" በ1 ዓመት ጊዜ 300 በልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ሕፃናት ነፃ የሕክምና አገልግሎት እንሰጣለን " - አቶ ብርሃን ተድላ
" ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል " በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ 300 በልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ሕፃናት ነጻ የሕክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከሰሞኑን ገልጿል።
ሕክምናው በህፃናት እና በአዋቂ የልብ ቀዶ ህክምና ከ25 ዓመት በላይ ልምድ ባላቸው እና 16 ሺህ በላይ ቀዶ ህክምናዎች ባደረጉት፣ ከህንድ አገር በመጡት ዶ/ር ሙስኮኒ ኮፓላ የሚመራ ነው ተብሏል።
ይህንን ህክምና ከሚፈልጉ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማዕከል #ከተመዘገቡ ህጻናት መካከል ነው በየዓመቱ ለ300 ህጻናት ያለ ክፍያ የቀዶ ጥገና ሕክምና የሚሰጠው።
የሆስፒታሉ መስራች ባለቤት አቶ ብርሃን ተድላ ፤ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ችግር በአንድ ሆስፒታል ጥረት ብቻ እንደማይቀረፍ ገልጸው አቅም ያላቸው ወገኖች ቢያንስ አንድ ልጅ በማሳከም አስተዋፅኦ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።
የነፃ ሕክምናው ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተገኝተው እንደነበር ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሆስፒታሉ ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia

#USA #Election
" ስደተኞች የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " - ዶናልድ ትራምፕ
ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች " የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው " በማለት ተናገሩ።
ትራምፕ ይህ ያሉት #ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት " ኒው ሃምሻየር " ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።
ትራምፕ ለ4 አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ ህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።
ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ #ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
" ከሁሉም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው " ሲሉ አክለዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው መስከረም ወር " ናሽናል ፐልስ " ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች " ደማችንን እየበከሉት ነው " የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።
በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር " ዘረኝነት እና ጥላቻ " የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።
የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን አሁንም ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።
ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ " የጀርመኖች ደም በጅዊሾች እየተበከለ ነው " የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ ነው ሲሉ ተችተውታል።
ስታሊ" ትራሞፕ ይህ ቃል በሁሉም የድጋፍ ሰልፎች ላይ እየደገሙት ነው። አደገኛ የሆኑ ንግግሮችን መደጋገም እንዲለመዱ ያደረጋል " ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ እንደተናገሩት ይህ በአሜሪካ የሚኖሩ ስደተኞችን ስጋት ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቴቨን ቹንግ እንዲህ አይነት ቃላት በመጽሀፍ፣ በዜና እና በቴሌቪዥን የተለመድ ናቸው በማለት በትራምፕ የቀረበውን ትችት " ትርጉም የለሽ " ሲሉ አጣጥለውት ነበር።
Credit - AL AIN News

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እሁድ ሲረዝም፣ ከአምዕሮኣችን የማይጠፋውን እንክፈት እንደሰት - ከ#ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ .☀️
Sundays can get long and so, let us open up the snack which has been our our minds #SunChips😋 #SunnyMoments .☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

በሻሸመኔ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ።
የቦንብ ፍንዳታው የደረሰው በአላቼ ክ/ከተማ ሲሆን በቆሻሻው መጣያ አካባቢ የፕላስቲክን ጠርሙስ ሲሰበስቡ የነበሩ ሁለት የ9 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች ህይወታቸው አልፏል።
የቦንብ ፍንዳታው የደረሰው ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው መንገድ ሲሆን ቦንቡ በአንድ ቆሻሻ ስር ተጥሎ ነበር።
#OBN

" ዜጎች አሁን በየዕለቱ እያሻቀበ ባለው #የኑሮ_ውድነት ራሳቸውን ሊያኖሩ የሚችሉበት ሁኔታ መፍጠር ካልተቻለ አገርንም አደጋ ላይ ይጥላል " - ኢሰማኮ
የሰራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የመትከል ጥያቄ እየተንከባለለ የመጣና የኢትዮጵ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ጭምር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ያቀረበበት በኢትዮጵያ ያሉ ሠራተኞችን ለምሬት የዳረገ ግን ምላሽ ያልተቸረው ጉዳይ መሆኑን ብዙዎች ሲያወሱ ይደመጣሉ።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን ያቀረቡ አንድ ሠራተኛ ፤ " በአዲስ አባባ ከ3,000 ብር በታች የቤት ኪራይ ለማግኘት አስቸጋሪ ነው። ለዛውም በኮምፒስታቶን የተጠጋገነ ቤት ነው። የወር ደመወዜ ደግሞ 3,000 ብር ነው። ታዲያ በዚህ ደመወዝ እንዴት መኖር ይቻላል ? " ሲሉ አማረዋል።
አክለውም ፤ " ምንም እንኳ ለኑሮ ውድነቱ የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም የደመወዝ ወለል አለመተከልም አንዱና ዋነኛው መንስኤ ነው። በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም መንግሥት ግን የአንድ ሰሞን አጀንዳ ከማድረግ በዘለለ መጽትሄ እየሰጠ አይደለም " የሚል ወቀሳ አቅርበዋል።
እኝህን ቅሬታ አቅራቢ ለአብነት ጠቀስን እንጂ እሮሮው በበርካቶች ዘንድ በተደጋጋሚ ሲናገር ይደመጣል።
የቅሬታ አቅራቢዎችን እሮሮ መነሻ በማድረግ ቲክቫህ ለኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) የስራ አስፈፃሚ አባል እና የኢንድስትሪ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዲርብሳ ለገሰ ተከታዮቹን ጥያቄዎች አቅርቧል።
* የኑሮ ውድነት በየዕለቱ እየጨመረ በሚስተዋልበት ሁኔታ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጥያቄ ግን ከቀጠሮ ባለፈ ለምን መፍትሄ አይሰጠውም ?
* ጉዳዩን በተመለከተ ከዚህ በፊት ለጠ/ ሚኒስትሩ ያቀረባችሁት ጥያቄ አሁንስ ከምን ደረሰ ?
* ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጥያቄ መፍትሄ ሳይሰጠው እየተንከባለለ የመጣ ጥያቄ ነው። አሁንስ ቢሆን እየተንከባለለ እንደማይቀጥል በምን እርግጠኛ መሆን ይቻላል ?
* ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቅጣጫ የሰጡበት ጉዳይስ በተግባራዊነቱ ምን ያክል እርግጠኛ መሆን ይቻላል?
አቶ ዲርብሳ ለገሰ ምን ምላሽ ሰጡ ?
- ለኑሮ ውድነት የራሱ የሆነ ፋክተር ስላለው ይኸኛውም አንደኛው ነው በሚል አንስተንላቸዋል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ። በአሁኑ ጊዜ የኑሮ ውድነቱ የከበደው ቢኖር ሠራተኛው ነው።
- የዚህ ጥያቄ እየተንከባለለ መሄድ ሠራተኞችን ብቻ ሳይሆን የሚጎዳው አገርንም ይጎዳል በእኛ እምነት ለማንም አይጠቅምም።
- ዜጎች አሁን በየዕለቱ እያሻቀበ ባለው የኑሮ ውድነት ራሳቸውን ሊያኖሩ የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ካልተቻለ #አገርንም_አደጋ_ላይ_ይጥላል።
- ይህ ጉዳዩ ትኩረት አግኝቶ እንዲኬድበት አቅጣጫ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በተለያዩ የሥራ መደራረብ ምክንያቶች አቅጣጫውን የተቀበሉ አካላት ባለመኖራቸው ነው እንጂ ባሉበት ቦታ ሆነው ክትትል እያደረግን እንገኛለን።
- በኢትዮጵያ ለኑሮ ውድነቱ የሠራተኛ ደመወዝ ማነስ ብቻ አይደለም። የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ግን ይህም እንደ አንድ ፋክተር ስለሚሆን ይህንንም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተናል።
- በኢትዮጵያ #ሰላም_እስከሌለና #ሰላም_መፍጠር እስካልተቻለ ድረስ ለኑሮ ውድነት በሌላ መንገድ ተገቢና ዘላቂ ምላሽ መስጠት ይገባል ተብሎ አይገመትም።
- አሁን ሠራተኞች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ይደርሱባቸዋል። #መፈናቀል፣ #መንገላታት ይደርስባቸዋል።
- መዘግየቱ ተገቢነት እንደሌለው ፣ ጉዳቱም ለሁላችን እንደሚሆን መንግሥትም ሊገምተው እንደሚገባ በየዕለቱ፣ በየጊዜው ማሳሰባቸን አይቀርም፣ ክትትል እናደርጋለን ውጤቱንም እናሳውቃችኋለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ባገኘው መረጃ ፦
* ሚኒመም ዌጅን በተመለከተ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አሉ።
* #ዓለም_አቀፍ_አማካሪዎችንም ጭምር በማካተት ልምዶችንና የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ለማስታረቅ የሚችያስችል ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው። ሲጠናቀቅ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ መረጃ ይሰጣል።
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል #ያልተተከለላቸው አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት (3) የአፍሪካ አገራት ብቻ ሲሆኑ ፣ የሠራተኞች የመነሻ የወለል ደመዎዝ ተጠንቶ የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም በ2011 ዓ.ም በወጣው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ላይ ተደንግጓል።
ኢሰማኮ ፦
° ጥናት በማጥናት ለሥራና ክህሎት ጨምሮ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በደብዳቤ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳልተሰጠው፣
° በ2015 ዓ.ም የሜይዴይ በዓል ጥያቄውን ሰላማዊ መልስ እንዲሰጠው በሰላማዊ መንገድ ለማንሳት ቢሞክርም ሰልፉ እንደተከለከለ፣
° ባሉት ጥያቄዎች ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርጎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅጣጫ እንዳስቀመጡ መግለጹ የሚታወስ ነው።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም አሳውቋል።
የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡
ወጣቱ #በማህበራዊ_መገናኛ_አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ) አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡
ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡
የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።
ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ ፤ በልዩ ልዩ ምክንያት የምንቀርባቸው ግለሰቦች ማንነታቸውን ጊዜ ወስደን ማረጋገጥ አለብን ብሏል።
በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።
ፎቶ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ህይወቱ ያለፈው የዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የስራ ባልደረባዎች እና ቤተሰቦቹ ዛሬ ምሽት ለዶ/ር እስራኤል የማስታወሻ ሻማ የማብራትና የፀሎት መርሃ ግብር አድርገዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ላይ ተገኝቶ ስነስርዓቱን ተካፍሏል።
ፍርድ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ከሰኞ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ20 ቀናት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ሂደቱን እየተከታተለ ያሳውቃል።