TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል) በታንዛኒያ የሰላም ድርድር እየተደረገ ነው ሲል መግለጫ አወጣ። ምንም እንኳን ከቀናት በፊት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በወታደራዊ አዛዦች አማካኝነት ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን ቢያሳውቁም እስከዛሬ ደረስ ከሁለቱም በኩል ምንም ነገር ሳይባል ቆይቷል። በዛሬው…
#Update
" ከ #ሸኔ ጋር ሁለተኛው ዙር ውይይት አሁንም ቀጥሏል፤ እየተካሄደ ነው የሚገኘው። ... በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም " - አምባሳደር መለስ ዓለም
መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።
ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትም ፤ በይፋዊ መግለጫ ድርድሩን በተመለከተ ምንም ሳይባል የቆየው ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ድርድሩ ስፍራ እንዲደርሱ በማሰብ መሆኑን አሳውቆ ነበር።
ታጣቂ ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ላለው ግጭት ሰላማዊ የፖለቲካ እልባት ለማግኘት ቁርጠኛ መሆኑንም አሳውቆ የሰላም ድርድሩ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።
እስከ ዛሬ ድረስ በመንግስት በኩል የሚወጡትን የድርድር መረጃዎች በተመለከተ ምንም ሳይባል ቆይቷል።
በዛሬው ዕለት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ " ሸኔ " ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።
" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።
አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ። " ብለዋል።
እንደ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ከሆነ የሰላም ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ሲሆን ኃላ ላይ የመንግሥት የፖለቲካ ሰዎች (የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮ) ወደ ታንዛኒያ አምርተው ድርድሩን ተቀላቅለዋል።
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይቻለውን የምታስችል . . . የዕድሜ ልክ መተማመኛ!!
ማን እንደ እናት!
እናት ባንክ
ማን እንደ እናት!
እናት ባንክ
በዚህ ጊዜ በትንሿ ኪስዎ በሚይዟት የአንድ ብር ሳንቲም ምን ይገዛባታል? እኛጋ ግን ዋጋ አላት!
150 ሜ.ባ የቴሌግራም ጥቅልን ጨምሮ 5 ደቂቃ የአየር ሰዓት 30 ሜባ ኢንተርኔት እና 86 አጭር መልዕክት ይግዙባት!
ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች የትዊተር ገፃችንን https://twitter.com/ethiotelecom ይከተሉ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

#ሶማሌክልል
በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ።
በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል።
የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።
" ምግብም፣ መድኃኒት የሚበቃ የላቸውም ችግሩ ከፍተኛ ነው። የተፈናቀሉት ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ...ትንሽ ከፍ የሚል ቦታ ከውሃ ትንሽ ወጣ ብለው ነው የተቀመጡት። ሰው በእግር ውሃው ውስጥ ሂዶ አህያም ያላቸው ለትራንስፖርት እየተጠቀሙ ከፍ ወዳለ ቦታ እየሄዱ ነው አሁን ከከተማው ብቻ ነው የወጡት እጂ ብዙም ከወንዙ አራቁም " ነው ያሉት።
ሴቶችና ህፃናት በምን ሁኔታ ይገኛሉ ?
አቶ አብዲራዛቅ በሰጡን ማብራሪያ፥ "እደዚህ አይነት ችግር ሲመጣ መጀመሪያ የሚጎዱት ሴቶችና ልጆች ናቸው። እስካሁን የሞቱት ጠቅላላ 28 ሰዎች ሲሆኑ ከ28ቱ ወደ ስምንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው" ብለዋል።
ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ምን ይመስላል ?
ዳይሬክተሩ ይህንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ " ያለነውን ሪሶርስ ተጠቅመን ከመንግሥትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሆነን የምንችለውን ድጋፍ እያረግን ነው። ግን ችግሩ በጣም ትልቅ ስለሆነ ለሁሉም ሰው መድረስ የሚያስችለን ሪሶርስ የለም። ከሁሉም አቅጣጫ የተሰበሰበ ገንዘብም ራሱ እስካሁን ሊበቃ አልቻለም " ብለዋል።
ለተፈናቀሉት ሰዎች ጥሬ ገንዘብ እየሰጠን ነው ያሉት አቶ አብዱራዛቅ፥ እደፍላጎታቸው እዲጠቀሙ 300 ሺሕ ለሚሆኑ አባውራዎች ለእያንዳንዳቸው 7 ሺሕ 700 ብር፣ ለ1 ሺሕ 200 አባውራዎች የእቃ ድጋፍ እንዳደረጉ ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ በጣም የሚያስፈልጋቸው ምግብ እንዲሁም የሚያድሩበት ቤት እንደሆነም ጠቁመዋል።
የጎርፍ አደጋው እየጨመረነው ወይስ እየቀነሰ ?
ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ዳይሬክተሩ፣ "#የመቀነስ ነገር የለም፣ ዝናቡ እየዘነበ ነው በጣም የወንዙ ውሃ ከፍተኛ እየሆነ ነው። አሁን #ስጋቱ እዳለ ነው የሚቀንስም አይመስልም። ዝናቡም የወንዙ ውኃም አንድ ላይ ተጨምሮ ችግር እየሆነ ነው መንገዶች ሁሉም ተዘጋግተዋል" ሲሉ አስረድተዋል።
ድጋፉን ለማድረስ በጣም ፈተና የሆነው ጉዳይ ምንድን ነው ?
" ፈታኝ የሆነው ነገር መቀሳቀስ አልቻልንም።
ሁሉም ቦታ ውሃ ነው። ልጆቹ [ድጋፍ ሰጪዎቹ] በብዛት በጋሪ ነው የሚንቀሳቀሱት። ሕዝቡም እደዛ ነው የሚንቀሳቀሰው። ሰው የሚበላ አዞም ይኖራል፤ይፈራሉ። በመኪና መሄድ አይቻልም። ውኃው በጣም እየጨመረ ነው። በጣም አስቸጋሪ ነው አይደርስም ያልንበት ቦታ ጎርፉ እየደረሰ ነው " ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለውም፥ " ብዙ ሰውም በዚህ ምክንያት እየተፈናቀለ ነው። እደዚህ አይነት ጎርፍ አይተን አናውቅም። ህዝቡ ራሱ እደዚህ አይነት ጎርፍ አላየንም የሚል ነገር ነው ያለው። በሜትሮሎጅ መረጃ መሠረት ጎርፍ እንደሚኖር ለህዝቡ መነገር ነበረበት። በሚያስፈልገው ልክ አልተሰራም መሰለኝ። ለወደፊትም ከተማው በወንዙ በኩል ሳይሆን በሌላኛዉ በከፍታው በኩል ቢያድግ ጥሩ ነው" ሲሉ አቶ አብዲራዛቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
በመጨረሻም፣ መንግሥትና ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም፣ ጉዳቱ በጣም ከባድ ስለሆነ ድጋፍ ተፈናቃዮችን መዳረስ እንዳልቻለ፣ ርብርብ በማድረግ ሕዝቡን መታደግ እንደሚገባም ጥሪ ቀርባል።

#ኑሮውድነት
በኢትዮጵያ ቋሚ ወርሃዊ ደመወዝ ያላቸውና ዝቅተኛ ተከፋይ ነዋሪዎች በየጊዜው የሚጨምረው የዋጋ ንረትን መቋቋም እየከበዳቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ አባባይ ዘመነ በአዲስ አበባ በአንድ የመንግሥት መ/ቤት ተቀጥረው ይሰራሉ።
ከጊዜ ወደጊዜ የኑሮው ጫና እየጨመአ ነው የሚሉት አቶ አባባይ በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ በመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ ቤት ተከራይቶ፣ ምግብ ገዝቶ፣ የትራንስፖርት ከፍሎ ለመኖር ከአቅም በላይ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጫናው ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ እንዳለው ሁሉ እኛም ላይ አለ የሚሉት አቶ አባባይ ፤ መንግሥትም ይህንን ያውቀዋል ብለዋል።
የሁለት ሴት ልጆች እናቷ አብዮት ሃብቴ ደግሞ የ1800 ብር ደመወዝተኛ እንደሆኑ ገልጸው አሁን ባለው ሁኔታ ኑሮውን መቋቋም ፍፁም እንደተሳናቸው ገልጸዋል።
የመንግሥት ምገባ ባይኖር (ቁርስ እና ምሳ) ደግሞ የከፋ ችግር እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ባለኝ ደመወዝ ወር መድረስ አልችልም ያሉት ወ/ሮ አብዮት " አንድ ኪሎ ከጥቁሩ ዝቅ ያለው ጤፍ 120 ብር ነው የምንገዛው በጣም ውድ ነው ፤ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ ያብርድልን እንጂ ኑሮ በጣም ከባድ ነው " ብለዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰውአለ አባተ ስለ ጉዳዩ ምን ይላሉ ?
