TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ተመላላሽ የሕክምና ቀጠሮ ቢኖረንም ሆስፒታሉ ዝግ ስለሆነ አገልግልት ማግኘት አልቻልንም " - ተገልጋዮች ➡️ " ከ6 እስከ 9 ወራት ታግሰን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ስራ አቁመናል" - የጤና ባለሙያዎች 🔴 " የትርፍ ሰዓት ክፍያ አልተከፈለንም ብለዉ መደበኛ ስራቸዉን በሚያቆሙ ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን " - የዞን አስተዳዳሪ በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ…
#Update
#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ 14 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች ከስራ ቦታቸዉ ተወስደው ታስረዋል " - የሀንጣጤ ሆስፒታል ባለሙያዎች

" ' ለሚዲያ መረጃ ስለሰጣችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል ' የሚሉ አመራሮችም አሉ ! "

በሲዳማ ክልል፤ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓት ክፊያ ባለመከፈሉ ለሎካ አባያ ወረዳ፣ ለማዕከላዊ ሲዳማ ዞንና ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ በደብዳቤ ካሳወቁ በኋላ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆማቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ማሳወቃቸው ይታወሳል።

በወቅቱ ስለ ጉዳዩ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ ፥ የሠራተኛዉ ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን ገልፀዉ ክፍያዉ እንዲፈፀም ከክልሉ መንግስት ብድር መጠየቃቸዉንና በቅርቡ እንደሚከፈላቸዉ ገልፀዉ የነበረ ሲሆን " የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆም መብታቸዉ ነዉ " ሲሉ ገልጸውም ነበር።

ትላንት የሆስፒታሉ ሠራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት " ሁሉም ሰራተኛ በአንድነት ተፈራርሞ ባስገባዉ ደብዳቤ መሰረት ከባለፈዉ ሳምንት ጀምሮ የትርፍ ሰዓት ስራ ብቻ ያቆሙ ቢሆንም የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክር እና 7 የማኔጀመንት አካላትን ጨምሮ 14 የሚሆኑ የሆስፒታሉ ባለሙያዎችን ፖሊስ ከስራ ቦታቸዉ ጭምር ወስዶ አስሯቸዋል " ብለዋል።

" ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆሙ ሰበብ ተደርጎ በመደበኛ ስራዉ ላይ እንከን እንዳይፈለግበትና ላለመከሰስ የስራ ሰዓቱን በአግባቡ እየተጠቀመ ነዉ " የሚሉት ሠራተኞቹ  " ትላንት ጠዋት በድንገት 2 ዶክተሮች፣ 7 ነርሶችንና ሌሎች ባለሙያዎችን 'ትፈለጋላችሁ' በሚል ያለ ፍርድ ቤት መጥሪያ ከነ ጋዎናቸዉ ጭምር ወደ ሀንጣጤ ፖሊስ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" ሁሉም የሆስፒታሉ ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብንሄድም ' ከበላይ አካላት ታዘን ነዉ ' የሚል ምላሽ ነዉ የተሰጠን " ብለዋል።

ሠራተኞቹ ቀኑን ሙሉ እዛዉ ለመሆን መወሰናቸዉንና ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ የተወሰኑ አመራሮች ወደ ፖሊስ ጣቢያ የመጡ ቢሆንም የታሰሩት ሳይፈቱ ወደ ' ቤታችሁ ሂዱ ' ተብለው እስኪጨላልም እዛዉ የቀሩ ባለሙያዎች እንደነበሩ አስረድተዋል።

" የትርፍ ሰዓት ክፍያ ካልተከፈለን ብለን ስራ አላቆምን " የሚሉት የጤና ባለሙያዎቹ " አይደለም መደበኛ ስራ ለማቆም ምንም ሳይከፈለን በብዙ ችግሮች ዉስጥ ሆነን እራሳችንን እየጎዳን ከ8 ወራት በላይ የትርፍ ሰዓቱን ስራ ጭምር ስንሰራ ቆይተናል ነገሮች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ በደብዳቤ አሳዉቀን የትርፍ ሰዓቱን ስራ ለማቆም ተገደናል " ብለዋል።

