TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ስደተኞቹ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት የሌላቸው ሆነው በህጋዊ የመከላከያ ሠራዊት መኪና ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው አዛዛኝ ድርጊት ነው " - የኧሌ ዞን ኮሚኒኬሽን

* መነሻቸው ከኤርትራ አድርገው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው።

* ስደተኞቹ ሲጓጓዙ የነበረው ንብረትነቱ የፌዴራል መንግሥት በሆነው የመከላከያ ኦራል መኪና ነው ፤ የኦራል መኪናው ኮድ መሠ 2-2347 ነው።

በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ኬንያ ሲጓዙ የነበሩ 53 ሕገ-ወጥ ኤርትራውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኧሌ ዞን አስታውቋል።

ሕገ-ወጥ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት እሁድ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም. ምሽት ከኧሌ ወደ ደቡብ ኦሞ ሲያልፉ እንደሆነ የዞኑ ሰላም እና የፀጥታ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።

የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ አምሳሉ አንጋቶም ምን አሉ (ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት) ?

- በደላሎች አማካኝነት ተሰባስበው ጉዞ የጀመሩት ኤርትራውያኑ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መነሻቸውን ያደረጉ ናቸው።

- ከተጓዦቹ መካከል ሴቶች ያሉበት ሲሆን 6 ሕጻናትም አሉበት። በወራት የሚቆጠር ዕድሜ ያላቸው እና ጡት የሚጠቡ ሕጻናት ጭምር አሉበት።

- ስደተኞቹ የተያዙት በአካባቢው የነበሩ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ መኪናውን ካስቆሙ በኋላ ነው።

- ኤርትራውያኑ የተጫኑት በኢትዯጵያ መከላከያ ሠራዊት " ኦራል "ተሽከርካሪ ኮድ መሠ 2-2347 ነበር።

- እነዚህን ያመጣው ደላላ ነው። ደላላው እስከ መከላከያ ሠራዊት ድረስ ገብቶ ጥርጣሬ እንዳይኖር በዚያ መኪና እንዲጫኑ ተደርጓል።

- የመከላከያ ሠራዊት መኪና በምን አግባብ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ሌላ አገር ለማጓጓዝ አገልግሎት ላይ እንደዋለ በትክክል አልታወቀም።

- የመኪናው አሽከርካሪ በምን ምክንያት ስደተኞቹን ሲያጓጉዝ እንደነበረ ለቀረበለት ጥያቄ " አለቃዬ ነው ያዘዘኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

- ጉዳዩ በአቅራቢያው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት ክፍል ከተገለጸ በኋላ ከትናንት ጀምሮ ከሠራዊቱ አመራር ጋር ንግግር ተደርጎ ተሽከርካሪውን እና አሽከርካሪውን ተወስደዋል።

- 53ቱ ኤርትራውያን ስደተኞች እስካሁን ደረስ በዞኑ የኮላንጎ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል።

የኧሌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ማግሴ ጉያሎ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል።

ስደተኞቹን በአቅራቢያ ወደሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለማስገባት ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ስደተኞቹ ምን አሉ ? ከዚህ በፊት ለሥራ ፍለጋ ሱዳን ሄደው እየሰሩ ባሉበት በሀገርቱ ጦርነት ስለነበር በመተማ በኩል አድርገው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡና አሁን ደግሞ ወደ ኬንያ እየሄዱ እንዳለ መናገራቸውን ተገልጿል።

ነገር ግን ስደተኞቹ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት የሌላቸው ሆነው በህጋዊ የመከላከያ ሠራዊት መኪና ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው አዛዛኝ ድርጊት መሆኑን የዞኑ መንግሥት አሳውቋል።

ስደተኞቹ በአሁኑ ሰዓት በኧሌ ዞን መንግስት አማካይነት ምግብና ዉሃ እየተሰጣቸው ተጠልለው ይገኛሉ።

መረጃው ከኧሌ ዞን ኮሚኒኬሽንና ከቢቢሲ አማርኛው ክፍል የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Axum #EthiopianAirlines የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል። ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም። የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ…
#Axum

" እንደኛ ፍላጎትማ #ለህዳር_ጽዮን እንዲደርስ ነበር ... እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን የአክሱም ኤርፖርታችን ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን ይጀምራል " - አቶ ለማ ያዴቻ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጦርነት ምክንያት እጅግ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን እንደሚጀምር አሳውቋል።

በተለይም የአክሱም ነዋሪዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች ፣ በጦርነት የወደመው የአክሱም ኤርፖርት መቼ ስራ ይጀምራል የሚል ጥያቄ አላቸው።

ከዚህ ቀደም ከተሰጠው ማብራሪያ በኃላ
(https://t.iss.one/tikvahethiopia/82211?single) የጥገናው ስራ ከምን ደረሰ የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያደቻ ፤ የአውሮፕላን ማረፊያውን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ስራውን ማከናወን እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

አቶ ለማ ፤ " እንደሚታወቀው የመንግሥት የግዢ ስርዓት አለ፤ ጨረታ ወጥቶ በስነስርዓት evaluate ተደርጎ ጨረታው መሰጠት ያለበት " ብለዋል።

" እንደኛ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ለህዳር ጽዮን እናደርስ ነበር ፤ መሬት ላይ ያለው የግዢ ስርዓት የጨረታው ስርዓት ለዛ ጊዜ አላደረሰንም " ሲሉ ተናግረዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው መቼ ነው ወደ አገልግሎት የሚመለሰው ? ለሚለው ጥያቄም አቶ ለማ " ኤርፖርቱ በጣም ነው የተጎዳው ፤ ስራው መሰረታዊ ስራ ይፈልጋል ፤ ተጫራች ምርጫ ጨርሰናል የመጨረሻዎቹ negotiation ላይ ነው ያለውነው ከ10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ታውቆ ስራውን ይጀምራል " ብለዋል።

" እነሱንም ግፊት የምናደርግባቸው በሁለት እና በሶስት ወር ውስጥ ሰርተው ሊጨርሱ ይችላሉ ፥ ግን ደግሞ ካንትራክተሩ ሲመጣ የራሱን Schedule / መርሃ ግብር  ይዞ ስለሚመጣ የነሱንም Schedule ማክብረ ይጠበቅብናል " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሆነው ሆኖ ግን በእርግጠኝነት የምናገረው ክረምት ከመግባቱ በፊት የአክሱም ኤርፖርታችን ስራውን ይጀምራል ፣ ቱሪስቶችን እናመጣለን ፣ የአካባቢው ነዋሪም የሚገባውን አገልግሎት እንዲያገኝ እናደርጋለን ፀንተንም እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።

እጅግ ከፍተኛ ምዕመን ይገኝበታል ተብሎ ለሚጠበቀው ለህዳር ጽዮን በዓል አየር መንገዱ አቅራቢው ባለው የሽረ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ በረራዎችን ለማሳደግ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው አቶ ለማ ያደቻ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃለምልልስ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችን ባሉበት ሆነው ኑሮዎን ያቅልሉ፡፡

*9335# ይደውሉ
አግልግሎቱን ለማግኘት አቅራቢያዎ በሚገኙት ቅርንጫፎቻችንን ጎራ ይበሉ!

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ: https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

#globalbankethiopia #mobilebanking #makeitease
አንድ ቀለም ፌስቲቫል !

ህዳር 22 / December 2 በመስቀል አደባባይ በመገኘት ከልጆችዎና ከወዳጆችዎ ጋር የማይረሳ የደስታ ጊዜ ያሳልፉ።

በእለቱ ልጆች ከወላጆቻቸው ጋር የማይረሳ የደስታ ጊዜ ያሳልፋሉ። በውሃ እየተንቦራጨቁ ይፈነጥዛሉ፣ጭቃ ያቦካሉ፣ሸክላ ይሰራሉ፣ ስእል ይስላሉ ሀሳባቸውንም በጭቃ ይገልፃሉ። ከእናቶች ጋር ጥጥ ይፈትላሉ ። ሲለቅሙ : ሲያበጥሩ ሲወቅጡና ሲጋግሩ ይውላሉ ።
በሺ የሚቆጠሩ ህፃናት ልደታቸው ይከበራል፣ አብረው ሲጫወቱ እና ሲደሰቱ ይውላሉ።
የሚበላ  የሚጠጣ ነገር ይዘው አቅራቢዎች ሊያስተናግዶችሁ ተዘጋጅተዋል።

ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ እስከ 11 ድረስ ቀኑን ሙሉ።
ሌሎችም አዳዲስ አስደሳች ሰርፕራይዞች ይኖራሉ።
መግቢያ ዋጋ ለልጆች 200 ብር ለወላጆች በነጻ 😊 ሁለታቹም ኑ !

