TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MinistryofLaborandSkills

ወደ ቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ በትላንትናው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

አጠቃላይ የመግቢያ ነጥቡ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ተጨማሪ መረጃ ፦

(ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል)

- ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እዲሆን ተደርጓል።

- አዲሱ ፖሊሲ ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ዲግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ ትይዩ እንዲሆን አድርጓል።

- በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን ይችላሉ።

- ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ይስተናገዳሉ።

- በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል።

- በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሃይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው ይሰለጥናሉ።

- በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ደረጃ አንድ እና ሁለት 110 ሺህ 15 ፣ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412 ሺህ 557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110 ሺህ 15 ፣ በደረጃ ስድስት 2 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀበል ዝግጅት ተደርጓል።

- የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል።

- ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ይስተናገዳሉ።

መረጃው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
#ላሊበላ

" ' ቫይብሬሽን ትንሽ ነበረ የሚባለው ' ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉ ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው... ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለም ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷ አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት " - አቶ አበባው አያሌው

(በኢዮብ ትኩዬ)

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ስለላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ጉዳት ደርሷል ስለሚባለው ጉዳይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ቀርቦላቸው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአማራ ፤ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያንና ቅርስ ዙሪያ በፋኖ ታጣቂዎችና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ሰሞኑን ተደረገ በተባለ የተኩስ ልውውጥ በቅርሱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ፣ ከባድ መሳሪያ እየተተኮሰ በመሆኑ ከፍተኛ ንዝረት እንዳለ በዚህም ቅርሱ አደጋ እንተጋረጠበት የተለያዩ መረጃዎች በማኅበራዊ ሚዲያው ሲንሸራሸሩ ተስተውለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ " ቅዱስ ቅርሱ " አደጋ ላይ እንደሆነ ገልጸው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፦
* በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ?
* ስለ ጉዳዩ የሚወጡት መረጃዎች ምን ያህል እውነተኛነት አላቸው ?
* አዲስ ስንጥቅ አለ ? የሚሉትን ጥያቄዎችና አጠቃላይ ስለጉዳዩ ያለው ማብራሪያ ምን እንደሆነ ለቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርቧል።

በቅርሱ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይስ የለም ? ተብሎ በመጀመሪያ ጥያቄ የቀረበላቸው የቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው ኮሚቴ ተልኮ ተረጋግጧል ያሉትን ሁኔታ ከማብራራት ጀምረው እንደሚከተለው ገልጸዋል።

" ላሊበላ አካባቢ ግጭት ነበረ። ከዚያ በመነሳት ነው ' በጥይት ተመቷል ' ይሉ የነበረው " ሲሉ ያስረዱት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኅዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም 7 ሰዎች ያሉበት (ከደብሩ ካህናት 3 ሰዎች፣ ከላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት 3 ሰዎች፣ በቦታው ከሚገኝ የቅርስ ባለሥልጣን 1 ሰው) ኮሚቴ ተዋቅሮ ከ3፡00 እስከ 6፡40 ገደማ ዞረው ቅርሱን አይተዋል ብለዋል።

በዚህም የሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ኮሚቴ ፦
- ቤተ አማኑኤልን፣
- ቤተ ሊባኖስ፣
- ቤተ ገብርኤል ያሉባቹውን ቦታዎች ተመክተዋል ነው ያሉት።

አቶ አበባው አክለውም ፤ " ' በቤተ ገብርኤል አናቱ ላይ ጥይት አርፏል' የሚል ነው ወሬው እዛ ሲወራ የነበረው " ብለው፣ "ቤተ ገብርኤል ተወጥቶ ታይቷል። ጥይት ያረፈበት ምንም ነገር የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

2ኛው ደግሞ ' ቤተ ሊባኖስ አካባቢ ጥይት ተተኮሰ ' የሚል ነገር እንደነበር ገልጸው፣ " እዛም ላይ ምንም ምልክት የለም። እንዳውም ጥገና እየሰራንበት ነው። 'ቤተ አማኑኤል ላይ ደግሞ የመጠለያውን ብረቱን ጥይት መትቶታል' የሚል ነው፣ ምንም የተመታ የለም። በቦታው የነበሩ ጥበቃዎች አሉ ፣ የተመታ ነገር የለም፣ ግን ሲተኮስ #ቫይብሬሽን ስለነበረው ቃቃ ይል ነበር መጠለያው ከዚያ ውጭ ምንም ነገር የለም " ሲሉ ከኮሚቴዎቹ ያገኙትን ምላሽ አስረድተዋል።