ሁሉም ሠራተኛ የትርፍ ሰዓት ስራ ባቆመበት ሁኔታ የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ የማኔጅመንት አባላትንና የተወሰኑ ሠራተኞችን ለይቶ የማሰሩ ጉዳይ ተገብነት የሌለው እና የሚመለከታቸዉ አካላት በአፋጣኝ እልባት ሊሰጡበት የሚገባ ጉዳይ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

" ' ሚዲያ ላይ ስለከሰሳችሁ ሚዲያ የሚከፍላችሁ መስሏችኋል' የሚሉ አመራሮች ነበሩ " ያሉን ቅሬታ አቅራቢዎቹ " ሜዲካል ዳይሬክተሩንና ማኔጅመንቱን ' ለምን ሠራተኛ ታሳምፃላችሁ፣ ከወረዳዉና ከዞኑ መንግስት የሚተላለፍላችሁን መመሪያ ለምን አታስፈፅሙም ' ብለዉ የሚያስፈራሩም ነበሩ " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታዉቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የከፍተኛ አመራሮችን ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጓል።

ከዚህ ቀደም የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በስልክ መረጃ የሰጡን ቢሆንም አሁን ላይ " ወደ ቦታዉ በአካል ካልመጣችሁ መረጃ መስጠት አልችልም " በማለታቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

ፈቃደኛ ሲሆኑ ምላሻቸዉን የምናካትት ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በቀጣይ 10 ቀናት እስከ 200 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከማይናማር ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሰራ ነው " - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ➡️ " ወደ 242 ልጆች ነገ አርብ ከማይናማር ወደ ታይላንድ እንደሚገቡ ነግሮናል " - ኮሚቴው የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በማይናማር በአስከፊ ሁኔታ የሚገኙ ወደ 700 የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገለጸ። የሚኒስቴሩ…
#Update : በማይናማር ' ዲኬቢኤ ' ካምፕ የነበሩ 252 ኢትዮጵያውያን ትላንት ለታይላንድ የቀረበች በማይናማር በምትገኝ ማይዋዲ ወደምትባል ከተማ መሻገራቸውን፣ ይህም ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችላቸው አንድ እርምጃ መሆኑን የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህም፣ ኢትዮጵያውያኑንና የሌሎች ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 276 ወጣቶችን የዲሞክራቲክ ካረን ጦር ወደ ማይዋዲ እንደላከ ኮሚቴው ነግሮናል።

ኢትዮጵያውኑ በማይናማር በሚገኘው የዲሞክራቲክ ካረን ጦር (ዲኬቢኤ) ሥር የነበሩ፣ በመጀመሪያ ወደ ታይላንድ እንዲያሻግራቸው፣ ከዚያ ወደ ሀገራቸው እንዲመልሳቸው የመንግስትን ምላሽ ደጋግመው ሲጠይቁ የነበሩ ናቸው።

ኮሚቴው " አሁንም ገና መንግስት ወደ ቦታው ወኪል መላክ አለበት። ‘ለኤንጂኦ ውክልና ሰጥተናል’ ነው ያሉት ግን በኤንጂኦ ውክልና ብቻ ተላልፈው ወደ ኢትዮጵያ መተላለፍ አይችሉም። ለዚህ ጉዳይ የመንግስት ደሊጌሽን ያስፈልጋል " ብሏል።

" በተጨማሪም፣ በማይናማር ቢጄኤፍ ካምፕ ስክሪን አውት ተደርገው፣ ፓስፓርት ተሰጥቷቸው የተቀመጡ ወደ 495 ኢትዮጵያውያን አሉ። እንዲሁም የመንግስትን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሦስት ልጆች በስቃይ ናቸው የዛሬዎቹ ልጆቻቸን ከወጡበት አካባቢ ያሉ ማለት ነው " ሲል አክሏል።

" ከዚህ ቀደም ልጆቻችን በአንድ ወቅት ከካምፕ ባመለጡበት ወቅት በፓሊስ ታግተው የተመለሱ ወደ 26፣ በቢጂኤፍ ካምፕ አካባቢም ሌሎች 14 ልጆቻችን በስቃይ ላይ ናቸው። የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው ያሉት " ብለዋል።

" ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቀናል። ልጆቹን ከነሙሉ ስማቸውና ከነፓስፓርት ቁጥራቸው አስተላልፈናል። ‘ለሁለቱም ኤምባሲዎች እናሳውቃለን’ ብለውናል " ሲል ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ወቅዱስ ፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለመላው የሮማ ካቶሊካዊ መሪዎች እና በመላው ዓለም ላሉ ምእመናን እንዲሁም በኢትዮጵያ ላሉ ካቶሊካውያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ገልጸዋል።…
#Update

በዓለም ላይ ከ1.4 ቢሊየን በላይ ተከታዮች ያላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በትናንው ዕለት 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕይወታቸው ማለፉን ማስታወቋ ይታወሳል።

ቫቲካግ ዛሬ እንዳስታወቀችው የፖፕ ፍራንሲስ ሞት ምክንያት በስትሮክ እና የልብ ህመም ነው።

የስርአተ ቀብራቸውን ቀን ለመወሰንም ካርዲናሎች በቫቲካን ተሰብስበው ነበር።

በዚህም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ቅዳሜ እንደሚፈጸም ቫቲካን አስታውቋል።

በሌላ በኩል ፥ እንደ ቤተክርስቲያኒቱ ሕግ የአዲሱ ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ምርጫ ከ15 እስከ 20 ቀን ውስጥ ይጀመራል።

አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስኪመረጥ ድረስ ቤተክርስቲያኒቱ በካርዲናሎች ቡድን ትመራለች። ቀጣዩን ሊቀ ጳጳስም የሚመርጠውም ይኸው የካርዲናሎች ቡድን ነው።

የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን 252 ካርዲናሎች ያሏት ሲሆን እንደ ቫቲካን ከሆነ በሊቀ ጳጳስ ምርጫው ላይ ድምፅ መስጠት የሚችሉት 138ቱ ካርዳናሎች ብቻ ናቸው።

ከ1975 ጀምሮ በሊቀ ጳጳስ ምርጫው ላይ ድምፅ መስጠት የሚችሉት ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በታች የሆኑ ካርዲናሎች ብቻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ካርዲናሎቹ በእነዚህ ጊዜያት ከውጪው ዓለም ጋር መገናኘት የማይችሉ ሲሆን የምርጫው ሂደትም በጣም ሚስጥራዊ ነው።

ካርዲናሎቹ አዲስ ሊቀ ጳጳስ እስኪመርጡ ድረስ ይቆያሉ። ረጅሙ የቆይታ ጊዜ በ13ኛው ክፍለ ዘመን ሊቀ ጳጳስ ለመምረጥ 3 አመት የቆዩበት ነው።

በ2013 ፖፕ ፍራንሲስ ሲመረጡ ከአንድ ቀን ብዙም ያልተሻገረ ነበር።

መረጃው የቫቲካንን እና ዩኤስ ቱዴይ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ " - የጤና ባለሙያዎች

" የ4 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ተከፍሎን ስራ ጀምረናል፤ በወረዳዉ ስራ ሲዘጋ መክፈል የተለመደ ነው !! "


ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት ሥራ ማቆማቸውንና 14 ሰዎች መታሰራቸውን በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ የሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል።

ጤና ባለሙያዎቹ ዛራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከታሰሩት 14 ባለሙያዎች 7ቱ ሲፈቱ 7ቱ አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

ካልተከፈለዉ የ9 ወራት ዉዝፍ ዉስጥ የ4 ወራት ክፊያ መፈጸሙን ተከትሎ ሥራ መጀመራቸውን የገለጹት ባለሞያዎቹ " የትርፍ ሰዓት ስራ ከቆመ በኋላ ክፍያ መፈፀም በወረዳዉ የተለመደ ጉዳይ ነዉ " ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ከታሰሩ 5ኛ ቀናቸዉን የያዙት የታሰሩ የጤና ባለሙያዎች " እንዲፈቱ በተደጋጋሚ እየጠየቅን ነዉ ያሉት ሰራተኞቹ እስካሁን ግን ግልፅ ምክንያት አልተነገረንም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳዳሪና ፖሊስ አዛዥን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።  በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTOC ዛሬ ማለዳ ቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ አካሂዶ ነበር። በዚህም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፎኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል። በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ  ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት  ለረቡዕ ሚያዝያ…
#Update

ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታገደ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያን መሰረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብሮ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ እንዲያከናውን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን ፍቃድ መሰጠቱ ይታወሳል።

ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት " ቅድስት ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም " በሚል ርእስ የተላለፈው ትምህርት ውዝግብ በማሰነሳቱና ቋሚ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ለመስጠት ለረቡዕ ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ የያዘ በመሆኑና ጉዳዩ በሚገባ ተጣርቶ ውሳኔ እስከሚሰጠው ድረስ ከመምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን የተሰጠው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው መታገዱን የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዛሬ አሳውቋል።

በሌላ በኩል የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ለፍኖተ ጽድቅ በጻፈው ደብዳቤ " ማኅበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ርቱዕ እምነትን ከሥነ ምግባር ጋር ይዞ የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያን ያሳዘነ፣ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለጠላት መሳለቂያ እንድትሆን ያደረገ ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ጋር የሚቃረን ' እመቤታችን ቤዛ አይደለችም ' የሚል ጤናማ ያልሆነ ትምህርት ሚያዝያ 10 ቀን 2017 ዓም በማኅበሩ ሚዲያ ማስተላለፉን ተመልክተናል " ሲል ገልጿል።

በዕለተ ስቅለት የተላለፈው ትምህርት ቪዲዩ በአስቸኳይ ከማኅበሩ ዩቲዩብ እንዲወርድ እንዲያደርግና በዕለቱ የተላለፈውን ትምህርት ሙሉ ቪዲዮ ቅጂ ለመምሪያው እንዲያቀርብ እንዲሁም ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቷል።

#EOTC #FenoteTsidk

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም ስለ አክሲዮን ሽያጩ ምን አለ ?

-  ኢትዮ ቴሌኮም ለ121 ቀናት የ10% ድርሻ አክሲዮን ሲሸጥ ቆይቷል።

- አጠቃላይ 47,377 ኢንቨስተሮች ተሳትፈዋል ፤ ሼሮችን ገዝተዋል።

- አጠቃላይ 10.7 ሚሊዮን ሼር ተሸጧል።

- አጠቃላይ 3.2 ቢሊዮን ብር አሴት/ value ተፈጥሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ፍራንቼስኮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት በቅድስት መንበር የቅድስት ማርያም ባዚሊካ ተፈጽሟል።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገራት መሪዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

Photo Credit - CNN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" የበሽታው ስርጭት አሁንም በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑ ህብረተሰቡ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶችን ጠንቅቆ በማወቅ እራሱን ከበሽታው መከላከል አለበት " - ሲስተር ሰፊ ደርብ

በአማራ ክልል ከሳምንት በፊት " ቡሬ ባቡና " በተባለ የፀበል ስፍራ ሁለት ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገልጿል።

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ በተለይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ወረዳ "ቡሬ ባቡና " በተባለ የፀበል ስፍራ ከመጋቢት 29 / 2017 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ ሁለት ሰዎች ሙተዋል።

ሰዎቹ የሞቱት ከሚያዝ 5/እስከ 12/2017 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ሲሆን አንዱ በፀበል ስፍራው ሌላው ደግሞ ከፀበል ስፍራው ወደሚኖርበት ሰከላ ወረዳ ከሄደ በኃላ መሞታቸውን ሲስተር ደርብ ገልፀዋል።

ከመጋቢት 19 / 2017 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ በሶስት ማለትም፦

- በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው " በርሜን ጊዮርጊስ " ፤

- በሰሜን ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ " አንዳሳ " ፀበል እንዲሁም

- በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራው ፍል ውሃ በተባሉ የፀበል ስፍራዎች በብዛት የበሽታው ስርጭት ሲታይባቸው መቆየቱ ይታወሳል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ "ቡሬ ባቡና "በተባለ የፀበል ስፍራ አዲስ ወረርሽኝ ተከስቷል ብለዋል ሲስተር ሰፊ ደርብ።