- የብር የመግዛት አቅም በየጊዜው መዳከም ቋሚ ደመወዝተኞች በኑሮ ውድነቱ እንዲጎዱ አድርጓል።
- ደመወዛቸው ቋሚ ነው፤ ገንዘቡ ደግሞ የመግዛት አቅሙ ከዋጋ ንረት ጋር በተገናኘ እጅግ በጣም አዘቅዝቋል። የዛሬ ዓመት 100 ብር ይገዛ የነበረው የፍጆታ እቃ ዛሬ ምን ያህል ይገዛል ? ተብሎ ሲታሰብ የመግዛት አቅሙ ቀንሷል።
- ገቢያቸው ቋሚ ከሆነና ካልጨመረ የዋጋ ንረቱ በጨመረ ቁጥር የሚጠቀሙት የፍጆት መጠን እየቀነሰ ይመጣል። ቁርስ፣ ምሳና እራት ይበላ የነበረ ሰው ዛሬ ምናልባት ቁርስና እራት ብቻ ሊበላ ይችላል። እንጀራ ይበላ ከነበረ ዳቦ ብቻ ይበላ ይሆናል።
- በአጠቃላይ ቋሚ ደሞዝተኛ የሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች እጅግ እየተጎዱ ናቸው። በቋሚ ገቢ ኑሮን መምራት ከባድ እየሆነ መጥቷል።
- የኑሮ ውድነት ጫናውን ለማቃለል የሚያስችል የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግ ጥሩ ነው።
- መንግሥት 'ደመወዝ የማልጨምረው ዋጋ ንረትን ያባብሳል' በሚል ነው ግን የዋጋ ንረቱ እስካለ ድረስ ቋሚ ገቢ ያለው ሰራተኛ በአግባቡ የዋጋ ንረቱን ሊሸከምለት የሚችል የገንዘብ መጠን በደመወዝ ጭማሪ መልክ ማግኘት አለበት።
- አንዱ ዋጋን የሚያንረው መንግሥት በመንግሥታዊ ሚዲያዎች የሚያደርገው የፕሮፖጋንዳ ስራ ነው፤ 'ደመወዝ ተጨመረ' የሚል ዜና በተደጋጋሚ ሲሰራ ገበያው ይረበሻል። የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ በውስጥ የመንግሥት አሰራር ቢሆንና በሚዲያ ባይጮህ ተፅእኖው ያን ያህል ላይሆን ይችላል።
- በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የነዳጅ እጥረት፣ የአቅርቦት እጥረት የፍላጎት መጨመር የሚያመጣቸው የዋጋ ንረቶች እንደተጠበቁ ሆነው ይሄን ሊያሟላና የማህበረሰቡን ኑሮ ሊደጉም በሚችል መንገድ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግ ጥሩ ነው።
የመንግሥት ሰራተኛው አቶ አባባይ ግን ከደመወዝ ጭማሪው ይልቅ መንግስት ውድነቱን ለመቆጣጠር ቢሰራ መልካም ነው ይላሉ። ዋጋ ሲጨምር ሃይ ባይ ሊኖር ይገባል ብለዋል። ተቆጣጣሪ ከሌለ ደመወዝ ቢጨመር ያለው ዋጋ ከዚህ ሊጨምር ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።
በኑሮ ውድነትና ደመወዝ ጉዳይ የሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ስመኝ ውቤ፤ ጉዳዩ ሁሉንም እንደሚመለከት ገልጸው የተለየ ምላሽ እንደማይሰጡ ተናገረዋል።
ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ስለ ደመወዝ ጭማሪ በተመለከት ወደፊት በሂደት የሚታይ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። #VOAAmH

#SouthEthiopia " በእኛ ደረጃ የደረሰን ኦፊሻል መረጃ የለም። ቅሬታም የለም። ስለዚህ ዞኖቹን አናግራቸዋለሁ " - አቶ ወገኔ ብዙነህ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ውስጥ በመዋቅር ጥያቄ ምክንያት " ወጣቶች በጅምላ ታስረው ይገኛሉ " ሲሉ የታሳሪ ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጭ፤ በቅርቡ ተዋቀረ ወደተባለው ኮሬ ዞን (የቀድሞው…
#Update
" ተበደልኩ የሚል አካል እኛ ጋ መምጣት ይችላል " - አቶ ወገኔ ብዙነህ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ዳኖ ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ' ለምን የመዋቅር ጥያቄ ጠየቃችሁ ' በሚል በፖሊስ እየተደበደቡ እየታሰሩ ስለመሆናቸውን ገልጸዋል።
ሰዎች ሸሽተው ጫካ ገብተዋልና የክልሉ መንግሥት ይድረስልን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ፦
- ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ማታ አንድ ሰው ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ወደ አርባ ምንጭ ሪፈር ተጽፎለታል።
- ኅዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከትምህርት ቤት ሲመለስ የነበረ አንድ ተማሪ ተደብድቧል። በተመሳሳይ በእርሻ ቦታ የነበረ አንድ አርሶ አደር ተደብድቧል።