ከሰሜን ምሥራቅ ግሩፕ ቀጥሎ የደቡብ ምዕራብ ግሩፕ ደግሞ ፦
- ቤተ መድኃኒዓለም፣
- ቤተ ማርያም፣
- ቤተ ጎለጎልታ ያሉበትን ቦታ እንደተመለከተ፣ እዚያ ሲባል የነበረው ደግሞ 'የቤተ መድኃኒዓለምን መጠለያ ብረቱን መትቶታል' የሚል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ " ጥይት ሲያርፍ ምልክት ይኖረዋል። ግን ዙረው አይተዋል። ምንም ነገር የለም " ብለዋል።

አንድ ያሳዩአቸው የመጠለያው አናት ሸራ ከጎኑ ቀዳዳ አለ ' ተመትቶ ነው ' የሚል ነው፣ ያቺ ደግሞ ሸራ ቀዶ መግባትም ብዙም ትልቅ ችግር እንደማይኖረው የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ጎለጎልታ፣ ቤተ ደናግል እንዲሁም ቤተ ጊዮርጊስ ምንም የተኩስ ምልክት እንደሌለ ተናግረዋል።

አክለውም ፣ ' ትንሽ #ቫይብሬሽን ነበረ ' የሚባለው ሲተኮስ ይሄ እውነታ ነው እዚያ ያሉት ኮሚቴዎችም ያረጋገጡት ነው" ብለው፣ የአካባቢው ማኅበሰሰብ የደብሩ ካህናት ሆነው አጠቃለሁ የሚለውን ኃይል በግዝትም ቢሆን ወደ ቅርሱ እንዳይጠጋ ማድረግ፣ በመንግሥት በኩል ቅርስ ጥበቃም፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ምንም አይነት ታጣቂ ቡድን በአካባቢው እንዳይኖር ለማድረግ መስራት፣ ከዚያ ውጭ ደግሞ ቤተ ክህነትም ሆነ የመንግሥት አካላት መግለጫ ሲያወጡ ጠይቀው እንዲያወጡ የሚደረግበት ሁኔታ እንዲፈጠር ከኮሚትዎቹ ጋር መወያየታቸውን አስረድተዋል።

ኮሚቴው ቦታው ላይ ተገኝቶ ሳይመለከት የቆየበት ምክንያትን ሲያስረዱም አቶ አበባው ፤ " #ሀዘን ሆኖ ነው አካባቢው ያዘገየነው። ብዙ ሰው አልቋል። በቦታው ድንኳን አለ፣ እንዲያው በትኩሱ ተነሱና እዩ ከምንላቸው ብለን ነው " ብለዋል።

አክለው " ቅርስ ፖለቲካ አይሆንም፣ ያኔ የነበሩ ሰዎች ቅርሱን ለእኛ አውርሰውናል ሲሆን እንጠብቀዋለን እንጂ በእኛ የፖለቲካ ንትርክ ውስጥ ቅርስን አናስገባም፣ ከፖለቲካም ከምንም በላይ ነው፣ መተኪያ የለውም፣ ይህን ማንም ማሰብ አለበት" ነው ያሉት።

" ከዚያ ውጭ ቀጣይ የምንሰራው ንዝረቱ ካለ ምን አስከትሏል የሚለውን ነው። እያንዳንዷን ስንጥቅ እናውቅምታለን። አዲስ ስንጥቅ ካለ እናሳውቃለን " ሲሉ ገልጸዋል።

ባደረጋችሁት ዳሰሳ አሁን አዲስ ስንጥቅ የለም? የሚል ጥያቄ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ዋና ዳይሬክተሩ በሰጡት ምላሽ፣ "የላሊበላን ያሉትን ስንጥቆች ካህናቱም ያውቋቸዋል። እዚያ ያለው ጽሕፈት ቤት ኃላፊም ያውቀዋል። የእኛም ባለሙያ ያውቀዋል። አዲስ ስንጥቅ የለም ኢን ኬዝ ግን ቫይብሬሽኑ ስንጥቅ አስፍቶ ይሆን እንዴ? የሚለውን ለማረጋገጥ 3ዲ ስካን እናወጣለን። አሁን ያለውን እናያለን፣ እናነጻጽራለን እንጅ ላሊበላ ስንጥቅ በስንጥቅ ነው 22 ቦታዎች ተሰንጥቀው እየተጠገኑ ነው" ብለዋል።

አቶ አበባው በሰጡት አክለው ማብራሪያ፣ "ተመታ የሚባለው ቤተ ሙዚየሙ መግቢያ መድኃኒዓለምን ግን ጥይት መትቶታል። ጥይቷም አጥሯ ላይ እንደተሰካች ናት፣ እሷን ነው እያነሱ ሲበትኑ የነበረው ያ ደግሞ አጥሯ ላይ ግንብ ነው በ2012 ዓ.ም የተሰራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሁለተኛ ጥይት ያለችው ቤተ ደናግል ማርያም ጋ ኢህአዴግ ሰቆጣ ሲገባ የደርግ ወታደሮች እዛ ገብተው ነበር ይተኩሱ ነበር እሷም አለች" ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ስለጉዳዩ ምን ማብራሪያ እንዳላቸው የተደረግልው ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ ጉዳዩን በተመለከተ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ቅዱስ ቅርሱ አደጋ ላይ እንደሆነና ልንታደገው እንደሚገባ ገልጸው ነበር።

የብፁዕነታቸው መግለጫ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አበባው፣ "አቡነ ኤርሚያስ ትልቅ ሰው ናቸው ግን ሰው ሊያሳስታቸው ይችላል። ሁሉም ልጆቻቸው ናቸው ፤ እዚያ ያሉት በኮሚቴው የተገመገመው ትክክል አልነበረም የሚል ነው ፤ እርሳቸውም ትንሽ ቹኩለዋል " ብለዋል።

አክለውም ፣ " በመንግሥት በኩልም ግጭት የለም በቦታው ላይ ማለት ትክክል አልነበረም ግጭት ነበረ በእርግጥ " ያሉት አቶ አበባው ፣ " እርሳቸው በተፈጥሯቸው የእውነት ሰው ናቸው ከመቆርቆር የተነሳ ሊሆን ይችላል። መቆርቆሩንም እንወደዋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በመቐለ ከተማ በአድማ ምክንያት ለአንድ ቀን ተቋርጦ የነበረው የታክሲ አገልግሎት ዛሬ በከፊል ሲሰጥ ውሏል። የታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች ለአንድ ቀን የጠሩት ስራ የማቆም አድማ " ሰርአት አልበኝነት ነው " ያሉት ተጠቃሚዎች ፤ " መንግስት አፋጣኝና ወቅቱ የሚዋጅ እርምጃ መውሰድ ይገባዋል " ብለው ነበር።  ለምለም ኪሓ ፣ ሓወልትና ህዳሴ የተባሉ ሦስት የታክሲ ማህበራት ህዳር 3/2016…
#Update

ከአንድ ቀን አድማ በኋላ በከፊል ጀምሮ የነበረው የመቐለ የታክሲ አገልግሎት መልሶ ተቋርጠዋል።

የታክሲ አገልግሎቱ ህዳር 3 ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የተናገሩት ተገልጋዮች ህዳር 4/2016 ዓ.ም ከሰአት በኃላ በከፊል የጀመረ ቢሆንም ፤ ከህዳር 5 ጀምሮ መልሶ በመቋረጡ ለከፍተኛ እንግልት መዳረጋቸው ይገልፃሉ።

ስለ አገልግሎቱ መቋረጥ የታክሲ ማህበራት አቤቱታ ሲያቀርቡ ፤መንግስት ደግሞ ለሚድያ መግለጫ ሰጥቷል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አቤቱታውና መግለጫው ተመልክቶታል።

ህዳር 05/2016 አምስት የመቐለ የታክሲ ማህበራት በጋራ ለመንግስት ያቀረቡት የፅሁፍ አቤቱታ እንደሚያመለክተው። "ስራ የማቆም አድማው ከእወቅናችን ውጭ የተደረገ ኢ-ህጋዊ ተግባር ቢሆንም ያለውን የኑሮና የመለዋወጫ እቃ ውድነትና ግምት ውስጥ  ያስገባ የታሪፍ ማስተካከያ ተደርጎ አገልግሎቱ እንዲቀጥል እንጠይቃለን "  ይላል።

የክልሉ መንግስት በትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ በኩል ለሚድያ በሰጠው መግለጫ ፤ " በተቀመጠው የታሪፍ መመሪያ መሰረት ትርፍ መጫንና ያልተፈቀደ ታሪፍ ማስከፈል ህጋዊ አይደለም ፍፁም የተከለከለ ነው ፤ ስለዚህ ይህንን በመቀበል አገልግሎቱ መቀጠል ይገባል " ብሏል።

ቢሮው አያይዞ በአገልግሎት የማቆም አድማው የተሳተፈ የታክሲ ባለቤትና አሽከርካሪ እያንዳንዱ ብር 1200 እየተቀጣ እንዲመለስ ያሳሰበ ሲሆን የተቀመጠው ቅጣት የማይተገብሩ ታክሲዎች የሰሌዳ ቁጥራቸው እየተፈታ አገልግሎት ከመስጠት እየተከለከሉ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል አረጋግጠዋል።

የትግራይ የትራንስፓርትና መገናኛ ቢሮ ህዳር 3/2016 ዓ.ም ለሚድያ በሰጠው መግለጫ ፤ የታክሲ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አገልግሎት የማቋረጥና አድማ የመምታት ደርጊቱ ችላ ተብሎ የማይታለፍ ህጋዊ እርምጃና ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን በመገንዘብ ስራቸው ይቀጥሉ ዘንድ መምከሩ ፤ የመንግስት ምክርና ማሳሰብያ ችላ ብሎ በአድማ የሚቀጥል ባለንብረትና አሽከርካሪ ግን ጥብቅ እርምጃ ይወሰድበታል ሲል ማስጠንቀቁን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መዘገቡ ይታወሳል
 
@tikvahethiopia
በሲቢኢ ብር ወደ ሁሉም ባንክ
ገንዘብ መላክ እና መቀበል ተጀመረ!
******************
ወደ *847# በመደወል ወይም የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎን በማዘመን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ!

ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለ#መክሰስTime - ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️

When the snack is too good to share 😋 Let us indulge in #SnackTime with #SUNChips and share #SunnyMoments.☀️

Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia
" 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫነት ይደግፋሉ " - የአፍሮባሮሜትር ጥናት

(በኢዮብ ትኩዬ)

66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንደሚሹ መመላከቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ #አፍሮባሮሜትር ይፋ ካደረገው ጥናት ተረድቷል።

የዳሰሳ ጥናቱ ከላይ ከተጠቀሰው የገደብ ፍላጎት በተጨማሪ 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ መንግሥቱን መሻሻል እንደሚፈልጉ፣ ነገር ግን የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና በባንዲራው ያለውን አርማ በተመለከተ የሕዝቡ አስተያየት እንደተከፋፈለ ያስረዳል።

በጥናቱ ቁልፍ ግኝቶች መሠረት፦

- 67 በመቶ ኢትዮጵያውያን የሕገ መንግሥቱን መሻሻል የሚደግፉ፣ 16 በመቶዎቹ  ሕገ መንግሥቱ  ሙሉ ለሙሉ እንዲወገድ፣ እንዲሁም ቀሪዎቹ 16 በመቶዎቹ ደግሞ አሁን ባለበት እንዲቀጥል የሚፈልጉ ናቸው።

- በ2012 ዓ.ም ከተካሄደው የአፍሮባሮሜትር ዳሰሳ ጥናት አንጻር፣ በዚህ ጥናት ሕገ መንግሥቱ እንዲቀየር የደገፉ በአምስት በመቶ ብልጫ አላቸው። 

ይህንኑን ብልጫ በተመለከተ የተቀመጠውና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የጥናቱ ግራፋዊ መግለጫ፣ በ2020 69 በመቶቹ፣ በ2023 67 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ሕገ መንግሥቱ መሻሻል እንዳለበት፣ በ2020 18 በመቶ፣ በ2023 16 በመቶዎቹ ዜጎች ሕገ መንግሥቱ ባለበት እንዲቀጥል እንዲሁም በ2020 11 በመቶ፣ በ2030 16 በመቶዎቹ ዜጎች ደግሞ ሕገ መንግሥቱ በአዲስ ይቀየር ብለው እንደሚስማሙ ያስረዳል።

- የተጠቆሙ የሕገ መንንግሥት ማሻሻያዎችን በተመለከተ፣ 67 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች የሥራ ቋንቋዎችን ለፌደራል መንግሥት እንዲደረግ፣ 66 በመቶዎቹ የጠቅላላ ሚኒስትር የሥልጣን ዘመን እንዲገደብ እንዲሁም በ2012 ዓ.ም 35 በመቶ፣ በአሁኑ ጥናት ደግሞ 53 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል ለማድረግ በአብላጫ ይደግፋሉ።

በዚህም 67 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ቋንቋዎች ለሕገ መንግሥቱ እንደሚያስፈልግ፣ 30 በመቶ የሚሆኑት አያስፈልግም ብለው እንደሚቃወሙ እንዲሁም 4 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከመቃወሙም ከመደገፉም እንዳልሆኑ የጥናቱ ገላጭ ግራፍ ያስገነዝባል።

ገላጭ ግራፉ አክሎም፣ 66 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች የጠቅላይ ሚኒስትር የሥልጣን ገደብ እንዲደረግ፣ 27 በመቶዎቹ ደግሞ መገደቡን እንደሚቃወሙ እንዲሁም 7 በመቶ የሚሆኑት ከመደገፉም ከመቃወሙም እንዳልሆኑ ያሳያል።

በተጨማሪም 54 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች አዲስ አበባን የፌደሬሽኑ አባል ማድረግን እንደደሚደግፉ፣ 34 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ፣ 12 በመቶዎቹ ደግሞ ከመቃወሙም ከመደገፉም እንዳልሆኑ በግራፍ ተቀምጧል።

እንዲሁም፣ 46 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን አንቀጽ 39ኝን ለማስወገድ እንደሚደግፉ፣ 47 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ፣ 7 በመቶዎቹ ደግሞ ከመቃወሙም ሆነ ከመደገፉ ጎራ እንዳልሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም፣ 29 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች በባንዲራ መሀል ላይ ያለውን ብሔራዊ አርማ ማስወገድን እንደሚደግፉ፣ 62 በመቶዎቹ እንደሚቃወሙ እንዲሁም 9 በመቶዎቹ ደግሞ ከመደገፉም ከመቃወሙም ጎራ እንዳልሆኑ የጥናቱ ግራፍ ያስረዳል።

ጥናቱ የተካሄደው በ2,400 ቃለ መጠይቆች፣ ዕድሚያቸው 18 ከዚያ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን በማሳትፍ እንደሆነ፣ ከግንቦት 17 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መረጃው እንደተሰባሰበ፣ የናሙናው መጠን በአገር አቀፍ ደረጃ የተሰራና የስህተት ኅዳጉ +/-2 በመቶ፣ የአስተማማኝነት ደረጃው 95 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ሸኔ እያለ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል) በታንዛኒያ የሰላም ድርድር እየተደረገ ነው ሲል መግለጫ አወጣ። ምንም እንኳን ከቀናት በፊት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በወታደራዊ አዛዦች አማካኝነት ለሰላም ድርድር መቀመጣቸውን ቢያሳውቁም እስከዛሬ ደረስ ከሁለቱም በኩል ምንም ነገር ሳይባል ቆይቷል። በዛሬው…
#Update

" ከ #ሸኔ ጋር ሁለተኛው ዙር ውይይት አሁንም ቀጥሏል፤ እየተካሄደ ነው የሚገኘው። ... በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም " - አምባሳደር መለስ ዓለም

መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ጋር ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የሰላም ድርድሩ እየተካሄደ መሆኑን ማረጋገጫ የሰጠው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በሰጠው መግለጫ ነው።

ባለፉት ቀናት የዲፕሎማቲክ ምንጮች በታንዛኒያ ዳሬሰላም የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድር ላይ እንደተቀመጡ ፣ በዚሁ የሰላም ድርድር ላይ የታጣቂው ቡድን አመራሮች ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ወደ ዳሬሰላም እንዲሄዱ ተደርገው ድርድሩን እየተካፈሉ እንደሆነ መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትም ፤ በይፋዊ መግለጫ ድርድሩን በተመለከተ ምንም ሳይባል የቆየው ጃል መሮ ድሪባ እና ጃል ገመቹ አቦዬ ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ድርድሩ ስፍራ እንዲደርሱ በማሰብ መሆኑን አሳውቆ ነበር።

ታጣቂ ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል ላለው ግጭት  ሰላማዊ የፖለቲካ እልባት ለማግኘት ቁርጠኛ መሆኑንም አሳውቆ የሰላም ድርድሩ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚሰጥ ይፋ አድርጓል።

እስከ ዛሬ ድረስ በመንግስት በኩል የሚወጡትን የድርድር መረጃዎች በተመለከተ ምንም ሳይባል ቆይቷል።

በዛሬው ዕለት ግን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምንም እንኴን የተብራራ ነገር ባይገልጹም በታንዛኒያ ሁለተኛው ዙር ድርድር ከ " ሸኔ " ጋር እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የመጀመሪያው ዙር ከሸኔ ጋር የተደረገ ውይይት ነበር ሁለተኛ ዙር አሁንም ቀጥሏል። እየተካሄደ ነው የሚገኘው " ብለዋል።

" በእኛ በኩል ድርድሩ በመገናኛ ብዙሃን በኩል እንዲደረግ/እንዲሆን ፍቃደኛ አይደለንም። ስለዚህ ጊዜው ሲደርስና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ይፋ የሚሆን ይሆናል " ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ " የዲፕሎማሲ አንደኛው ባህሪ በግልፅም በይፋም የሚደረጉ ነገሮች እንዳሉ ሆነው ሌሎች ነገሮች ግን ጊዜያቸውን የሚጠብቁ እንደሆኑ መረዳት ያስፈልጋል። ግን እየተከናወነ እንደሆነ እገልፃለሁ። " ብለዋል።

እንደ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ከሆነ የሰላም ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ሲሆን ኃላ ላይ የመንግሥት የፖለቲካ ሰዎች (የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የፍትህ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮ) ወደ ታንዛኒያ አምርተው ድርድሩን ተቀላቅለዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማይቻለውን የምታስችል . . .  የዕድሜ ልክ መተማመኛ!!
ማን እንደ እናት!
እናት ባንክ
በዚህ ጊዜ በትንሿ ኪስዎ በሚይዟት የአንድ ብር ሳንቲም ምን ይገዛባታል? እኛጋ ግን ዋጋ አላት!

150 ሜ.ባ የቴሌግራም ጥቅልን ጨምሮ 5 ደቂቃ የአየር ሰዓት 30 ሜባ ኢንተርኔት እና 86 አጭር መልዕክት ይግዙባት!

ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎች የትዊተር ገፃችንን https://twitter.com/ethiotelecom ይከተሉ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
ሰላም ይስበኩ፤ ይሸለሙ!

https://www.cardeth.org/am/peace-messaging
#ሶማሌክልል

በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ።

በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል።

የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ አሕመድ በጎርፉ የተጎዱት ከ600,000 በላይ ሰዎች እንደሚሆኑና ከ300 ሺሕ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንና የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸዋል።

" ምግብም፣ መድኃኒት የሚበቃ የላቸውም ችግሩ ከፍተኛ ነው። የተፈናቀሉት ሰዎች እርዳታ ይፈልጋሉ። ...ትንሽ ከፍ የሚል ቦታ  ከውሃ ትንሽ ወጣ ብለው ነው የተቀመጡት። ሰው በእግር ውሃው ውስጥ ሂዶ አህያም ያላቸው ለትራንስፖርት እየተጠቀሙ ከፍ ወዳለ ቦታ እየሄዱ ነው አሁን ከከተማው ብቻ ነው የወጡት እጂ ብዙም ከወንዙ አራቁም " ነው ያሉት።

ሴቶችና ህፃናት በምን ሁኔታ ይገኛሉ ?

አቶ አብዲራዛቅ በሰጡን ማብራሪያ፥ "እደዚህ አይነት ችግር ሲመጣ መጀመሪያ የሚጎዱት ሴቶችና ልጆች ናቸው። እስካሁን የሞቱት ጠቅላላ 28 ሰዎች ሲሆኑ ከ28ቱ ወደ ስምንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው" ብለዋል።

ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍ ምን ይመስላል ?

ዳይሬክተሩ ይህንን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፥ " ያለነውን ሪሶርስ ተጠቅመን ከመንግሥትና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ሆነን የምንችለውን ድጋፍ እያረግን ነው። ግን ችግሩ በጣም ትልቅ ስለሆነ ለሁሉም ሰው መድረስ የሚያስችለን ሪሶርስ የለም። ከሁሉም አቅጣጫ የተሰበሰበ ገንዘብም ራሱ እስካሁን ሊበቃ አልቻለም " ብለዋል።

ለተፈናቀሉት ሰዎች ጥሬ ገንዘብ እየሰጠን ነው ያሉት አቶ አብዱራዛቅ፥ እደፍላጎታቸው እዲጠቀሙ 300 ሺሕ ለሚሆኑ አባውራዎች ለእያንዳንዳቸው 7 ሺሕ 700 ብር፣ ለ1 ሺሕ 200 አባውራዎች የእቃ ድጋፍ እንዳደረጉ ጠቅሰዋል።

አሁን ላይ በጣም የሚያስፈልጋቸው ምግብ እንዲሁም የሚያድሩበት ቤት እንደሆነም ጠቁመዋል።

የጎርፍ አደጋው እየጨመረነው ወይስ እየቀነሰ ?

ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ዳይሬክተሩ፣ "#የመቀነስ ነገር የለም፣ ዝናቡ እየዘነበ ነው በጣም የወንዙ ውሃ ከፍተኛ እየሆነ ነው። አሁን #ስጋቱ እዳለ ነው የሚቀንስም አይመስልም። ዝናቡም የወንዙ ውኃም አንድ ላይ ተጨምሮ ችግር እየሆነ ነው መንገዶች ሁሉም ተዘጋግተዋል" ሲሉ አስረድተዋል።

ድጋፉን ለማድረስ በጣም ፈተና የሆነው ጉዳይ ምንድን ነው ?

" ፈታኝ የሆነው ነገር መቀሳቀስ አልቻልንም።
ሁሉም ቦታ ውሃ ነው። ልጆቹ [ድጋፍ ሰጪዎቹ] በብዛት በጋሪ ነው የሚንቀሳቀሱት። ሕዝቡም እደዛ ነው የሚንቀሳቀሰው። ሰው የሚበላ አዞም ይኖራል፤ይፈራሉ። በመኪና መሄድ አይቻልም። ውኃው በጣም እየጨመረ ነው። በጣም አስቸጋሪ ነው አይደርስም ያልንበት ቦታ ጎርፉ እየደረሰ ነው " ሲሉ ለጥያቄው ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፥ " ብዙ ሰውም በዚህ ምክንያት እየተፈናቀለ ነው። እደዚህ አይነት ጎርፍ አይተን አናውቅም። ህዝቡ ራሱ እደዚህ አይነት ጎርፍ አላየንም የሚል ነገር ነው ያለው። በሜትሮሎጅ መረጃ መሠረት ጎርፍ እንደሚኖር ለህዝቡ መነገር ነበረበት። በሚያስፈልገው ልክ አልተሰራም መሰለኝ። ለወደፊትም ከተማው በወንዙ በኩል ሳይሆን በሌላኛዉ በከፍታው በኩል ቢያድግ ጥሩ ነው" ሲሉ አቶ አብዲራዛቅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በመጨረሻም፣ መንግሥትና ከሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ እየተደረገ ቢሆንም፣ ጉዳቱ በጣም ከባድ ስለሆነ ድጋፍ ተፈናቃዮችን መዳረስ እንዳልቻለ፣ ርብርብ በማድረግ ሕዝቡን መታደግ እንደሚገባም ጥሪ ቀርባል።

@tikvahethiopia
#ኑሮውድነት

በኢትዮጵያ ቋሚ ወርሃዊ ደመወዝ ያላቸውና ዝቅተኛ ተከፋይ ነዋሪዎች በየጊዜው የሚጨምረው የዋጋ ንረትን መቋቋም እየከበዳቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

አቶ አባባይ ዘመነ በአዲስ አበባ በአንድ የመንግሥት መ/ቤት ተቀጥረው ይሰራሉ።

ከጊዜ ወደጊዜ የኑሮው ጫና እየጨመአ ነው የሚሉት አቶ አባባይ በተለይ አዲስ አበባ ውስጥ በመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ ቤት ተከራይቶ፣ ምግብ ገዝቶ፣ የትራንስፖርት ከፍሎ ለመኖር ከአቅም በላይ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጫናው ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ እንዳለው ሁሉ እኛም ላይ አለ የሚሉት አቶ አባባይ ፤ መንግሥትም ይህንን ያውቀዋል ብለዋል።

የሁለት ሴት ልጆች እናቷ አብዮት ሃብቴ ደግሞ የ1800 ብር ደመወዝተኛ እንደሆኑ ገልጸው አሁን ባለው ሁኔታ ኑሮውን መቋቋም ፍፁም እንደተሳናቸው ገልጸዋል።

የመንግሥት ምገባ ባይኖር (ቁርስ እና ምሳ) ደግሞ የከፋ ችግር እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ባለኝ ደመወዝ ወር መድረስ አልችልም ያሉት ወ/ሮ አብዮት " አንድ ኪሎ ከጥቁሩ ዝቅ ያለው ጤፍ 120 ብር ነው የምንገዛው በጣም ውድ ነው ፤ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ ያብርድልን እንጂ ኑሮ በጣም ከባድ ነው " ብለዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰውአለ አባተ ስለ ጉዳዩ ምን ይላሉ ?

- የብር የመግዛት አቅም በየጊዜው መዳከም ቋሚ ደመወዝተኞች በኑሮ ውድነቱ እንዲጎዱ አድርጓል።

- ደመወዛቸው ቋሚ ነው፤ ገንዘቡ ደግሞ የመግዛት አቅሙ ከዋጋ ንረት ጋር በተገናኘ እጅግ በጣም አዘቅዝቋል። የዛሬ ዓመት 100 ብር ይገዛ የነበረው የፍጆታ እቃ ዛሬ ምን ያህል ይገዛል ? ተብሎ ሲታሰብ የመግዛት አቅሙ ቀንሷል።

- ገቢያቸው ቋሚ ከሆነና ካልጨመረ የዋጋ ንረቱ በጨመረ ቁጥር የሚጠቀሙት የፍጆት መጠን እየቀነሰ ይመጣል። ቁርስ፣ ምሳና እራት ይበላ የነበረ ሰው ዛሬ ምናልባት ቁርስና እራት ብቻ ሊበላ ይችላል። እንጀራ ይበላ ከነበረ ዳቦ ብቻ ይበላ ይሆናል።

- በአጠቃላይ ቋሚ ደሞዝተኛ የሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች እጅግ እየተጎዱ ናቸው። በቋሚ ገቢ ኑሮን መምራት ከባድ እየሆነ መጥቷል።

- የኑሮ ውድነት ጫናውን ለማቃለል የሚያስችል የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግ ጥሩ ነው።

- መንግሥት 'ደመወዝ የማልጨምረው ዋጋ ንረትን ያባብሳል' በሚል ነው ግን የዋጋ ንረቱ እስካለ ድረስ ቋሚ ገቢ ያለው ሰራተኛ በአግባቡ የዋጋ ንረቱን ሊሸከምለት የሚችል የገንዘብ መጠን በደመወዝ ጭማሪ መልክ ማግኘት አለበት።

- አንዱ ዋጋን የሚያንረው መንግሥት በመንግሥታዊ ሚዲያዎች የሚያደርገው የፕሮፖጋንዳ ስራ ነው፤ 'ደመወዝ ተጨመረ' የሚል ዜና በተደጋጋሚ ሲሰራ ገበያው ይረበሻል። የደመወዝ ጭማሪ ሲደረግ በውስጥ የመንግሥት አሰራር ቢሆንና በሚዲያ ባይጮህ ተፅእኖው ያን ያህል ላይሆን ይችላል።

- በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የነዳጅ እጥረት፣ የአቅርቦት እጥረት የፍላጎት መጨመር የሚያመጣቸው የዋጋ ንረቶች እንደተጠበቁ ሆነው ይሄን ሊያሟላና የማህበረሰቡን ኑሮ ሊደጉም በሚችል መንገድ የደመወዝ ጭማሪ ቢደረግ ጥሩ ነው።

የመንግሥት ሰራተኛው አቶ አባባይ ግን ከደመወዝ ጭማሪው ይልቅ መንግስት ውድነቱን ለመቆጣጠር ቢሰራ መልካም ነው ይላሉ። ዋጋ ሲጨምር ሃይ ባይ ሊኖር ይገባል  ብለዋል። ተቆጣጣሪ ከሌለ ደመወዝ ቢጨመር ያለው ዋጋ ከዚህ ሊጨምር ይችላል ሲሉ ገልጸዋል።

በኑሮ ውድነትና ደመወዝ ጉዳይ የሰቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ስመኝ ውቤ፤ ጉዳዩ ሁሉንም እንደሚመለከት ገልጸው የተለየ ምላሽ እንደማይሰጡ ተናገረዋል።

ከዚህ ቀደም የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ስለ ደመወዝ ጭማሪ በተመለከት ወደፊት በሂደት የሚታይ እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። #VOAAmH

@tikvahethiopia