ታህሳስ 24 2017ዓ.ም በቋራ ወረዳ በርሚል ጊዮርጊስ ከተከስተው የኮሌራ ወረርሽኝ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 10 / 2017 ዓ.ም ድረስ በወረርሽኙ 15ሰዎች ይወታቸው አልፏል።

ከሁለት ሺ 118 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸውን ሲስተር ሰፊ አክለዋል።

ባለፈው ሳምንት ምንም አይነት ሞት አለመመዝገቡን የተናገሩት ሲስተር ሰፊ ደርብ የበሽታው ስርጭት አሁንም በእጅጉ እየተስፋፋ በመሆኑ ህብረተሰቡ የበሽታውን መተላለፊያ መንገዶችን ጠንቅቆ በማወቅ እራሱን ከበሽታው መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBDR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር ተሰጥቶ የነበረው የዘገባ ፍቃድ ለጊዜው ታገደ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያን መሰረት እምነት፣ ሥርዓተ አምልኮና ትውፊት አክብሮ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ዘገባ እንዲያከናውን ለፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን ፍቃድ መሰጠቱ ይታወሳል። ሆኖም ግን በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በዕለተ ስቅለት " ቅድስት ድንግል…
#Update

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በመኖሪያ ቤታቸው ተአቅበው እንዲቆዩ ቋሚ ሲኖዶስ ወሳኔ አሳለፈ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከቤተክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ በፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማኅበር አዳራሽ የሰጡትን ትምህርትና በማኅበሩ ሚዲያ የተላለፈበትን ሁኔታ በተመለከተ በዛሬ መደበኛ ጉባኤ ተወያይቶ ለመወሰን በያዘው ቀጠሮ መሰረት ውይይት ካደረገ በኋላ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም ፦

1. ፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር በተለያዩ ጊዜያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውጪ በሚዲያው ያስተላለፈው የስሕተት ትምህርት የቤተክርስቲያኗን አባቶች፣ ሊቃውንቱንና መላው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያሳዘነ በመሆኑ በማህበራት ምዝገባ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ በኩል ጊዜያዊ የእገዳ ደብዳቤ እንዲደርሰው እና በመምሪያው በኩል አስፈላጊው ጥብቅ ክትትል እንዲደረግ ሆኖ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ይቻል ዘንድ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም አድርጓል።

ቋሚ ሲኖዶስ ያቋቋማቸው አጣሪ ልዑካን አጠቃላይ የማህበሩን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እና በሚዲያው ያስተላለፋቸውን የስህተት ትምህርቶች በተመለከተ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከማህበራት ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያ ጋር በመነጋገር በሚገባ መርምርውና አጣርተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርቡ ወስኗል።

2. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያኗ የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ ወንሷል።

3. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ ወስኗል።

4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኝ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት ለፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር ሚዲያ የአየር ሰዓት የሰጠበትን ዝርዝር ሁኔታና ከማኅበሩ ጋር በተያያዘ አየር ላይ ያዋላቸውን ትምህርቶች የሚያሳይ ሪፖርት እንዲያቀርብ እንዲደረግ ወስኗል።

መረጃው የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ ከትርፍ ሰዓት ክፊያ ጋር በተያያዘ ሁለት ሳምንት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩ የጤና ባለሙያዎች በዋስ መፈታታቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከስፍራዉ አረጋግጧል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከሚያዚያ 8/2017 ዓ/ም ጀምሮ 14 የጤና ባለሙያዎች ታስረዉ የነበረ ሲሆን 7ቱ ከቀናት እስር በኋላ ተለቀዉ 7ቱ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ በሀንጣጤ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የቆዩ ቆይተዋል።

ዛሬ እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ መደረጉን የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በሚገኘዉ ሀንጣጤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉ የጤና ባለሙያዎች ከ6 እስከ 9 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ባለመከፈሉ ከወረዳ እስከ ክልል መዋቅር አሳዉቀዉ የትርፍ ሰዓት ስራ ማቆማቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳዉቀዉ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ ከእስር ተፈቱ የተባሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማግኘት ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም።

ጉዳዩን አሁንም በቅርበት የምንከታተል ይሆናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia