TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ኔፓል ሀገሪቱ ላይ " ቲክቶክ " እንዲታገድ ወሰነች። ኔፓል ፤ ማህበራዊ መስተጋብርን የሚረብሹና የቤተሰብን መዋቅር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያውኩ ይዘቶችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ያለችውን የቻይናውን " #ቲክቶክ " መተግበሪያ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈች። ሀገሪቱ ፤ " ቲክቶክ " በማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለች ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የሚለቀቁት…
#ቲክቶክ

ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ?

ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል።

ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲያጠፉ 30 ቀናት ሰጥቷቸው ነበር ፤ እንዲሁም ኒውዮርክን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች የመንግሥት ሰራተኞች " ቲክቶክ " ን እንዳያወርዱ ከልክለዋል።

በተጨማሪም ባይደን በሀገር ደረጃ ከሁሉም መሳሪያዎች ላይ መተግበሪያው እንዲታገድ እንዲያደርጉ የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

ለምንድነው መንግሥታት ቲክቶክን ለማገድ የሚንቀሳቀሱት ?

በተለይ ምእራባውያኑ ቀጥታ ጉዳዩን #ከቻይና ጋር ያገኛኙታል።

የምዕራቡ ዓለም የሕግ አውጪዎች እና ተቆጣጣሪዎች " ቲክቶክ " / ባለንብረቱ የባይትዳንስ የተጠቃሚ መረጃዎችን በቻይና መንግሥት እጅ እንዲገቡ ያደርጋል የሚል አቋም አላቸው።

ለዚህም እንደማያሳያ የሚያደርጉት የቻይና መንግሥት ለደህንነት ጉዳይ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚስጥር ከቻይና ኩባንያዎች እና ዜጎች መረጃዎችን መውሰድ የሚያስችለው ህግ እንዳለው በመግለፅ ነው።

ቲክቶክ መሰል ክሶችን ለረጅም ጊዜ ውድቅ አድርጓል።

- ህንድ በ2020 ላይ ነው ያገደችው።
- የብሪታኒያ ፣ የፈረንሳይ፣ የኒውዝላንድ ፣ የአውስትራሊያ፣ ካናዳ #ፓርላማዎች ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች እንዲታገድ አድርገዋል።
-  የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በተመሳሳይ ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች ላይ አግዷል። የወረደውንም አስጠፍቷል።
- ካናዳ የመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ፣ የመንግሥት ሰራተኞችም እንዳያወርዱት አድርጋለች።
- የዴንማርክ መከላከያ ሰራዊት ሰራተኞቹ በሙሉ እንዳይጠቀሙ አድርጓል። ስልካቸው ላይ ተጭኖ የነበረውንም አስጠፍቷል።
- ኖርዌይ በመንግሥት ሰራተኞች ስልክ ላይ እንዳይሰራ አድርጋለች።

በተጨማሪ ፦

* አፍጋኒስታን #ወጣቶችን ከአጓጉል ነገር ለመጠበቅ በሚል 2022 ላይ አድግዳለች።

* ኪርጊስታን በዚህ ዓመት የሀገሪቱን ባህል ወግ እና ስርዓት እየበረዘው ፣ ለልጆች፣ ለወጣቶች የአእምሮ ጠንቅ ነው በማለት አድጋለች።

* ኔፓል እና ሶማሊያም እንዲሁ እንዲታገድ ከወሰኑ ሀገራት መካከል ናቸው።

አሜሪካ ለማገድ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ አለ ?

ካለፈው ዓመት ህዳር ጀምሮ እጅግ በርካታ ግዛቶች " ቲክቶክ " ን  ከመንግስት መሳሪያዎች አግደዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች ለምሳሌ ፦ እንደ ቴክሳስ ፣ ኦውበርን ፣ ቦይስ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች አፕሊኬሽኑ #በዋይፋይ እንዳይሰራ አድርገው አግደዋል።

አሜሪካ ውስጥ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ቲክቶክ ሱስ የሚያሲዝ እንደሆነና ወጣቶችን እና ህፃናት ልጆችን አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል በሚል የሚከሱ ግዛቶችም አሉ።

ኮንግረሱ ቲክቶክ እንዲታገድ ይፈልጋል ? እንዲታገድ የሚፈልጉ የኮንግረሱ አባላት አሉ። (ከዚህ ቀደም የቀድሞው ፕሬዜዳንት ትራምፕ የማገድ እንቅስቃሴን እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል)

ምንም እንኳን አሜሪካ ውስጥ በመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዲሁም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ዋይፋይ ቲክቶክ ቢታገድም 150 ሚሊዮን ነው ተብሎ ከሚገመተው ተጠቃሚ ላይ እንዲታገድ ለማድረግ ረጅም ሂደት ሊጠይቅ እንደሚችል በዘርፉ ላይ ያሉ ፀሀፊዎች ይናገራሉ።

" ቲክቶክ " በየጊዜው የሚነሱበትን በተለይም የደህንነት እና የቁጥጥር ክሶች ውድቅ ሲያደርግ ቆይቷል።

@tikvahethiopia
' ቤቲንግ ' ሊታገድ ነው ?

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ መሆኑን የሚገልፁ በትክክል ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ሲሰራጩ ተስተውሏል።

ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን እየተሰራጩ ያሉት መልዕክቶች ፍፁም ስህተት ናቸው ብሏል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ።

" ' አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው ' በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት መሆኑን እንገልፃለን " ያለው አስተዳደሩ " የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ  ሎተሪን   በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከ ' ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ / ' ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር #እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ  ፤ ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ነው ዘርፉ #ሊታገድ ይገባል በሚል እየሰራ እንደሆነ አሳውቆ የነበረው።

የስፖርት ውርርድ ' ቁማር ነው ' ብሎ የሚያምነው ይኸው የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ፤ በተለያየ ጊዜ ሰርቻቸዋለሁ ባላቸው የዳሰሳ ጥናቶች ቤቲንግ ለወጣቱና ለታዳጊው ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ መሆኑን አመላካች መሆኑን ፤ ቁማር ታዳጊዎችን ይሁን አዋቂ ሰዎችን ወዳልተፈለገ መንገድ ሊወስድ የሚችል ማህበራዊ ቀውስ እንደሆነና ማንኛውም ሰው ሰርቶ የመለወጥ እሳቤውን የሚያቀጭጭ፣ ቤተሰብን ጭምር ወደ መበተን ሊያደርስ የሚችል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝቦ ነበር።

ወጣቶች እና ታዲጊዎች ለቤቲንግ ውርርድ ሲሉ ያላቸውን ነገር በሙሉ እስከማውጣት ይደርሳሉ ፤ ወጣቶች ስራን ከመስራት ይልቅ በአቋራጭ መክበር እንዲያስቡ በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን የሚቀንስ ተግባር ነው የሚልው መ/ቤቱ ቤቲንግ እንዲታገድ ፍቃድ ለሚሰጡት የንግድ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተቋማት አስፈላጊውን የግንዛቤ እና የማሳወቅ ስራ ቢሰራም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ባለማድረጋቸው ለውሳኔው መዘግየት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጾ ነበር።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤቲንግ እንዲታገድ ብርቱ እንቅስቃሴ ማድረግ መጀመሩን ካሳወቀ ወራት ቢቆጠርም እስካሁን በጉዳዩ ላይ አዲስ ነገር የለም።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ግን በ ' ቤቲንግ ' ኮሚሽን (15%) በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያስገኛል (ለሀገር) ፣ በርካታ ሰው በተለይ ሴቶችን ቀጥሯል ፣ ለማህበራዊ ጉዳይ ከገቢው ያውላል ፣ ቤት ይከራያል ፣ ገንዘብ ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ ያደርጋል ... ይህ ሁሉ ጥቅሞቹ ናቸው ብሎ ያምናል።

