#AddisAbaba
" የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም ዝውውር አይደረግም " - ኤጀንሲው
በአዲስ አበባ 7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ የማረጋገጥ እና ምዝገባ ከትላንት ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።
ማረጋገጥ እና ምዝገባው ለመጪዎቹ 5 ወራት ይቀጥላል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ፤ ከዚህ በፊት በ6 ዙር ባደረገው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ምዝገባ ከ383,000 በላይ ይዞታዎች አረጋግጦ በካዳስተር ሲስተም መመዝገቡን አሳውቋል።
ኤጀንሲው ምዝገባው መካሄዱ አንድ ይዞታ በማን፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደተያዘ እና በይዞታው ላይ ለተፈጠረው መብት ህጋዊ ዋስትና አና ከለላ በመስጠት የመሬት ነክ ገበያውን በተሻለ መንገድ ለመቆጣጠር ያስችላል ብሏል።
7ተኛ ዙር የይዞታ ማረጋገጡ ምዝገባ በ7 ክፍለ ከተሞች ይካሄዳል የተባለ ሲሆን 85 ቀጠናዎች እና 386 ሰፈሮችን ያካትታል።
ምዝገባው የማያካሄዱ ባለይዞታዎች ምንም አይነት ህጋዊ ዋስትና እና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው አሳውቆ ባለይዞታዎች እና በይዞታዎች ላይ ጥቅም አለን የሚሉ ሁሉ በምዝገባው ላይ ሊሳተፉ ይገባል ብሏል።
ምዝገባው እስከ ሚያዝያ 28 ድረስ ባሉት 5 ወራት የሚካሄድ ሲሆን ከ15 ቀናት በኋላ ጀምሮ ባለይዞታዎች አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በመሄድ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።
ለማመልከት ሲኬድ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በመያዝ ሲሆን የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት የከናወናል።
የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ስራው በሚሰራባቸው አካባቢዎች ምዝገባው እስኪጠናቀው ድረስ ምንም አይነት የስም ዝውውር እንዳማይደረግ ተገልጿል።
7ተኛ ዙር የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ የሚካሄድባቸው አካባቢዎች፦
* ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣ 5፣ 8፣ እና 10
* የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣ 5፣6፣7 ፣8 እና 9
* ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣5፣11፣12እና14
* አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4፣5 እና 8
* ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣3፣4፣5እና 6
* አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ11፣12፣13እና 14
* ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 እና 13 ናቸው ተብሏል።
የይዞታ ማረጋገጡ ስራ የሚከናዎነው በስልታዊ ዘዴ ወይም በመደዳ ሲሆን የይዞታ ማረጋገጥ ስራ በታወጀባቸው በ7 ክፍለ ከተማዎች እና በ30 ወረዳዎች ውስጥ በ85 ቀጠናዎችና በ386 ሰፈሮች የይዞታ ማረጋገጥ ስራው ይካሄዳል።
በተጠቀሰው አካባቢ ባለይዞታ የሆኑ ሰዎች #በጊዜ እንዲያስመዘግቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳስቧል።
@tikvahethiopia

አትሌት ለተሰንበት ግደይ አሸናፊ ሆነች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም አትሌቲክስ ኢንተርናሽናል ፌርፕሌይ (ስፖርታዊ ጨዋነት) ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።
አትሌቷ የሽልማቱ አሸናፊ የሆነችው በቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን ጋር በነበራት ቅፅበት መሆኑ ተገልጿል።
አትሌት ሲፋን በውድድሩ ላይ መውደቋን ተከትሎ አትሌት ለተሰንበት #ስታፅናናት እንደነበር አይዘነጋም።
አትሌት ለተሰንበት ከሽልማቱ በኋላ ፤ " ሲፋን ሀሰን ስትወድቅ እኔም ከልቤ ተሰምቶኝ ነበር ምክንያቱም የውድቀትን ስሜት አውቀዋለሁ የ2023 ፌር ፕሌይ ሽልማት በማሸነፌ ተደስቻለሁ። "ብላለች።
Via @tikvahethsport

ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግብይት! የM-PESA መተግበሪያን ዛሬውኑ አውርደን እንጠቀም ፤ ህይወታችንን ቀለል እናድርግ!
ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #FurtherAheadTogether

#EMA
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፤ " የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ ያግዛቸዋል " ያለውን ስልጠና ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከሚገ ኙ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ የሚኒ ሚዲያ አባላት ተማሪዎች መስጠቱን ገለጸ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ ፤ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በርካታ መገናኛ ብዙኃን እየተበራከቱ መሆናቸውንና በዚህም በርካታ የተሳሳቱ፣ ሀገርን የሚያፈርሱ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ሐሰተኛና የጥላቻ ንግግሮች ሲሰራጩ እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል።
መ/ቤታቸው የሰጠው ስልጠናም ታዳጊዎች መገናኛ ብዙኃንን ሲጠቀሙ ፤ የትኛው መረጃ ትክክል እንደሆነ እና እንዳልሆነ እና የትኛው መረጃ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ ነው የሚለውን በመለየት እና ባለማሰራጨት፣ ባለማጋራት እንዲሁም ተሰራጭቶ ሲያገኙ ለባለሥልጣኑ በመጠቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ፤ ስልጠናው ተማሪዎቹ ከወዲሁ የጥላቻ ንግግርን እና የሐሰተኛ መረጃን አስከፊነት እንዲረዱ እና መከላከያ መንገዶችንም እንዲያውቁ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።
" ወጣቶች ነገ የሚረከቧት ሀገር ከጥላቻ የፀዳች እንድትሆን ጥላቻን በመፀየፍ የሀገርን አንድነትና የህዝቦችን አብሮነት ለማፅናት የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ የበኩላቸውን ዛሬ ላይ መወጣት ይኖርባቸዋል " ሲሉም አሳስበዋል።
ይህ ስልጠና የማስጀመሪያ ነው ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ወደፊት በአዲስአበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም 2ተኛ ደረጅ ት/ቤቶች እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መሰል ስልጠና ለመስጠት ውጥን መኖሩን አመልክቷል።

#Tigray
በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ህጋዊ የቤት መሸጥና ማዘዋወር አገልግሎት ከህዳር 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደገና መጀመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ያረፈበት መመሪያ ያስረዳል።
መሬታ በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ አገልግሎትም አርብ ህዳር 28/2016 ዓ.ም በይፋ መጀመሩንና የመቐለ ከተማ አስተዳደር 300 ቦታዎቸ በሊዝ ጨረታ ለፈላጊዎች ማቅረቡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ሰነድ መሸጫው ቦታ ድረስ በመሄድ አረጋግጧል።
የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እንዳረጋገጠው የመሬት ሊዝ ጨረታ ሰነድ በብር 3 ሺህ መሸጡንና ለአንድ ካሬ መሬት የመነሻ ዋጋ ብር 4,500 መቅረቡ ብዙዎቹ አላስደሰተም።
በተያያዘ ታግዶ የቆየው የተሽከርካሪ ሽያጭና ዝውውር ተፈቅዷል።
እስከ አሁን ከአንድ ሺህ በላይ የተሰረቁ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬዎች መኖራቸውንና እነዚህ ለመቆጣጠር የመሸጥና የማዘዋወር አገልግሎት ሳይጀመር ለመዘግየቱ ምክንያት እንደሆነ የገለፁት የትግራይ ትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ሃላፊ አቶ መንግስቱ ፤ አስፈላጊው የማጣራት ተግባር ከተከናወነ በኃላ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ከህዳር 16/2016 ዓ.ም ጅምሮ አገልግሎቱ እንዲቀጥል መወሰኑን አብራርተዋል።
የመሸጫና ዝውውር አገልግሎቱ እንዲያከናውኑ የተፈቀደላቸው ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በቢሮው ተመዝግበው ለነበሩ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንደሆነ ፤ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በኃላ የተደረገው የሽያጭና ዝውውር አገለግሎት ህጋዊ እንዲሆን ግን ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልገው አቶ ታደለ አክለው ገልፀዋል ።
ጦርነቱ ከተጀመረ በኃላ ከሌሎች የአገሪቱ አከባቢዎች ወደ ትግራይ የገቡ ህጋዊነታቸው የሚያጠራጥሩ ተሽከርካሪዎች የማጣራት ስራ እንዲካሄድ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አቅጣጫ ሰጥቶበት ወደ ስራ እንደተገባ ሃላፊው መግለፃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#ኢንጪኒ
በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ አደኣ በርጋ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት የኢንጪኒ ከተማ ባለሥልጣን እና የጸጥታ አስከባሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
የከተማው ነዋሪዎች ምን አሉ ?
ስማቸው ለደህንነታቸው ሲባል እንዲገለፅ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦
* የሰባት ሰዎች አስከሬን ዛሬ ጠዋት ተገኝቷል።
* ማረሚያ ቤት ተሰብሮ እስረኞች ተለቀዋል።
* ህዳር 28 ቀን ለ29 ቀን 2016 ዓ.ም. አጥቢያ ከሌሊቱ ስድስት ሰኣት ጀምሮ ነው ጥቃት የተፈፀመው።
* የወረዳው ማረሚያ ቤት ተሰብሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተለቀዋል።
* በታጣቂዎቹ ጥቃት የከተማዋ አስተዳዳሪን (ብርሃኑ ሃብትዬ) ጨምሮ የሰዎች ህይወት አልፏል።
* በተለያዩ ጥበቃ ስራ የሚሰሩ እንዲሁም በማረሚያ ቤት ጥበቃ ላይ ነበሩ የተባሉ ፖሊሶችም መገደላቸውን ሰምተናል።
* ዛሬ ጠዋት ህዝቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ወጥቶ አስክረ ሲሰበሰብ ነበር። ቢያንስ ወደ ሰባት አስከሬን ተገኝተዋል፡፡ የተጎዱትም ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡
* በግምት ከእኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰባት ሰዓት ሰምተን የማናውቅ አይነት የተኩስ እሩምታ ነው ስንሰማ ያደርነው።
ሌላኛው ነዋሪ ፦
- በወረዳው የፖሊስ ጣቢያ ላይም ጥቃት ደርሷል።
- የወረዳው መሳሪያ ግምጃ ቤትም ተሰብሯል መባሉን ጠዋት ሰምተናል፡፡
- ሲንቄ ባንክ ላይም ከፍተኛ የመሰባበር ጉዳት ደርሷል፡፡ ሌሎች ባንኮች ግን ምንም አልሆኑም፡፡
- ታጣቂዎቹ በያቅጣጫው ወደ ከተማው መግባታቸው ነው የተሰማው፡፡ እኛ ወጥተን ማየት ፈጽሞ የማይታሰብ ብሆንም ጠዋት እንደሰማነው ቁጥራቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
- የቆሰሉ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡ አንድ ከታጣቂዎች የሞተ ሰው ግን አስከረኑ እስከ ከሰኣት አልተነሳም፡፡ እኛ ጠዋት እንደተመለከትነው ሰባት አስከሬን ቆጥረናል።
ሌላኛዋ ለደህንነታቸው የሰጉና ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ፦
• ታጣቂዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንደመሆናቸው በከተማው ውስጥ በነበሩ የመንግስት ጸጥታ ሃይል ሚመለሱ አልነበሩም።
• አሁን ከቤት ለመውጣትም ሰግተናል፡፡ ወንድ ወንዱ ብቻ እየወጣ የሞቱትን ማንሳት ለቅሶ መድረስ ነው ያለው፡፡
• ከተማዋ ጸጥ ብላለች፡፡ ሱቆችን ጨምሮ ምንም የተከፈተ ነገርም የለም።
ኃላፊዎች ምን አሉ ?
📞 ሬድዮ ጣቢያው ለወረዳው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ፋና ረጋሳ ቢደውልም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
☎ ለኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛም ስልክ ቢመታላቸውም ስልካቸው አነሳም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዴቼቨለ ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን ይገልጻል።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መፍትሄው_ምንድነው?
በአስሩ አማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ከራቁ ወራት አልፈዋል።
ተማሪዎቹ ሳይጠሩ / የሚጠሩበትን ጊዜ ሳያውቁ የፊታችን ሰኞ የ2016 ትምህርት ዘመን 4ኛው ወር ይገባል።
እስካሁን በእነዚህ ተማሪዎች ጉዳይ በይፋ አንዳች የተባለ ነገር የለም።
ተማሪዎቹም ሆኑ ወላጆቻቸው የትምህርታቸው ጉዳይ ቀን ከሌት ሀሳብ የሆነባቸው ሲሆን መንግሥት አሁንም ጊዜው ከዚህ ሳይረፍድ አለኝ የሚለውን መፍትሄ እንዲያሳውቃቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ።
በሌሎች የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን አሁን የመግቢያ ጥሪ ያልተደረገላቸው / መቼ እንደሚደረግላቸው እንኳን የማያውቁ ተማሪዎች በምን አግባብ ከሌሎች ተቋማት ተማሪዎች ጋር እኩል ለሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እንደሚቀመጡ ከአሁኑ ጭንቀት እንደሆነባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከምንም በላይ ከእድሜ እኩዮቻቸውና ባቾቻቸው ወደኃላ ቀርተው ቤት መቀመጣቸው ለከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንደዳረጋቸው በተደጋጋሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አስረድተዋል።
ተማሪዎቹ በህይወታቸው መቀለድ እንዲያቆም፣ የትምህርታቸው ጉዳይ መፍትሄ እንዲያገኝ ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም በይፋ ምን እያሰበ እንዳለ በመግለጫ እንዲያሳውቃቸው ድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
በክልሉ ያለው ተላዋዋጭ የሆነ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ተቋማት ተማሪዎችን ለመጥራት ፈተና እንደሆነባቸው ከዚህ ቀደም መግለፃቸው አይዘነጋም።