ትኬቱን በቴሌ ብር ላይ ያገኙታል።
በ 0911447443 እና  0908808182 ይደውሉልን።

#አንድቀለምፌስቲቫል
#onecolorfestival
#ኑ_ጭቃ_እናቡካ
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምላሽ በረራው ለምን ተሰረዘ ? ዛሬ ከሰዓት በኃላ ወደ ደሴ ኮምቦልቻ በረራ ለማድረግ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱ በኃላ " በረራው ተሰርዟል " የተባሉ መንገደኞች ለምን በረራው እንደተሰረዘ በአግባቡ እንዳልተነገራቸውና ይቅርታም ባለመጠየቃቸው ምክንያት እንዳዘኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚመለከተው ክፍል ቅሬታውን አቅርቦ ምላሽ ጠይቋል። አየር መንገዱ…
" ትላንት የተሰረዘው በረራችን ወደ ዛሬ ጥዋት እንደተቀየረ ከተነገረን በኃላ ይሄን በረራ አናቀውም ተብለናል " - መንገደኞች

በትላንትናው ዕለት ወደ ደሴ ኮምቦልቻ በረራ ለማድረግ ሁሉንም ሂደት ጨርሰው ወደ አውሮፕላን ውስጥ ከገቡ በኃላ በረራው የተሰረዘባቸው መንገደኞች " ይቅርታ የጠየቃቸውም ሆነ ለምን ይህ እንደተደረገ ያስረዳቸው አካል እንደሌለና በዚህም እጅግ ማዘናቸውን " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለፃቸው ይታወሳል።

ተጓዦቹ ቀጣይ በየትኛው በረራ እንደሚሄዱም እንዳልተነገራቸው ገልጸውም ነበር።

አየር መንገዱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ማብራሪያ ፤ የምሽቱ በረራ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መግባት ስለማይችል (በተለምዶ "SunSet" በመድረሱ) መሰረዙን መግለፁ አይዘነጋም።

ከዚሁ በረራ ጋር በተያያዘ ትላንት ምሽት ተጓዦች በእጅ ስልካቸው የተሰረዘው በረራ ወደ ዛሬ ጥዋት 1:30 እንደተቀየረ የሚገልጽ የፅሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በደረሳቸው የፅሁፍ መልዕክት አማካኝነት በረራቸውን ለማድረግ በለሊት ወደ ኤርፖርት እንደሄዱ ሁሉን ጨርሰው ወደ አውሮፕላኑ ለመሄድ ሲዘጋጁ በስፍራ የነበረ ሰራተኛ " እኛ ስለዚህ በረራ የምናቀው ነገር የለም " ብሎ መሄድ እንደማይችሉ እንደነገራቸው ገልጸዋል።

ከፍለው በሚስተናገዱበት በራሳቸው ተቋም ይህም መሰል ድርጊት በማጋጠሙ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው የገለፁት መንገደኞች የአየር መንገዱ #የበላይ_አካላት በአፋጣኝ መፍትሄ ይፈልጉን ብለዋል።

" ሲሆን ሲሆን ይቅርታ ተጠይቀን በአግባቡ ተስተናግደን መሄድ ሲገባን እንዲህ ያለውን መልስ ማግኝታችን አሳዝኖናል " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ከተጓዦች መካከል ለአስቸኳይ የስራ ጉዳይ ወደ ደሴ ኮምቦልቻ ትላንት መግባት የነበረባቸው ሰራተኞች፣ ህፃናት፣ ወላዶች ይገኙበታል።

ፎቶ፦ ትላንት የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ

@tikvahethiopia
" እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም ? በረሃብ ማለቅ አለብን ? " - ተፈናቃዮች

ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ በ2015 ዓ/ም በነበረው ማንነት ተኮር ግጭት የተነሳ ቤት እና ንብረታቸውን ጥለው ወደ አማራ ክልል፤ ቻግኒ የመጡ ተፈናቃዮች እርዳታ እየተደረገልን አይደለም፤ በረሃብ ምክንያት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 2 ህፃናት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል።

በቻግኒ የሚገኙት 2000 የሚደርሱ ተፈናቃይ ወገኖች ሲሆኑ በግለሰብ ፍርስራሽ ቤቶች እና ጅምር ፎቆች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።

የተፈናቃዮቹ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሀሰን፦

" ካለፈው ሳምንት ብቻ ሁለት ህፃናት በረሃብ ምክንያት ሞተውብናል።

እኛ እስከ ዞን እስከ ክልል ድረስ ወስደን ደብዳቤ አስገብተናል። ዞኑ እራሱ ፈርሞ የሞቱትን ሰዎች ዝርዝር በዛ ላይ አልተጠቀሱም ግን እንደሞቱ ሪፖርት አድርገናል።

በረሃብ ምክንያት ህፃን 34፣ ትላልቅ ሰዎች 21 በአጠቃላይ 55 ሰዎች እንደሞቱብን ሪፖርት አድርገናል።

እኛ ሰው ጠግቦ ይደር እያልን አይደለም ያለነው ቢያንስ ቀምሶ ይደር ህይወት ይዳን ነው። ምናለ መንግስት እንኳን ባያግዘን ሌላ ድርጅቶች ገባ ብለው ቢያግዙን ይሄ ሁሉ ጉዳት ይሄ ሁሉ ህዝብ እንዴት በረሃብ ይሞትብናል ?

ሰዎች ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሄድ ብለው የቀን ስራ ሰርተው እንዳበላ ያልታደሰ መታወቂያ ይዛችሁ አትሄዱም ተብለን ተዘግቶብናል። ተንቀሳቅሰን የቀን ስራ ካልሰራን እንዴት አድርገን ነው ህይወታችንን ማቆየት የምንችለው ? መንግሥትም እያገዘን አይደለም።

መንግሥት በቅርብ ወደሀገራችሁ ትገባላችሁ የሚል ነገር አንስቷል። ይሄም ቢሆን ደስ ይለናል በተለያዩ ቦታዎችም ምዝገባ አለ የሚባል ነገር አለ እዚህ ዞን ግን እስካሁን የመጣም ሆነ የተጠየቅነው ነገር የለም።

ወይ እርዳታ አልተደረገ፣ ወይ ወደተፈናቀልንበት ቦታ መንግስት ያለውን ነገር አረጋግጦ እየመለሰን አይደለም፣ እንዴት ነው የምንሆነው ኢትዮጵያዊ አይደለንም እኛ በረሃብ ማለቅ አለብን ? "

ከተፈናቃዮች መካከል አንዲት 60 ዓመት እናት፤ " እመጫትም ወልዳ የምትበላው የምትቀምሰው አጥታ ቁጭ ብለናል። እየተሰቃየች ነው ያለችው ተቸግረን ነው ያለነው በጣም በጣም ተሰቃይተናል " ብለዋል።

በምስራቅ ወለጋ ለ52 ዓመታት እንደኖሩ የሚናገሩት የ75 ዓመት እድሜ ያላቸው አዛውንት አቶ ሀሰን መሀመድ ከ8 ልጆቻቸው 5 ወንድ ልጆቻቸው በግጭቱ እንደተገደሉና አሁን ላይ ከቀሪ 3 ሴት ልጆቻቸው ጋር በቻግኒ የግለሰብ ፍርስራሽ ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

የሚላስ የሚቀመስ የለንም የሚሉት አዛውንቱ " በጣም አጣዳፊ የሆነብን የምግብ ጉዳይ ነው፤ ልጆችን እየቀብርን ነው በረሃብ ምክንያት መንግስት ሊሰማን አልቻለም አላወቀንም እንዳንል አንድ ጊዜ እርዳታ መጥቶልናል፤ ስማችንም በኮምፒዩተር ገብቶ ይታወቃል። መጠለያ አልተሰጠንም የትም ተበትነን በየከተማው በየበረዳው ተቀምጠን ነው በደል የደረሰብን ብርዱ ፀሀዩ ረሃቡ እየተፈራረቀብን ነው " ብለዋል።

የቻግኒ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ተወካይ ባለሞያ አቶ የሱፍ ሁሴን ምን አሉ ?

- ባለፈው ዓመት ግንቦት ላይ ነው እርዳታ የመጣው። አንዴ ተሰጣቸው ቆመ እስካሁን የለም።

- በረሃብ ተጎድተው ታመው የተኙ ሰዎች አሉ፣ በቂ ህክምና እንዳያገኙ ብር የላቸውም።

- ሃምሳ አምስት ሰው እንደሞተባቸው ለኛ ሪፖርት ሰጥተውናል። እሱን ደግሞ ለዞን ለክልል በደብዳቤ አሳውቀናል። ኮሚቴም ሄዶ እንዲያነጋግር ተደርጓል።

- ክልሉ 'እርዳታ አለ ግን ለማድረስ የመንገድ የፀጥታ ሁኔታ ችግር በመሆኑ ማድረስ አልችልም' የሚል ነው።

ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/VOA-11-29 #VOA

@tikvahethiopia