TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አመራሮች በአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ተሰምቷል።

ውይይት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሲሆን ሰዓታትን የወሰደ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።

ከፍተኛ አመራሮቹ ከውይይቱ በኃላ ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ፦
- በእገታ ወንጀል፣
- በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣
- በተደራጀ ከባድ የዝርፊያ ወንጀል
- ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ የሜትር ታክሲዎችን ተጠቅመው #የሰው_ግድያ፣ የሞባይል ንጥቂያ እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
- በርካታ የሺሻ ማስጨሻ፣
- #የጭፈራ_ቤቶች እንዲሁም ሕገ-ወጥ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን አስረድተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን " የቁማር ቤቶች (betting) " ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን በእነዚህም ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን ገልጸዋል።

እነዚህ ወንጀሎች ለኅብረተሰቡ የፀጥታ ሥጋት በማይሆኑበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተከታታይ ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በየጊዜው ውጤቱ እየተገመገመ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

* የሜትር ታክሲ፣
* የሞተር ሳይክል
* የባጃጅ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲይዝ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራልም ያሉ ሲሆን በወንጀል ተሳትፈው ከተገኙ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይ ለሚካሄድ ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ለጥያቄና መልስ ውድድራችን ዝግጁ ነዎት?
3ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ታህሳስ 11 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!
https://t.iss.one/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#እንድታውቁት

ስትሮክ ፦

ስትሮክ በተለያየ ምከንያት ኦክስጅንን ለአእምሮ ሚያደርሰው የደም አቅርቦት ሲስተጓጎል እና በአንጎላችን ውስጥና ዙሪያው ባሉት ሽፋኖች ላይ የደም መፈሰስ ሲከሰት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡

መንስኤውስ ?

- ስትሮክን በደም ስር መደፈን  ወይም መዘጋት ምክንያት የሚመጣ (Ischemic stroke) እና በመድማት ምክንያት (hemorahgic stroke) ብለን ልንከፍለው እንችላለን።

1. Ischemic stroke የምንለው አእምሯችን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች በረጋ ደም አሊያም Atheroscleorsis በተባለ የደም ስር መጠንከር እና መጥበብ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሲዘጋ ሚመጣ የስትሮክ አይነት ሲሆን ይህም ሁለት አይነት ይችላሉ::Embolic የሚባልው ከአእምሮአችን ውጪ ከሌላ የሰውነታችን አካል በተለይ ከልብ፣በአንገት አካባቢ ካለ የደም ቧንቧ የረጋ ደም  ወደ አእምሯችን ሲሄድ እና አእምሯችን በቂ የሆነ ኦክስጅን የያዘ ደም እንዳያገኝ ሲያስተጓጎለው የሚፈጠር ሲሆን;ሁለተኛው ደግሞ thrombotic ሲባል ለአእምሮአችን ኦክስጅን እና ንጥረ ነገሮችን ሚያደርሰው የደምስር ውስጥ የደም መርጋቱ ወይም የደም ስሩ መጠንከሩ ሲፈጠር ነው።

2. Hemorrhagic stroke የምንለው አእምሮ ውሰጥ የደም ስር በተለያየ ምክንያት ሲፈነዳ እና ደም ወደ ጭንቅላታችን ሲፈስ ነው ይህም የሚፈሰው ደም ተጠራቅሞ አእመሮ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት ጫናው የደረሰበት የአእምሮ ክፍል ኦክስጅን እንዳያገኝ ሲሆን የሚከሰት የስትሮክ አይነት ነው።

- እንደ የደምግፊት፣ ስኳር፣ ከፍተኛ የኮሌስተሮል መጠን፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ የልብ ህመም ለስትሮክ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡

ምልክቶቹ ፦
° ድንገተኛ እና ሀይለኛ የእራስ ምታት
° የፊት እና የሰውነት በአንድ ጎን ወይም ሙሉ     በሙሉ  መደንዘዝ
° እራስን መሳት እና ሚዛንን ለመቆጣጠር መቸገር
° ግራ መጋባት
° ሽንትን እና ሠገራን መቆጣጠር አአለመቻል
° በትክክል መናገር አለመቻል

ስትሮክን ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል።

▪️የደም ግፊትን በመቆጣጠርና በየጊዜው በመከታተል
▪️ስኳርን በመቆጣጠርና በየጊዜው በመከታተል
▪️አልኮል በመቀነስ
▪️ሲጋራ ባለማጨስ
▪️የሰውነትን ክብደትን በመቆጣጠር ልንከላከለው እንችላለን ፡፡

- ለስትሮክ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት ከማገገማችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ቶሎ መታከም እጅግ ወሳኝ ነው።

- በምርመራ ወቅት የደም ስኳር መጠን፣ሙሉ የደም ምርመራ፣ የደም መርጋት ምርመራ፣የልብ ምርመራ፣በመጨረሻም CT scan እንደ አስፈላጊነቱ MRI በማዘዝ ትክክለኛውን የስትሮክ አይነት ማረጋገጥ ይቻላል።

☑️ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን ካሳየ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርበታል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ወ/ሮ ሜላተወርቅ እና አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መለየታቸው ተነገረ። በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ አመልክቷል። በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ…
#NEBE

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል ።

ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ የሾመው በ1 ድምፀ ተዓቅቦ በአበላጫ ድምፅ ነው።

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ማናቸው ?

- ወ/ሮ ሜላትወርቅ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት አዲስ አይደሉም። ቦርዱን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

- ለሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል።

- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ምርቋ ሜላትወርቅ የሥራ ሕይወታቸው የሚጀምረው በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ነው። በኮሚሽኑ ከጀማሪ የሕግ ኦፊሰርነት እስከ ኦፕሬሽን ኃላፊነት ድረስ ሰርተዋል።

- የኒው ጀኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተባባሪ መሥራችም ናቸው።

- የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ የሕግ ድርጅት አቋቁመው ነበር።

- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ከሰላም እና ደኅንነት ጥናቶች ተቋም (አይፒኤስኤስ) የማስተርስ ዲግሪያቸው ተቀብለዋል።

- ከአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በሕዝብ አስተዳደር ሌላ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው።

- በአካዳሚክ፣ በፖሊሲ እና በፐብሊክ ሴክትር ባለሙያነት፣ በሁለትዮሽ እና በዘርፈ ባለብዙወገን ስምምነቶች ተደራዳሪነት፣ በግልግል ዳኝነት አማካሪ በመሆን ሰፊ ልምድ እንዳላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።

ቀጣይ ምን ይጠብቃቸዋል ?

* የቀድሞዋ ሰብሳቢ ወ/ሪ ብርቱካን ሚደቅሳ ያላጠናቀቋቸው የቤት ሥራዎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።

* ቀዳሚው እና ትልቁ ያለፈው ምርጫ ባልተካሄደባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ምርጫ ማካሄድ ነው።

* ለሁለት ዓመት ጦርነት ሲካሄድበት በቆየው የትግራይ ክልል የፓርላማም የክልል ም/ ቤት ምርጫ አልተካሄደም። ክልሉ ላለፉት 3 ዓመታት በሕዝብ ተ/ም/ቤት ተወካይ የለውም። ቦርዱ በተያዘው 2016 ዓ.ም. በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ መያዙን ለፓርላማ አስታውቆ ነበር። መጪው የቦርዱ ሰብሳቢ ይህን ዕቅድ ያሳኩታል ወይ የሚለው በሂደት የሚታይ ጉዳይ ነው።

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫ ያልተደረገባቸው ቦታዎች አሉ።

- በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በፀጥታ ችግር ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎችም አሉ።

-  የአካባቢ ምርጫም ዋነኛ የቤት ሥራ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከህ/ተ/ም/ቤት እና ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው ያሰባሰበው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ' ኬኖ ' ለሚባለው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አልሰጠሁም " - የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

" ኬኖ " ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመስጠቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ ፤ ቤቲንግ ቤቶችና ሌሎችም ቁጥር በማስገመት ለሚያጫወቱት " ኬኖ " አስተዳደሩ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ ይህን ጨዋታ በሚያጫውቱ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብሏል።

በቀጣይም ጨዋታውን ሲያጫውቱ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡ 

" ኬኖ " ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች እያዘወተሩት የሚገኝና በብዛት ብራቸውን የሚከስሩበት የቁማር ዓይነት ነው፡፡

መረጃው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (EPA) ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል።

ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው።

ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል።

አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት  አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ ህይወቱ በመልካም ስነምግባሩና በተግባቢነቱ በርካቶች እንደሚያውቁት ለመረዳት ችለናል።

ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ ይፈፀማል።

ገዳይ እንዳልተያዘ ለመረዳት ተችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል፤ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ምርመራ ላይ መሆኑን ገልጾ ሲጠናቀቅ በሚዲያ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሺርካ

ባለፈው ህዳር ወር በርካታ ሰዎች በተገደሉበት ሺርካ ወረዳ ትላንት ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ/ም ግድያ መፈፀሙ ተሰምቷል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳ ጋላማ በሚባል አካባቢ ታህሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም 4 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂ  ኃይሎች መገደላቸውን የ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቢዥን " ምእመናን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አራቱ ምእመናን በጉዞ ላይ ሳሉ ከሚጓዙበት  መኪና በማስወረድ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተጠቁሟል።

ከሟቾች መካከል በሺርካ ወረዳ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአቋቋም  መምህር እንደሚገኙበት ተገልጿል።

እየተፈፀመ ያለውን ተከታታይ ግድያ ለማስቆም የመንግስት የጸጥታ አካል  ምንም አይነት እርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መሰል ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

ባለፈው ህዳር ወር ከጨቅላ ህፃን አንስቶ እስከ 70 ዓመት አዛውንት እንዲሁም በርካታ የአንድ ቤተሰብ አባላት በዚሁ ወረዳ መገደላቸው ይታወሳል።

ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን መንግስት በአሸባሪነት የፈጀውን ' ሸኔ ' (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።

ህፃን፣ አቅመ ደካማዎችን፣ ሴቶችን ሳይለይ #እየገደለ ያለው ይሄው ቡድን ነው ብሎ ነበር።

ታጣቂ ቡድኑ ግን ኃይላችን " በሰላማዊ ሰዎች ላይ እርምጃ አልወሰደም " በሚል ውንጀላውን አስተባብሎ የነበረ ሲሆን የክልሉ መንግሥት ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ብሎ ነበር።

በሺርካ ወረዳ ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ ውጥቶ በነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ላይ ፤ " የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑን ገልጸው መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ተማፅነው " እንደነበር መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
በአዲሱ Tecno Pop 8 ሁሉም ፎቶዎች ልዩ ናቸው!

አዲሱ Tecno ‘Pop 8’ ብርሃን በሌለበት ቦታ ቁልጭ አድርጎ ማንሳት እንዲችል 13 ሜጋ ፒክስል ፖርትሬት ካሜራ እና 8 ሜጋ ፒክስል ሰልፊ ካሜራ ከሁለት የፍላሽ ላይት ጋር አጣምሮ የቀረበ ሲሆን የፈለጉትን ፎቶ፣ ፊልም እና ጌም ያለገደብ መጠቀም እንዲችሉ ታስቦ 1ቴራ ባይት ኤክስቴንድድ ሚሞሪ ማካተቱ አገልግሎቱን በእጥፍ እንዲጨምር አድርጎታል!

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia
በVoLTE አዲስ ተሞክሮ
አሁን በነባሩ የ4G እና አዲሱ 5G ኔትወርክ ኩልል ባለ የድምጽ ጥሪ ያለ ተጨማሪ መተግበሪያ በቀጥታ ጥርት ያለ የቪዲዮ ጥሪ ያለተጨማሪ ክፍያ በነባሩ የድምጽ ጥሪ ዋጋ ማድረግ ተችሏል።

ምን ይሄ ብቻ በስልክዎ እየተነጋገሩ ኢንተርኔት ሳይቋረጥ መጠቀም ይችላሉ።

ምን ላድርግ አላሉም እኛ አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችሉ ስልኮች ላላቸው ደንበኞቻችን በሙሉ አቅርበናል የአንድሮይድ ተጠቃሚ ከሆኑ ቨርዥኑ ከ9 በላይ መሆኑን ያረጋግጡ።

ለተጨማሪ መረጃ : https://bit.ly/48q2myG

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል። ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው። ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት  አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ…
#ግድያ #የፖሊስ_ምላሽ

" ፖሊስ ሥራውን እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ መዝናኛ 'በጥይት ተመትቶ ተገደለ' መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " ብለዋል።

ኮማንደሩ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ሰው ወዲያው እንደሞተ ወደ ሚዲያ መውጣት አለበት ? " ሲሉ ጠይቀው፣ " በጣም አሁን እኮ አንዳንድ ፀሐፊዎች እንዳውም ፎቶ ግራፉን ሁሉ ' ተጠርጣሪ ይሄ ነው ' እያሉ እየለጠፉ ነው። ይሄ ኢቲካል እኮ አይደለም " ብለዋል።

አክለውም፣ " ይሄን ሰውየ እኮ ፍርድ ቤት ነው 'ጥፋተኛ ነህ' ብሎ ጥፋተኛ መሆኑን የሚገልጽለት እንጂ ግለሰብ እየተነሳ 'ጥፋተኛ ነው' ብሎ ፎቶ እየለጠፉ ትክክል እኮ አይደለም " ብለዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ የጉዳዩን አሳሳቢነት ሲያስረዱም ፦

- " ፍርድ ቤት እኮ ጥፋተኛ እስከሚለው እኮ ነፃ ሆኖ የመቆጠር መብት አለው። "

- " ከሕግ አንጻር እኮ ማዬት መቻል አለብን። ይሄ ነገር #የሚያስከትለውን ነገር ማየት መቻል አለበት። "

- " ቤተሰቦቹን ማሰብ መቻል አለበት። አሁን እነዚህ ሰዎች #ጎረቤታሞች ቢሆኑ እኮ የዛ ቤተሰብ መጥቶ እዚህ ልጅ ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው። እንዴት እንደዚህ አይታሰብም ? ብቻ በአጠቃላይ በጣም ቀውሷል ሚዲያው ፤ ከባድ ቀውስ ላይ ነው ያለነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የሟቹን ጉዳይ በተመለከተ ፖሊስ ያገኘው መረጃ እና የጀመረው ምርመራ እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው ኮማንደር ማርቆስ፣ " ፖሊስ ሥራ እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን። አሁን ሥራ እየተሰራ ነው " ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

የአባተ አበበን ጉዳይ በተመለከተ እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

ይህን መረጃ አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ግድያ #የፖሊስ_ምላሽ " ፖሊስ ሥራውን እየሰራ ነው። ግልጽ ማድረግ በሚገባን ሰዓት ላይ ግልጽ እናደርጋለን " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ አቶ አባተ አበበ የተባሉ ግለሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ መዝናኛ 'በጥይት ተመትቶ ተገደለ' መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል። የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት…
#AddisAbaba

ፖሊስ በአቶ አባተ አበበ ግድያ ሲፈለግ የነበረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የግድያ ተጠርጣሪው አቶ ተስፋዬ ሆርዶፋ የተባሉ ግለሰብ መሆናቸውን ገልጿል።

አቶ አባተ አበበ ታህሳስ 7/2016 ዓ/ም አዲስ አበባ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ ዝቅ ብሎ በሚገኝ ጭፈራ ቤት ' በጥይት ' ተመተው መገደላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አመልክቷል።

@tikvahethiopia