TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው

" ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። "

በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

መግለጫው በክልሉ በተለያዩ ጊዜ በድሮን / አየር ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ፣ በርካታ ሰዎች ግጭት ሽሽት አካባቢያቸውን ጥለው መሸሻቸውን፣ ከፍርድ ውጭ የሚፈፀመው ግድያ መቀጠሉን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ግድያም መፈፀሙን ያስረዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ : ለወራት የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ዐውድ እና አሉታዊ የሰብአዊ መብቶች እንድምታው " ተፋላሚ ኃይሎች ሲቪል ሰዎችንና ንብረቶችን፣ የሕዝብ አገልግሎቶችን እና መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ከማድረግ ሊቆጠቡ፣ መንግሥት የማኅበራዊ አገልግሎቶች እዲቀጥሉ አስቻይ ሁኔታ ሊፈጥር ይገባል። " በአማራ ክልል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። መግለጫው በክልሉ በተለያዩ…
#አማራ

በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ዛሬ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተላከልን መግለጫ መረዳት ችለናል።

ከኢሰመኮ በደረሰን መግለጫ ፤ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል።

በተጨማሪም እነዚህ አካባቢዎችና ወረዳዎች በአንድ ወቅት ላይ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በሌላ ወቅት ደግሞ በታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የትጥቅ ግጭቱ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ በከባድ መሣሪያ እና አልፎ አልፎ በአየር / ድሮን ድብደባ ጭምር የታገዘ ነው።

በግጭቱ ዐውድ ውስጥ #የአየር /#ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል።

ለምሳሌ ፦

- በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በረኸት ወረዳ፣ ' መጥተህ ብላ ' ከተማ ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት የአንድ ዓመት ከሰባት ወር ሕፃንን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች #ተገድለዋል፤ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- በደብረ ማርቆስ ከተማ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተፈጸመ የድሮን ጥቃት  ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

- በደንበጫ ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በከባድ መሣሪያ ድብደባ ምክንያት ሲቪል ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል።

ኮሚሽኑ እነዚህን መረጃዎች ያገኘው የአካባቢውን ነዋሪዎች እና የዓይን ምስክሮችን በማነጋገር ነው።

በአንዳንድ አካባቢዎች ጥቃትን አልያም ግጭትን በመሸሽ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ ከቀያቸው ተፈናቅለው በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችሏል።

በምንጃር ወረዳ ውስጥ የአውራ ጎዳና ጎጥ ነዋሪዎች ከመስከረም 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከቀያቸው ተፈናቀለው ቢያንስ 3ዐዐዐ የሚሆኑት አሞራ ቤቴ ቀበሌ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤትና ክፍት ሜዳ ላይ (በዛፍ ሥር) ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፣ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ መተሃራና አዋሽን ጨምሮ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለዋል።

ለተፈናቃዮች የተወሰነ ድጋፍ በማኅበረሰቡና እና በአንድ ተራድዖ ድርጅት የተደረገ ቢሆንም፣ በቂ ባለመሆኑ በአሳሳቢ ሁኔታ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

የነዋሪዎችን መፈናቀል ተከትሎ ሰብላቸው እንደወደመ፣ ንብረታቸው እንደተዘረፈ፣ የቤቶቻቸው ጣራያ እና በር እየተነቀለ እንደተወሰደ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ቤቶቻቸውን ከአጎራባች ክልል በመጡ ኃይሎች በኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ጭምር ማፍረስ እንደተጀመረ ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የመንግሥት ኃላፊዎች አስረድተዋል።

በመንግሥት የጸጥታ ኃይል አባላት የሚፈጸሙ ከሕግ ውጪ የሆኑ ግድያዎች አሁንም መቀጠላቸውን ኢሰመኮ ተዓማኒ መረጃዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ገልጿል።

ግጭቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦

- " ፋኖን ትደግፋላችሁ "

- " ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ "

- " መሣሪያ አምጡ "


- " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች ተገኝተዋል።

እንደማሳያ ፦

▪️በባሕር ዳር ሰባታሚት አካባቢ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2016 ዓ.ም. #ሦስት_ወንድማማቾችን ጨምሮ በርካታ ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

▪️በሰሜን ጎጃም ዞን፣ አዴት ከተማ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፍልሰታ ደብረ ማሪያም የሚኖሩ 12 የአብነት ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

▪️ በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ አማኑኤል ከተማ ጥቅምት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢያንስ 8 ሲቪል ሰዎች በቤት ለቤት ፍተሻ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።

▪️በምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ፣ ግንደወይን ከተማ ሞጣ በር ተብሎ በሚጠራ አካባቢ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም. አንድ በጥይት የቆሰለን ግለሰብ እናቱና እህቱ በባጃጅ አሳፍረው ወደ ሕክምና ተቋም በመውሰድ ላይ እያሉ፣ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ባጃጁን አስቁመው ሁሉንም ተሳፋሪዎች ካስወረዱ በኋላ " የቆሰለው እኛን ሲዋጋ ነው " በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራቱን ሰዎች በጥይት እንደገደሏቸው ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች አስረድተዋል።

በባሕር ዳር፣ በፍኖተሰላም፣ በጎንደር እና በወልድያ ከተሞች በትጥቅ ግጭቱ ቆስለው ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ የተወሰኑ ሲቪል ሰዎች እና የታጣቂ ቡድኑ አባላት በመሆን በመንግሥት የጸጥታ አካላት የተጠረጠሩ ሰዎች ሕክምናቸው እዲቋረጥ ተደርጎ #ወዳልታወቀ_ስፍራ ከተወሰዱ በኋላ ፣ ከፊሎቹ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ወደ ሕክምና ተቋማቱ ሲመለሱ ቀሪዎቹ ያሉበት ሁኔታ ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ማረጋገጥ አልተቻለም።
 
በሌላ በኩል በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች ተፈጽመዋል።

ለምሳሌ ፦

መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ሲሄዱ ' አለምበር ከተማ ' አካባቢ በታጣቂዎች ተገድለዋል።

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ማረሚያ ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ታራሚዎችና ተጠርጣሪዎች እንዲያመልጡ ተደርጓል። 
 
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል ፤ በተለይም ከመንግሥት ተቋማት ጭምር በሚደርሱት መረጃዎች መሠረት በግጭቱ ዐውድ የሚፈጸሙ የአስገድዶ መድፈር ድርጊቶች በጣም አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ተገቢው ምርመራ ተደረጎ አርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ነው፡፡

የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በተለያዩ የጤና ተቋማት መድረስ የቻሉትን ተጎጂዎች ቁጥር ብቻ መሠረት በማድረግ ከሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ ቢያንስ #2ዐዐ_የአስገድዶ_መድፈር ተጎጂዎች በጤና ተቋማት ተመዝግበዋል፤ ከተጎጂዎች መካከልም የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሴቶች እና የጤና ባለሞያ ሴቶች ጭምር ይገኙበታል።

ከትጥቅ ግጭቱ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ፦
🔹ሲቪል ሰዎች እና የሲቪል የንግድ እና የመሠረተ ልማት ተቋማት ላይ ዝርፊያ ተፈፅሟል።
🔹የማሳ ላይ ሰብል ውድመት ጨምሮ በሲቪል ሰዎች፣ በሕዝብ እና በመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት ደርሷል።
🔹ሕፃናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል በአንዳንድ አካባቢዎች የትምህርት ተቋማት ለወታደራዊ አገልግሎት ውለዋል። ይህ ደግሞ አፋጣኝ ትኩረት የሚሻ ነው።

በክልሉ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ከተፈቀደላቸው ተቋማት በስተቀር ይህ መግለጫ እስከ ወጣበት ጊዜ ድረስ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን፣ በተለይም በግጭት ላይ ባሉ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎትም ጨምሮ ተቋርጧል።

(ዛሬ ከ #ኢሰመኮ የተላከል ሙሉ መግለጫ በዚህ ታገኛላችሁ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82609?single)

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የታሪፍ ጭማሪ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ በተሰማሩ የሚዲ-ባሶች እና የሚኒ-ባስ ታክሲዎች ላይ #የታሪፍ_ጭማሪ አድርጓል።

አዲሱ ታሪፍ ከነገ ጥቅምት 20 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢሮው አስታውቋል፡፡

(ዝርዝር ታሪፉን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
በቴሌኮም ዘርፍ፣ ዲጂታል ሶሉሽኖች፣ በቴክኖሎጂ እና በአገልግሎቶቻችን ዙሪያ:-

👉 የሚወያዩበት
👉 ሃሳብ የሚሰጡበት
👉 ልምድና ተሞክሮ የሚጋሩበትን

ቴሌፎረም የድረ-ገጽ መድረክ https://teleforum.ethiotelecom.et ቤተሰብ ይሁኑ!
#ጥቆማ #ከጠቀማችሁ

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወርሰው የሚገኙ 171 ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ተጨራቾች የጨረታ ሰንድ በመግዛት በጨረታው ላይ የሚወጡትን ተሽከርካሪዎች በአካል በመመልከት መጫረት ትችላላችሁ ተብሏል። ጨረታው በ26/02/2016 ዓ/ም ጥዋት 4 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:15 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0221118429 ላይ መወደል ይቻላል።

አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የቤትና የጭነት ተሸከርካሪዎች ፦
- DUMP TRUCK፣
- IVECO FIAT፣
- TOYOTA HAILUX፣
- TOYOTA COROLLA፣
- TOYOTA  VITZ፣
- TOYOTA HAICE፣
- TOYOTA YARIS፣
- TOYOTA CHR፣
- HYUNDAI፣
- SUZUKI፣
- MISTUBUSHI ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውብት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የተጠቀሱት ተሸከርካሪዎች የጨረታ ሰነድ ከቀን 20/02/2016 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት ይቻላል።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

  የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከፎኔክስ ኢንደስትሪ ኃ/የ/የግ/ማህበር የተያዘ፦
- የኘላስቲክ ወንበር ማምረቻ ማሽን፣  የማሽኑ ማቀዝቀዣ (cooler)፣ የማሽኑ ጥሬ ዕቃዎችና ሌሎች ተጓዳኝ ዕቃዎች፣

ከተክለብርሃን አምባየ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ ፦
- የተለያዩ መጠን ያላቸው የመብራት አምፖሎች፣
- ፍሎረሰንቶች፣
- ፖውዛዎች እና የውሃ ተቀባሪና ተንጠልጣይ የተለያዩ ቧንቧዎች፣

🚘 ከቲ.አይ.ቢ ኬተሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህ እና ኦክስፎርድ አማልጌትድ ኃ/የተ/ የግ/ማህበር የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 3 ተሽከርካሪዎች ናቸው።

(ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ በምስሉ ይመልከቱ)

#ጉምሩክኮሚሽን #አዲስዘመን #ገቢዎችሚኒስቴር

* ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በጥቆማ መልክ የቀረበ።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአፖሎ ሲገበያዩ ሁሉም ነገር ቅናሽ አለው! ምን ቅናሽ ብቻ ከንክኪ ነጻ የሆነ ቀልጣፋ እና  ፈጣን አገልግሎትም ያገኛሉ!
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። 
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo 

የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/BoAEth
 
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" መንግስት የሚወስነውን የሆነ አካል ተነስቶ ' ይህ ይሁን ፤ ይህ ደግሞ አይሁን ' ማለት ትክክል አይደለም " - አቶ ረዳኢ ኃለፎም

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ " ወቅቱን ያልጠበቀና ህገወጥ ነው " በማለት እንዳይካሄድ ክልከላ ያስተላለፉበት የህወሓት የካድሬዎች ስብሰባ የአጠራሩን አግባብነት ከተነጋገሩበት በኃላ ፓርቲው ያጋጠሙትን አደጋዎች አስመልክቶ ባፀደቀው ዋና አጀንዳ ላይ ከ2 ሳምንት በኃላ ተገናኝቶ ለመወያየት ወስነው ተበትነዋል።

ምንም እንኳን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ክልከላ ቢጥልም የህወሓት ካድሬዎች ቅዳሜና እሁድ መቐለ ሰማዕታት አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው ነበር።

የስብሰባው መጠናቀቅን ተከትሎ ፓርቲው ባሰራጨው መግለጫ ፤ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አስቀድሞ ካድሬዎችን ሰብሰበው ባለማናገራቸው ወቅሷል።

በፓርቲው ላይ ያጠላው አደጋ ምንድነው ? በሚል በተቀረፀ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ ላይ ችግሩን በተረጋጋ መንፈስ ለመገምገምና የውስጥ ማጥራት ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን ፓርቲው ገልጿል።

በዶክተር ደብረፅዮ ገ/ሚካኤል የተመራው የፓርቲው የካድሬዎች ስብሰባ የስብሰባው ዋና አጀንዳዎች በሆኑ ጉዳዮች ላይ ከሁለት ሳምንታት በኃላ እንዲታዩ ውሳኔውን አሳልፎ ተበትኗል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ በፓርቲው ካድሬዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ተቋማዊ አሰራርን ያልተከተለ ነው በሚል የተቸው ፓርቲው እርምት እንዲደረግ ጠይቋል።

ባለፈው ሳምንት ከመንግስት የስራ ኃላፊነት ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 6 ከዞን አመራሮች ከአቶ ጌታቸው ረዳ በተላከላቸው ደብዳቤ ከስልጥን እንዲነሱ መደረጉ አይዘነጋም።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምን አለ ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረዳኢ ኃለፎም ስብሰባው እንዳይካሄድ ያገድነው ተሳታፊዎቹ የመንግስት ሰራተኞች እና አመራሮች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቅድሚያ የሰጣቸው ተግባራት በመኖራቸው ነው ብለዋል።

አቶ ረዳኢ ሃለፎም ፦

" ጊዜያዊ አስተዳደሩ ስብሰባው ትክክል አይደለም ያለው በአሁን ሰዓት መሰራት ለሚገባቸው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት ላይ ጉዳት ሳያደርስ የመሰብሰብ እና አንበጣን የመከላከል ተግባራት የትኩረት አቅጣጫ በማስቀመጡ ነው።

ይኸውም ቅድሚ እንዲሰጠው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን በህወሓት መሪዎችም ጭምር መግባባት ላይ ተደርሶ ስብሰባው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ስለተወሰነ ነው።

ስብሰባው የተካሄደው ከዚህ የጋራ ውሳኔ በኃላ ነው። መንግስት የሚወስነውን የሆነ አካል ተነስቶ ' ይህ ይሁን ፤ ይህ ደግሞ አይሁን ' ማለት ትክክል አይደለም።

ከኃላፊነት የተነሱት ሰዎች ከአሁን በፊት የተመደቡት በስብሰባ አይደለም፤ ከስራ ቦታ ሲነሱም በስብሰባ አይሆንም። በስብሰባ እገሌን መድቡት እገሌን ደግሞ አቆዩት ማለት ትክክል አይደለም።

ሹመት በሚገባቸው ቦታዎች ላይ ሰዎች ይሾማሉ ከስራ ምድብ ማንሳት በሚያስፈልግበት ጊዜ ደግሞ ይነሳሉ። ከዚህ ውጭ ያለው ስክነትና ማስተዋል የጎደለበት ጩኸት ነው። "

የዚህ መረጃ ባለቤት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ መሆኑን እንገልፃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ድሬዳዋ 🔹" የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን  አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የለውም " - ቤተክርስቲያን 🔸" ቦታውን ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " - የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤት የድሬደዋ መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ቤተክርስቲያኗ ካለችበት ቦታ እንድትነሳ የሚል ደብዳቤ…
የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጉዳይ መፍትሄ አግኝቷል ?

ዛሬ የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናንን ወቅታዊ ሁኔታ በመሚመለከት በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መግለጫ ሰጥታለች።

በዚህም መግለጫ ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ፤ የድሬዳዋ ማህበረ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን ህንጻና ሌሎች ተያያዥ ህንጻዎች ያሉበትን ይዞታ ለሌላ አገልግሎት ለማዋል በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የተላለፈው ውሳኔ ቤተ ክርሰቲያኗን ብቻ ሳይሆን መላውን ህዝበ ምዕመን በእጅጉ ማስደንገጡ ተገልጿል።

ይህ ውሳኔ እንደገና እንዲጤን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር ብርቱ ክትትል በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ተመላክቷል።

የከተማው አስተዳደርም በተለይም ከንቲባው ሁኔታውን በጥንቃቄና በሃላፊነት ስሜት እየተከታተሉ ሲሆን ከቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ጋርም ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸው በመግለጫው ላይ ተመላክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጉዳዩ የማይመለከተውና በየትኛም መንገድ ድርሻ የሌለው አንድ አካል፤ ችግሩ መፍትሔ እንዳገኘ አድርጎ በዛሬው ዕለት በራሱ ማህበራዊ ገጽ (Facebook) የተሳሳተ መረጃ አውጥቷል ብሏል የቤተክርስቲያንኒቱ መግለጫ።

ስም ያልጠቀሰው መግለጫው ይኸው አካል ይህንን ስህተት በአስቸኳይ እንዲያርም ጥብቅ ማሳሰቢያ የደረሰው መሆኑን ገልጿል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ እስከምታውቀው ድረስ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ምንም ዓይነት ውሳኔ ያልተሠጠ መሆኑንና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ አሠራር ኦፊሴላዊ መረጃ እስከምትሰጥ ድረስ ህዝበ ምዕመኑ በትዕግስትና በጸሎት እንዲጠባበቅ አሳስባለች።

@tikvahethiopia
ብርቱ አጋር!!
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123

#globalbankethiopia #GBE #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian #digitalbanking #Globaldigital
#ምደባ

ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማብራሪያ ፦

- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።

- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፤ በነዚህ ውስጥ ይመደባሉ።

- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል።

- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ መደረጉ ተገልጿል።

- የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን እንደሚያግፅ ተነላክቷል። ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል።

- የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት  ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር እንደሚያግዝ ተገልጿል።

- የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው ተብሏል። በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡

-  በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል።

- በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል።

- የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል።

ትምህርት ሚኒስቴር ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ  የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን አሳስቧል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SafaricomEthiopia

ቡና በምንገባበዝበት ብር የሳፋሪኮምን 4GB YouTube ጥቅል ገዝተን 200ደቂቃ ሙሉ ባልተገደበ የኢንተርኔት ፍጥነት በአዝናኝ ቪዲዮዎች ፈታ እንበል። ዛሬውኑ ወደ *777# በመደወል ጥቅሉን እንግዛ።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
መምህራን ምን አሉ ?

• " የመምህራን ደመወዝ ይቆረጣል የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ አሳማኝ አይደለም "

• " የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች አይልኩም "

• " አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው ይጠብቃሉ፤ ግማሽ ደመወዝ ብቻ የሚከፈልበት ጊዜም አለ "


የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ መምህራን ደመወዝ ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱ ተገልጿል።

የማኅበሩ ጉባዔ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ ከኦሮሚያ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ከሲዳማና ከሌሎቸም ክልሎች መምህራን ደመወዛቸው ያላግባብ እንደሚቆረጥ በስፋት መነሳቱን በስብሰባው የተሳተፉ የማኅበሩ አመራሮች ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አማኑኤል ጳውሎስ እንደገለጹት፣ በክልሉ እስከ 60 በመቶ የሚደርስ የመምህራን ደመወዝ እንደሚቆረጥና ለዚህም የሚሰጠው ምክንያት አሳማኝ አይደለም ብለዋል።

የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች እንደማይልኩ፣ በጀቱ ለማዳበሪያ ክፍያ ዋለ በሚል ወደ መምህራን ሳይደረስ እንደሚቀር መምህራን መናገራቸው ተሰምቷል፡፡

አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው እንደሚጠብቁና ግማሽ ደመወዝ ብቻ እንደሚከፈላቸውም ተነግሯል፡፡

መንግሥት በአንድ በኩል ስለትምህርት ጥራት እየተናገረ፣ በሌላ በኩል የመምህራን ደመወዝ እንደማይከፈል፣ የደረጃ ዕድገትና የትምህርት ማሻሻያ እንደማይደረግ በጉባዔው ላይ መነጋገሪያ ነበር ተብሏል፡፡

የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንዳሉት፣ በክልሉ በርካታ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው መምህራን ውስን መሆናቸውን፣ የበጀት እጥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ያጠቃቸው መምህራን በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚከናወን ሥራ ከ2017 ዓ.ም. በጀት መበደራቸው ተገልጿል፡፡

ማኅበሩ በጅግጅጋ ባከሄደው ወይይት የመምህራኑ ጉዳዩ በስፋት መነሳቱ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ለዚህ ችግር ክልሎች ጉዳዩን በባለቤትነት ወስደው መፍትሔ እንዲፈልጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) መናገራቸውን፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ከሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይትም ማኅበሩ ከዚህ ቀደም በደብዳቤና በሪፖርት መልክ ሲያቀርባቸው የነበሩ ጥያቄዎችን፣ የትምህርት ሚኒስትሩን በአካል በማግኘት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይሩ የሚችሉ ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ብለዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች የሚገኙ መምህራን በጉባዔው የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻል ለመንግሥት ጥያቄ አቅርበው ሚኒስትሩ እንደ ሁኔታው እየታየ ወደፊት የመምህራኑን ሕይወት ሊቀይር የሚችል ሥራ ይከናወናል ማለታቸውን ዮሐንስ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በመድረኩ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ከአፋር ክልል ተፈናቅለው ወደ ትግራይ ክልል የሄዱ 500 መምህራን ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ምክክር ተደርጎበታል ብለዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም. ክረምት ተቋርጦ የነበረው የመምህራን የክረምት ትምህርት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ጉባዔውን በተመለከተ ሚኒስትሩን ጠቅሶ በድረ ገጹ እንዳሠፈረው፣ አገሪቱ አሁን ላለችበት አገራዊ ችግር የትምህርት ሥርዓት መውደቁ ምክንያት በመሆኑ፣ የመምህራን ማኅበር ችግሩን ተነጋግሮ መፍታት እንዳለበትና ማኅበሩ የሙያውን ክብር ለመመለስ ከኅብረተሰቡ ጋር ወይይት በማድረግ ተጠያቂነት እንዲሰፍን እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia