TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ሰላማዊ ዜጎችን ያልለየ ግድያ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ይፈጸማል ሲል ከሷል።

በመግለጫው ምን አለ ?

- በኦሮሚያ ተደጋጋሚ ግድያ እና የጅምላ እስሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሳያቋርጥ ይፈጸማል።

-  ህዳር 30 እና ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም. በአቡና ግንደበረት እርጃጆ፣ ጫፌ ኤረርና ፊኖ ቀበሌያት 8 ንጹሃን ዜጎች በጠራራ ጸሃይ ተገድለው ሁለት ሰዎች ቆስለዋል።

-  በቄሌም ወለጋ ዞን ጊዳሚ  ውስጥ ጸሎት ላይ እያሉ ከመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንዲወጡ ተደርገው የተገደሉ 9 አማኞች በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች ነው።

- ከቀናት በፊት በአጋምሳ "ቆርቆቤ' በሚባል ቦታ ላይ መንግስት በስልጣን ላይ እያለ የፋኖ ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል። የአገምሳ ወጣቶች እህል ለመሰብሰብ በሲኖትራክ መኪና ወደ ምእራብ ጎጃም ሲጓዙ በተፈፀመው ጥቃት ከ13 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

- በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ሲርካ ወረዳ በሚገኙ መንደሮች በዋጂ ራፋሳ፣ ቢዱ ባላ፣ ሄላ አመጃ፣ ሄላ ጠሬታ፣ ገለቤ አማጃ፣ ማካራራ፣ ሶጂዪ ሳዲ፣ ጋላቤ ሁሉል እና ሌሎች ቦታዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት በመክፈት ህፃናትን ጨምሮ ከ50 በላይ  ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- የመንግስት ወታደሮች ህዳር 15 በደምቢ ዶሎ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ በመክፈት የሰዎችን ህይወት ቀጥፈዋል።

- ህዳር 13 ቀን 2016 በቡኖ በደሌ ዞን ጨዋቃ ወረዳ በሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ጥቃት ተማሪዎችን ጨምሮ 52 ሰዎች ተገድለዋል።

ለኦነግ ፓርቲ መግለጫ የመንግስት ምላሽ ምንድነው ?

ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ፦

* መንግስት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚወሰድው እርምጃ አይኖርም።

* በንጹሃን ዜጎች ላይ ርምጃ የሚወስደው አሸባሪው የሸኔ ቡድን ነው። በቅርቡ ሽርካ ወረዳ በርካታ ንጹሐንን የቀጠፈውን አሰቃቂ ጥቃት የፈፀመው ይኸው ቡድን ነው። ከግድያ ባለፈ በአከባቢው የነዋሪዎችን ቤት አቃጥሏል።

* ንጹሃን ዜጎችን ከጥቃት ለመጠበቅና የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚረዳ ወታደራዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

* እርምጃዎቹ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠሩ ብቻ ናቸው። ለአብነትም በቡኖ በደሌ ወረዳ ጨዋቃ ወረዳ የተወሰደው ሸማቂውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ አድርጓል። እርምጃው ታጣቂ ቡድኑ ለጥቃት ሲዘጋጅ የተወሰደ ነው።

* ለአሸባሪ ቡድን የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ ወንጀል በመሆኑ ድጋፍ የሚሆኑት ሴሎቹ ላይ እርምጃ ይወሰዳል እንጂ ንጹሐንን መንግስት አይገድልም።

* በሺ የሚቆጠሩ ያሏቸው የታጣቂ ቡድኑ አባላት ለመንግስት እጅ ሰጥተው የታሃድሶ ስልጣና እየወሰዱ ነው።

" ለመሆኑ ሰዎች የሚገድሉት በመንግሥት የፀጥታ ኃይል ብቻ ነው ? " በሚል ለኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

አቶ ለሚ ፦

" ለሚፈፀሙ ለሁሉም ግድያዎች መንግስት ኃላፊነት መውሰድ የሚኖርበት የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት ብቸኛው ተቋም እሱ በመሆኑ ነው።

