TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የመኪና ባለንብረቶች መኪና ስታሳጥቡ በተቻለ መጠን ከስፍራው አትራቁ ፤ ወይም ቁልፍ ጥላችሁ ባትሄዱ ይመረጣል " - አዲስ አበባ ፖሊስ

እንዲያጥብ የተሰጠውን ተሽከርካሪ ሰርቆ የተሰወረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ እንዲያጥብ የተሰጠውን ተሽከርካሪ ሰርቆ ከአዲስ አበባ በመውጣት ከተሰወረ በኃላ ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ ከነተሽከርካሪው ሊያዝ ችሏል።

የፖሊስ መረጃ ግለሰቡ " ስራ በማጣት ተቸግሬአለሁ " በሚል ምክንያት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አባዶ ገደራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የመኪና እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ጠይቆ ስራ እንደጀመረ ያሳያል።

ስራ በጀመረ በሶስተኛው ቀን ግን ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ሰዓት ገደማ ሲሆን የግል ተበዳይ የሰሌዳ ቁጥር " ኮድ 3-B12112 አ.አ " የሆነች ተሽከርካሪያቸውን እንዲያጥብላቸው ከነቁልፉ በእምነት ቢሰጡትም ተሽከርካሪውን አስነስቶ  ከአዲስ አበባ ውጪ ይዞ መሰወሩን የአባዶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።

ፖሊስ የግል ተበዳይን አቤቱታ ተቀብሎ ክትትል ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ተጠርጣሪው መኪናውን ይዞ ወደ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን ከተማ እንደተጓዘ በማረጋገጥ እና ወደ ስፍራው በመሄድ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል፡፡

ፖሊስ በከተማው ለሚፈፀሙ የተሽከርካሪ ስርቆቶች በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ችግሮች መካከል አሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በቂ ጥንቃቄ አለማድረጋቸውና መዘናጋታቸው ነው ያለ ሲሆን በተለይም መኪናቸውን በሚያሳጥቡበት ወቅት በተቻለ መጠን ከስፍራው ባይርቁ አልያም ቁልፍ ጥለው ባይሄዱ  ይመረጣል ብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ አገልግሎት ፈላጊ በመምሰል እና አሽከርካሪዎችን በማስፈራራት ሁለት ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ማዋሉን ገለጸ።

የተሰረቁት ተሽከርካሪዎችም ተመልሰዋል ብሏል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ሁለት ግለሰቦች ከሌሊቱ 6 ሰዓት ገደማ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B15712 አ.አ አሽከርካሪን ከገርጂ ወደ መገናኛ እንዲያደርሳቸው ከተስማሙ በኋላ አሽከርካሪውን #በመደብደብ ተሽከርካሪውን ቀምተው ያመልጣሉ፡፡

የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት የደረሰው የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ወንጀል ፈፃሚዎቹን ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ተገልጿል።

እነዚሁ ወንጀል ፈፃሚዎች ሐምሌ 13 ቀን 2015 ዓ/ም በተመሳሳይ ዘዴ አሽከርካሪን በማስፈራራትና በመደብደብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- A75796 አ.አ ተሽከርካሪን ይዘው ከተሰወሩ በኋላ የሰረቁትን መኪና #በ200_ሺህ_ብር እንደሸጡ እና ገዢውም አሳልፎ ለሌላ ግለሰብ እንደሸጠው ፖሊስ አደረኩት ባለው ምርመራ ማረጋገጡን ገልጿል።

ፖሊስ የተሰረቁትን ሁለት ተሽከርካሪዎች ማስመለሱን ገልጾ በአጠቃላይ በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ አላቸው የተባሉ 5 ግለሰቦች ተይዘው ምርመራ የተጣራባቸው ነው ብሏል።

በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት መዝገቡን ለአቃቤ ህግ መላኩንም አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ የተሰረቁ ንብረቶችን የሚገዙ ህገ-ወጦች ለመሰል ወንጀል መበራከት ምክንያት ሆነዋል ያለ ሲሆን የተሰረቁ እቃዎችን የሚገዙ ህገ-ወጦችን ለመቆጣጠር እየሰራ ያለውን ስራ እንደሚያጠናክር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ቴክኖ ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ ምርጫዎ ያድርጉ!

በአዲሱ ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ እንደፍላጎትዎ ከአንዱ ማሳያ ወደ ሌላ እንዲገለብጡ የሚያስችል ልዩ ባለሁለት ስክሪን ዲዛይን ያለው ፣ ሁለቱንም ማያ ገጾች በተመሳሳይ ጊዜ መጠቀም ወይም በቀላል የእጅ ምልክት መቀያየር የሚችሉ ሲሆን በማንኛው ጊዜ እና በየትኛውም ቦታ ሆነው ሁሉንም አይነት አገልግሎት በብቃት የሚያከናውኑበት ዘመናዊ ስልክ ነው።  የቴክኖ ‘ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ የሞባይል ስልክ ብቻ ሳይሆን የሚኮሩበት ምርጫ ነው።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
ስኬትዎ የኛም ስኬት ነው!

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን

የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

#Globalbankethiopia #sharedsuccess
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን መካከል በታንዛኒያ የሁለተኛ ዙር የሰላም ንግግር መጀመሩን " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ዘግቧል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ የሰላም ንግግሩ ጥቂት ቀናትን እንዳስቆጠረና ከሁለቱም ወገኖች የተወጣጡ የጦር አባላት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ መሆኑን ያስረዳል። ከዚህ ቀደም ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው…
#Oromia

ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ በመንግሥትም ሆነ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን) በኩል ይፋዊ መግለጫ ሆነ ማብራሪያ ባይሰጥም በታንዛኒያ፣ ዳሬሰላም ውስጥ ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር መጀመሩን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

ዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለፁት ድርድሩ እየተመራ ያለው በጦር አዛዦች ነው።

የመንግሥት የተደራዳሪ ቡድን የሚመራው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ ዕዝ አዛዥ በነበሩት ጄነራል ጌታቸው ጉዲና ሲሆን በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል ደግሞ በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ነው።

ጃል መሮ ከወለጋ ጫካ በኢጋድ፣ በአሜሪካ፣ በኖርዌይ መንግሥታት አስተባባሪነት ነው በአውሮፕላን ወደ #ኬንያ ከዛም ታንዛኒያ እንዲገቡ የተደረጉት።

ከጃል መሮ በተጨማሪ የደቡብ ኦሮሚያ አዛዡ ገመቹ ረጋሳ (ጃል ገመቹ አቦዬ) ከነበሩበት ቦረና አካባቢ በኬንያ አድርገው ወደ ዳሬሰላም እንዲገቡ መደረጉን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ተናግረዋል።

ሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንዲሳካ ኢጋድ፣ አማሪካ፣ ኖርዌይ፣ ኬንያ ድጋፍ እና የማመቻቸት ስራን እየሰሩ ነው ተብሏል።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መሪዎች ከመንግሥት ጋር ፊት ለፊት መገናኘታቸው ለሰላም ድርድሩ ተስፋ እንደሰጠው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ተጫማሪ አራት ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን አነሱ። ከስልጣን ያነሷቸው ፦ - አቶ አለም ገ/ዋህድ የህወሓት የፓለቲካዊ ጉዳዮች ሃላፊና ዋና ፓሊት ቢሮ አባል ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አማካሪ - የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሊያ ካሳ ከደቡባዊ ምስራቅ ዋና አስተዳዳሪ - የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባል አቶ ተኽላይ ገ/መድህን…
" በህወሓት ውስጥ የተለመደ የሐሳብ ልዩነት አለ፣ ሁሌም ግን ብዙሃኑ ያሸንፋል " - አቶ ረዳኢ ሓለፎም

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ 4 ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ማንሳታቸው ይታወቃል።

አቶ ጌታቸው ከስልጣን ያነሷቸው ፤ አቶ አለም ገ/ዋህድ ፣ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ፣ አቶ ተኽላይ ገ/መድህን እንዲሁም አቶ አማኒኤል አሰፋ ናቸው።

ይህንን በተመለከተ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም የተወሰደው እርምጃ ማነኛውም አስተዳደር የሚያደርገው የተለመደ ተግባር ነው ብለውታል።

" ሰዎች መመደብም፣ ሰዎች ከምደባቸው ማንሳትም የአንድ መንግሥት መደበኛ ሥራ ተደርጎ የሚታይ ነው " ያሉት አቶ ረዳኢ " እርምጃው የተለየ መልክ የለውም " ብለዋል።

አቶ ረዳኢ በህወሓት ውስጥ የሐሳብ ልዩነት እና ግልፅ ልዩነት ስለመኖሩ ከሬድዮ ጣቢያው ተጠይቀው  " በህወሓት ውስጥ የተለመደ የሐሳብ ልዩነት አለ፣ ሁሌም ግን ብዙሃኑ ያሸንፋል " ሲሉ መግለፃቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ረዳኢ ሓለፎም የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

በአዲስ አበባ በከተማ " ጉንፋን መሰል " ህመም መከሰቱና ነዋሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የጤና ባለሙያዎች እየመከሩ ናቸው።

በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሃኪም ዶ/ር ስንሻው አባይ ፤ በአዲስ አበባ በከተማ ለተከሰተው " ጉንፋን መሰል ህመም " ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ጉንፋን መሰል ህመሙ፦
- ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
- ሳል፣
- ራስ ምታት፣
- ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
- ድካም፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ዶክተሩ ፤ ሰሞኑን የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም የላይኛውን የመተንፈሻ አካል ክፍል የሚያጠቃ ነው ብለዋል፡፡

ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
* ፈሳሽ መውሰድ፣
* ከቅዝቃዜ ራስን ማራቅ (ሙቀቱን የተመጣጠነ ማድረግ)፣
* መኖሪያ ቤትን አየር እንዲያገኝ ማድረግ፣
* በቂ የሆነ እረፍት መውሰድ እና የመሳሰሉትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን መክረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በቤት ውስጥ የእፅዋት ዝርያዎችን በፍም (እሳት) ላይ በማጨስ ጭሱን መታጠን ሳንባ እንዲያብጥ ወይም እንዲቆጣ በማድረግ ለጉዳት እንደሚዳርግ ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ ፦
° በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት፣
° በንግድ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በማድረግ፣
° የእጅን ንፅህና በአግባቡ በመጠበቅ እንዲሁም አስም ያለባቸው ምልክቶቹ እንደታዩባቸው ወደ ህክምና ተቋማት ሄደው መታየት እንዳለባቸው መክረዋል።

የጤና ሚኒስቴር ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን በ2 ሺህ ያህል ናሙናዎች ላይ ምርመራ አድርጎ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ይፋ አድርጓል።

የዝናብ ወራት ማለፉን ተከትሎ በጥቅምትና ህዳር ወቅት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ ይከሰታል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ ግብረ-ሃይል ዋና አስተባባሪ ዶክተር መብራቱ ማሴቦ ፤ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጉንፋንና ኢንፍሉዌንዛ በሽታ መከሰቱን ተናግረዋል።

" እጅን በመታጠብ፣ አፍና አፍንጫን በመሸፈን በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል " ያሉ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቂ እረፍት በመውሰድ፣ ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች በመጠቀምና ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጤና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር፣ በርና መስኮቶችን በመክፈት፤ በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር በማድረግ መከላከል እንደሚቻልም ነው የገለፁት፡፡

መረጃው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና ኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SunChips

ከሰዓት ድካም ሲጫነን፣ አንድ መፍትሄ! #መክሰስTime ደርሷል! - ከ #ሰንቺፕስ ጋር 😋 #ሰኒሞመንትስ ☀️

#SnackTime is here, to make us let loose and enjoy our afternoon once again - with #SunChips 😋 and #SunnyMoments. ☀️

Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
@samcomptech

አዳዴስ  ላፕቶፕች ገብተዋል!!!!

ለተማሪዎች፣ ለቢሮ ሰራተኞች፣ ለጌመሮች, ለቪዴዮ ኢዲተሮች ፣ ለግራፌክስ ስራዎች ፣ ለዴዛይነሮች አዳዴስ  ላፕቶፕች እና ስልኮች  በቅናሽ እና ከአንድ አመት ዋስትና ጋር እናቀርባለን።
🔵 @samcomptech

በሚገርም ፍጥነት ፣ ቅለት እና ከ 10 ሰሀት በላይ የባትሪ ቆይታ ያላቸዉ  ዘመናዊ ላፕቶፖችም አሉን።

ቴሌግራም ላይ ሁሉም ዝርዝር አለ በመቀላቀል  የሜፈልጉትን ይምረጡ  ።
🔵https://t.iss.one/samcomptech 🔵 
🔼@sww2844

ስልክ፤ 0928442662 / 0940141114
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#SouthEthiopia

" በእኛ ደረጃ የደረሰን ኦፊሻል መረጃ የለም። ቅሬታም የለም። ስለዚህ ዞኖቹን አናግራቸዋለሁ " - አቶ ወገኔ ብዙነህ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ውስጥ በመዋቅር ጥያቄ ምክንያት " ወጣቶች በጅምላ ታስረው ይገኛሉ " ሲሉ የታሳሪ ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

አንድ ለደኅንነታቸው ሲባል ሥማቸው እዳይጠቀስ የጠየቁ ምንጭ፤ በቅርቡ ተዋቀረ ወደተባለው ኮሬ ዞን (የቀድሞው አማሮ ልዩ ወረዳ) የተካለለ ቦታ ወደ ዳኖ ማዕቀፍ እንዲመለስ የሚል ጥያቄ እንደተነሳ፣ በዚህም ማኅበረሰቡ ላይ ቅሬታ በመፈጠሩ ወጣቶች መንገድ ዘግተው ስለነበር የሃይማኖት አባቶች በሰጧቸው ምክር መንገዱ እንደተክፈተ ገልጸዋል።

መንገድ ዘጉ የተባሉትም ለምን እንደዘጉ ከሃይማኖት አባቶች ጥያቄ ሲቀርብላቸው 'እኛ መንገድ ለመዝጋት ፈልገን ሳይሆን ባለሥልጣናት መጥተው እንዲያወያዩን ፈልገን ነው' በማለት መንገዱን እንዲከፈት ተደርጓል ብለዋል።

የሃይማኖት አባቶችም ሕዝቡ እንድታወያዩት ይፈልጋል ብለው ለባለሥልጣናቱ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስረድተዋል።

በተያያዘም ጥቅምት 11/2016 ዓ.ም እንደተጻፈ የሚያስረዳው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው የቅሬታ አቅራቢዎቹ ደብዳቤ፣ ከዳኖ ቀበሌ የወጣው መዋቅር እንዲመለስ በመጠየቃቸው ምክንያት አሉታዊ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው መሆኑና ሰዎች በተለይም ወጣቶችን እያሳደዱ የማሰር ተግባር መፈፀሙን ያስረዳል።

የታሳሪ ቤተሰቦች ሕዝቡን #ማወያየት ሲገባ መንገድ ያልዘጉ ወጣቶችን መንገድ ዘግታችኋል ተብለው በጅምላ ታስረዋል ያሉ ሲሆን መንገድ ተዘጋ ቢባል እንኳ አሁን የታሰሩት ሰዎች መንገድ የዘጉ እንዳልሆኑና ያለጥፋታቸው ከአንድ ወር በላይ እንደታሰሩ፣ በቀጠሯቸው ጊዜም ዳኞች እንደማይገኙ አስረድተው፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ፍትህ እንዲያሰጡ ጠይቀዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሁነቱን ያስረዱ ሌላኛው የዓይን እማኝ  " ሦስት በአራት የሆነች ክፍል አለች እዚያ ውስጥ አንድ ላይ ነው ታራሚዎች የሚታጎሩት። እስር ቤቱ ውስጥ ላይ ደግሞ አያያዝ በጣም ያስጠላል ትኋን አለ፣ ቁንጫ አለ። በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህ ብቻ አይደለም እዚያ ከታሰሩት ሰዎች መካከል ተመርጠው ጥቆማ ለመስጠት የሚቀመጡ አሉ፣ ተንኮል ካሰቡ ሲፈልጉ አሳልፈው ለፖሊስ ይሰጣሉ። የተቀጠረው ተረኛ ፓሊስ በአንድ ግለሰብ ጥቆማ ብቻ መጥቶ ይቀጠቅጣል " ሲሉ አስረድተዋል።

ወጣቶች በጅምላ ታስረዋል መባሉን በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የቀድሞ የአማሮ ልዩ ወረዳ ባለስልጣን ፣ በመዋቅር ጥያቄ ምክንያት ወጣቶች እደታሰሩና በቀጠሮ ቀንም ዳኞች ስለማይገኙ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) ከእስር እንዳልተፈቱ ገልጸዋል።

የኮሬ ዞን አስተዳደር፣ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ባለድርሻ አካላት ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ ባይሆኑም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥቷል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " በእኛ ደረጃ የደረሰን ኦፊሻል መረጃ የለም። ቅሬታም የለም። ስለዚህ ዞኖችን አናግራቸዋለሁ " ብለዋል።

አክለውም፣ ቅሬታ በቀረበበት መንገድ የታሰሩበት ሁኔታ በፍጹም ትክክል  እንዳልሆነ ገልጸው፣ " እንዲህ አይነት ችግሮችን ቢያንስ የመዋቅር ዞኑ አልፈታ ካለ እኛ ጋ ማድረስ ነበረባቸው አሰራሩም እንደዛ ነው። እኛ ቼክ እናደርጋለን " የሚል ምላሽ ሰጥዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በጉዳዩ ዙሪያ ክትትል እንደተደረገና የእስር ቤት አያያዝ ሁኔታው የሚገለጸው ኮሚሽኑ በሚያወጣው ሪፓርት እንደሆነ አስረድቷል።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

የታፈነው ህፃን ከ12 ቀናት በኋላ መገኘቱ የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ አስታወቀ።

የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ አዛዥ ደሳለኝ አድማሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ እንዳሉት ፤ 4 ሚሊዮን ብር የማስለቀቅያ ክፍያ የተጠየቀበት ሚልክያስ ፋኑስ የተባለ ህፃን ከ12 ቀናት ፍለጋ በኋላ ተገኝቷል።

የአፈናው አፈፃፀም እና መገኘት አስመልክቶ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከህፃኑ ቤተሰብና ከፓሊስ መረጃዎችን አሰባስቧል።
                  
ህፃን ሚልክያስ ፋኑስ ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዒዲግራት ' ጎልጎታ ' ወደ ተባለ ትምህርት ቤት በመሄድ ሳለ አጂብ ተብሎ ከሚጠራ ቦታ ሞተር ሳይክል የያዙ ሁለት ሰዎች ከታላቅ ወንድሙ ነጥለው ይዘውት ይሰወራሉ።

የህፃን ሚልክያስ ወላጆች ከታላቅ ወንድሙ ባገኙት መረጃ ወድያውኑ ወደ ዓዲግራት ከተማ ፓሊስ አመልክተዋል።

ጎን ለጎንም የህፃን  ሚልክያስ ፎቶ በማህበራዊ የትስስር ገፅ በማውጣት ፍለጋቸው አጠናከሩ።

የህፃን ሚልክያስ ታፍኖ የመሰወር መረጃ በበርካታ የትግራይ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተንሸራሽረዋል።

በዚሁ መሃል ህፃን ሚልክያስ አፍነው የሰወሩ ሰዎች አገናኝ ሶስተኛ ሰው በመቅጠር ህፃኑ ለመልቀቅ የ4 ሚሊዮን ብር ክፍያ ይጠይቃሉ። 

የህፃን ሚልክያስ ወላጆች የተባሉት ባለመፈፀማቸው ጥቅምት 15 የጠፋው ልጃቸው እስከ ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም ድምፁ ሳይሰማ ይቆያል። ይህም ጉዳይ እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

ሆኖም ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም ተማሪ ህፃን ሚልክያስ ከዓዲግራት ከተማ ውጭ በአንዲት አቅጣጫ መገኘቱ የሚያበስር የሞባይል ድምፅ ወደ ህፃኑ ወላጆች አቃጨለ።

ህፃን ልጃቸው አለበት ወደ ተባለ ቦታ በፍጥነት የደረሱት ወላጆች በአካሉ የተመለከቱት ጉዳት ባይኖርም ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል ወስደውታል።  

የህፃኑ ቤተሰብና በርካታ የማህበራዊ የትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ተማሪ ሚልክያስ በመገኘቱ ደስታቸው ከገለፁ በኋላ ፤ ትራፊክ ፓሊስ የመንጃ ፍቃድ ሳይኖራቸው ሞተር ሳይክል በሚያሽከርክሩ ግለሰቦች ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ አስተያየት ሰጥተዋል።

የዓዲግራት ከተማ ፓሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፀው ህፃን ሚልክያስ ፤ ከከተማው ክልል ውጭ ቤተሰቦቹን 4 ሚሊዮን ብር ከፍለው እንዲያስለቅቁት ሲያደራደር በነበረው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው በኩል መገኘቱን አስታውቀዋል።

የዓዲግራት ፓሊስ አክሎ እንዳለው ህፃኑ ያፈኑ ፣ በአፋኞቹና በቤተሰብ መካከል 4 ሚሊዮን ብር በመክፈል እንዲለቀቅ ሲያደራድር የነበረ በድምር ሶስት ተጠርጣሪዎች ለመያዘ ከዞኑ ፣ ከአጎራባች ወረዳ ፓሊስና ከቴሌ ጋር በመቀናጀት እየሰራ እንደሆነ አስታውቆ ህዝቡም ተጠርጣሪዎቹ በመያዝ የበኩሉ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከትግራይ ፓሊስ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአራት ዓመት በፊት ተመሳሳይ የወንጀል ደርጊት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ውለው  በህግ ተገቢ ቅጣት አግኝተዋል።    
                         
@tikvahethiopia
ከመስኮት ወደ በር....
**
ያኔ ሀ ብለን ስንጀምር በ23 ቅርንጫፎች በተለየ መስኮት ነበር፡፡

ጳጉሜ 2፣ 2011 ዓ.ም የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያው ቅርንጫፍ በር ለደንበኞቻችን ተከፈተ፡፡ ቢላል ቅርንጫፍ፡፡ 

አሁን በ153 የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ ቅርንጫፎች፣ በአጠቃላይ በ1934 ቅርንጫፎች የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን፡፡

ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ!

ትክክለኘውን የቴሌግራም ቻናል https://t.iss.one/combankethofficial
ሁሉንም በአንድ ላይ ማከናውን የሚችል ስማርት ስልክ እየፈለጉ ከሆነ፣ ‘ቴክኖ ፋንተም ቪ ፍሊፕ 5ጂ’ ለእርሶ ነው!

የ5ኛው ትውልድ ወይም 5ጂ ዓለም የደረሰበት የመጨረሻው ፈጣን የሞባይል ኔትዎርክ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም፣ እንከን የለሽ አገልግሎት እንዲስጥ ታስቦ በኦክታ ኮር ሲፒዩ(Octa Core CPU) በመታጀብ በፍጥነቱ የተመሰከረለት ሚዲያቴክ ዲምነሲቲ 8050 (Mediatek Dimensity 8050) ፕሮሰሰር የተገጠመለት፣ ማንኛውንም አይነት መተግበሪያ በፍጥነት እና ያለእንከን እንዲሰራ የሚያረገው 256 ጂቢ ሜሞሪ ከ(8+8) virtual RAM ያካተተ እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ደግፎ ለረጅም ጊዜ ያለ ማቋረጥ አገልግሎት ማስጠቀም የሚያስችል 45ዋት የፍጥነት ቻርጅ በመጠቀም 45 ደቂቃ ብቻ ሙሉ ቻርጅ የማድርግ አቅም ያለው ባለ4000 ሚሊአሚፒር ባትሪ ያካተተ ነው ።

ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#PhantomVFlip#TecnoMobile #TecnoEthiopia
🔹 " እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው #በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው " የመ/ግ/ን/ባ

በመንግሥት የግዥ ሒደት እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆኑን፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘንድሮ በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሲስተም ተግባራዊ ተደርጎና አፈጻጸሙን ለማሳደግ፣ ከንግድ ማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ምን አሉ ?

- በመንግሥት በግዥ ሥርዓት ውስጥ፣ ከ80 እስከ ከ90 በመቶ በላይ ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው ብለዋል።

- ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የመንግሥት ተቋም #በጨረታ አንደኛ የወጣ ድርጅት እያለ ሦስተኛ ከወጣው ጋር ውል መግባቱን፣ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

- ከኮንስትራክሽን ጋር ተያይዞ ጨረታ የሚያወጡ የመንግሥት ተቋማት #የሚፈልጉዋቸው ተጫራቾች ካልመጡ እስከ #መሰረዝ እንደሚደርሱ አመልክተዋል።

- የመንግሥት ተቋማት ተጫራቾችን ሆን ብለው ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ሕጎችን እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሙ፣ ያሸነፉ ተጫራቾችንም #እንዲሰላቹ በማድረግ ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

- በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምክንያት የሚመጡ ክሶች መኖራቸውን ገልጸው በዓመት እስከ 150 የሚደርሱ ክሶች እንደሚስተናግዱ ተናግረዋል። በአብዛኛው ጨረታ የማውጣትና የሚገመገምበት መሥፈርት በመለያየቱ ምክንያት በርካታ ተጫራቾች ክስ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢጋድ አባል አገሮችና የነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ ምን አሉ ?

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ከታዩ ክፍተቶች አንዱ በጠቅላላ የመንግሥት ግዥ መባሉ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- የመንግሥት ግዥ ተብሎ ስያሜ ቢሰጠውም የመንግሥት ተቋማትና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚገናኙ በመሆናቸው ከስያሜ ጀምሮ ማስተካከያ ይፈልጋል ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ሙስናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጻዋል። ከዚህ ቀደም #በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ግዥዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እየቀረቡ እንደነበርና ሥርዓቱ መዘመኑ በተወሰነ መንገድ ችግሩን መቀረፉን አስረድተዋል፡፡

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ለሚታዩ የሙስና ብልሹ አሠራርን ከሥሩ ማድረቅ እንደሚገባ፣ በተለይ ተጫራጮች ወደ ተቋማት ሲሄዱ #ሲስተም_የለም የሚለው ቋንቋ የችግሩ መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- ተጫራቾች ወይም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለሙስና እንዳይጋለጡ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሞጋችና ተከራካሪ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የመንግሥት ግዥ የንብረት ባለሥልጣን የመንግሥት ግዥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ከበደ ምን አሉ ?

- የነባሩ የወረቀት የግዥ ሥርዓት የሙስና ተጋላጭነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መኖሩ የሚቀርፏቸው ችግሮች ሰፊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለብዙ ተጫራቾች ዕድል ከመስጠት አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

- የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት በ2015 ዓ.ም. ሲጀመር የተመዘገቡት የንግድ ማኅበረሰብ አባላት 100 ብቻ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከ15‚000 በላይ ተሻግረዋል።

- ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ 70 በመቶ የሚውለው ለግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ይህም በገንዘብ ሲቀየር 560 ቢሊዮን ብር ለግዥ እንደሚውል ተናግረዋል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia