TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ? በረሃብ ማለቅ አለብን ? " - ተፈናቃዮች

ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በ2015 ዓ/ም በነበረው ማንነት ተኮር ግጭት የተነሳ ቤት እና ንብረታቸውን ጥለው ወደ አማራ ክልል፤ ቻግኒ የመጡ ተፈናቃዮች እርዳታ እየተደረገልን አይደለም፤ በረሃብ ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 2 ህፃናት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።

በቻግኒ የሚገኙት 2000 የሚደርሱ ተፈናቃይ ወገኖች ሲሆኑ በግለሰብ ፍርስራሽ ቤቶች እና ጅምር ፎቆች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።

የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሀሰን፦

" ካለፈው ሳምንት ብቻ ሁለት ህፃናት በረሃብ ምክንያት ሞተውብናል።

እኛ እስከ ዞን እስከ ክልል ድረስ ወስደን ደብዳቤ አስገብተናል። ዞኑ እራሱ ፈርሞ የሞቱትን ሰዎች ዝርዝር በዛ ላይ አልተጠቀሱም ግን እንደሞቱ ሪፖርት አድርገናል።

በረሃብ ምክንያት ህፃን 34፣ ትላልቅ ሰዎች 21 በአጠቃላይ 55 ሰዎች እንደሞቱብን ሪፖርት አድርገናል።

እኛ ሰው ጠግቦ ይደር እያልን አይደለም ያለነው ቢያንስ ቀምሶ ይደር ህይወት ይዳን ነው። ምናለ መንግስት እንኳን ባያግዘን ሌላ ድርጅቶች ገባ ብለው ቢያግዙን ይሄ ሁሉ ጉዳት ይሄ ሁሉ ህዝብ እንዴት በረሃብ ይሞትብናል ?

ሰዎች ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሄድ ብለው የቀን ስራ ሰርተው እንዳበላ ያልታደሰ መታወቂያ ይዛችሁ አትሄዱም ተብለን ተዘግቶብናል። ተንቀሳቅሰን የቀን ስራ ካልሰራን እንዴት አድርገን ነው ህይወታችንን ማቆየት የምንችለው ? መንግሥትም እያገዘን አይደለም።

መንግሥት በቅርብ ወደሀገራችሁ ትገባላችሁ የሚል ነገር አንስቷል። ይሄም ቢሆን ደስ ይለናል በተለያዩ ቦታዎችም ምዝገባ አለ የሚባል ነገር አለ እዚህ ዞን ግን እስካሁን የመጣም ሆነ የተጠየቅነው ነገር የለም።

ወይ እርዳታ አልተደረገ፣ ወይ ወደተፈናቀልንበት ቦታ መንግስት ያለውን ነገር አረጋግጦ እየመለሰን አይደለም፣ እንዴት ነው የምንሆነው ኢትዮጵያዊ አይደለንም እኛ በረሃብ ማለቅ አለብን ? "

ከተፈናቃዮች መካከል አንዲት 60 ዓመት እናት፤ " እመጫትም ወልዳ የምትበላው የምትቀምሰው አጥታ ቁጭ ብለናል። እየተሰቃየች ነው ያለችው ተቸግረን ነው ያለነው በጣም በጣም ተሰቃይተናል " ብለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ለ52 ዓመታት እንደኖሩ የሚናገሩት የ75 ዓመት እድሜ ያላቸው አዛውንት አቶ ሀሰን መሀመድ ከ8 ልጆቻቸው 5 ወንድ ልጆቻቸው በግጭቱ እንደተገደሉና አሁን ላይ ከቀሪ 3 ሴት ልጆቻቸው ጋር በቻግኒ የግለሰብ ፍርስራሽ ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የሚላስ የሚቀመስ የለንም የሚሉት አዛውንቱ " በጣም አጣዳፊ የሆነብን የምግብ ጉዳይ ነው፤ ልጆችን እየቀብርን ነው በረሃብ ምክንያት መንግስት ሊሰማን አልቻለም አላወቀንም እንዳንል አንድ ጊዜ እርዳታ መጥቶልናል፤ ስማችንም በኮምፒዩተር ገብቶ ይታወቃል። መጠለያ አልተሰጠንም የትም ተበትነን በየከተማው በየበረዳው ተቀምጠን ነው በደል የደረሰብን ብርዱ ፀሀዩ ረሃቡ እየተፈራረቀብን ነው " ብለዋል።

የቻግኒ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ተወካይ ባለሞያ አቶ የሱፍ ሁሴን ምን አሉ ?

- ባለፈው ዓመት ግንቦት ላይ ነው እርዳታ የመጣው። አንዴ ተሰጣቸው ቆመ እስካሁን የለም።

- በረሃብ ተጎድተው ታመው የተኙ ሰዎች አሉ፣ በቂ ህክምና እንዳያገኙ ብር የላቸውም።

- ሃምሳ አምስት ሰው እንደሞተባቸው ለኛ ሪፖርት ሰጥተውናል። እሱን ደግሞ ለዞን ለክልል በደብዳቤ አሳውቀናል። ኮሚቴም ሄዶ እንዲያነጋግር ተደርጓል።

- ክልሉ 'እርዳታ አለ ግን ለማድረስ የመንገድ የፀጥታ ሁኔታ ችግር በመሆኑ ማድረስ አልችልም' የሚል ነው።

ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/VOA-11-29 #VOA

@tikvahethiopia
ሳፋሪኮም በሚያቀርብልን ያልተገደበ የኢንተርኔት ፍጥነት ፌስቡክ በመጠቀም መረጃ እናግኝ ፣ እንዝናና!

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia
#FurtherAheadTogether
" በተለይ በእነዚህ 5 ዓመታት ውስጥ በተፈጠሩ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዱ ካሉ ሴክተሮች ውስጥ አንዱ የማይክሮ ፋይናንስ ሴክተር ነው " - አቶ ተክሌ በቀለ

ከባንክ የተገለሉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ማኅበረሰቦች፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች ብድር በመስጠት ከ5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ተደራሽ ያደረገው የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር በጸጥታ ችግሮች ፈተና ውስጥ መግባቱን ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በዘርፉ ተጠቃሚ ከማድረግ፣ በቴክኞሎጅ ታግዞ ከመስራት አኳያ ክፍተቶች እንዳሉ በደንበኞች ቅሬታ ሲነሳ ይደመጣል።

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ ከበደ ፣ የፋይናንስ ሴክተሩ ትልቁ ችግር በቴክኖሎጂዎች ታግዞ አገልግሎት የመስጠት ችግር እንደሆነ፣ ችግሩን ለመፍታት ሲስተም እንደተበለጸገ አስረድተዋል።

ሴቶችና አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊ ከማድረግ አኳያ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " የሴቶችን ተሳትፎ ከመጨመር አኳያ፣ ስንጀምር ከነበረው አንፃር ስናይ አሁን ያለው በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሏል የሚል ነው ያለን አረዳድ፣ ምክንያቱም ከማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞች አንፃር ወደ 48 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው " ብለዋል። በርካታ አካል ጉዳተኞችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎችም ተሳታፊ እየሆኑ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

የማኅበሩ የሥልጠና፣ የምርመራና የማማከር ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ተክሌ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በየትኛውም አለም ችግር ሲፈጠር (ጦርነት፣ ግጭት፣ ሲፈጠሩ) በመጀመሪያ ደረጃ የሚጎዳው የፋይናይስና የቱሪዝም ዘርፉ ነው " ብለዋል።

" የፋይናንስ ዘርፍ በጣም ሴንሴቲቭ ነው " ያሉት ኃላፊው፣ " ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥም በተለይ በእነዚህ አምስት ዓመታት ውስጥ በተፈጠሩ ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዱ ካሉ ሴክተሮች አንዱ የማይክሮ ፋይናይስ ሴክተር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ ደንበኞች በጦርነትና ግጭት ሳቢያ የመሞት፣ ማምረትና ማርባት አለመቻል ችግር ስለሚደስባቸው የተበደሩትን ገንዘብ ሳይመልሱ እንደሚቀሩ ጥቅሰው፣ የሰላም አለመረጋጋት በሴክተሩ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ ያለ በጣም አንገብጋቢና አደገኛ ችግር ነው ብለዋል።