የታጠቀ ኃይል እኮ መንግስት አልሆነም፡፡ የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግስት ነው። " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ባለቤት ዶቼቨለ ሬድዮ እንዲሁም መግለጫው ከኦነግ ማህበራዊ ትስድር ገፅ የተገኘ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
" ማንኛውም ግለሰብ እኔ ከልጆቼና ከቤተሰቦቼ ጋር እራሴ አወርዳለሁ ካለ #አይገደድም " - የአ/አ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር

በአዲስ አበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የማህበር ቤቶች፣ ሪል ስቴት ያሉባቸው አካባቢዎች ላይ ጫኝ እና አውራጆች በሚጠይቁት ያልተመጣጠነ ክፍያና በሚፈጥሩት ግብግብ በርካቶች እንደሚማረሩ ይታወቃል።

" እቃዬን እኔ እራሴ አወርዳለሁ " ሲባልም አንዳንድ ጫኝ እና አውራጆች ከአፃያፊ ቃላት ውርወራ ጀምሮ ለግብግብ እና ፀብ እስከማጋበዝም ይደርሳሉ።

" መንግስት እስካደራጀን ድረስ ባለቤቱ ፈለገም አልፈለገም እቃውን የምናወርደው እኛ ነን " እስከማለትም ይደርሳሉ።

አንዳንዴም እቃዎች እንዲጎዱ ፣ እነሱ ካላወረዱት እዛ አካባቢ ላይ በነፃነት ለመንቀሳቀስ ስጋት እንስከመሆንም ይደርሳል።

በዚህ ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ይቀርፋል፣ ነዋሪዎችንም ከምሬት እና እንግልት ያታደጋል የተባለው መመሪያ ማንኛውም ህገወጥና ነዋሪዎችን የሚያማርሩ ተግባራትን ይከለክላል።

" ግለሰቡ እኔ ከልጆቼ፣ ከቤተሰቤ ጋር ሆኜ አወርዳለሁ ካለ አይገደድም ፤ እራሱ ማውረድ ይችላል። ማህበራቱም እኛ ነን የተደራጀነው ማስወረድ አትችሉም ማለት አይችሉም " ሲሉ አቶ ማስረሻ ሃብቴ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አማካሪ ተናግረዋል።

የባለቤቱን መብት መጠበቅ የማህበራቱ ግዴታ እንዳሆነ ገልጸዋል።

በስምምነት  እቃው የሚወርድ ከሆነ ደግሞ ጫኝ እና አውራጅ ማህበሩ ሙሉ ኃላፊነት ለእቃው ይወስዳል ብለዋል።

አቅምን ያላገናዘበ ፣ ከእቃው ጋር ያልተመጣጠነ ክፍያም እንዳይኖር የዋጋ ተመን መውጣቱን አቶ ማስረሻ ገልጸዋል።

" ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ተቀምጦለታል "  ያሉት አቶ ማስረሻ " የራሱ የሆነ ርቀት አለው ለምሳሌ ከተሽከርካሪ ከወረደበት 50 ሜትር የመጀመሪያ ዋጋ አለ ከዛ በኃላ እያጨመረ ይሄዳል። ኮንዶሚየም ላይ የሚወጣ ከሆነ እስከ ብሎክ ስር 50 ሜትር ከሆነ ከታች ወደላይ ዋጋው እያጨመረ ይሄዳል።  " ብለዋል።

ቢሮው ተግባራዊ ስለተደረገው መመሪያ በጫኝ እና አውራጅ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች እና ማህበራት የ2 ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ሁሉም የሚመርጠን በምክንያት ነው! ባሉበት ሆነው የአፖሎ ዲጂታል ባንክን በመጠቀም አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ይውሰዱ፡፡

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

አቢሲንያ  የሁሉም ምርጫ!

#Apollodigitalbank #loan #apolloloan #instantloan
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ
እስከ 55% የሚደርስ ቅናሽ ከጥሪ ማሳመሪያ ስጦታ ጋር!

ከመደበኛ ጥቅሎቻችን እስከ 55% ቅናሽ የተደረገባቸውን ልዩ የቴሌብር ወርሃዊ የድምጽ እና ዳታ ጥቅሎች ከጥሪ ማሳመሪያ ስጦታ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ (https://onelink.to/fpgu4m) አቅርበናል!

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
ፎቶ፦ 4.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ነው የሚገኘው የተባለው የዓድዋ ዜሮዜሮ ፕሮጀክት #ወደመጠናቀቁ መሆኑ ተነግሯል።

ፕሮጀክቱ በውስጡ ፦
- በዓድዋ ጦርነት የተሰዉ ጀግኖችን የሚዘክር ሙዚየም፣
- የመዝናኛ ሥራዎች፣
- ካፍቴሪያዎች፣
- ሲኒማ ቤቶችና ሁለገብ አዳራሾችን
- የህፃናት መጫወቻ
- አንድ ሺህ (1000) መኪና ማቆም የሚያስችል ፖርኪንግ
- የንግድ ቤቶችን የያዘ ነው ተብሏል።

የዓድዋ ድል የተበሰረበት ነጋሪት በሙዚየሙ ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን #የአጼ_ምኒልክ እና #እቴጌ_ጣይቱን የሚዘክር ሃውልትም ይቀመጣል ተብሏል።

በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል የተባለው ይኸው ፕሮጀክት የተወሰኑ ሥራዎች ብቻ እንደቀሩት ተገልጿል። በ45 ቀናት ውስጥም ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋል ተብሏል።

Credit - AMC & EPA

@tikvahethiopia
21 ዓመት ?

እጅግ አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ ሁለት የገዛ ልጆቹን አስገድዶ ያደፈረው አባት የ21 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት።

ድርጊቱ የተፈፀመው በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በጫኖ ሚሌ ቀበሌ ነው።

አረመኔያዊ በሆነ መንገድ አስገድዶ መደፈር የተፈፀማባቸው የ16 እና የ17 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እህትማማቾች ናቸው።

ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ወላጅ አባታቸው #በዛብህ_ኡንዱሮ ቀኑን በመራበት ውሎ ምሽት የወለዳቸው ልጆች ወዳሉበት መኖሪያ ቤቱ ይደርሳል።

ቤተሰብ ሙሉ ነው። እንደ ወትሮው ሁሉ አባታቸውን እጅ አስታጥበው እራቱን እንዲመገብ አድርገው ወደማደሪያቸው ሲያመሩ ምሽቱ ወደ እኩለ ለሊት እየተጠጋ ነበር።

በዚህም ወቅት ነው አባታቸው በፕላስቲክ ውሃ መያዣ የሞላውን #የአልኮል_መጠጥ ሁለቱ እህትማማቾች ተገደው እንዲጠጡ ማድረግ ይጀምራል።

የአልኮል መጠጡን ተገደው የጠጡት እህትማማቾች ራሳቸውን ወደመሳት ሲቃረቡ በግምት ከለሊቱ 9 ሰዓት ገደማ እያፈራረቀ አረመኒያዊ ተግባሩን ፈፀመ፤ አስገድዶ ደፈራቸው።

ይህ መረጃ የደረሰው ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ዐቃቤ ህግ ምርመራውን ያካሂዳል፡፡

እውነታውን ሊያስረዱ የሚችሉ የሰውና የሐኪም ማስረጃ ያገኘው ዐቃቤ ህግ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ያጠናቅቅና ለወረዳው ፍ/ቤት መዝገቡን ያስረክባል፡፡

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤትም ዐቃቤ ሕግ አጠናቆ ያቀረበውን የአስገድዶ የመድፈር ወንጀል ተከሳሽ በዛብህ ኡንዱሮ እንዲያስተባብል በሰጠው ብይን ተከሳሽ ማስተባበል ባለመቻሉ ምክንያት ጥፋተኛ ነህ ሲል ወስኗል፡፡

በዚህም መሠረት ለመስማት ቀርቶ ለማሰብ የሚከብደውን ይህን ወንጀል የፈፀመውን ተከሳሽ በዛብህ ኡንዱሮን በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ በመወሰን እንደ ማረሚያ ቤት እንዲወርድ መደረጉን ከደቡብ ሬድዬና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 25 የግል ኮሌጆች ለ2016 ዓ.ም ምንም አይነት አዲስ ሰልጣኝ መቀበል እንዳይችሉ እግድ ተጣለባቸው። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ፤ የግል ኮሌጆች የምዝገባ ፍቃድ ለመውሰድ መረጃ እንዲያቀርቡ በደባድቤ የጠየቃቸው ኮሌጆች መረጃ ለማቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው እግድ እንደጣለባቸው አሳውቋል። በመሆኑም፦ - ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማርያም…
#AddisAbaba #Update

ከዚህ ቀደም የምዝገባ እገዳ ተጥሎባቸው ከነበሩ 25 ኮሌጆች ውስጥ 24ቱ እገዳው ሲነሳላቸው አንድ ኮሌጅ ፍቃዱ ተሰርዞበታል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ፤ የግል ኮሌጆች የምዝገባ ፍቃድ ለመውሰድ የሰልጣኞች ምዘና ውጤት መረጃ እንዲያቀርቡ በደብዳቤ የጠየቃቸው 25 ኮሌጆች መረጃ ለማቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ምንም አይነት አዲስ ሰልጣኝ እንዳይቀበሉ እግድ እንደጣለባቸው ይታወሳል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ኮሌጆቹ አስፈላጊውን መረጃ እስከ 30/03/2016 ዓ.ም እንዲያቀርቡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ በዚህ ጊዜ ያላቀረበ እውቅና ፍቃዱ እንደሚሰረዝ ገልጾ ነበር።

በዚሁ መሰረት ምን ያህል ኮሌጆች በተባለው ጊዜ ማስረጃቸውን አቀረቡ ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለስልጣን መ/ቤቱን ጠይቋል።

ከ25ቱ ኮሌጆች 24ቱ አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረባቸው እገዳው ሲነሳላቸው " ኦርቢት ኮሌጅ " ግን በጊዜ ገደቡ መረጃ ባለማቅረቡ እውቅና ፍቃዱ እንደተሰረዘበት ባለስልጣን መ/ቤቱ ገልጿል።

(እገዳው የተነሳላቸውን ኮሌጆች ዝርዝር ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
📣 ኢትዮጵያ ለሚገኙ ወጣት ሴቶች የቀረበ ጥሪ!

ስቴም ፖወር (STEMpower) ከአይቢኤም (IBM) እና ከፊንላንድ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሥራ አጥ ወጣት ሴቶችን ተግባራዊ የሥራ ክህሎት ለመስጠት ያለመ "ትጋት" የተሰኘ ፕሮግራም አስተዋውቀዋል።

#ነጻ በሚሰጠውና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት በሚያስገኘው በዚህ ስልጠና ምን ምን ተካተዋል?

- Project Management
- Web Development
- Cyber Security
- Digital Marketing
- Data Analytics
- Information Technology
- Job Readiness, and Work Readiness

እነዚህን ኮርሶች ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ ተመዝገቡ 👉 https://shorturl.at/acpU1
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

ቴሌግራም- https://t.iss.one/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
#ETHIOPIA #Eurobond

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።

ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል።

ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። ገንዘብ ሚኒስቴር የክፍያ መጠኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል እንደሚቻል ገልጿል። ክፍያውን ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች በፍትሃዊነት እኩል ለማስተናገድ ነው ብሏል። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #Eurobond

ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም።

የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር።

ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው በ10 ዓመት ውስጥ ነው።

እስከዚያው ድረስ መንግሥት በዓመት ሁለት / 2 ጊዜ የሚፈጸም የ6.625 በመቶ ዓመታዊ ወለድ ለቦንዱ ገዢዎች ይከፍላል።

ኢትዮጵያ ባለፈው ሰኞ ዕለት 33 ሚሊዮን ዶላር ወለድ መክፈል የነበረባት ቢሆንም ክፍያውን ሳትፈጽም ቀናት አልፈዋል።

" የክፍያ መጡኑን በአሁኑ የሀገሪቷ አቅም መክፈል ይቻላል ፤ ላለመክፈል የተወሰነው ሁሉንም አበዳሪዎች እኩል ለማስተናገድ ነው " - ገንዘብ ሚኒስቴር

የብድር ቦንዱን አስመልክቶ ትላንትና ከቦንድ ገዢዎች ጋር የገንዘብ ሚኒስቴር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ በነበሩበት ውይይት ተደርጎ ነበር።

ይህን በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- ኢትዮጵያ #የታኅሣሥ_ወርን ወለድ ያላስተላለፈችው ክፍያውን ለማዘግየት ወስና ነው። ይህም ለገዢዎቹ ተገልጿል።

- ኢትዮጵያ #ወለዱን_ለመክፈል የሚያስችል ገንዘብ አላት።

- ክፍያውን የማዘግየት ውሳኔ ላይ የተደረሰው ሁሉንም የውጪ አበዳሪዎች በፍትሐዊነት ለማስተናገድ ሲባል ነው።

- አበዳሪዎች #በፍትሐዊነት ለመመልከት አለመቻል በዕዳ ሽግሽግ ላይ ከሌሎች የውጭ አበዳሪዎች ጋር የሚደረገውን ውይይት አደጋ ላይ ይጥለዋል። ወለዱ ቢከፍል መስተገጓጎል ሊያጋጥም ይችላል።

- በቅርቡ ከኦፊሴላዊ አበዳሪዎች ጋር የብድር ክፍያ ሽግሽግን በተመለከተ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- #የቦንድ_ገዢዎችን ጨምሮ ሌሎች አበዳሪዎችም ተመሳሳይ አይነት የብድር ክፍያ ማስተካከያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ከሁሉም አበዳሪዎች ጋር በሚኖር ግንኙነት ላይ #ወጥነት እና #እኩልነትን ለማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የብድር እፎይታ ....

* ኢትዮጵያ ላለባት ብድር #የብድር_እፎይታ ለማግኘት በ " ቡድን 20 " የጋራ ማዕቀፍ በኩል የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ ውይይት ስታካሂድ ቆይታ ነበር።

* ባለፈው ኅዳር ወር በቻይናና በፈረንሳይ በሚመራው የፓሪስ ክለብ አማካኝነት የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

* በዚህ ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያ ለአበዳሪዎቿ መክፈል የሚጠበቅባትን ብድር እና ወለድ 2 ዓመት ገደማ አትከፍልም።

* ይህ የዕዳ ክፍያ ሽግሽግ በየዓመቱ የሚከፈለውን 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዕዳ በጊዜያዊነት የሚያስቀር ነው።

ኢትዮጵያ የዚህን አይነቱን ስምምነት የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንዱን ከገዙ የግል ባለሀብቶች ጋርም ለመፈጸም ትፈልጋለች።

የዋናው ብድር የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘምና በየዓመቱ የሚከፈለውን የወለድ ምጣኔው ከ6.625 በመቶ ወደ 5.5 በመቶ ዝቅ ማድረግ ሀሳብ አላት።

መንግሥት የብድር አከፋፈሉ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የፈለገው ከሌሎች አገራት ጋር በሚያደርገው የብድር ሽግሽግ ላይ አበዳሪዎችን በተመሳሳይ መልኩ ማስተናገድን በተመለከተ ስጋት እንዳይነሳ በማሰብ መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት የብድር አከፋፈል ማስተካከያው ላይ ከቦንዱ ገዢዎች ጋር በተቻለ ፍጥነት ስምምነት ላይ መድረስ ጠንካራ ፍላጎት አለው።

የቦንዱ ገዢዎች ጋር ያለው ስሜት ምንድነው ?

° ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለዱን በቀኑ እንደማትከፍል ማስታወቋ በቦንዱ ገዢዎች ዘንድ በመልካም አልተወሰደም።

° የቦንዱ ገዢዎች ኮሚቴ የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔ አላስፈላጊ እና አሳዛኝ አድርጎ እንደሚመለከተው ገልጿል።

° የኢትዮጵያ መንግሥት ውሳኔውን የማያጥፍም ከሆነ ከፍ ያለ ዳፋ ይኖረዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ባለፈው #ሰኞ መክፈል የነበረባትን ወለድ ለቦንድ ገዢዎች ለማስተላለፍ የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜ ተሰጥቷታል።

በእነዚህ በተሰጡ ቀናት ውስጥ ወለዱን የማትከፍል ከሆነ ውልን አለማክበር (#technical_default) እንደሚገጥማት የዘርፉ ባለሞያዎች ተናግረዋል።

" ፊች " የተሰኘው የአገራትን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣ አሜሪካ ተቋም ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል ደረጃ ከነበረበት " ሲሲ " (CC) ደረጃ ወደ " ሲ " (C) ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል።

ተቋሙ ለዚህ ደረጃ ምደባ የጠቀሰው አንዱ ምክንያት ኢትዮጵያ የቦንዱን ወለድ በቀኑ አለመክፈሏል ነው ያለ ሲሆን በ14 ቀናት ውስጥ ክፍያው ካልተፈጸመ ይህንን ደረጃ በድጋሚ ዝቅ እንደሚያደርገው ገልጿል።

Credit - BBC AMAHRIC / REUTERS

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ኮንስታብል ማክቤል ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ በተኮሰው ጥይት ነው የዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ህይወት ያለፈው " - ፖሊስ

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የተባለ የጤና ባለሞያ በተተኮሰበት ጥይት ተመቶ #ተገድሏል

ግድያው የተፈፀመው #በፖሊስ_አባል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

ፖሊስ ስለጉዳዩ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሰሞኑን " ቦሌ አትላስ " አካባቢ ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን በተባለ ግለሰብ ላይ ተፈፅሟል ከተባለው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

ፖሊስ ምርመራ መዝገቡን ዋቢ አድርጎ እንዳስረዳው በቀን 28/3/2016 ዓ.ም ከንጋቱ 11:20 ሰአት ላይ ነው ዶ/ር እስራኤል ጥላሁን ወንጀሉ የተፈጸመበት።

ወንጀሉ የተፈፀመው ወረዳ 4 ልዩ ስሙ " አዲስ ህይወት ሆስፒታል " አካባቢ ነው ብሏል።

ዶክተር እስራኤል ያሽከረክራት የነበረችው ተሽከርካሪ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 36734 አ.አ ሲሆን፤ በወቅቱ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 28177 የሆነ #ቪትስ ተሽከርካሪ የያዘ ግለሰብ የመኪና " መስታወት - ስፖኪዮ ገጭቶ አመለጠኝ " በሚል ከፍተኛ ድምጽ እያሰማ ከኋላ ይከተለው ነበር፡፡

ወደ 11፡20 አካባቢም " ፋሲካ የመኪና መሸጫ " የሚባል ቦታ ሲደርስ፤ በአካባቢው ያሉ ኑሯቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች " ያዘው ያዘው " የሚል ድምጽ በማሰማት ከፍተኛ ግርግርና ወከባ ሲፈጥሩ፤ በዚያን ሰአት #ኮንስታብል_ማክቤል_ሮባ የተባለ የፖሊስ አባል፤ ለስራ በታጠቀው ታጣፊ ክላሽ " የመኪናውን ጎማውን መትቼ ለማስቆም " በሚል በተኮሰው ጥይት የዶ/ር እስራኤል ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስረድቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አንዳንድ ግዜ ወዲያውኑ መረጃ የማይሰጠው #ከምርመራ_ሂደቱ ጋር በተያያዘ የሚበላሹ ነገሮች ስለሚኖሩ ነው ያለ ሲሆን ቀጣይ የምርመራ መዝገቡ እየታየ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የትርታ ኤፍ ኤም 97.6 ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ያሳውቃል።

* በጉዳዩ ላይ ከሟች ቤተሰቦች / ከቅርብ ጓደኞች መረጃ የሚገኝ ከሆነ ተከታትለን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia