TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል "
በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።
በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።
በአደጋው ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።
የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።
ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

ብርቱ አጋር!!
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅልጥፍ ያለ አስተማማኝ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ መቷል! ዛሬውኑ M-PESAን አውርደን እንጠቀም።
#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether
#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርዶጋን ምን አሉ ? የቱርክ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ዙሪያ ይህን ብለዋል ፦ - በሲቪሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ወይም በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ትክክል አይደለም፤ አንቀበለውም። - በእስራኤል ግዛት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንቃወማለን። - በጋዛ ውስጥ ንጹሃን ያለየ ' #ጭፍጨፋ ' በፍጹም አንቀበልም። - አሳፋሪ ዘዴዎችን…
#እስራኤል #ፍልስጤም
ዛሬ አንድ ሳምንቱን የያዘውና ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም የተባለው እጅግ ደም አፋሳሹ የእስራኤል እና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ቀጥሏል።
አጫጭር መረጃዎች ፦
- እስራኤል እየወሰደችው ባለው ጥቃት የሞቱ ፍልስጤናውያን ቁጥር 1,900 ደርሰዋል። ከሞቱት ውስጥ እጅግ በርከታ ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል። 7,696 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል።
- ሃማስ በሚፈፅመው ጥቃት በእስራኤል በኩል የሞቱ ሰዎች 1400 የደረሱ ሲሆን 3,418 ሰዎች ተጎድተዋል።
- በዌስት ባንክ ውስጥ 52 ሰዎች ሲገደሉ፣ 700 ተጎድተዋል።
- እስራኤል " ሃማስን እስከወዲያኛው አጠፋዋለሁ ፤ ላደረገው ድርጊትም ዋጋውን አስከፍለዋለው " እያለች ሲሆን አሁን ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ ገና መጀማሪያው እንዳሆነ ገልጻለች።
- እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ያሉ ሁሉም ሲቪሎች በሰዓታት ውስጥ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። በሰሜናዊ ጋዛ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ሀገራት እና ተቋማት እስራኤል ውሳኔዋን እንድታጥፍ እየጠየቁ ናቸው። እንደ ተመድ መረጃ በአስር ሺዎች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።
- በጋዛ ላይ የነዳጅ፣ የምግብ፣ የውሃ እገዳው አሁንም እንደቀጠለ ነው።
- ሐማስ እስራኤል ላይ አሁንም የሮኬቶች ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሏል።
- የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ የፍልስጤሙን " ሃማስ " በመደገፍ እንደሚሰለፍ አስታውቋል። ቡድኑ ጊዜው ሲደርስ ጦርነቱን ከሃማስ ጎን ሆኖ ለመሳተፍ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ባለፉት ቀናት በሊባኖስ በኩል አንዳንድ የግጭት ምልክቶች የታዩ ሲሆን እስራኤል ድንበሯን ጥሰው ሊገቡ ነበሩ ያለቻቸውን ሰዎች በድሮን መታ መግደሏ ተነግሯል።
- ሐማስ አግቶ ከወሰዳቸው ሰዎች ውስጥ 13 እስራኤላውያንን እና የውጭ አገራት ዜጎች እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለችው የአየር ጥቃቶች መገደላቸው አሳውቋል።
- የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ጦርነቱ ቀጠና ሄደው ከእስራኤል ጠ/ሚ እስራኤል ውስጥ፣ ከፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ሞሀሙድ አባስ ጋር ዮርዳኖስ ውስጥ ተገናኝተው መከረዋል። በኃላም ወደ አጋርናታችንን እናሳያለን ብለው ትላንት እስራኤልን ጎብኝተው ነበር። በኃላም ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተው ከሀገሪቱ አመራሮች ጋር ስለጦርነቱ መክረዋል።
- ጦርነቱ እንዲቆም እና መሄጃ ለጠፋባቸው ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ በተለያዩ ወገኖች ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
More @BirlikEthiopia
https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

#እንድታውቁት
" በዓለማችን በየ2 ደቂቃ ልዩነቱ በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ " - የዓለም ጤና ድርጅት
የማህፀን በር ካንሰር (Cervical Cancer) ፦
- የማህፀን በር ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ ካንሰሮች በገዳይነቱ በዓለም 4ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ 2ኛ ላይ ተቀምጧል::
- ይህ የካንሰር ዓይነት 99.7% መነሻው (Human papilloma virus) የተባለ ቫይረስ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በጾታዊ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ነው፡፡ ይህ የቫይረስ ዓይነት ከ200 በላይ ዓይነቶች ሲኖሩት የማህፀን በር ካንሰር የሚያመጡት ጥቂቶቹ ሲሆኑ HPV 16 እና HPV 18 የተባሉት ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡
- ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ፣ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች፣ ከአንድ ሰው በላይ ጋር ግንኙነት ሚያደርጉ እና የአባላዘር በሽታ ያለባቸው ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።
- ለብዙ ጊዜ ምልክት ሳያሳይ በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል፡፡
ምልክቶቹም-
▪️ከግንኙነት በዃላ በብልት በኩል መድማት
▪️የወር አበባ ካለቀ በዃላ እና በሁለት የወር አበባ ጊዜ መካከል ያለ መድማት
▪️በብልት በኩል ያልተለመደ ጠረን ያለው ፈሳሽ መዉጣት
▪️ከ Menopause (ማረጥ) በኋላ የሚኖር የማህፀን መድማት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- በዓለማችን በየ 2ደቂቃ ልዩነቱ በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ከ90 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደኛ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ ነው፡፡
- ይህንን ደግሞ ታዳጊ ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር ክትባትን በመከተብ እንዲሁም እድሜያችው 21 እና በላይ የሆኑ ሴቶች ቢያንስ በየ3 ዓመቱ ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡:
- ይህ በሽታ በአግባቡ በሚደረግ ቅድመ ምርመራ በጊዜ ከተገኘ በህክምና የመዳን አድሉ ከፍተኛ ነው።
▫️ስለዚህ ታዳጊ ሴቶችን ክትባቱን በማስከተብ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ በየ3 አመት ሚደረገውን ቅድመ ምርመራ በማድረግ በበሽታው ምክንያት የሚከሰት የጤና መጓደልን እና ሞትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡
#WHO #TikvahEthiopia

#ትግራይ " የሚቋረጥ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም ፤ ባንኮች ግን ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናሉ " - የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ም/ቤቱ በትግራይ ክልል ደረጃ የታወጀው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት አስመልክቶ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው የህክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት የማይቋረጥ ሲሆን የባንከ አገልግሎት ግን…
#ትግራይ
" በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ
በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።
ፕረዚደንቱ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በይፋ መታወጅ አስመልክተው ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ለክልሉ የመንግስት ፣ የግልና የውጭ ሚድያዎች ሰፊ ቃለ-መጠይቅና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ በተካሄደው ደም አፋሳሽና እልህ አስጨራሽ ጦርነት የተሰው ታጋዮች ቁጥር እንዲገልፁ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ " ... በትግሉ ስለተሰውት ታጋዮች ቁጥር ብዙ ተረት ነው የሚወራው ፤ የተሰውት ታጋዮች ቁጠር እንገልፃለን። ለጊዜው ግን መግለፁ አስፈላጊ ሆኖ ስላልታየን እናቆየዋለን " ብለዋል።
" ... ለትግራይ ህልውና የተከፈለ ዋጋ የሚመጥነው ደረጃና ዋጋ መስጠት አለብን ሲባል ለያንዳንዱ የተሰዋ ታጋይ ፤ ለያንዳንዱ የተሰዋበት ቤተሰብ የክብር የምስክር ወረቀት ልከናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " የተሰውት ታጋዮች ቁጥር በእጃችን ይገኛል። ከቁጥሩ ባሻገር ግን እጅግ ከባድና ውድ ዋጋ ከፍለናል። ለህልውናችን የተከፈለ በመሆኑም ግን የሚያስቆጨን አይሆንም ሊባል ይችላል " ሲሉ አክለዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ብዙ ልጆቻችን ከፍለናል። ጠላቶች (ፕሬዜዳንቱ ጠላቶች ያሏቸውን በስም አልገለጿቸውም) የኛ የመስዋእት ኪሳራ በማብዛት የነሱ ለማሳነስ እንደማነፃፀሪያ በማቅረብ ብዙ ይናገራሉ። በበኩሌ አሁን ካለው የተሰዋ ታጋይ ቁጥር ሩብ ፤ ከሩብ በታች ፤ አንድ መቶኛው እንኳን ብንከፍል ዋጋው ከባድ ነው የሚል እምነት አለኝ። " ብለዋል።
" አልተሳካልንም እንጂ ያለ አንድ ታጋይና ያለ አንድ ወጣት መስዋእት ፣ ራሳችን በራሳችን የማስተዳደር መብታችን የምናረጋግጥበት ዕድል ቢኖር እመርጥ ነበር " ሲሉ አክለዋል።
ፕሬዜዳንቱ በስም ያልጠሯቸውና " ጠላቶች " ሲሉ የጠሯቸው ኃይሎች " አሁን ላይ መጥራት በጀመሩት የተዛባና የተጋነነ ቁጥር በመደናገር ሌላው ያልሆነ ቁጥር ሲጠራ ቢውል ለኔ 20 ሺህ ተባለ ፣ 10 ሺህ ተባለ ፣ ህልውናችን ለማረጋገጥ አንድ ሰው ይሰዋ 20 ሺህ ዋጋው እጅግ ከባድ ነው " ብለዋል።
" በተሰውት ታጋዮች ዝርዝር ፦
- የዩኒቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች ፣
- ጥሩ አምራች አርሶ አደሮች
- ሃኪሞች ሁሉም አይነት የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። በአጠቃላይ ትግራይን በሰላም ጊዜ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ የማሸጋገር አቅም የነበራቸው በመስዋእትነት አጥተናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " ይህንን መስዋእትነት ዋጋ መስጠት እንዳለ ሆኖ ፤ ቁጥሩ ጠላት በሚለው ደረጃ እንዳልሆነ መረዳቱ ስጋታችን ቀንሶ ያረጋጋናል " ማለታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ሰነ-ሰርዓት ከጥቅምት 3 አስከ 5 በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ በመካሄድ ፤ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም " በሃዘን አንገታችን እንደፋም " በሚል መሪ ቃል በሚካሄድ የህዝብ ሰልፍ እንደሚጠቃለል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የተዘጋጀ ነው።

Don't miss out! You have 3 days to submit your application for the Jasiri Talent Investor program. If you're considering applying, now is the time to go to jasiri.org/application and get your application in before the deadline. #Jasiri4Africa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD: ይህን የ4 ደቂቃ መረጃ ዳሰሳ ጥናት በመሙላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የምንሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ መመርያ ያግዙ።
👉 https://09u34jhg43098.typeform.com/to/nToapX9c
(የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል)

#ወልቂጤ
- " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " - የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር
- " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " - የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን
- " ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " - የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፓስት
አዲስ በተዋቀረው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማና ቀቤና ልዩ ወረዳ መከከል በተቀሰቀሰ ግጭት በንጹሐን ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ነዋሪዎቹ በገለጹት መሠረት፣ ከጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት በንጹሐን ላይ ጉዳት ደርሷል፣ ቤት ተቃጥሏል ብለዋል።
ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ፣ እንደቆሰሉ፣ ተኩስ እንደቆመና እንዳልቆመ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረቡላቸው አንድ የአካባቢው ነዋሪ፣ " አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በጥይት ተመቶ ሞቷል። እኔ ባለኝ መረጃ መሠረት 25 በላይ ሲቭል ሰዎች ቆስለዋል። ከትላንት 7 ጀምሮ ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት ድረስ ተኩስ ነበር አሁን ቆማል " ብለዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸውና ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣን፣ " በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። ቤቶች ተቃጥለዋል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ግጭቱ በቀቤና ልዩ ወረዳና በወልቂጤ ከተማ የወሰን ይገባኛል ጥያቄን መሠረት በማድረጉ ከዚህ በፊትም አለመረጋጋት እንደነበር ገልጸው፣ አሁንም እንዳይባባስ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በጥምረት እየሰሩ ነው ብለዋል።
ተመሳሳይ ጥያቄ የቀረበላቸው የጉራጌ ዞን ፓሊስ ኮሚሽን ዋና ኢኒስፔክተር ገና በበኩላቹው፣ " በቦታው አድማ የመበተን ሥራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ኮማንድ ፖስት ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ጉዳያ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ፣ " በቀን 02 ቀን 2016 ዓ.ም በወልቂጤ ከተማ የተቀሰቀሰው አመጽ እንዲበርድ የጸጥታ ኃይላት በሆደ ሰፊነት ግጭቱ እንዲበርድ እና የሚደርሰው ቁሳዊና ሰብዓዊ ጉዳት ለመቀነስ በኃላፊነት ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል " ብሏል።
አክሎም ፣ " ይህን እንጅ ግጭቱ እንዲባባስ በሚፈልጉ አካላት ንብረት ወድሟል፣ በሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል " ሲል አስታውቋል።
" በዜጎች ላይ የሚደርሰው አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ለመቀነስ የዞኑ ኮማንድ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጣል ወስኗል " ያለው መግለጫው፣ " በመሆኑም ከዛሬ ጥቅምት 03/2016 ጀምሮ በተሽከርካሪዎች እና በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ገደብ ተጥሏል " ሲል አስገንዝቧል።
" በዚህ መሰረት የትኛውም ተሽከርካሪ ማለትም ፦
- ሞተር ሳይክል፣
- ባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ)፣
- አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ የህዝብ አመላላሽ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ሰዎች ላይ ከ11:00 እስከ ጠዋት 1:00 ድረስ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል " ብሏል።
መረጃው በአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

#ትግራይ " በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።…
" ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል " - ቅዱስነታቸው
ብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በትግራይ ክልል በተካሔደው ጦርነት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች እየተከናወነ ያለውን የኀዘን ሥነ ሥርዓት በማስመለክት አባታዊ የማጽናኛ መልእክት አስተላለፉ።
ከቅዱስነታቸው መልዕክት የተወሰደ ፦
" ዛሬ በትግራይ ክልል እየተዘከሩ ስላሉ ወገኖች በእጅጉ ማዘናችንን እንገልጣለን ።
ይህ እንዳይመጣ ብዙ ተማጽኖ ስናቀርብ የነበረ ቢሆንም ሽበት እና ክህነት የማይከበርበት ዘመን ላይ ደርሰን ለዚህ ኀዘን በቅተናል።
ዛሬ በትግራይ ክልል የማይለቀስበት ቤት የለም። የተሰዉት ልጆቻችን በሕይወተ ሥጋ ኖረው ቢሆን ብዙ ታሪክ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም እነዚህ የቤተሰብና የቤተ ክርስቲያን እንዲሁም የሀገር ተስፋዎች በእሸት በመቅረታቸው በኀዘን በተሰበረ ልብ ሁነን ለነፍሳቸው ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንዲሰጥልን እንጸልያለን።
በኀዘን የተጎዳችሁ አባቶችና እናቶችም ይህ ቢሆን ኖሮ እያላችሁ ራሳችሁን እንዳትጎዱ፤ የእናንተ መጎሳቆል የሞቱትን ቀና አያደርግምና ልባችሁን እንድታበረቱ እናሳስባለን ምክንያቱም መቃብር መጨረሻችን ያልሆነ የትንሣኤ ሕዝብ ነን፡፡
በምድር ላይ ስንኖር ማንም ለራሱ መከራን አያቅድምና የታቀዱ ቀኖችንም ለማለፍ ሕገ ተፈጥሮ አይፈቅድልንምና በሆነውና በሚሆነው ነገር ሁሉ ' እንደ ፈቃድህ ይሁን ' እያሉ ልብን ማሳረፍ ይገባል በማለት እንመክራለን፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#Update
በትግራይ የተለያዩ ከተሞች በጦርነቱ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የጥዋፍ ማብራት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በተለይም በክልሉ መዲና መቐለ ሰማዕታት ሃውልት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመቐለ ነዋሪ በተገኘበት ነው ስነስርዓቱ የተከናወነው።
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ከመቐለ፣ ዓዲግራት ፣ ማይጨው ፣ ሽረ እንዳስላሴ (በቴሌቪዥን ትግራይ)