TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
የእስራኤልና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ዛሬም መቀጠሉ ተነግሯል። ጦርነቱ ሰፍቶ ሌሎች ኃይሎችም እንዳይጨመሩ ስጋቶች ከቀን ወደ ቀን እያየሉ ነው።
ጥቂት አጭር መረጃዎች ፦
- እስራኤል የሰብዓዊ እርዳታ በግብፅ እና ጋዛ ድንበር በኩል ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዲገባ ፈቅዳለች ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ቢዘገብም የእስራኤል ጦር " የተኩስ አቁም የሚባል ነገር የለም ፤ መሻገሪያዎቹም እንደተዘጉ ናቸው ከወንጀለኛው ሃማስ ጋር መዋጋታችንን እና ማጥቃታችንን እንቀጥላለን። ጋዛ የትግላችን ማዕከል ናት የታገቱ እስራኤላውያንን ይዛለች " ብሏል።
- " ሃማስ የፍልጤምን ህዝብ አይወክልም " ያሉት የፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ " በሁለቱም በኩል በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈፀመውን ግድያ እቃወማለሁ ፤ በሁለቱም በኩል የታገቱ እና የታሰሩ እስረኞች ሊለቀቁ ይገባል " ብለዋል።
- ኢራን በጋዛ ውስጥ ላለው ጦርነት የፖለቲካ መፍትሄዎች የሚያገኝበት ጊዜ እያለቀ ነው ስትል አስጠንቅቃለች። ኢራን የጦርነቱ መስፋፋት ወደማይቀርበት ደረጃ መቃረቡን አመልክታለች።
- የእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ፤ " ግባችን ድል ማድረግና እና ሀማስን ማስወገድ ነው " ብለዋል። " ኢራንን እና ለሂዝቦላህን ተጠንቀቁ " ብለዋቸዋል። " ለቤተሰቦቻችን ግዴታ አለብን " ያሉት ኔታንያሁ " የታገቱትን ሰዎችን እስክንመልስ ድረስ አንታክትም።" ብለዋል።
- ሃማስ ያገታቸውን ሰዎች ለመልቀቅ እስራኤል ውስጥ የታሰሩ 6000 እስረኞች እንዲለቀቁ መጠየቁ ተዘግቧል። ሃማስ አሁን ላይ ከ200 - 250 የሚደርሱ ታጋቾችን መያዙን አመልክቷል። 22 የእስራኤል ታጋቾች በእስራኤል የአየር ጥቃት ተገድለዋል ሲል ገልጿል።
- የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን ለተወሰኑ የአሜሪካ ወታደሮች እስራኤል በምትፈልጋቸው ጊዜ " ለመሰማራት ዝግጁ ሁኑ " የሚል ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፎክስ ኒውስ አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው ወደ 2,000 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች ተመርጠዋል ፤ ነገር ግን ይህ ቁጥር አልተረጋገጠም ተብሏል።
ተጨማሪ መረጃዎች፦ https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
Via @BirlikEthiopia
@tikvahethiopia

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
ስልክዎን በመጠቀም ብቻ እንዴት የአፖሎ ዲጂታል አካውንት መክፈት እንደሚችሉ ለማወቅ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
የቴሌግራም ቻነላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/BoAEth/1018
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #howto #howtovideo #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#ኢትዮጵያ #ቻይና የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ቻይና አቅንተው በቻይና ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ናቸው። ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በወጣ መረጃ የቻይናው ጠ/ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በኃላም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል። በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የምጣኔ ኃብት ትብብር ግንኙነት ማጠናከሪያ መንገዶች ላይ መክረዋል ተብሏል። ከሁለትዮሽ…
#UPDATE
ቻይና የሚገኙት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር በመሆን ከቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ ፤ በኢትዮጵያ #ብሪክስን መቀላቀል ሁነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩን " እንኳን ደስ ያለዎ " ብለዋቸዋል።
የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነትም ከሁሉን አቀፍ ፅኑ ግንኙነት ወደ ሁኔታ የማይፈታው ስልታዊ ትብብር እና ወዳጅነት (All Weather Strategic Cooperation Partnership) ደረጃ ከፍ ማለቱን በይፋ አብስረዋል።
ፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አድንቀው ከቻይናው አረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ጋር ተናባቢ በመሆኑ የግሪን ቤልት እና ሮድ አካል ሆኖ ሊደገፍ እንደሚችል አረጋግጠዋል ተብሏል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፤ የቻይና ኢንቬስትመንት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እመርታ የሚኖረውን አስተዋፅዖ ያነሱ ሲሆን በተለይም በ5ቱ ቁልፍ ምሰሶዎች፦
- በግብርና
- ማኑፋክቸሪንግ
- አይሲቲ
- ማእድን ልማት እና ቱሪዝም #ተጨማሪ ኢንቬስትመንት እንዲኖር የማበረታቻ ጥሪ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት መረጃ ያሳያል።

የሩስያ ፕሬዜዳንት ፑቲን ቻይና ገብተዋል።
ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና የስራ ጉብኝት ለማድረግ እንዲሁም " የቤልት ኤንድ ሮድ " ዓለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል።
በሁለት ቀን የቻይና ቆይታቸው ወቅት ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት እና ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።
ፑቲን በተለይ ሀገራቸው ከ #ዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ እምብዛም ከሀገር ሲወጡ እንዳልነበር ይታወቃል።

" እውነቱን ለመናገር ነዋሪዎቹ እርቧቸዋል። እያለቀሱ ነው የተናገሩት። ድረሱልን እያሉ ነው " - አቶ ምሕረት መላኩ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የአማራ ክልል መንግሥት ድርቅ በተከሰተባቸው ቦታዎች የዕለት ድጋፍ ለማድረስ ቢስማማም በጸጥታ ችግር መድረስ እንዳልቻለ ገልጸዋል። ኃላፊው ከ1.2…
#አማራ
• " ከ13,000 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው " - የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት
• " በሰሃላ ወረዳ 94 በመቶ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች፣ 45 በመቶ ከአምስት ዓመት በታች ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል " - የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በአበርገሌና ፃግብጅ ወረዳዎች ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ ተፈናቅለው ከነበሩ ከ79,000 በላይ ነዋሪዎች መካከል እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) ወደየቄያቸው መመለስ ያልቻሉ ሰዎች በከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መምሪያ ጽሕፈት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዞኑ አደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዝናሽ ወርቁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ከ13,000 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው " ብለዋል።
ተፈናቃዮቹ ወደቤታቸው ያልተመለሱበትን ምክንያት ሲያብራሩም ወ/ሮ ዝናሽ፣ " በፃግብጅ ወረዳ 5፣ በአበርገሌ ወረዳ 12 ቀበሌዎች ከሕወሓት ታጣቂዎች ነጻ ስላልወጡ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም፣ በዚህም ምክንያት በአበርገሌ ወረዳ 5,087፣ በፃግብጅ ወረዳ 8,233 ተፈንቃዮች በዞኑ ዋና ከተማ በኅብረተሰቡ ተጠልለው እንደሚገኙ አስረድተው፣ " ወይ ሰላም ሆኖ ወደ ቤታቸው አልገቡ ወይ ድጋፍ እየተደረገ በመጠለያ ጣቢያ በመንግሥት ውስጥ አልሆኑም፣ ችግራቸውን ሙሉ ለሙሉ ቀርፈናል ብለን አናስብም። በሚያሳዝን ደረጃ ላይ ነው ያለት " ሲሉ ገልጸዋል።
በዞኑ የተከሰተው ድርቅ በተመለከተ ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም፣ ረሃቡ እየበረታባቸው መሆኑን፣ የጸጥታ ችግር፣ ድርቅ ባለባቸው ወረዳዎች ወረርሽኝ እንዳለም አስረድተዋል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሙሉዓለም ወንድሙ በበኩላቸው፣ " ድርቁ ያስከተለውን ጉዳት በተመለከተ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥናት እያጥኑ ነው " ብለዋል።
አክለውም፣ እስካሁን ባለው ጥናት ግኝት መሠረት ብቻ፣ " በሰሃላ ወረዳ 94 በመቶ ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች፣ 45 በመቶ ከአምስት ዓመት በታች ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተዋል " ብለዋል።
የሕጻናቱ በምግብ እጥረት መጎዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ በጥናት መረጋገጡን ሲያስረዱም አቶ ሙሉዓለም፣ " ቢያንስ የሚጠበቀው በጣም ከፍተኛ ቢሆን 15 በመቶ ነበር። ይሄ ግን 30 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ይህን የመሰለ አስከፊ ጉዳት ነው ያለው " ሲሉ ገልጸዋል።
" የጸጥታ ችግር ባለባቸው ወረዳዎችም የመድኃኒት እጥረት አለ " ያሉት ተወካዩ፣ " ከጎንደር የመድኃኒት አቅርቦት ድርጅት ነው መድኃኒት የሚቀርብ የነበረው፣ ካለው የጽጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ከድርቁ ጋር ለሚከሰቱ ወረርሽኞችም ሆነ ከድርቁ በፊት ለተከሰተው የወባ በሽታ ወረርሽኝ መድኃኒት መቅረብ አልቻለም " ብለዋል።
የተከዜ ድልድይ መሰበሩን ተከትሎ በሰሃላ ወረዳ ላሉ ሰዎች የምግብ ድጋፍ ማድረስም እንዳልተቻለ ገልጸው፣ " በሚገርም ሁኔታ እንደዚህ አይነት አስቸጋሪ ወረዳ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ብዬ አላስብም " ሲሉም ተናግረዋል።
በመጨረሻም፣ መንግሥት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#ትግራይ
በትግራይ የሃዘን ድንኳኖች እየፈረሱ ናቸው። የሃዘን ማቅ ለብሳ የሰነበተችው መቐለ ከተማ ወደ ቀደመው እንቅስቃሴ መመለስ ጀምራለች።
ባንኮች ጨምሮ የተዘጋጉ የንግድ ተቋማት ተከፍተዋል። ሰውና መኪና ተጠምተው የነበሩ መንገዶች መሙላት ጀምረዋል።
የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ በመቐለ ዓዲሓቂ የሰማእታት ሃውልት በተካሄደ " ይበቃል አንገታችን ለሃዘን አንደፋም " በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ማሳረግያ አግኝቷል።
በማሳረግያ ስነ-ሰርዓቱ መልእክት ያስተላለፉት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " አንባ ይብቃ ሃዘችን ተቋቁመን ሰማእታቱ የተውልን አደራ ለመፈፀም እንትጋ ፤ ትግራይ መለወጥ የሚችሉ ወድ የህዝብ ልጆች ከፍለናል ፤ የተከፈለው መስዋእት ውድ በመሆኑ የጋራ ስቃያችን ወደ የጋራ ድል ለመቀየር እየተነጋገርን እየተመካከርን መስራት አለብን " ብለዋል።
ፕረዚደንቱ በማከልም ፤ " ላጋጠመን ችግር መንስኤው ምንድን ነው ? ውስጣዊ ወይም ደግሞ ውጫዊ ? የሚለው ጥያቄ በሚገባ በመመለስ ተጠያቂነት በማረጋገጥ ችግሩ ለአንዴና ለመጨረሻ የማይደግምበት ሁኔታ መፈጠር አለብን ፤ የውስጥ የአመራር ድክመታችን በማረም በተከፈለው መስዋእትነት የሃሳብ ብዙህነት እንዲጎመራ ፤ ሰላማዊ የፓለቲካ ትግል ሰር እንዲሰድ ማስቻልና መሰል ለውጦች በማስፋት የተጀመረው ሰላም በማስፋትና በማጠናከር ህያው ሆኖ እንዲኖር መስራት ይጠበቅብናል " ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ከጎቤታችን ኤርትራ ጨምሮ ከአማራና ዓፋር ክልሎች በሰላምና በወንድማማችነት በመደጋገፍ ለመኖር እንፈልጋለን። በየ30 አመቱ ዋጋ እያስከፈለን ያለው የፓለቲካ አካሄድ ከምንጩ በመመርመር አይነተኛ ለውጥ ለማድረግ የምንገደድበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። " ሲሉ ተናግረዋል።
የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ በመወከል መልእክት ያስተላለፉት የመቐለ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አቡነ መርሃ ክርስቶስ " የፈሰሰው ደም የከፈልነው ህይወት ይብቃን ከአሁን በኃላ አንድነታችንና ክብራችን በማፅናት የተፈናቀሉት ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ መሪዎች ሰላማዊ የሆነ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ አለባችሁ " ብለዋል።
የሰማእታት ቤተሰብ ተወካይ ወ/ሮ ብርሃን ተካ በበኩላቸው ለህዝባቸው ክቡር መስዋእት የከፈሉ ልጆቻችን ህያው ሆኖው እንዲኖሩ ከተፈለገ ብቃት ባለው አመራር የሚመራ ጤነኛና አስተዋያይ የፓለቲካ ምህዳር ሲፈጠር ነው ፣ ስለሆነም መሪዎቻችን ከትናንት ስህተታችሁ በመማር ህደ ሰፊና ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት ማስቀረት የሚችል አቅም ማጎልበት አለባችሁ " ብለዋል።
በማሳረግያ ስነ-ሰርአቱ ለሰማእታት በጳጳሳትና በእስልምና ሃይማኖት ከፍተኛ አመራሮች የተመራ የፀሎተ ፍትሃትና የዱዓ ስነ-ሰርአት የተከናወነ ሲሆን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ዶብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጨምሮ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ኣመራሮች ፣ የሃይማኖት አባቶች ከሰባቱ የመቐለ ክፍለከተሞች የተውጣጡ የሰማእታት ቤተሰቦችና ነዋሪዎች በቦታው መገኘታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
መረጃው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
ተጨማሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትግርኛ ፦ @tikvahethiopiaTigrigna
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaTigrigna

በአዲሱ የ5G ኔትወርክ ያለገደብ🏃♂🏃♀
ያልተገደቡ ወርሃዊ የ5G ዳታ ጥቅሎችን ከ10%_ተጨማሪ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ ወይም በማይ ኢትዮቴል እና በ*999# በመግዛት የአዲሱን ትውልድ ኔትወርክ የኢንተርኔት ፍጥነት ያጣጥሙ!
በአዲስ አበባ የ5G አገልግሎት የሚያስጠቅም ስልክ ያላቸውን ደንበኞቻችንን አገልግሎት ወደ 5G አሳድገናል::
ለዝርዝር መረጃ: https://bit.ly/3RQ2McR
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ
#አዲስ_ዓመት_አዲስ_ፍጥነት_ምቾት_እና_አኗኗር
#5G

ዩኒሴፍ በ98 ሀገራት ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየውን የ U-Report ሥርዓት እያስተዋወቀ ነው።
ዩኒሴፍ፥ በኢትዮጵያ ወጣቶች በሚመለከታቸው ነገር ላይ እንዲሁም ማኅበረሰባቸውን በሚጠቅም ጉዳይ ላይ ድምጽ እንዲሆኑና እንዲሳተፉ የሚያስችል ሥርዓት መጀመሩን ገልጿል።
በ98 ሀገራት ላይ ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው ይህ ሥርዓት ወጣቶች በልማት ሥራዎች፣ በሰብዓዊ ተግባራት እንዲሁም በራሳቸው ጉዳዮች ላይ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉና ድምጻቸውን እንዲያሰሙ የሚያግዝ ነው።
በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ U-Report አስተባባሪ ሕይወት ገበየው ይህ ሥርዓት በኢትዮጵያ መተግበሩ፥ የወጣቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎን ከመጨመር በላይ ዓለም አቀፍ ተቋማትም የወጣቱን ሀሳብ ትኩረት ያደረገ ሥራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን ይገልጻሉ።
ይህ አዲስ የሚተገበረው የዩኒሴፍ U-Report ኢኒሽዬቲቭም በጅማሮው ከ200,000 በላይ ወጣቶችን በበጎፈቃደኝነት ለማሳተፍ አስቧል።
ወጣቱ ድምጹን ለማሰማት፣ ተጽዕኖ ለመፍጠርና ለማኅበረሰቡ ድምጽ ለመሆን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የጠየቁት አስተባባሪዋ ዩኒሴፍ የ U-Report መመዝገቢያ መንገዱን ለቲክቫህ ቤተሰቦች አስተዋውቀዋል።
በዚህም ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቦት(Bot) የተዘጋጀ ሲሆን @ureportethiopia_bot በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

#Update በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰው ግጭት ንጹሐን መገደላቸውንና ነዋሪዎችና ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። ሥሜ ባይጠቀስ ያሉ አንድ የቀቤና ልዩ ወረዳ ነዋሪ " ሰሞኑን ሁለት የቀቤና ወጣቶች ተገድለዋል " ብለዋል። ሌላኛው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ ደግሞ " አንድ የወልቂጤ ሰው በወጣቶች ተገድሏል " ሲሉ ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ…
#Update
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማና በቀቤና ልዩ ወረዳ 'በወሰን ይገባኛል' ጥያቄ የተነሳው ግጭት በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው ታማኝ ምንጭ፣ " ግጭቱ ወደ ገጠሩ የመዛመት ሁኔታ ነው የሚስተዋለው። ወልቂጤ ከተማ አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር የከፋ ነገር የለም " ብለዋል።
ወሸርቤ፣ ወልቂጤ ዙሪያ ግጭቱ መዛመት አዝማሚያ ያንዣበበባቸው የገጠር ቦታዎች መሆናቸውን አክለዋል።
ወሸርቤን ጨምሮ በወልቂጤ ገጠራማው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ የጸጥታ አካላት በወጣቶች ላይ ድብደባ እየፈጸሙ ነው ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የቀቤና ልዩ ወረዳ ምንጭ በበኩላችው፣ " ጥያቂያችን ይመለስ በማለት የሚሞግቱ ወጣቶች ለምን ይደበደባሉ ? ይህ ልክ አይደለም። ጉዳዩን በውይይት መፍታት ይሻላል " የሚል አጭር ቃል አስቀምጠዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወልቂጤ ከተማ ምንጭ ግጭቱ እንዴት ወደ ገጠሩ የመዛመት አዝማሚያ ተፈጠረ ምክንያቱ ምንድን ነው ? ብሎ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፣ " የጸጥታው ኃይል ችግር የፈጠሩ አካላትን አሳዶ መያዝ ሲጀምር ጥፋተኞቹ ለመደበቅ የመሸሽ ሁኔታዎች ይስተዋላል " ሲሉ አስረድተዋል።
በመንግሥት በኩል ግጭቱን ለማስቆም ያለውን እንቅስቃሴ በተለከተም፣ " የተሻለ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። ተጨማሪ የጸጥታ አካላት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው። በዚህ በአሰሳ በርካታ የጦር መሳርያዎች ገጀራ፣ ቆንጮራ በቁጥጥር ስር ውለዋል" ነው ያሉት ብለዋል።
ይሁን እንጅ ግጭቱ ሊቆም የሚችለው በሁለቱም ወገኖች ያሉ ጥያቄዎች መልስ ሲያገኙ እንደመሆኑ መጠን በመንግሥት በኩል እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) በተጨባጭ የጸጥታ ስራ ካልሆነ በስተቀር የፖለቲካ ስራው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም " ሲሉ አክለዋል።
በግጭቱ ምክንያት ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወልቂጤ በዩንቨርስቲና በዎሊሶ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑም ተመላክቷል።
በግጭቱ አንድ ፓሊስ ላይ ጉዳት መድረሱን፣ በሁለቱም ወገኖች ሦስት ሰዎች መገደላችውን መዘገባችን ይታወሳል።
መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።