#ተክለሃይማኖት_ጠቅላላ_ሆስፒታል
የሳምባ ህክምና ክፍላችን በዘመናዊ መሣሪያዎች የተደራጀና በሃገሪቱ አንቱታን ያተረፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱት የሳንባ እና ፅኑ ህሙማን ሰብስፔሻሊስት ዶ/ር አምሳሉ በቀለ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
በክፍሉ የሚሰጡ ምርመራዎች እና ህክምናዎች የአስም ፣ የብሮንካይት፣ የሳንባ ኢንፌክሽን፣ የሳንባ ሽፋን ዉሃ መቋጠር፣ የቲቢ፣ የአየር ቱቦ አለርጂ ህክምና፣ ስፓይሮሜትር (የሳንባን ስራ ለማወቅ እና የጉዳቱን መጠን ለመለየት)፣ ጂን ኤክስፕርት (አስተማማኝ የቲቢ ምርመራና መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ባክቴሪያ ለመለየት)
📞 8175 / 0940 33 33 33
Facebook: https://www.facebook.com/teklehaimanothospital
Instagram: https://www.instagram.com/teklehaimanotgeneral
Telegram: https://t.iss.one/teklehaimanothospital1
Twitter: https://twitter.com/TeklehaimanotG4
Website: www.teklehaimanothospital.com
E-mail: [email protected]

#SunChips
ከፓፕሪካ እስከ ቶማቶ፣ ለሁሉም ያማረውን መርጦ ይመቻቻል። ከ#ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️ #መክሰስTime
From Paprika to Tomato, everyone gets the flavour they desire with #SUNChips 😋 and #SunnyMoments.☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia

" ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኃላ ህክምና ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም " - ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ተገደሉ።
ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ሊተርፉ ሳይችሉ ቀርቶ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አሳውቀዋል።
ብፁዕነታቸው የግድያው ምክንያት እንደማይታወቅ ገልጸው በክስተቱ የተሰማቸውን መሪር ኃዘን ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከኢኦተቤ ቴቪ ነው ያገኘው።

#EOTC
ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳወቀ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ነገ መግለጫ ይሰጣል።
መግለጫው በምን ጉዳይ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ባይገለፅም #በወቅታዊ_ጉዳዮች ዙሪያ እንደሆነ ተነግሯል።
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ለሚሰጠው መግለጫ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ላልሆኑና በቤተክርስቲያኗ ህዝብ ግንኙነት ለተመዘገቡ መገናኛ ብዙሃን በስፍራው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።