#ድሬዳዋ
🔹" የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የለውም " - ቤተክርስቲያን
🔸" ቦታውን ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " - የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤት
የድሬደዋ መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ቤተክርስቲያኗ ካለችበት ቦታ እንድትነሳ የሚል ደብዳቤ እንደላከላት አስታውቃለች።
ቤተክርስቲያኗ የከተማው አስተዳደር ውሳኔውን በ2 ቀን ውስጥ እንዲያስተካክል ጠይቃለች።
ቤተክርስቲያኗ ፤ ለ40 አመታት በስፍራው የቆየች እና ህጋዊ ይዞታ እንዳላት የገለፀች ሲሆን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ግን ለሆቴል ስራ በሚል በአንድ ወር ውስጥ ከቦታው እንድትነሳ ደብዳቤ መላኩን አስረድታለች።
የቤተክርስቲያኗ ዋና ሰብሳቢ ቄስ በላቸው አምባሮ ፤ " የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ለቤትክረስቲያኗ በላከው ደብደቤ እንዳስቀመጠው ቦታው ለሆቴል ቱሪዝም መፈለጉን የሚገልፅ ነው " ብለዋል።
ነገር ግን የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የሌለው እና በምዕመን መካከል ሁከትን መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
" ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያኗ ለከተማዋ መንገድ ስራ በሚል ተባበሪ በመሆን የተወሰኑ ሜትሮችን ወደ ውስጥ ተጠግታለች " ያሉት ቄስ በላቸው፣ " ይህ ግን በህልውናዋ ላይ የመጣ ነው " ብለዋል፡፡
ስለሆነም የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ካቢኔ የወሰነውን ውሳኔ በሁለት ቀን ውስጥ እንዲያስተካክል የጠየቁ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ቤተክርስቲያኗ ሌሎች ህጋዊ አማራጮችን እንደምትጠቀም አስገንዝበዋል።
የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጸህፈት ቤት በበኩሉ ቤተክርስቲያኗ እንድትናሳ ካቢኔው ወስኖ ለቤተክርስቲያኗ ደብዳቤ መላኩን አረጋግጧል።
የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ፤ " ቦታው ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " ብለዋል።
ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ ጉዳዩን ተቃውማ ደብዳቤ ከመላክ ውጭ ከጽ/ቤቱ ጋር አልተነጋገረችም ያሉ ሲሆን ሁሉም ነገር የሚፈታው በንግግር ነው ብለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የሀገር_ውስጥ_ተፈናቃዮች_የሰብአዊ_መብቶች_ሁኔታ_ዓመታዊ_ሪፖርት.pdf
#ትግራይ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት " ኃላፊነት የጎደለው ነው " በማለት እንደማይቀበለው አስታወቀ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ " የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈናቃዮች አስመልክቶ ባወጣው ሁለተኛው ዘገባ የፌደራል መንግስት ባደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ተጋሩ በብዛት ወደ ቄያቸው እንደተመለሱ፤ ሰብአዊ ድጋፍም እየቀረበላቸው እንደሆነ አስመስሎ ይፋዊ ዘገባ አውጥቷል " ሲል ገልጿል።
" በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጋሩ ከቄያቸው ተፈናቅለው በከፋ ሁኔታ በሚገኙበት ወቅት ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ በማለት ሌተ ተቀን ቢወተውትም የወገኖቻችን መመለስ በሚመለከት አንዳች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባልተደረገበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደለው ዘገባ ማውጣቱ ፤ ከአሁን በፊት በትግራይ ህዝብ ላይ ሲያደርስ የነበረውን በደል የሚያስቀጥል " ነው ብሏል።
ሪፖርቱ " በትግራይ ህዝብ ስቃይ መቀለድ ነው " ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ሆን ብሎ የዓለም ማህበረሰብ ለማሳሳት ያዘጋጀው ቅጥፈት ስለሆነ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።
የፌደራል መንግስት ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደላቸው ዘገባዎች ሆነ ተብሎ በመዋቅሩ ሲለቀቁ የሰላም ሂደቱ የሚያውኩ ፣ መተማመን የሚያጎድሉ መሆናቸው ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢ እርምጃ ወስዶ እንዲያርም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥሪ ማቅረቡን በመቐለ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከላይ ያለውን መግለጫ ካወጣው በኃላ አጭር መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሰራጭቷል።
ኮሚሽኑ " በተፈናቃዮች 2ኛ ዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው የጂኦግራፊ ወሰኑ ትግራይን አልሸፈነም ይህም በዝግጅቱ ወቅት ተደራሽ ስላልነበረ መሆኑን እናረጋግጣለን " ብሏል። ኮሚሽኑ የተሳሳተ መረጃን ለማረም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ (IRA) ጋር መተባበሩን እንደሚቀጥል አመልክቷል።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
በማማፔይስ መተግበሪያ ቪዛ ወይም ማስተር ካርድዎን ተጠቅመው ገንዘብ በነፃ ወደ ኢትዮጵያ ይላኩ፡፡
የሞባይል መተግበሪያውን ከ Play Store በማውረድ ይጠቀሙ።
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.mamapays&hl=en&gl=US
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth
#mamapays #visa #mastercard #የሁሉም_ምርጫ

#Sidama #Hawassa #Motor
በሀዋሳ ከተማ ከሞተር ሳይክል የታርጋ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ክፍል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአንፃሩ የሞተር ባለቤቶች ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ ታርጋ የላቹም ብሎ ያሳድደናል " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።
አንዳንዶች ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ክልል ታርጋ ወደ ሲዳማ ታርጋ መቀየር አለበት በሚል የመያዝና የማንገላታት ነገርም አለ ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ፤ ህብረተሰቡ ህጋዊ ታርጋ በማዉጣት ህጋዊ ይሆን ዘንድ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ኢንስፔክተር ተስፋዬ አክለውም፤ " የደቡብ ታርጋ አየተያዘ ነዉ " የሚባለዉ #ስህተት መሆኑን በመግለጽ ማንም በነጻነት ማሽከርከር እንደሚችል ገልጸዋል።
" በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሞተሮች ካሉ ስህተት ነው፤ ይለቀቃሉ። የደቡብ ክልል ታርጋ እስካልሸጠ እስካለወጠ ድረስ ችግር የለውም " ሲሉ አረጋግጠዋል።
ከአዲስ ታርጋ ጋር በተያያዘ በጹሑፍ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ አባላት ታርጋ የላቹም ብለው ያሳድዱናል። እኔ በግሌ 2% ግብር ከከፈልኩ ወራቶች ተቆጥረዋል ነገር ግን ታርጋ ማግኘት አልቻልኩም የሚመለከተው አካል መፍትኤ ይስጠን፤ ትራፊክ ፓሊስ አባላት እያንገላቱን ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ይህንን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳንቾ ችግሩ መኖሩን በማመን ችግሩ ከሀገራዊ የዶላር ችግር ጋር ተያይዞ የመጣ (ለታርጋ ማሳተሚያ) መሆኑን አንስተዋል።
" አሁን ላይ ህትመቱ በማለቁ በሚቀጥለዉ ሳምንት ይሰጣል " ብለዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ታርጋ ያልደረሳቸዉ አሸከርካሪዎች ሪሲት በማሳየት እንዲንቀሳቀሱ የተያዙትም እንዲለቀቁ ከከተማዉ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዉናል።
መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

#እገታ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው። በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን…
#እገታ
ከ3 ሳምንት በፊት መስከረም 20/2016 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከባቱ ከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱት 6 ሰዎች ውስጥ 3ቱ ቢለቀቁም ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ እስካሁን እንደታገቱ ናቸው።
ከዚህ ቀደም ስማቸው ይፋ እድንዳይሆን ጠይቀው መረጃ የሰጡ የፕሮጀክቱ ሰራተኛ ታጋቾቹ እያንዳንዳቸው በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተጠየቀባቸው / በድምሩ የተጠየቀው 60 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረው ነበር።
ከታጋቾቹ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ፤ ታጋቾቹን የማስለቀቅ ጥረት መቀጠሉን በማስረዳት እስካሁን 3ቱን ማስለቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።
" ግማሾቹ ተለቀዋል፡፡ የተቀሩትንም ለማስለቀቅ ጥረቶች ቀጥለዋል " ያሉት አቶ ሞገስ ተለቀዋል የተባሉ 3ቱ ሰራተኞች በምን አይነት መንገድ እንደተለቀቁና የተቀሩት 3ቱ ደግሞ ለምን ሳይለቀቁ ቀሩ የሚለውን ጥያቄ ለታጋቾቹ ደህንነት በሚል ሳያብራሩት ቀርተዋል፡፡
ከእገታ ነፃ ከወጡት ውስጥ አንደኛው #ኬንያዊ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እንዲሁም የታጋች ቤተሰቦች እገታውንና የተለቀቁትን ታጋቾች በተመለከተ " ለደህንነታችን መልካም አይደለም " በማለት ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት አልፈለጉም።
ፌዴራል ፖሊስ ስለ ተስፋፋው የ #እገታ ተግባር ምን ይላል ? እገታን ለማስቀረት መንግሥት ምን እየሰራ ነው ?
የፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ አቶ ጄኢላን አብዲ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከል ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ያሻዋል ብለዋል።
" እገታን ሰራዊት በማዘዝና ኮማንድ በመስጠት ሙሉ በሙሉ የምንከላከለው አይደለም፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ተደብቀው እንደዚህ አይነት ድርጊት ሚፈጽሙ አካላት አሉ፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።
" ህዝብ ጋር ተባብረን መረጃ ስንቀበል አስቀድመን ያስቀረነውም ሆነ ያስለቀቅናቸው እገታዎች አሉ፡፡ " ያለቱ አቶ ጄይላን " ህብረተሰቡ ነው መጠቆም ያለበት እደዚህ አይነት ነገሮችን፡፡ " ብለዋል።
° ህብረተሰቡ ጥቆማዎችን በሚሰጥበት ወቅት ከአጋቾች ለሚደርስበት ጥቃት ምን ያህል የማምለጥ ዋስትና ይኖረዋል ? የጸጥታ ኃይሉ በፍጥነት የመድረስ ሁኔታ ላይ ጥያቄ አይነሳም ወይ ? የተባሉት የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ፦
" ከህብረተሰቡ ራሱ ጥንቃቄ የጎደሉ አካሄዶች ይስተዋላሉ፡፡
ለምሳሌ መሬት ትገዛለህ ይህን ያህል ብር ይዘህ ና ተብለው የታገቱ አሉ፡፡ እገታ ድንገት በአጋቾች የሚፈጸም እንደመሆኑም እያንዳንዱን ነገር መከላከል አዳጋች ነው፡፡
እገታ ደግሞ ሳይጠበቅ ቶሎ የሚፈጸም ተግባር ስለሆነ ቶሎ ለመቆጣጠር አመቺ አይደለም፡፡ " ሲሉ መልሰዋል።
አቶ ጀኢላን ፤ ፖሊስ ጥቆማ ከደረሰው ቶሎ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራ በመድረስ እርምጃ ለመውሰድ ሚያስችል የተሸለ ቴክኖሎጂ አለው ያሉ ሲሆን በየስፍራው ፖሊሶችም እንዲኖሩ የሚያስችል የቁጥጥር ስርኣት መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡
አሁን አሁን በአደንዳዥ እፆች የሚደገፍ የእገታ ወንጀል በተለይ #በከተሞች መበራከታቸውንም ያስገነዘቡት አቶ ጀኢላን " ወንጀሉ ከተፈጸመም በኋላ በርካታ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
እገታ በሚፈጸምበት ጊዜ ፖሊስ የራሱ ወታደራዊ ስልት የሚጠቀም ይሆናል እንጂ ከአጋጆች ጋር በምንም አይደራደርም ያሉ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ተግባር ላይ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ / ዶቼ ቨለ ነው።

Photo
#Update
ኢሰመኮ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር መነጋገሩን ዛሬ በላከልን መግለጫ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥቅምት 9/2016 ዓ/ም ይፋ ያደረገውን ሁለተኛውን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በሚመለከት ትላንት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።
በዚሁ መግለጭ ፤ የኮሚሽኑ ሪፖርት በጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በብዛት ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው እንደተመለሱ እና ሰብአዊ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንደሆነ ተደርጎ የተገለጸው ስሕተት ስለሆነ ሊስተካከል ይገባል ተብሏል።
ይህ ተከትሎ ኢሰመኮ ወዲያውኑ በሰጠው አጭር ማብራሪያ ሪፖርቱ ይህንን መሰል መረጃ እንደማያካትት፣ የሪፖርቱ አካባቢያዊ ወሰን የትግራይ ክልልን እንደማይጨምር በሪፖርቱ የተገለጸ መሆኑንና በተሳሳተ አረዳድ ስለተሰራጨው የተሳሳተ መረጃና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር እንደሚነጋገር ይፋ አድርጓል።
በዚሁ መሰረት ፤ ኮሚሽኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር የተነጋገረ ሲሆን፣ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ሁኔታ ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜና ፦
- አፋር፣
- አማራ፣
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣
- ኦሮሚያ፣
- ደቡብ ኢትዮጵያ፣
- ማእከላዊ ኢትዮጵያ፣
- ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ክልሎች የሚሸፍን መሆኑን አስረድቷል።
ስለሆነም የትግራይ ክልል በሪፖርቱ የተሸፈነ አለመሆኑን በድጋሚ ለማስረዳትና ለማሳወቅ ተችሏል ሲል ኮሚሽኑ በላከልን መግለጫ ገልጿል።
የትግራይ ክልል በዚህ የጊዜ ወሰን ሊካተትበት ያልቻለበት ምክንያት ሪፖርቱ በተጠናቀረበት ወቅት ክልሉ በጦርነት ሳቢያ ተደራሽ ስላልነበር፣ እንዲሁም የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ የሚሸፍን ሌላ የክትትል ሥራ እየተካሄደ በመሆኑ እና ከዚህ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች መሆኑ ተመላክቷል።
(ከኢሰመኮ የተላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር መግለጫ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82525?single
የኢሰመኮ ሁለተኛው ዓመታዊ ሪፖርት በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82424

#MoE
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ከሚማሩት ትምህርት ውጪ ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሔደው ለሚያደርጓቸው የተግባር ላይ ልምምዶች የሚደረግ ወጪ÷ ከምርቃት በኋላ በሚከፍሉት የወጪ መጋራት ውስጥ እንዲካተት ጥናት መጀመሩ ተገለጸ፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወጪ መጋራት (Cost Sharing) መመርያ መሠረት ወደ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀላቀሉ አዳዲስ ተማሪዎች÷ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ተመርቀው እስኪወጡ ድረስ፣ መንግሥት ለምግብና ለመኝታ ያወጣውን ወጪ በሚገቡት ውል መሠረት ከምርቃት በኋላ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተደንግጓል፡፡
ተማሪዎች ወደ ተግባር ልምምድ ሲወጡ ለሚቆዩባቸው ጊዜያት ለሚኖራቸው የተግባር ላይ ትምህርት፣ ከምረቃ በኋላ ከወጪ መጋራት ጋር ተደምሮ እንዲከፍሉ ለማድረግ የትምህርት ሚኒስቴር ዕቅድ መያዙንና ጥናት መጀመሩን፣ በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ተሾመ ዳንኤል ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
ሐሳቡ በጥናት ላይ መሆኑንና ዓላማውም ወደፊት ተማሪዎች የተግባር ላይ ልምምድን ትኩረት ሰጥተው እንዲማሩ ለማድረግ በማሰብ የታቀደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ለክፍያው የልማት አጋር ድርጅቶች ለትምህርት ተቋማትና ኢንዱስትሪዎች ትስስር የሚመድቡት ገንዘብ ስለሚኖር፣ ከዚህ ገንዘብ ለወጪ መጋራት ሊከፈል የሚችልበት አሠራርም ሊዘረጋ እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡
መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።
@tikvahuniversity

#Amhara #Oromia
ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ "የታሰበው በጸጥታ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ከክልላችን ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሦ የማቋቋም ሥራ ነው" ብለዋል።
አክለውም፣ "በጸጥታ ምክንያት ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ አብይ ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ መሪ ዕቅዱን ያወጣል" ሲሉ አስረድተዋል።
የአማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው፣ "ሁለታችን ተቀናጅተን ለመስራት የሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በዛ መሰረት ታይም ቴብሉን እናስቀምጣለን መቼ ይመለሱ? መቼ ወደዛ እናጓጉዝ? የሚለው በቅዳችን ነው የሚመለሰው" ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ_ወረዳ ከአሥር በላይ ቀበሌዎች፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ታጣቂ ቡድኑ በንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹ፣ ይህ በእንዲህ እንያለ ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቧል።
አቶ ወንድወሰን ለዚሁ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን መገድ ሁለታችንም አንሰራም" ብለዋል።
አክለውም፣ " ሰሜን ሸዋ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ወጣ ገባ የሚል ነው እናተም እደምታውቁት አማራ ክልልም የጸጥታ ችግር አለ። ይህን በዘላቂ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን ነው የምናስበው፣። ሆሮ ጉድሩ ያለውም ቢሆን አሸባሪው ሸኔ ወጣ ገባ እያለ ችግር ሊፈጥር ይችላል " ብለው፣ በቅድሚያ የጸጥታውን ችግር የምረጋግጥ ሥር እንደሚከናወን አስረድተዋል።
አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " የጸጥታው ችግር በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች የማስፈሩም መልሶ የማቋቋሙም ሥራ ይሰራል። የጸጥታ ችግር ያልተረጋገጠበት አካባቢዎች ደግሞ እያረጋገጥን ነው መልሰን የምናቋቁመው፣ ዛሬ መልሰን ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን ነው የሚሰራው " ሲሉ ተናግረዋል።
የሁለቱም ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ከመመለስ በፊት ይህን ሥራ ለማስኬድ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ መረጃዎችን ያጠራል።
ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-27