- በአንድ ቀን ሰባት ከዎች ታስረዋል። ከዞኑ የመጡ ፓሊሶች ናቸው እንዲህ ያደረጉት ብለዋል።
ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መካከል አንድ አባት ልጃቸው ሰሞኑን ያልጥፋቱ እንደታሰረ ገልጸው፣ የተማሩና ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ባለስልጣናት ጭምር ' እናንተ ናችሁ ሕዝቡን የመዋቅር ጥያቄ እንዲያነሳ የምታደርጉት ' ተብለው እየታሰሩ እንደሆነ፣ አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት ድርቅ ጉዳት እንዳደረሰባቸው አሁን እንኳ የእርሻ ወቅት ቢሆንም በጸጥታ ምክንያት ማረስ፣ ማረም እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
ፖሊስ የሚያሳድዳቸው ለምን እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም ከአምስት በላይ ነዎሪዎች ምላሽ የሰጡት፣ " የመዋቅር ጥያቄ ለምን ጠየቃችሁ ? " በሚል ነው። የመዋቅር አደረጃጀት ሲሰሩ ደግሞ ሕዝቡን አላወያዩም፣ አሁንም እንዲያወያዩን እንፈልጋለን ሲሉ ነው።
ነዋሪዎች " እየደረሰብን ነው " ያሉትን ጥቃት በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ጥያቄ አቅርቧል።
የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ኃላፊው ምን አሉ ?
አቶ ወገኔ ፤ ፖሊስ እያደረሰው ነው ስለሚባለው ጥቃት መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል።
" ተበደልኩ የሚል አካል እኛ ጋ መምጣት ይችላል " ብለዋል።
በደብዳቤ ጭምር ጥያቄ እንዳቀረቡላችሁ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ፤ ለዚህስ ጉዳይ ምን አይነት ምላሽ አላችሁ ? ለሚለው ጥያቄ፦ " በፍጹም የደረሰኝ የለም፣ ስልኬን ያውቁታል ቴሌግራም ላይ ጥያቄያቸውን አታች ያድርጉልኝ " ሲሉ ተናግረዋል።
የመዋቅር ጥያቄን በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ ፤ " እኔ ነኝ ዞኑን አደራጅቼ ላውንች አድርጌ የመጣሁት። መንገድ ቆፍረው ወግተው በሌላ መንገድ ነው የወጣሁት። እንደዚህ አይነት ኬዞች እንዳሉ አውቃለሁ " ብለው፣ ፖሊስ አደረሰው ስለሚባለው ጥቃት የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ፣ ሁኔታውን ግን እንደሚከታተሉ አስረድተዋል።
ከሁለት ሳምንት በፊት ወጣቶች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች በገለጹት መሠረት ጠይቀናችሁ ክትትል እናደርጋለን ብላችሁ ነበር ለምን ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ወገኔ፣ " ከዚህ በፊት ከእናተ ባገኘነው ጥቆማ ኮሚዩኒኬት አድርገን ' መንገድ የዘጉ፣ መሳሪያ አውጥተው ለማስፈራራት የሞከሩ የተወሰኑ ሰዎች ላይ ሕግ የማስከበር ሥራ ሰርተናል የሚል ነው እንጂ የአስተዳደር ጥያቄ መጠየቅ በእንደዚህ አይነት መንገድ በፍጹም የወሰድነው እርምጃ የለም ' የሚል ነው ከዞኑ እያገኘሁት ያለሁት ምላሽ " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ የዞን አመራሮችን ለመነጋገር ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካም። አሁንም የዞን አመራሮችን ምላሽ ለማግኘት እንጥራለን።

#MekelleUniversity
የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ29ኛ ዙር ከ2000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂ ተማሪዎች 40 በመቶ ሴቶች ናቸው።
ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ምረቃ ጎን ለጎን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉም አክብረዋል።
በምረቓው ስነ-ሰርአት የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ተወካይ ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር ንግግር አድርገው ነበር።
ባለፉት 3 አመታት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል።
ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በተገኘው አንፃራዊ እርጋታ ዪኒቨስቲው ተስተጓጉሎ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ፈጥኖ መጀመሩን ገልጸዋል።
የ17 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የነገ ተስፋ አንግበው ወደ ስራ በመመለስ ተማሪዎችን ለዛሬ ምረቃ ላበቁ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
ዩኒቨርስቲው የድህረ ጦርነት እቅድ በማዘጋጀት ፤ ከፌደራልና በአገሪቱ ክልሎች እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲ በመነጋገርና በመፃፃፍ ያለፉት 3 የጦርነት አመታት የሚያካክስ ስራ ለመስራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዩቨርሲቲው በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመረዳት የፌደራል መንግስት የመደበለት አነስተኛ በጀትና የሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ በአፋጣኝ በመመለስ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራውና ተልእኮው እንዲመለስ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ሰክሬተሰሪያት ሃላፊና የመቐለ የኒቨርስቲ ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፤ መቐለ ዩንቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተቋቆቁሞና ወደ ስራ ተመልሶ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ድንቅ የምረቃ ስነ-ሰርአት ማዘጋጀቱ ነገ ለመድረስ ያቀደውን እንደሚያሳካ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።
ይህንን የሆነው ለሰላም በተከፈለው እጅግ ወድ ዋጋ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሆኑ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል የተጀመረው ሰላም ስር እንዲሰድ በተሰማሩበት ሁሉ ሰላምና ልማት መስበክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዩኒቨርስቲው በ29 አመታት ጉዞው የዛሬ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#ATTENTION🔊
በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ በመሙላቱ / ከመደበኛ ፍሰቱ ወጥቶ ሞልቶ በመፍሰሱ ዜጎቻችን እየተጎዱ ነው።
እንደ ዳሰነች ወረዳ አስተዳደር መረጃ ፦
- በ34 ቀበሌያትና በ7 ደሴቶች የሚኖሩ 79,828 ቤተሰብ አባላት በወንዙ ሙላት የተጎዱ ተጎድተዋል።
- በወረዳው ካሉ 40 ቀበሌያቶች 34ቱ ቀበሌያት በውሃ የመዋጥና የመከበብ አደጋ ያጋጠማቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ 27ቱ ቀበሌያት ሙሉ በሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል ፤ 7ቱ ቀበሌያት ደግሞ በቀጣይ ስጋት ውስጥ ናቸው።
- በኦሞ ወንዝ ሙላት ሳቢያ 1,435.75 ሄ/ር በመስኖ የተዘራ ሰብልና 123,000 ሄ/ር የእንስሳት የግጦሽ መሬት ሙሉ በሙሉ በውሃ ተሸፍኗል።
- በደሴቶች ውስጥ የነበሩና በውሃ ሙላት የተከበቡ እንስሳት ብዛት 2,993,135 ሲሆን ከዚህ ውስጥ አስካሁን ከውኃ ሙላት የወጡ 889,454 እንስሶች ናቸው።
- በውሃ መጥለቅለቁ 8 የሰው ጤና ኬላዎች፣ 1 ጤና ጣቢያ፣ 6 ትምህርት ቤቶች፣ 6 የእንስሳት ጤና ኬላ፣ 5 የአርብቶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያ ፣ 4 የመኖ ቤል እስቶር እና በ14 ቀበሌያት በስራ እድል ፈጠራ በማህበራት ተደራጅተው ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት ተበድረው ወደ ስራ የገቡ እና በፕሮጀክት የታቀፉ 32 ማህበራትና 15 ሼዶች ሙሉ ለሙሉ በውሃ ሙላት ተውጠዋል፤ ስራም አቁመዋል።
በአደጋው ለተጎዱ ወገኖች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመተባበርና በመቀናጀት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።