" ቤቲንግ " አትራፊ እንደሆነ የሚገልጸው አስተዳደሩ " ጨዋታ " እንጂ " ቁማር " አይደለም ብሎ ያምናል። በስርዓት እንዲመራም መመሪያዎችን አውጥቶ እየሰራ እንደሆነና " እኛ ጨዋታውን አቅርበናል ፤ ተጫዋቹ ደግሞ በኃላፊነት መጫወት አለበት " ባይ ነው።

ማህበራዊ ቀውስ ያመጣ እንደሆነ ኃላፊነት ያለባቸው አካላት አጥንተው ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል በሚል ከሚታገድ በህግ እንዲመራና የማይገባቸው ሰዎች እንዳይጫወቱ ክትትል  ቢደረግ የተሻለ መሆኑ ታምኖበት እየተሰራ እንደሆነ በከወራት በፊት ገልጿል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ " ከጥር 3 ጀምሮ ቤቲንግ ይታገዳል " የሚሉ ምንጫቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ የነበረ ሲሆን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ይህ ፍፁም የተሳሳተ ነው ፤ ማንኛውም ቤቲንግ / የስፖርት ውርርድ ነክ መረጃ የሚገኘው ከኔው ነው እንጂ ከሌላ አይደለም ሲል አስገንዝቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
ቀላል የመክፈያ ዘዴ ከቴሌብር !

በቴሌብር ሱፐርአፕ ወይም *127# ግብይት ሲፈፅሙ ከአገልግሎት አቅራቢዎች/ነጋዴዎች በሚደርስዎ የክፍያ መጠየቂያ መልዕክት መሠረት የተጠየቁትን የክፍያ መጠን እና የጠያቂውን ማንነት አረጋግጠው የሚስጥር ቁጥርዎን ብቻ በማስገባት ክፍያዎን መፈጸም ይችላሉ፡፡

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጊዳሚ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ጊዳሚ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የመካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ጸሎት ላይ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ተወስደው ተገድለዋል። ድርጊቱ የተፈፀመው አርብ ኅዳር 14/2016 ዓ.ም. ሌሊት 8 ሰዓት አካባቢ ነው። የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የወንጌል እና ቲዎሎጂ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ለሊሳ ዳንዴል ምን አሉ ? (ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ…
" ቤተክርስቲያን ለፍትህ ድምጿን  ስታሰማ ብትቆይም ምላሽ የተሰጠበት አንድም ጊዜ አልነበረም " - መካነ ኢየሱስ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፤ በኦሮሚያ ክልል ቄሌም ወለጋ ዞን፤ በጊዳሚ ወረዳ በአባላቶቿ ላይ የደረሰውን ግድያ አስመልከቶ  ዛሬ መግለጫ አውጥታለች።

በመግለጫዋ ፤ በኦሮሚያ ክልል፣ በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ፤ መነ ሃሞ በመባል በሚታወቀው ቀበሌ " ቶኩማ መነ ሃሞ " በተሰኘ የመካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ላይ በቤተ ክርስቲያን በጸሎት ላይ  ከነበሩት 17 ሰዎች መካከል ማንነታቸው ተጣርቶ ባልታወቁ ታጣቂዎች 9 የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙ በሚዲያዎች መግለፁን ጠቁማለች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዩን በሚመለከት መረጃዎችን ለማግኘት የሚቻላትን ሁሉ ስታደርግ የነበረ ቢሆንም፤ መንግስትም ባለው ሃላፊነት መሠረት ሁኔታውን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል በሚል ተስፋ እስካሁን ዝምታን መርጣ መቆየቷን ገልጻለች።

ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የተገደሉት ሰዎች ከፖለቲካ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ንጹሐን ዜጎች መሆናቸውን የገለፀው ቤተ ክርስቲያኒቱ ድርጊቱን በጽኑ አውህዛ ፤ ኃዘንዋን ገልጻለች።

የዚህ እኩይ ተግባር ሰለባ የሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት፡-

1. ተሊላ ላሜሳ ታሲሳ
2. ቶሊና ላሜሳ ታሲሳ
3. ታምራት ላሜሳ ታሲሳ
4. ቀበና ቡልቻ ጉተማ
5. ጌታቸው ቤከታ ታይሳ
6. ሂካ አያና ያደሳ
7. ጅረኛ ድንገታ ቴሶ
8. ሰለሞን ድንገታ ቴሶ
9. ሲራጅ ደኑ መሆናቸውንና ሁላቸውም በወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ የነበሩ እንደሆኑ ገልጻለች።

አምስቱ ከሁለት ቤተሰቦች የሆኑ ወንድማማች ሲሆኑ ከዘጠኙ አራቱ የቤተሰብ ኃላፊዎች ናቸው ብላለች።

ቤተክርስቲያኒቱ በጊዳሚ የተከሰተው ይህ በግፍ መገደል በዓይነቱ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ገልጻለች።

ከዚህም በፊት በተለያዩ ቦታዎች፤ ለምሳሌ፦

- ባለፈው ዓመት በምስራቅ ወለጋ በሳሲጋ ወረዳ 15 የቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናን በዕሁድ የአምልኮ አገልግሎት ላይ እያሉ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በጅምላ ተገድለዋል።

- በምዕራብ ወለጋ ዞን በቦጂ ወረዳ በዕሁድ አምልኮ ላይ የነበሩ ሶስት ወጣቶች በታጣቂዎች ተገድለዋል።

በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች በምእመናን ላይ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተከሰቱ መሆኑን ጠቅሳለች።

ለነዚህ ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለፍትህ ድምጽዋን ስታሰማ ብትቆይም ምላሽ የተሰጠበት አንድም ጊዜ አንዳልነበር አስረድታለች።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በማንኛውም ደረጃ የሚገኙ የፌደራል መንግስትና የክልል ህግ አውጪ፣ ህግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካላት ብርቱ ክትትል በማድረግ ህዳር 14/2016 ዓ/ም እና ከዚያም በፊት ላይ የተፈጸመውን በደል እንዲጣራና አጥፊዎቹ ወደ ህግ እንዲቀርቡ ያደርጉ ዘንድ መንግስትን ዳግመኛ አበክራ ጠይቃለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። ከጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም  ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቀደም ሲል በስራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? - ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም - ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም - ኬሮሲን በሊትር…
#እንድታውቁት

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ?

- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ነው።

@tikvahethiopia
#ኮሬ #ዳርባማናና

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ዳርባ ማናና ወረዳ 2 ወጣቶች መገደላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአከባቢው ነዋሪዎች ለማወቅ ችሏል።

አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ የቀድሞ አማሮ ልዩ ወረዳ ባለሥልጣን ደግሞ ፤ ወጣቶቹ የተገደሉት ሲጠፉ የነበሩ መከላከያ ሠራዊትን ለማስመለጥ ሞክራችኋል ተብለው እንደሆነ ተናግረዋል።

በመንግስት የፀጥታ ኃይል የተገደለው አንደኛው ወጣት ሳሙኤል ሰለሞን እንደሚባልና ይኸው ወጣት ቀጥታ ሞተር ሳይክል ላይ እንደነበር ተመቶ እንደተገደለ ገልጸዋል።

ሌላኛው አቡለ ጸጋዬ የተባለ ወጣት ጉጂ ቦሬ ወደ ተባለ ካምፕ ከተወሰደ ከቀናት በኃላ ስቃይ ተፈፅሞበት መገደሉን ገልጸዋል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ የአካባቢው ነዋሪ  በበኩላቸው ፦

* ከመከላከያ ሲኮበልሉ የነበሩ አባሎችን ሲፈልጉ የነበሩ የመንግሥት ሠራዊቶች ሁለት በሞተር ሲጓዙ የነበሩ ወጣቶችን ኮሬ ዞን ሸሮ ቀበሌ ሙራ ማንቻ የሚባል ቦታ ምሽት አራት ሰዓት ላይ እንዳገኟቸው ገልጸዋል።

* አንዱ ከጸጥታ ኃይሎቹ በተተኮሰ ጥይት ወዲያው እንደሞተ ፣ ሌላኛውን ደግሞ ለማምለጥ ሲሞክር ይዘውት ወደ ሌላ ቦታ ወስደውት እንደነበር ፤ በኃላም እሁድ 7 ሰዓት ላይ እንደተረሸነ መስማታቸውን ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ ምን ምላሽ እንዳላቸው የኮሬ ዞን ምክትል ፖሊስ አዛዥ አቶ ሲዳሞ ማደቦን ጠይቋል።

ምክትል ፖሊስ አዛዡ  ፤ " በዚህ ነገር ላይ እኔ መግለጫ መስጠት አልችልም፣ ምክንያቱም ወጣቶች በሆነውም ባልሆነውም ቅሬታ ሊያቀርቡ ይችላሉ። መንግሥት እንደ መንግሥት እርምጃ ሊወስድ ይችላል " ብለዋል።

አክለውም፣ " የምሰጠው ነገር ከሕግ ጋር ሊጋጭ ስለሚችል ተነጋግረን ነው መረጃ የምንሰጠው " ሲሉ አክለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ጥያቄ ለዞኑ ፓሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አራርሶ ነጋሽ አቅርቧል።

ሁለት ወጣቶች በጸጥታ ኃይል ለምን እንደተገደሉ ሲጠየቁ ከአሥር ደቂቃ በኋላ እንዲደወል ቀጠሮ ቢሰጡም በቀጠሮው ሰዓት በድጋሚ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በተጨማሪ፦ " እባክዎ ስልክዎን ያንሱና ምላሽ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ። የወከሉት ሕዝብ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየተተኮሰበት እየተገደለ እንደሆነ እየገለፀልን ነው ፤ በዚህ ጉዳይም ከ10 ደቂቃ በኋላ ደውሉ ብለው ነበር " ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተላከላቸው የጽሑፍ መልዕክትም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ከዚህ ባለፈ ፦

- የኮሬ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ አየለ ስልክ ባላማንሳታቸው፣

- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ "ስብሰባ ላይ ነኝ" በማለታቸውና በድጋሚ ሲድልወልም ስልክ ባለማንሳታቸው ምላሻቸውን ለማካተት አልቻልንም።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የክልሉ ቅርንጫፍ በበኩሉ፣ ስለሁለቱ ወጣቶች እስካሁን መረጃ ባይደርሰውም በዞኑ ባለው የጸጥታ ችግር ነዋሪዎች እየተደበደቡ መሆኑን ከዚህ በፊትም እንደተከታተለ አስረድቷል።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ  ፤ ' ቀጣይ ምዕራፍ ለሁለንተናዊ ለውጥ! ' በሚል መሪ ቃል የምስጋናና የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዶ ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ " ከለውጡ ወዲህ ለተገኘው ፍትሃዊ አገልግሎት እና ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ ለሰጡት ምላሽ " በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ እና ለከንቲባ አዳነች አቤቤ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስፍራው ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል።

በምን ጉዳይ ምላሽ ተሰጠ ተባለ ?

በመድረኩ ላይ ፦

- የህዝበ ሙስሊሙ መሪ ተቋም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ፅ/ቤት ህጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ሆኖ እንዲመሰረትና ተቋማዊ አደረጃጀቱ እንዲሻሻል መደረጉ።

- በሸሪያ ህግ የሚመሩ ወለድ አልባ ባንኮች እንዲመሰረቱ መደረጉ።

- በአዲስ አበባ ለህዝበ ሙስሊሙ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ የቦታ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ በመመለሳቸው የሚሉት ተነስተዋል።

በሌላ በኩል፤ በታላቁ አሊም ሀጅ ሙሃመድ ሳኒ ሀቢብ ስም ማእከል ሊገነባ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከሉ ግንባታ በለሚ ኮራ ክፍለ ከተማ በአራት ሺ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ይሆናል። ማእከሉን በሃላፊነት እንዲያስገነቡ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሱልጧን ሀጅ አማን ለኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሀጅ ኢብራሂም አስረክበዋል።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ

@tikvahethiopia