶ ጌታቸው የፌዴራል መንግሥቱና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ " ይህን ገዳይ መሣሪያ ለማጥፋት " የበኩላቸውን አድርገዋል ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን ደግሞ እያንዣበበ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ለመግታት የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ከ1977 ቱም የከፋ ነው ማለቱ ይታወሳል።

ከዚህ ቀደም ቃላቸውን የሰጡ በእድሜያቸው የገፉ የትግራይ ነዋሪዎች አሁን የተከሰተው ድርቅ ከ1977ቱ የከፋ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ የፌዴራል መንግሥት " በትግራይ ክልል የተከሰተዉ ድርቅ ከ1977ቱ ድርቅ ጋር ወደሚስተካከልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው " የሚባለው ፍፁም የተሳሳተ ነዉ ብሏል።

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ፤ " በትግራይ ክልል የተከሰተዉ ድርቅ በ1977 ተከስቶ ከነበረው ድርቅ ጋር ወደሚስተካከል ደረጃ እየደረሰ ነው" በሚል የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም የተሳሳተ ነው ሲሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

እንደዚህ አይነት ቁዉስ ሲፈጠር ማወጅ ያለበት በፌደራል መንግስት በኩል የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፤ ምክር ቤቱ በትግራይ ክልል በአራቱ ዞኖች ድርቅ መከሰቱን ቢያረጋግጥም ከ1977ቱ ድርቅ ጋር ይስተካከላል የሚል ማረጋገጫ እስካሁን አለመውጣቱን ገልጸዋል፡፡

መንግስት አሁን ላይ ለትግራይ ክልል በቂ የሆነ የምግብ አቅርቦት እያቀረበ ይገኛል ብለዋል።

@tikvahethiopia
ለማንኛውም ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን ለሚመለከቱ ጥያቄና አስተያየትዎ ነፃ የጥሪ መስመራችንን (8118) ይጠቀሙ፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

#Global_Bank_Ethiopia #OurSharedSuccess #CallCenter #CustomerService #CustomerServiceLine #8112
አዲስ መኪና የማሸነፍ እድል እንፈልጋለን? M-PESA ላይ በቀላሉ እንመዝገብ እና በM-PESA ግብይቶችን ፈፅመን አዲሱን መኪና የግላችን እናድርግ

የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
#ሆሮጉድሩወለጋ

• " ... የተፈፀመው ጥቃት የድሮን ነው። በዚህም በቤተክርስትያኒቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ የበቆሎ እርሻ ውስጥ ምርት በመሰብሰብ በላይ የነበሩ ሰዎች ተገድለዋል " - ፓስተር ተካልኝ ዳባ

• " ተፈፅሟል የተባለው የድሮን ጥቃት ፍጹም ሐሰት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ባለችው የሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በደረሰ "ድንገተኛ ጥቃት " አባላቶቿ መገደላቸውን አውግዛለች።

ጥቃቱ ታህሳስ 15 የተፈፀመ ሲሆን በጥቃቱ 8 የቤተክርስትያኒቷ አባል የሆኑ ግለሰቦች ተገድለዋል። 5 ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ይገኛሉ።

የሆሮ ጉዱሩ አካባቢ የሙሉ ወንጌል ኃላፊ የሆኑት ፓስተር ተካልኝ ዳባ ምን አሉ ?

- ታሕሳስ 15 ቀን 2016 በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በቤተክርስትያኒቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ የበቆሎ እርሻ ውስጥ ምርት በመሰብሰብ በላይ የነበሩ ሰዎች ተገድለዋል።

- በጥቃቱ ሁለት የሦስተኛ እና የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተገድለዋል።

- በድሮን ጥቃቱ የቤተክርስትያኒቷን መሪ ጨምሮ፣ በአጠቃላይ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

የተገደሉት ዜጎች ስም ፦

• አቶ ሀብታሙ ንጋቱ - የአጥቢያዋ መሪ
• አቶ በየነ ጥቂ - የአጥቢያዋ ጥበቃ ሠራተኛ
• አቶ ጉደታ ፍጤ - ዲያቆን
• አቶ ታዴ መንገሻ - ዲያቆን
• ወጣት ዳመና ሊካሳ - የኪቦርድ ተጫዋች
• ተማሪ ዱጋሳ ዋኬኔ - የኪቦርድ ተጫዋች
• ተማሪ አብዲ ጥላሁን - ዘማሪ
• ተማሪ ኦብሳ ታረሳ - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል

ቆስለው በሆስፒታል ያሉት፦
• አቶ ታሜ ንጉሳ - የአጥቢያዋ መሪ አገልጋይ
• አቶ ፋጠኔ ገላና - ዲያቆን
• አቶ ስንታየሁ ታከለ - የጸሎት አገልጋይ
• ወ/ሮ ሽቱ ኢምሩ - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል
• ወ/ሮ ባጩ ገላና - የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል

በሌላ በኩል ፤ የቤተክርስትያኒቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ በሰጡት መግለጫ ፤ በአንድ በኩል ድርጊቱ በድሮን መፈፀሙ ሲዘገብ መንግሥት ደግሞ በድሮን የተፈፀመ እንዳልሆነና በአካባቢው ታጣቂዎች መፈፀሙን መግለፁን አስንተዋል።

" ድርጊቱ በየትኛውም አካል በምንም መልኩ ይፈጸም፤. . . .ጉዳዩ በማን እንደተፈጸመ ተጣርቶ ፍትህ እንዲሰፍን " እንፈልጋለን ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " በተመሳሳይ በአማራ ክልላዊ መንግሥት በዱር ቤቴ እንዲሁም በቡሬ ከተማ በአባሎቿ ላይ የሞት፥ የስደትና የንብረት ጉዳት "  መድረሱን ገልጸዋል።

በምዕራብ ኢትዮጵያም የአማኞችን ንብረት መውረስና መፈናቀል እየደረስ እንዳለ፣ ይህን የሰብዓዊ መብት መጣስና የዜጎችን ጉዳት የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲያጣራ ጠይቀዋል።

መጋቢ ላኮ ፤ " ገለልተኛ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ጉዳዩን በአንክሮ በማየት እንዲያጣራ እና እውነቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ " ጥሪ አቅርበዋል።

የመንግሥት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፣ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በባሮ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተፈፅሟል የተባለውም የድሮን ጥቃት " ፍጹም ሐሰት " ብለዋል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት እና የሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
#ኤዶ

በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ  በምትገኘው በሲዳማ ክልል፣ ወንዶ ገነት ወረዳ የኤዶ ቀበሌ በትላንትናው ዕለት አለመረጋጋት መፈጠሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከፀጥታ አከላት እንዲሁም ከነዋሪዎች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

" ኤዶ " በኦሮሚያ እና ሲዳማ አዋሳኝ የምትገኝ ቀበሌ ስትሆን ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ መሰል አለመረጋጋት ፣ መንገድ የመዝጋት፣ ንግድ እና ትራንስፖርት የማስተጓጎል ችግሮች ሲከሰቱ ነበር።

በተለይ አካባቢው ላይ ከዓመታት በፊት ህዝበ ውሳኔ ከተደረገ በኃላ ውጤቱን ተከትሎ አስተዳደራዊ መዋቅር ከተዘረጋ ወዲህ በተለያዩ ጊዜ መንገድ መዝጋቶችና አንዳንድ የብጥብጥ ሙከራዎች ሲደረጉ ይስተዋላል ብለዋል ነዋሪዎች።

በትናንትናው እለትም እንዲህ ያለዉ ሙከራ መሞከሩን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡና የቀበሌዋ እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል።

ወቅት እየጠበቀ በሚፈጠረው መሰል ችግር ሰዎች ስራ ወጥተው መግባት፣ መንገድ ሄደው መመለስ እንደሚቸገሩና የንግድ እንቅስቃሴ ክፉኛ እንደሚያስተጓጎል ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ የወንዶ ገነት ወረዳ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ፤  " በሲዳማ ክልል በውንዶ ገነት ወረዳ በኤዶ ቀበሌ ታሕሳሰ 19 ከቀኑ 4 ሰአት ጀምሮ መንገድ ዝግ ሆኖ ዛሬም ተዘግቶ ወሏል " ብለዋል።

" ኤዶ " ላይ ችግር መኖሩን ተከትሎ ነዋሪዎች በሻሸመኔ አድረገው ወደ ወንዶ ገነት ለመጓዝ መገደዳቸውን ለመረዳት ተችሏል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የወረዳዉ የጸጥታ ጉዳይ ተጠሪ አቶ ሀማሮ ሀይሶ እንደሚገልጹት ፤ በአንድ ትምህርት ቤት ዉስጥ የተጀመረ ረብሻ በመስፋቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ከመቋረጡ በላይ አንድ ሞተረኛ #ተጎድቶ ሆስፒታል መግባቱን የገለጹ ሲሆን ምሽቱን የሲዳማ ክልል የጸጥታ ኃይል ቀበሌዋን መቆጣጠሩንና የትራንስፖርት ችግሩ መፈታቱን ገልጸውልናል።

በትምህርት ቤት የተጀመረዉ ረብሻ ወደት/ቤቱ የሄዱ እንግዶች ላይ ተቃዉሞ መሰማቱን ተከትሎ የተጀመረ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ሀማሮ ይህን ችግር የሚያስጀምሩና የሚመሩ ጸረሰላም ወንጀለኞች እንደሚታወቁና በዚህና በሌሎች ወንጀሎች እንደሚፈለጉ ገልጸዋል።

ከዚህዉ ጋር በተያያዘ አስተያዬታቸዉን የሰጡን የአካባቢዉ ነዋሪና የጸጥታ አካል ደግሞ እንዲህ ያለዉ ሙከራ በተደጋጋሚ እየተሞከረ መሆኑን በማንሳት ችግሩን ከስሩ ለመፍታት በዛኛዉ በኩል  አጎራባች የሆኑ የኦሮሚያና በዚህኛዉም በኩል ያሉ የሲዳማ ቀበሌ ነዋሪዎች ዉይይት ያስፈልጋቸዋል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
የሹፌሮች ጉዳይ . . .

" በ2 ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ " - ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር

በጅማና በአዲስ አበባ ከተማ መካከል ‘አስጎሪ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሲያሽከረክሩ በነበሩ ሹፌሮችና ተሽከርካሪዎች ላይ ታጣቂዎች ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ/ም ጥቃት ማድረሳቸውን ስሜ ከመጠቀስ ይቆይ ያሉ የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዓይን እማኙ በሰጡት ቃል፣ “ ዓይኔ እያዬ ነው ሹፌሮቹን የገደሏቸው። ተሽከርካሪዎቹንም አቃጠሏቸው ” ሲሉ የተመለከቱትን አስረድተዋል።

ጥቃቱን የፈጸሙት እነማን እንደሆኑ፣ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ፣ ምን ያህል ተሽከርካሪዎች እንደተቃጠሉ እንዲገልጹ ጥያቄ የቀረበላቸው ታማኝ ምንጩ፣ ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እንደሆኑ፣ ሹፌሮች ከታጣቂዎቹ በተተኮሰ ጥይት እንደተመቱ፣ አንድ ሹፌር ሕይወት ማለፉን፣ ከ11 በላይ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን አብራርተዋል።

ስለ ሁኔታው ማብራሪያ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት የሹፌሮችን በታጣቂዎች እገታና ግድያ በጥልቀት በየወቅቱ የሚከታተለው ጣና የአሽከርካሪዎች ማኀበር (በማኀበራዊ ትስስር ገጹ “የሹፌሮች አንደበት) በበኩሉ፣ ማኀበሩ ባለው ክትትል መሠረት፣ “በሁለት ሳምንታት ብቻ ሰባት ሹፌሮች በታጣቂዎች ተገድለዋል። ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ የተገደሉት ወደ 70 ይደርሳሉ ” ብሏል።

ይህን ያሉት ማኀበሩን የሚመሩ አንድ ምንጭ አክለውም ሹፌሮች የተገደሉት በሰሜን ጎንደር ማክሰኝት፣ በመተሃራ፣ በቡታጅራ መስመር፣ በደሴ መስመር በኦሮሚያ ልዩ ዞንና በሌሎች አካባቢዎች መሆኑን አስረድተዋል።

“ ከቀናት በፊትም በኦሮሚያ ክልል በቡታጅራ መስመር ከአሥር በላይ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። አሽከርካሪዎችም በቅድሚያ  መንገዱን እያጣሩ መጓዝ አለባቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።

የታጣቂዎቹ ዋነኛ ፍላጎት ምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲያስረዱም፣ አንደኛ የገንዘብ ፍላጎት፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሰላምን ማወክ አላማቸው አድርገው በመነሳተቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ምን ቢደረግ መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ “ አሁን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር አለ። በፓርላማ እየቀረበ ‘ይህን ያህል አጓጓዝን፣ ይህን ያህል አመላለስን’ ይላል የተጓጓዘውን የአገሪቱን ምርት። በፓርላማ ግን ሹፌሮች ተገድለዋል ብሎ መናገር አለበት ” ብለዋል።

አክለውም፣ “ ችግሩ በሚስተዋልባቸው ክልሎች የተከሰቱትን ችግሮች እንዲስተካከሉ መጠየቅ ነበረበት። ያ ሲጠየቅ ግን አይስተዋልም ” ሲሉ ወቅሰዋል። ካልሆነ ግን አሽከርካሪዎች አድማ በምታት ከመንቀሳቀስ ተቆጥበው ሕይወታቸውን ማትረፍ ግድ ይላቸዋል ተብሏል።

በየወቅቱ የሚስተዋለውን ችግር በተመለከተና ለተነሳው ወቀሳ ምን ምላሽ እንዳለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ሚኒስቴር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።
 
ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia