" 3,241 የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወስዷል " - የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የስፖርት ውርርድ (ቤቲንግ) ቤቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
በዚህም መግለጫው በ " ህገ ወጥ መንገድ " ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸእ 3 ሺህ 241 የስፖርት ቤቲንግ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።
ወደ እርምጃ የተገባው የቤቲንግ ጨዋታ ፤ በከተማው አስተዳደር ላይ እንዲሁም ቀን በቀን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ህይወት ላይ እየፈጠረ ያለውን አሳሳቢ ችግር በመረዳት ነው ብሏል።
ቢሮው ለማሸግ ምክንያት ናቸው ያላቸው ዝርዝር ጉዳዮች ምንድናቸው ?
- ከስፖርት መጫወቻነቱ ባለፈ ሀገር ተረካቢ ትውልድን እያጠፍ በመሆኑ፤
- ከፍተኛ የወንጀል ማስፍፊያ እየሆነ በመምጣቱ
- የከተማውን ወጣት ግዜውን አላግባብ በስፍራው እያሳለፈ በመምጣቱ፤
- ከተፈቀደላቸው ፈቃድ ዉጪ እየሰሩ በመምጣታቸው
- የሰዉ ልጅ ህይወት አላግባብ እየጠፋ በመምጣቱ፤
- ተማሪዎችም ትምህርታቸውን ትተዉ በቦታው እየተገኙ በተገቢው መንገድም እንዳይማሩ በማድረጉ ፤
- የመማር ማስተማሩን ሂደት እያወከ በመምጣቱ የሚሉት ተነስተዋል።
ቢሮው በመግለጫው. ከትምህርት ተቋም 200 ራዲየስ ርቀት ላይ መገኝት እንዱሁም እድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች በቦታው ላይ መገኝት እንደማይገባቸው የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህግ እንደሚደነግግ አስገንዝቧል።
እርምጃው ፦
° የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣
° #የብሔራዊ_ሎተሪ_አስተዳደር፣
° የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን፣
° የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣናት በቤቶቹ ላይ የልየታ ምልከታ ካደረጉ በኃላ የተወሰደ ነው ተብሏል።
ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
ምንም እንኳን በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ እየሰሩ ነው በተባሉ የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ የማሸግ እርምጃ ቢወሰድም በአጠቃላይ የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ / ኢትዮጵያ ውስጥ #አልታገደም።
በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ ነው የሚሉ ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ከተሰራጩ በኃላ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም ስህተት እንደሆነና የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አሳውቆ ነበር።
ከዚህ ቀደም ከ " ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ " ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሙሉ በሙሉ #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ ነበር።
መ/ቤቱ " ቤቲንግ " በወጣቱና ለታዳጊው ላይ ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምን ሲሆን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን " ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " ብሎ እንደማይወስደው ፣ በዚህ ዘርፍ በርካታ ሰው ተቀጥሮ እንደሚሰራ ከዚህ ቀደም ገልጿል።
ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር " ቤቲንግ " በስርዓት እንዲመራ መመሪያዎች ወጥቶ እየተሰራበት እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።
ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።
በዚህ ጉዳይ አስተያየት ካላችሁ በ @Birlikethiopia ገብታችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
@tikvahethiopia

#Poll
የስፖርት ውርርድ ወይም ቤቲንግን በተመለከተ በማህበረሰቡ ፣ ፍቃዱን በሚሰጠው የመንግሥት አካል፣ ይህንን በሚቃወም ሌላ አካል ብዙ ሲባል ነበር። እርሶ ከየትኛው ኖት ?

Anonymous Poll
74%
ወጣት እና ታዳጊዎችን የከፋ ችግር ላይ እየጣለ ነው። ትውልድን እያጠፋ ነው። ቤተሰብ በመሰረቱ ሰዎች ላይም ቀውስ እየፈጠረ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ሊታገድ ይገባል።
26%
በአግባቡ በመመሪያ ከተሰራ ለኢኮኖሚ በጎ አስተዋፅኦ አለው። ከጉዳቱ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው። የወጡ ክልከላዋች በክትትል እንዲፈፀሙ ይደረጉ እንጂ ሊታገድ አይገባም።
#EGYPT🇪🇬
የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ የሀገራቸውን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በማሸነፋቸው ለቀጣይ 5 ዓመታት ሀገሪቱን ይመራሉ።
አል ሲ ሲ ይህ ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን ምርጫ ሲያሸንፉ ነው።
3 ተፎካካሪዎች በነበሩበት በዚህ ምርጫ ሲሲ 89.6% ድምፅ እንዳገኙ የሀገሪቱ የምርጫ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba
የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አመራሮች በአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ተሰምቷል።
ውይይት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሲሆን ሰዓታትን የወሰደ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።
ከፍተኛ አመራሮቹ ከውይይቱ በኃላ ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ፦
- በእገታ ወንጀል፣
- በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣
- በተደራጀ ከባድ የዝርፊያ ወንጀል
- ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ የሜትር ታክሲዎችን ተጠቅመው #የሰው_ግድያ፣ የሞባይል ንጥቂያ እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ፦
- በርካታ የሺሻ ማስጨሻ፣
- #የጭፈራ_ቤቶች እንዲሁም ሕገ-ወጥ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን አስረድተዋል።
የፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን " የቁማር ቤቶች (betting) " ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን በእነዚህም ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን ገልጸዋል።
እነዚህ ወንጀሎች ለኅብረተሰቡ የፀጥታ ሥጋት በማይሆኑበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተከታታይ ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።
በየጊዜው ውጤቱ እየተገመገመ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
* የሜትር ታክሲ፣
* የሞተር ሳይክል
* የባጃጅ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲይዝ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራልም ያሉ ሲሆን በወንጀል ተሳትፈው ከተገኙ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።
በቀጣይ ለሚካሄድ ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።

#አቢሲንያ_ባንክ
ለጥያቄና መልስ ውድድራችን ዝግጁ ነዎት?
3ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ታህሳስ 11 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!
https://t.iss.one/BoAEth
#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

#እንድታውቁት
ስትሮክ ፦
ስትሮክ በተለያየ ምከንያት ኦክስጅንን ለአእምሮ ሚያደርሰው የደም አቅርቦት ሲስተጓጎል እና በአንጎላችን ውስጥና ዙሪያው ባሉት ሽፋኖች ላይ የደም መፈሰስ ሲከሰት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡
መንስኤውስ ?
- ስትሮክን በደም ስር መደፈን ወይም መዘጋት ምክንያት የሚመጣ (Ischemic stroke) እና በመድማት ምክንያት (hemorahgic stroke) ብለን ልንከፍለው እንችላለን።
1. Ischemic stroke የምንለው አእምሯችን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች በረጋ ደም አሊያም Atheroscleorsis በተባለ የደም ስር መጠንከር እና መጥበብ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሲዘጋ ሚመጣ የስትሮክ አይነት ሲሆን ይህም ሁለት አይነት ይችላሉ::Embolic የሚባልው ከአእምሮአችን ውጪ ከሌላ የሰውነታችን አካል በተለይ ከልብ፣በአንገት አካባቢ ካለ የደም ቧንቧ የረጋ ደም ወደ አእምሯችን ሲሄድ እና አእምሯችን በቂ የሆነ ኦክስጅን የያዘ ደም እንዳያገኝ ሲያስተጓጎለው የሚፈጠር ሲሆን;ሁለተኛው ደግሞ thrombotic ሲባል ለአእምሮአችን ኦክስጅን እና ንጥረ ነገሮችን ሚያደርሰው የደምስር ውስጥ የደም መርጋቱ ወይም የደም ስሩ መጠንከሩ ሲፈጠር ነው።
2. Hemorrhagic stroke የምንለው አእምሮ ውሰጥ የደም ስር በተለያየ ምክንያት ሲፈነዳ እና ደም ወደ ጭንቅላታችን ሲፈስ ነው ይህም የሚፈሰው ደም ተጠራቅሞ አእመሮ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት ጫናው የደረሰበት የአእምሮ ክፍል ኦክስጅን እንዳያገኝ ሲሆን የሚከሰት የስትሮክ አይነት ነው።
- እንደ የደምግፊት፣ ስኳር፣ ከፍተኛ የኮሌስተሮል መጠን፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ የልብ ህመም ለስትሮክ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
ምልክቶቹ ፦
° ድንገተኛ እና ሀይለኛ የእራስ ምታት
° የፊት እና የሰውነት በአንድ ጎን ወይም ሙሉ በሙሉ መደንዘዝ
° እራስን መሳት እና ሚዛንን ለመቆጣጠር መቸገር
° ግራ መጋባት
° ሽንትን እና ሠገራን መቆጣጠር አአለመቻል
° በትክክል መናገር አለመቻል
ስትሮክን ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል።
▪️የደም ግፊትን በመቆጣጠርና በየጊዜው በመከታተል
▪️ስኳርን በመቆጣጠርና በየጊዜው በመከታተል
▪️አልኮል በመቀነስ
▪️ሲጋራ ባለማጨስ
▪️የሰውነትን ክብደትን በመቆጣጠር ልንከላከለው እንችላለን ፡፡
- ለስትሮክ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት ከማገገማችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ቶሎ መታከም እጅግ ወሳኝ ነው።
- በምርመራ ወቅት የደም ስኳር መጠን፣ሙሉ የደም ምርመራ፣ የደም መርጋት ምርመራ፣የልብ ምርመራ፣በመጨረሻም CT scan እንደ አስፈላጊነቱ MRI በማዘዝ ትክክለኛውን የስትሮክ አይነት ማረጋገጥ ይቻላል።
☑️ አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶችን ካሳየ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርበታል፡፡

#NEBE ወ/ሮ ሜላተወርቅ እና አቶ ታደሰ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነት የመጨረሻ እጩዎች ሆነው መለየታቸው ተነገረ። በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እጩ መልማይ ኮሚቴ ከህዳር 3 እስከ 13 ድረስ 56 ጥቆማዎችን በተለያዩ የጥቆማ መንገዶች መቀበሉን ገልጿል። ከእነዚህ መካከል 52ቱ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 4 ደግሞ ሴቶች እንደነበሩ አመልክቷል። በዚህም በተለያዩ ሶስት ዙሮች በተለያዩ…
#NEBE
ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ወ/ሮ ምዕላተወርቅ ሀይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል ።
ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ የሾመው በ1 ድምፀ ተዓቅቦ በአበላጫ ድምፅ ነው።
ወ/ሮ ሜላተወርቅ ማናቸው ?
- ወ/ሮ ሜላትወርቅ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት አዲስ አይደሉም። ቦርዱን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።
- ለሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ሰርተዋል።
- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ምርቋ ሜላትወርቅ የሥራ ሕይወታቸው የሚጀምረው በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ነው። በኮሚሽኑ ከጀማሪ የሕግ ኦፊሰርነት እስከ ኦፕሬሽን ኃላፊነት ድረስ ሰርተዋል።
- የኒው ጀኔሬሽን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተባባሪ መሥራችም ናቸው።
- የሕግ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ የሕግ ድርጅት አቋቁመው ነበር።
- ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ከሰላም እና ደኅንነት ጥናቶች ተቋም (አይፒኤስኤስ) የማስተርስ ዲግሪያቸው ተቀብለዋል።
- ከአሜሪካ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ኬኔዲ ትምህርት ቤት በሕዝብ አስተዳደር ሌላ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው።
- በአካዳሚክ፣ በፖሊሲ እና በፐብሊክ ሴክትር ባለሙያነት፣ በሁለትዮሽ እና በዘርፈ ባለብዙወገን ስምምነቶች ተደራዳሪነት፣ በግልግል ዳኝነት አማካሪ በመሆን ሰፊ ልምድ እንዳላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች ይናገራሉ።
ቀጣይ ምን ይጠብቃቸዋል ?
* የቀድሞዋ ሰብሳቢ ወ/ሪ ብርቱካን ሚደቅሳ ያላጠናቀቋቸው የቤት ሥራዎች ከፊታቸው ይጠብቃቸዋል።
* ቀዳሚው እና ትልቁ ያለፈው ምርጫ ባልተካሄደባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ምርጫ ማካሄድ ነው።
* ለሁለት ዓመት ጦርነት ሲካሄድበት በቆየው የትግራይ ክልል የፓርላማም የክልል ም/ ቤት ምርጫ አልተካሄደም። ክልሉ ላለፉት 3 ዓመታት በሕዝብ ተ/ም/ቤት ተወካይ የለውም። ቦርዱ በተያዘው 2016 ዓ.ም. በክልሉ ምርጫ ለማካሄድ ዕቅድ መያዙን ለፓርላማ አስታውቆ ነበር። መጪው የቦርዱ ሰብሳቢ ይህን ዕቅድ ያሳኩታል ወይ የሚለው በሂደት የሚታይ ጉዳይ ነው።
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫ ያልተደረገባቸው ቦታዎች አሉ።
- በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞኖች በፀጥታ ችግር ምርጫ ያልተካሄደባቸው አካባቢዎችም አሉ።
- የአካባቢ ምርጫም ዋነኛ የቤት ሥራ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከህ/ተ/ም/ቤት እና ከቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው ያሰባሰበው።

" ' ኬኖ ' ለሚባለው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አልሰጠሁም " - የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
" ኬኖ " ተብሎ ለሚጠራው የቁጥር ግመታ ጨዋታ ፈቃድ አለመስጠቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
አስተዳደሩ ፤ ቤቲንግ ቤቶችና ሌሎችም ቁጥር በማስገመት ለሚያጫወቱት " ኬኖ " አስተዳደሩ ፈቃድ ያልሰጠ ሲሆን፣ ይህን ጨዋታ በሚያጫውቱ ቤቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብሏል።
በቀጣይም ጨዋታውን ሲያጫውቱ በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡
" ኬኖ " ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ታዳጊዎች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች እያዘወተሩት የሚገኝና በብዛት ብራቸውን የሚከስሩበት የቁማር ዓይነት ነው፡፡
መረጃው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (EPA) ነው።

ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ አንድ ሰው በጥይት ተመቶ ተገድሏል።
ድርጊቱ የተፈፀመው ቦሌ ከኤድናሞል ወረድ ብሎ በሚገኝ አንድ የመዝናኛ ስፍራ አካባቢ ነው።
ምሽት አራት ሰዓት ገደማ ሟች #አባተ_አበበ በአንድ #መሳሪያ_በታጠቀ ግለሰብ በጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል።
አባተ አበበ ተወልዶ ባደገበት ፣ በሚኖርበት አካባቢ እንዲሁም ደግሞ በስራ ህይወቱ በመልካም ስነምግባሩና በተግባቢነቱ በርካቶች እንደሚያውቁት ለመረዳት ችለናል።
ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ ይፈፀማል።
ገዳይ እንዳልተያዘ ለመረዳት ተችሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ በሰጠው ቃል፤ ከዚህ ወንጀል ጋር በተያያዘ ምርመራ ላይ መሆኑን ገልጾ ሲጠናቀቅ በሚዲያ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል ብሏል።

#ሺርካ
ባለፈው ህዳር ወር በርካታ ሰዎች በተገደሉበት ሺርካ ወረዳ ትላንት ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ/ም ግድያ መፈፀሙ ተሰምቷል።
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሺርካ ወረዳ ጋላማ በሚባል አካባቢ ታህሣሥ 8 ቀን 2016 ዓ.ም 4 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን የ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቢዥን " ምእመናን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
አራቱ ምእመናን በጉዞ ላይ ሳሉ ከሚጓዙበት መኪና በማስወረድ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ተጠቁሟል።
ከሟቾች መካከል በሺርካ ወረዳ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የአቋቋም መምህር እንደሚገኙበት ተገልጿል።
እየተፈፀመ ያለውን ተከታታይ ግድያ ለማስቆም የመንግስት የጸጥታ አካል ምንም አይነት እርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ መሰል ጥቃቶች እንዲቆሙ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።
ባለፈው ህዳር ወር ከጨቅላ ህፃን አንስቶ እስከ 70 ዓመት አዛውንት እንዲሁም በርካታ የአንድ ቤተሰብ አባላት በዚሁ ወረዳ መገደላቸው ይታወሳል።
ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን መንግስት በአሸባሪነት የፈጀውን ' ሸኔ ' (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ ማድረጉ አይዘነጋም።
ህፃን፣ አቅመ ደካማዎችን፣ ሴቶችን ሳይለይ #እየገደለ ያለው ይሄው ቡድን ነው ብሎ ነበር።
ታጣቂ ቡድኑ ግን ኃይላችን " በሰላማዊ ሰዎች ላይ እርምጃ አልወሰደም " በሚል ውንጀላውን አስተባብሎ የነበረ ሲሆን የክልሉ መንግሥት ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ብሎ ነበር።
በሺርካ ወረዳ ከተፈፀሙ ግድያዎች ጋር በተያያዘ ውጥቶ በነበረው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት ላይ ፤ " የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሳቸው መሆኑን ገልጸው መንግሥት በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ተማፅነው " እንደነበር መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።