ግጭት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች በማይክሮ ፋይናንሱ ዘርፍ የደረሱትን ጉዳቶች እንዲያብራሩ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ በመላ አገሪቱ ያሉ ማይክሮ ፋይናንሶች ሁሉም ችግር ላይ እንደሆኑ፣ በአማራ፣ ትግራይ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የደረሰው ጉዳት በጣም ከፍተኛ እንደሆነና ገና እንዳልተጠና አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው ማኅበሩ ኅዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም መገናኛ በሚገኘው ኃይሌ ግራንድ 25ኛ ዓመት የኢዩበልዩ በዓል ባከረበበት ወቅት በግሉ ጥያቄ አቅርቦ ሲሆን፣ የማኅበሩ ደንበኞች 5 ሚልዮን እንደሆኑ፣ ሲመሰረት ተቋማቱ አራት እንደነበሩና አሁን ከ50 በላይ መድረሳቸው በመርሀ ግብሩ ተነግሯል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
የመምህር ፍስሃ ዓለሙ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

በጎንደር ከተማ የዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት መምህር ፍስሃ ዓለሙ በትላንትናው ዕለት ባልታወቁ ሰዎች በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።

ጉዳዩን የተከታተለው የጎንደር የቲክቫህ ቤተሰብ ድርጊቱ የተፈጸመው ህዳር 17 ለህዳር 18 / 2016 ዓ.ም በግምት ከሌሊት 10፡00 ስዓት አከባቢ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ሲጓዙ በነበረበት ወቅት ልዩ ቦታውም "ብሪጋታ ሰፍር" በተባለው ቦታ ነው።

ጉዳዩ በጸጥታ አካላት ክትትል እየተደረገበት መሆኑን የአራዳ ክፍለ ከተማ ሰላምና ደኅንነት ቢሮን ዋቢ አድርጎ የክፍለ ከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ የገለጸልን ሲሆን ቅርበት ካላቸው ምንጮች ደግሞ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰምቷል።

የመምህር ፍስሃ ባልታወቁ ሰዎች ተደብድበው መገኘታቸውንና ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ  ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።

የአከባቢው ምንጮች አኚህ ዐይነ ሥውር አባት የሞቱት በድንጋይ ተቀጥቅጠው እንደሆነ ቢጠቁሙም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሆስፒታሉ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

የመምህር ፍስሃ ሥርዓተ ቀብር ከሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ሽኝት ከተደረገለት በኋላ በትውልድ ቀያቸው ሰሜን ጎንደር በየዳ ወረዳ ኪዳነ-ምህረት ቤተክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።

መምህር ፍስሃ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 09 በሚገኘው የዓቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን የአቋቋም መምህር ሲሆኑ ህይወታቸው እስካለፈበት ህዳር 18 ድረስ በቤተ-ክርስቲያኒቱ  ወንበር ዘርግተው የአቋቋም ትምህርት ሲያስተምሩ ቆይተዋል።

መረጃውን የጎንደር የቲክቫህ-ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ነው የላከው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አህያ🫏 " ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ አለኝ " - አሰላ የሚገኘው የአህያ ቄራ አሰላ ከተማ የሚገኘው የአህያ ማረጃ ቄራ " የአህያ ምርቶች በሙሉ ለቻይና ገበያ የሚቀርብ እንጂ አገር ውስጥ የሚቀር ምርት የለም " አለ። " ሮግቻንድ " የተባለው የአህያ ማረጃ ቄራ አስተባባሪ የሆኑት ቺቺ አማን ቄራው በቀን ከ50 እስከ100 አህዮችን እያረደ ቆዳቸውን፣ ሥጋቸውን እና አጥንታቸውን…
#አህያ🫏

ሰሞኑን የአህያ ሥጋ በሆቴሎች ለምግብ እየቀረበ ነው የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ተስተውለዋል። ይህን ተከትሎም ነጋዴዎች የከብት ሥጋ ብናቀርብም የአህያ ሥጋ ነው በሚል የንግድ መቀዛቀዝና ኪሳራ ገጠመን ሲሉ አማረዋል።

በአዲስ አበባ ሆቴል ቤቶች ምግብ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ሥጋ የመመገብ ፍላጎታቸው እንደተዘጋ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ የሆነው የአህያ ሥጋ በአሰላ ሥጋ ቤቶች ተቀላቅሎ ለማኅበረሰቡ እየተሸጠ ተገኝቷል መባሉን ተከትሎ ባደረባቸው ሥጋት ጭምር ነው።

ብሩክ ኢትዮጵያ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጥበቃና ደኅንነት አለም ዓቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የማማከርና ልማት ባለሙያ ፍቅር ሽፈራው ከቀናት በፊት ፤ " ኢንፎርማሊ ባደረግነው አሰስመንት ወደ ምግብ ሥርዓቱ እየገባ ነው። ወደ ማኅበረሰቡ ከሥጋ ቤቶች ተቀላቅሎ የአህያ ሥጋ ወደ መሸጥ እየሄደ ነው " ሲሉ አሰላ ስላለው ሁኔታ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

አክለውም ፣ " ባለፈው የዛሬ ሁለት ሳምንት አካባቢ አሰላ ጋ አንድ ሦስት የሥጋ ቤቶች ተገኝተዋል፣ አይደንቲፋይ ተደርገዋል፣ የአህያ ሥጋዎችን መሸጥ የጀመሩ ማለት ነው " ማለታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተንቀሳቃሽ ምስል ተመልክቷል።

የተቋማቸው ሠራተኛ ስለአሰላ ሥጋ ቤቶች የአህያ ሥጋ አቀላቅለው እየሸጡ መያዛቸውን ስለመናገራቸው ፣ በአሰላ የአህያ ሥጋ ወደ ምግብ ሥርዓቱ እንደገባ የተቋማቸው ሠራተኛ እየመሰከረች ባለበት ሁኔታና የአህያ ቄራ በተፈቀደባት አገር ማኅበረሰቡ የአህያ ሥጋ ከሌሎች ከብቶች ሥጋ ጋር እየተቀላቀለ አይሸጥም ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻለዋል ? ለዚህ ማረጋገጫ ምን ዋስትና አላችሁ ? የአህያ ሥጋ ከሌሎች የከብት ሥጋዎች ጋር እንዳይቀላቀልስ በምን መልኩ ነው የምታጣሩት ? ምንስ ዋስትና አለ ? የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያብራሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አቅርቧል።

የድርጅቱ ከንትሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ቃሲም ምን ምላሽ ሰጡ ?

- ብሩክ ኢትዮጵያ የአህያ ሥጋ ወደ ምግብ ሥርዓቱ ገብቷል ብሎ ያጠናው ምንም አይነት ጥናት የለም።

- ይሄን መረጃ ትክክለኛነቱን ነው የምንጠራጥረው። ምክንያቱም ትክክል ከሆነ መረጃውን ያስተላለፉት ግለሰብ ለተናገሩት መረጃ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ማድረግ ያስፈልግ ነበር።

- ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ሊያስተላልፉት የሚችሉ የጤና መሰል ቀውሶች ከባድ ስለሆኑ እዚህ ያለውን ነገር አንድ ግለሰብ ተናገረ ተብሎ ሚዲያ ላይ ከማውጣት የተናገሩት ግለሰብ ከምን ተነስተው እንደንደተናገሩ፣ ተዘጉ የተባሉ ሉኳንዳ ቤቶች የትኞቹ ናቸው ? እርምጃ የወሰደው አካል ማነው ? የሚሉትን ጥያቄዎች ሁሉ መጣራት ነበረባቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የድርጅቱ የማማከር እና ልማት ባለሙያ ፍቅር ሽፈራውን ምን ማብራሪያ እንዳላቸው ለመጠየቅ ያደረገው  ሙከራ #አልተሳካም

