" አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው ከሚላሚ ከተማ ወደ ዋዩ ሲጓዝ መንገድ ስቶ በመገልበጡ ነው " - የቦረና ዞን ኮሚኒኬሽን
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልታሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
ከሟቾች በተጨማሪ ፤ በአደጋው ምክንያት በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ14 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ተነግሯል።
አደጋው የደረሰው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሚላሚ ከተማ ወደ ዋዩ ሲጓዝ መንገድ ስቶ በመገልበጡ መሆኑ ተገልጿል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በተልታሌና ወላይታ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መላካቸው ተገልጿል።
መረጃው የዞኑን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ኦቢኤን አፋን ኦሮሞ ነው።
@tikvahethiopia

Enhance the quality of your business communication through the utilization of a virtual PBX, in collaboration with our reliable associate, websprix!
Experience the convenience of cloud-based hosted telephony - make and receive calls from any Internet-connected device today! 📞💻
For more : https://www.ethiotelecom.et/cloud-based-hosted-ip-telephony/
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

" ይቅርታ የጠየቀን የለም ፤ ለምን በረራው እንደተሰረዘ ያሳወቀንም አካል የለም " - መንገደኞች
ዛሬ ከሰዓት ወደ ደሴ - ኮምቦልቻ ሊደረግ የነበረ የአየር በረራ መንገደኞች ወደ አውሮፕላኑ ከገቡ በኃላ እንደተሰረዘ ተሰምቷል።
በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እንደደረሰባቸው መንገደኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ለበረራው መሰረዝ ዝርዝር ምክንያት እንዳልተነገረቸው የገለፁት መንገደኞቹ " ይቅርታም አልተጠየቅንም ይህ የሆነው በዚህ ምክንያት ነውም አልተባልንም ድርጊቱ በእጅጉ አሳዝኖናል " ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎች አየር መንገዱ ምንም የሰጣቸው ምክንያት እንደሌለ ፤ ይቅርታም እንዳልጠየቃቸው ከመግለፅ ባለፈ የተጫነው ሻንጣቸውን እንዳልወሰዱ አመልክተዋል።
" ቀጣይ መቼ እንደምንሄድም የተባልነው ነገር የለም " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ከተጓዦች መካከል ለአስቸኳይ የስራ ጉዳይ ወደ ደሴ ኮምቦልቻ ዛሬ መግባት የነበረባቸው ሰራተኞች፣ ህፃናት፣ ወላዶች ይገኙበታል ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች በደረሰብን ነገር በእጅጉ አዝነናል ብለዋል።
በቀጣይ የሚደረገው በረራ ዛሬ እንግልት የደረሰባቸውን መንገደኞች ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባና መሰል ችግሮች ሲፈጠሩ ደንበኞችን ይቅርታ መጠየቅ መለመድ እንዳለበት ጠቁመዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ አየር መንገዱን ምን እንደተፈጠረ ለመጠየቅ ለሚመለከተው ክፍል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ምላሹ እንደደረሰን እናቀርባለን።
አመሻሹን ወደ አየር መንገዱ የጥሪ ማዕከል የደወሉ ደግሞ በጥሪ አስተናጋጆች ነገ ወደ ደሴ-ኮምቦልቻ በረራ እንዳለ የዛሬው በረራ ስለመሰረዙ ግን ምንም መረጃ እንደሌላቸው እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
የሚመለከተው የአየር መንገዱ ክፍል የሚሰጠንን ምላሽ የምናቀርበው ይሆናል።
ፎቶ ፦ ዛሬ ከሰዓት በአየር መንገዱ የደሴ ኮምቦልቻ የሀገር ውስጥ በረራ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የተላከ

TIKVAH-ETHIOPIA
" ይቅርታ የጠየቀን የለም ፤ ለምን በረራው እንደተሰረዘ ያሳወቀንም አካል የለም " - መንገደኞች ዛሬ ከሰዓት ወደ ደሴ - ኮምቦልቻ ሊደረግ የነበረ የአየር በረራ መንገደኞች ወደ አውሮፕላኑ ከገቡ በኃላ እንደተሰረዘ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆነ መጉላላት እንደደረሰባቸው መንገደኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ለበረራው መሰረዝ ዝርዝር ምክንያት እንዳልተነገረቸው የገለፁት መንገደኞቹ "…
#ምላሽ
በረራው ለምን ተሰረዘ ?
ዛሬ ከሰዓት በኃላ ወደ ደሴ ኮምቦልቻ በረራ ለማድረግ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከደረሱ በኃላ " በረራው ተሰርዟል " የተባሉ መንገደኞች ለምን በረራው እንደተሰረዘ በአግባቡ እንዳልተነገራቸውና ይቅርታም ባለመጠየቃቸው ምክንያት እንዳዘኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚመለከተው ክፍል ቅሬታውን አቅርቦ ምላሽ ጠይቋል።
አየር መንገዱ በሰጠው መረጃ መሰረት ቀን ላይ ወደ ደሴ - ኮምቦልቻ በረራዎች መደረጉን ገልጿል።
የምሽቱ በረራ ግን ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መግባት ስለማይችል (በተለምዶ "SunSet" በመድረሱ) መሰረዙ አመልክቷል።
የኮንቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ በምሽት የሚደረጉ በረራዎችን ማስተናገድ ባለመቻሉ በረራው ከመደረጉ በፊት በረራ ከመጀመሩ በፊት የሚነሳበት ሰዓት፣ የሚደርስበት እና የሚመለስበት ሰዓት ተሰልቶ በረራው መደረግ አለመደረጉ ይወሰናል ብሏል።
ይህ ተሰልቶ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት የማይደርስ ከሆነ በረራው ከወዲሁ የሚሰረዝ እንደሆነ ማብራሪያ የሰጠን አየር መንገዱ ወቅቱም ቀኑ አጭር በመሆኑ ቶሎ በመምሸቱ ይህ ማጋጠሙን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል።

" ስደተኞቹ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት የሌላቸው ሆነው በህጋዊ የመከላከያ ሠራዊት መኪና ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው አዛዛኝ ድርጊት ነው " - የኧሌ ዞን ኮሚኒኬሽን
* መነሻቸው ከኤርትራ አድርገው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው።
* ስደተኞቹ ሲጓጓዙ የነበረው ንብረትነቱ የፌዴራል መንግሥት በሆነው የመከላከያ ኦራል መኪና ነው ፤ የኦራል መኪናው ኮድ መሠ 2-2347 ነው።
በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ኬንያ ሲጓዙ የነበሩ 53 ሕገ-ወጥ ኤርትራውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኧሌ ዞን አስታውቋል።
ሕገ-ወጥ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት እሁድ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም. ምሽት ከኧሌ ወደ ደቡብ ኦሞ ሲያልፉ እንደሆነ የዞኑ ሰላም እና የፀጥታ ጽህፈት ቤት አሳውቋል።
የፅ/ቤት ኃላፊው አቶ አምሳሉ አንጋቶም ምን አሉ (ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት) ?
- በደላሎች አማካኝነት ተሰባስበው ጉዞ የጀመሩት ኤርትራውያኑ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መነሻቸውን ያደረጉ ናቸው።
- ከተጓዦቹ መካከል ሴቶች ያሉበት ሲሆን 6 ሕጻናትም አሉበት። በወራት የሚቆጠር ዕድሜ ያላቸው እና ጡት የሚጠቡ ሕጻናት ጭምር አሉበት።
- ስደተኞቹ የተያዙት በአካባቢው የነበሩ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ መኪናውን ካስቆሙ በኋላ ነው።
- ኤርትራውያኑ የተጫኑት በኢትዯጵያ መከላከያ ሠራዊት " ኦራል "ተሽከርካሪ ኮድ መሠ 2-2347 ነበር።
- እነዚህን ያመጣው ደላላ ነው። ደላላው እስከ መከላከያ ሠራዊት ድረስ ገብቶ ጥርጣሬ እንዳይኖር በዚያ መኪና እንዲጫኑ ተደርጓል።
- የመከላከያ ሠራዊት መኪና በምን አግባብ ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ወደ ሌላ አገር ለማጓጓዝ አገልግሎት ላይ እንደዋለ በትክክል አልታወቀም።
- የመኪናው አሽከርካሪ በምን ምክንያት ስደተኞቹን ሲያጓጉዝ እንደነበረ ለቀረበለት ጥያቄ " አለቃዬ ነው ያዘዘኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።
- ጉዳዩ በአቅራቢያው ለሚገኝ የመከላከያ ሠራዊት ክፍል ከተገለጸ በኋላ ከትናንት ጀምሮ ከሠራዊቱ አመራር ጋር ንግግር ተደርጎ ተሽከርካሪውን እና አሽከርካሪውን ተወስደዋል።
- 53ቱ ኤርትራውያን ስደተኞች እስካሁን ደረስ በዞኑ የኮላንጎ ዙሪያ ወረዳ አዳራሽ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል።
የኧሌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ማግሴ ጉያሎ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አሳውቀዋል።
ስደተኞቹን በአቅራቢያ ወደሚገኝ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለማስገባት ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ስደተኞቹ ምን አሉ ? ከዚህ በፊት ለሥራ ፍለጋ ሱዳን ሄደው እየሰሩ ባሉበት በሀገርቱ ጦርነት ስለነበር በመተማ በኩል አድርገው ወደ አዲስ አበባ እንደመጡና አሁን ደግሞ ወደ ኬንያ እየሄዱ እንዳለ መናገራቸውን ተገልጿል።
ነገር ግን ስደተኞቹ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት የሌላቸው ሆነው በህጋዊ የመከላከያ ሠራዊት መኪና ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው አዛዛኝ ድርጊት መሆኑን የዞኑ መንግሥት አሳውቋል።
ስደተኞቹ በአሁኑ ሰዓት በኧሌ ዞን መንግስት አማካይነት ምግብና ዉሃ እየተሰጣቸው ተጠልለው ይገኛሉ።
መረጃው ከኧሌ ዞን ኮሚኒኬሽንና ከቢቢሲ አማርኛው ክፍል የተገኘ ነው።

#Axum #EthiopianAirlines የአክሱም ኤርፖርትን ለመጠገን የእቃዎች ግዥ መጀመሩ ተነግሯል። ትግራይ ባስተናገደችው አስከፊው ጦርነት ወቅት ክፉኛ የወደመው የአክሱም ኤርፖርት እስካሁን ተጠግኖ ወደስራ አልተመለሰም። የአክሱም ህዝብ ኤርፖርቱ ባለመጠገኑ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየተከሰቱ ነው። በተለይም የተለያዩ አልባሳትን፣ ባህላዊ ጌጦችን እያዘጋጁ የሚሸጡ፣ ከቱሪዝም ገቢ የሚያገኙ ወገኖች ኤርፖርቱ…
#Axum
" እንደኛ ፍላጎትማ #ለህዳር_ጽዮን እንዲደርስ ነበር ... እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ግን የአክሱም ኤርፖርታችን ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን ይጀምራል " - አቶ ለማ ያዴቻ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጦርነት ምክንያት እጅግ ከፍተኛ ውድመት የደረሰበት የአክሱም አውሮፕላን ማረፊያ ክረምት ከመግባቱ በፊት ስራውን እንደሚጀምር አሳውቋል።
በተለይም የአክሱም ነዋሪዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች ፣ በጦርነት የወደመው የአክሱም ኤርፖርት መቼ ስራ ይጀምራል የሚል ጥያቄ አላቸው።
ከዚህ ቀደም ከተሰጠው ማብራሪያ በኃላ
(https://t.iss.one/tikvahethiopia/82211?single) የጥገናው ስራ ከምን ደረሰ የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ ለማ ያደቻ ፤ የአውሮፕላን ማረፊያውን ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ስራውን ማከናወን እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
አቶ ለማ ፤ " እንደሚታወቀው የመንግሥት የግዢ ስርዓት አለ፤ ጨረታ ወጥቶ በስነስርዓት evaluate ተደርጎ ጨረታው መሰጠት ያለበት " ብለዋል።
" እንደኛ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ለህዳር ጽዮን እናደርስ ነበር ፤ መሬት ላይ ያለው የግዢ ስርዓት የጨረታው ስርዓት ለዛ ጊዜ አላደረሰንም " ሲሉ ተናግረዋል።
የአውሮፕላን ማረፊያው መቼ ነው ወደ አገልግሎት የሚመለሰው ? ለሚለው ጥያቄም አቶ ለማ " ኤርፖርቱ በጣም ነው የተጎዳው ፤ ስራው መሰረታዊ ስራ ይፈልጋል ፤ ተጫራች ምርጫ ጨርሰናል የመጨረሻዎቹ negotiation ላይ ነው ያለውነው ከ10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ታውቆ ስራውን ይጀምራል " ብለዋል።
" እነሱንም ግፊት የምናደርግባቸው በሁለት እና በሶስት ወር ውስጥ ሰርተው ሊጨርሱ ይችላሉ ፥ ግን ደግሞ ካንትራክተሩ ሲመጣ የራሱን Schedule / መርሃ ግብር ይዞ ስለሚመጣ የነሱንም Schedule ማክብረ ይጠበቅብናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" የሆነው ሆኖ ግን በእርግጠኝነት የምናገረው ክረምት ከመግባቱ በፊት የአክሱም ኤርፖርታችን ስራውን ይጀምራል ፣ ቱሪስቶችን እናመጣለን ፣ የአካባቢው ነዋሪም የሚገባውን አገልግሎት እንዲያገኝ እናደርጋለን ፀንተንም እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።
እጅግ ከፍተኛ ምዕመን ይገኝበታል ተብሎ ለሚጠበቀው ለህዳር ጽዮን በዓል አየር መንገዱ አቅራቢው ባለው የሽረ አውሮፕላን ማረፊያ የሚደረጉ በረራዎችን ለማሳደግ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው አቶ ለማ ያደቻ ለኤፍ ቢ ሲ ከሰጡት ቃለምልልስ መሆኑን ያሳውቃል።