በተያያዘ ፤ አህዮች ታርደው ወደ ውጪ እየተላኩ ያሉት አጥንታቸው ጭምር ሳይቀር ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን የአህያ ቄራ አስፈለገ? የአህያ ቄራ አገር ውስጥ ካለ ሥጋው ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዳይቀርብ ለማድረግ ስለሚያስቸግር አህያን የሚፈልጉ አገራት ለምን አህዮቹን ከነነፍሳቸው ጭነው አይወስዱም? የሚሉ ጥያቄዎችም በማኅበረሰቡ ዘንድ ሲሰነዘሩ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ለዚሁ ሀሳብ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለብሩክ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር በሰጡት ምላሽ ፥ " አህዮች ለቆዳቸው ሲባል መታረድ የለባቸውም የሚል አቋም ነው ያለን። በቁምም ተንድተው ታረዱ፣ አገር ውስጥም ታረዱ ከዚህ ሥጋት ነጻ መሆን አለባቸው። አህዮች መታረድ የለባቸውም የሚል ጠንካራ አቋም ነው ያለው ድርጅቱ " ብለዋል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-29
#መክሰስTime ስንልማ አምሮታችንን ለማሳካት - ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
There never is a bad time for #SnackTime with #SUNChips 😋 and #SunnyMoments. ☀️

Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
#አክሱም

የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓልና የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ? 

አክሱም ከተማ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አመታዊ የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ታከብራለች።

አክሱምና ዙሪያዋ ለአገር ውስጥና ውጭ  ጎብኚዎች የሚማርኩ በርካታ ቅርሶች የሚገኙባት በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች አንዷ ነች።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአውዳሚው ጦርነት በኃላ የአክሱምና ዙሪያዋ የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለመታዘብ ቦታው ድረስ ተጉዞ ነበር።

ከቱሪስት እንቅስቃሴ አኳያ የሚመለከታቸው አካላት አነጋግሮ እንዲሁም የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ቀድመ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ተከታትሏል።
 
አቶ ኪዲ ተጠምቀ በአክሱም ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የቱሪስት ማእከል አስተባባሪ ናቸው።

በትግራይ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም ለሶስት አመታት የተካሄደው ደም አፋሳሽ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መቆሙ ተከትሎ ወደ አክሱም የሚደረገው የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ፍሰት መጀመሩ መልካም ቢሆንም ከጦርነቱ በፊት ከነበረው የጎብኚዎች ቁጥር  ጋር ሲነፀፀር እጅግ አነስተኛ ነው ብለዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በአንድ አመት ውስጥ ፦ የፊሊፕንስ  ፣ የቻይና ፣ የኬንያ፣ የጣልያን ፣ የአሜሪካ ፣ የካናዳ ፣ የፈረንሳይ ፣ የዩጋንዳ፣ የደቡብ አሜሪካ፣ የናምቢያ ፣ የአውስትራሊያ ፣የቤሌጅም፣ የሰፔን ፣ የጀርመን ፣ የፓኪስታን ፣ የኮሪያ ፣ የቼክ ሪፐብሊክ ፣ የሃንጋሪ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የህንድ ፣ የፓላንድ ፣ የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው 200 የውጭ ዜጎች አክሱም ጎብኝተዋል።

ከጦርነቱ በፊት አክሱም የተጠቀሰው ያህል ቁጥር ያለው ቱሪስት በአንድ ቀን ውስጥ ታስተናግድ ነበር ይላሉ አቶ ኪዱ ተጠምቀ።  

በተጨማሪ፦

- በጦርነቱ ምክንያት ውድመትና ዝርፍያ ደርሶባቸው የነበረው ደረጃቸው የጠበቁ ሆቴሎች እድሳት ተደርጎላቸው አገለግሎት እየሰጡ ነው።

- ከአክሱም በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ታሪካዊቷ የዓድዋ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎችም አገልግሎት እየሰጡ ነው።

- ለጉብኝት የሚመጡት ቱሪስቶች የማረፍያ እጥረት አይገጥማቸውም።

አቶ ኪዱ ፥ የፕሪቶሪያው ስምምነት ተከትሎ አንድ አመት የሞላው ተነፃፃሪ ሰላም በክልሉ እንዳለ ፣ የአክሱም አውሮፕላን ማረፍያ አገልግሎት ባይጀምርም የሽረ አውሮፕላን ማረፍያ ከአክሱም በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ መሆኑ ከሽረ ወደ አክሱም በመኪና የሚያጓጓዝ ደረጃው የጠበቀ የአስፋልት መንገድ መኖሩ ፣ በአክሱም ከተማ ለጎብኚዎች የሚያሰጋ የፀጥታ ስጋት እንደሌለ ሚድያዎች እንዲሁም የፌደራል የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መ/ቤት በተለያዩ የውጭ ቋንቋዎች መረጃ በተከታታይ ያለማሰራጨታቸው ለቱሪስቶች ቁጥር ማነስ አስተዋፅኦ አለው ያሉ ሲሆን ይህ እጥረት እንዲታረም አሳስበዋል።

አክሱም የፀጥታ ስጋት የሌለባት ደህንነቷ የተጠበቀና በበቂ ሁኔታ እንግዶችን እያስተናገደችን መሆኗን በማወቅ ቱሪስቶች / ምእመናን ወደ አክሱ። በልበ ሙሉነት እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል።

አንድም በመኪና ካልሆነም ከአዲስ አበባ በአውሮፕላን ወደ ሽረ በመምጣት ከሽረ አውሮፕላን ማረፍያ እስከ አክሱም 60 ኪሎ ሜትር ርቀት በመሆኑ ደረጃውን በጠበቀው የአስፋልት መንገድ በመኪና ተጉዞ አክሱም መግባት ይቻላል።

መረጀው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱም የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓልና የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ?  አክሱም ከተማ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አመታዊ የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ታከብራለች። አክሱምና ዙሪያዋ ለአገር ውስጥና ውጭ  ጎብኚዎች የሚማርኩ በርካታ ቅርሶች የሚገኙባት በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች አንዷ ነች። የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአውዳሚው ጦርነት በኃላ የአክሱምና ዙሪያዋ…
"  ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ባላቸው አቅም ያግዙ " - የአክሱም ከንቲባ

አክሱም እንግዶቿን አክብራ እየተቀበለች ነው።

የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም የሚሄድ ሰው በቆየው ትውፊት መሰረት በወጣቶች እግሩ እንዲታጠብ ይደረጋል። ይህ ተግባር የእንግዳ ተቀባይነት መገለጫ ነው። 

የዘንድሮ የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም ያቀኑ እንግዶች በአራት አቅጣጫ ለፅዮን ክብር ሲባል በወጣቶች በተዘጋጀው የእግር አጠባ እየተደረገላቸው ሲገቡ ውለዋል።

አክሱም ከጦርነቱ በኃላ የተሻለ በዓል ለማክበር ተዘጋጅታለች የሚሉት የከተማዋ ከንቲባ አቶ አበበ ብርሃነ፤ መንፈሳዊ በዓሉ ለማክበር የሚመጡት ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖች ባላቸው አቅም የመርዳት ሰብአዊ ሃላፊነት አንዳለባቸው ገልጸዋል።

በተያያዘ መረጃ ከአክሱም በ60 ኪሎሜትር ርቀት በሽረ እንዳስላሰ ከተማ በሚገኘው የሜጀር ሐየሎም አርአያ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል ለሚገቡ እንግዶች የአቀባበል ስነ-ስርዓት ሲከናወን ውሏል።

የአቀባበል ስነ-ስርአቱ በሽረ ከተማ  አስተዳደር መሪነትና አስተባባሪነት የተካሄደ ሲሆን የሽረ የከተማ ነዋሪ እንግዶቹ በደስታ ተቀብሎ ወደ አክሱም ሲሸኙ ውለዋል።

የህዳር ፅዮን በዓል ከመቐለና ሽረ አውሮፕላን ማረፍያዎች ወደ  አክሱም እንግዶች ለሚያጓጉዙ የመኪና ባለቤቶች ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ መመልከቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

የፎቶ ባለቤት ፦ DW TV

@tikvahethiopia            
#CBE

ነጋዴ ነዎት?

እንግዲያውስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርቻንት አፕ (Merchant APP) ተጠቅመው ክፍያዎትን ይቀበሉ።
==========

መርቻንት አፕ ነጋዴዎች ወይም የሽያጭ ባለሙያዎች ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡

መተግበሪያውን ከ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbebirr.merchantapp አውርደው በመጫን ባቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ይመዝገቡና መለያ ቁጥር (Till No.) ይውሰዱ ። ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር (Till No.) ወስደው ከሆነ በቀጥታ መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ፡፡

አጠቃቀሙ

1. መተግበሪያውን ከፍተው የደንበኛውን ስልክ ቁጥር በማስገባት ክፍያውን ያስጀምሩ፣

2. ገዥው የነጋዴውን መለያ ቁጥር (Till No.) እና የክፍያውን መጠን የያዘ መልእክት ስልኩ ላይ ይደርሰዋል። ትክክለኛነቱን አረጋግጦ የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) በማስገባት ክፍያውን ያከናውናል፡፡

3. የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል። አለቀ፡፡
" ... ክልሎች ትኩረት እና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል ' የሚል መረጃ ያቀርባሉ " - አቶ አታለል አቡሃይ

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ፦

- በአገር አቀፍ ደረጃ በድርቅ፣ በጎርፍና በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ትኩረት እንዲያገኙና የተሻለ ድጋፍ እንዲኖራቸው፣ ክልሎች የተጎጂዎችን ቁጥር #በማጋነን ያቀርባሉ።

- ክልሎች ትኩረት ለማግኘትና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል '  የሚል መረጃ ይሰጣሉ።

- እስካሁን ሁሉም ክልሎች ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል ' ብለው ለኮሚሽኑ ሪፖርት አላቀረቡም። የቅድሚያ ቅድሚያ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገናል ብለው ለላኩ ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገን ነው።

- የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ መስጠት ካቆሙበት ጊዜ ጀምሮ፣ መንግሥት በራሱ አቅም ያለውን ክምችት በመጠቀም አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ክልሎች አሰራጭቷል። (7.9 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ግብዓቶች ድጋፍ ተደርጓል)

- በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች የቅድሚያ ቅድሚያ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። እስካሁንም ለእነዚህ ሰዎች በሁለት ዙሮች የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

(በአጠቃላይ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ ይሻሉ)

* በአማራ ክልል ለ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በድርቅ የተጎዱ ናቸው።

* በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምሥራቅ ዞኖች የሚገኙ 981 ሺሕ ሰዎች በድርቅ ምክንያት ትልቅ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

* በአፋር ክልል ዞን አንድ፣ ዞን ሁለት፣ ዞን ሦስት፣ ዞን አራትና ዞን አምስት የሚገኙ 225 ሺሕ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው።

- በድርቅ፣ በጎርፍና በሌሎች ችግሮች የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያገኙ የሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ መንግሥት የሚከተለውን አሠራር ተከትለው ከሠሩ አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነን።

- በተለያዩ ጊዜያት ከክልሎች ጋር ተከታታይ ስብሰባ ስናደርህ ይህንን " ያህል ሰዎች ሞተውብኛል " በማለት ያነሳ ክልል የለም። ብዙ ጊዜ ጉዳዩን ለሌላ አጀንዳ ይጠቀሙበታል።




በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በድርቅ፣ በጎርፍ እና እንዲሁም ከቄያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ባለማግኘታቸው በራሃብ ህይወት እጠፋ መሆኑን መነገሩ ይታወቃል።

ለአብነት ከሰሞኑን በትግራይ ክልል ድርቅ በከፋባቸው ወረዳዎች በረሃብ ምክንያት የሰዎች ህይወት ስለመጥፋቱ በርካቶችም ለልመና መውጣታቸው፣ ተማሪዎችም መበተናቸው መነገሩ አይዘነጋም።

በተጨማሪ ከኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ባደረግ ጥቃት ተፈናቅለው አማራ ክልል ቻግኒ በየጅምር ፎቅ እና ቤት ፍርስራሽ ስር የሚገኙ ከ2000 በላይ ተፈናቃዮች እርዳታ ከተደረገላቸው ወራት ማለፉን ፣ የህፃናትን ጨምሮ የአዋቂዎች ህይወት መጥፋቱን ተፈናቃዮች ሪፖርት ማድረጋቸውና የከተማው አስተዳደርም ለበላይ አካላት ሪፖርት ማድረጉ መዘገቡ አይዘነጋም።

ከዚህ ባለፈ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በራሃብ ምክንያት ሰዎች መሞታቸው፣ የሚበላ የሚቀመስ መጥፋቱን የቀበሌና ዞን አመራሮች ማሳወቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia