TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በትግራይ ክልል " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት መታወጅ ተከትሎ ከቦታ ወደ ቦታ ለሚደረግ ጉዞ ከፍተኛ የትራንስፓርት እጥረት አጋጥሟል።

ያልተገባ የዋጋ ጭማሪም እየተደረገ ነው። 

የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክበር ቀን ስነ-ሰርአት ጥቅምት 2 ታውጆ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም እንደሚጠቃለልና ተዛማጅ ጉዳዮች አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተከታታይ ዘገባዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል።

የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል በመቐለ በሚገኙ ሁለቱ መነሃሪያዎች ያለውን ወቅታዊ የትራንስፓርት ሁኔታ ለመታዘብ ጥቅምት 1 እና 2  ከሌሊቱ 10:00 ሰአት ጀምሮ ቅኝት በማካሄድ ትዝብቱ አጋርተዋል።

ህዝቡ ወደየ አከባቢው በመሄድ የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ ለመሳተፍ ከሌሊቱ 10:00 ጀምሮ በሁለቱም መነሃሪያዎች ረጃጅም ሰልፎች ይሰለፋል።

የህዝብ መጓጓዣ ተሸከርካሪዎች በብዛት በመነሃሪያ ውስጥ ሲሆኑ የትራንስፓርት ስራ እንዲሰሩ ያልተፈቀደላቸው ጨምሮ የተወሰኑት ደግሞ ከመነሃሪያ ውጭ ዋጋ ጨምረው ይጭናሉ።

የዋጋ ጭማሪው ከሃምሳ በመቶ እስከ እጥፍ ማለትም እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲከፈል የነበረው 200 ብር ወደ 800 እስከ 1000 ብር ከፍ ማለቱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በአካል ታዝበዋል።

የትራንስፓርት እጥረቱ ከመቐለ ወደ ሌሎች ከተሞች ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ከተሞች ወደ መቐለ ጭምር ማጋጠሙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ወደ መኾኒ ራያና ወደ ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ከተማ ስልክ በመደወል አረጋግጧል።

ብርሃነ ገብረ የተባለ ከመቐለ ወደ ዓድዋ ለመጓዝ በተለምዶ ላጪ መነሃሪያ ተብሎ በሚጠራው ተገኝቶ በሰጠው አስተያየት ፤ " ትራፊክ ፓሊሶች ችግሩ እያዩ እርምጃ አይወሰዱም በርካታ መኪኖች ከመነሃሪያ ውጭ በመደበቅ 200 ብር የነበረውን ወደ 800 ፤ 600 ብር የነበረው ደግሞ ወደ 1500 ብር ከፍ በማድረግ ይጭናሉ ፤ አስተማሪና ችግር ፈቺ እርምጃና መፍትሄ የሚሰጥ በመጥፋቱ በሺ የሚቆጠር ተጓዥ ተጉላልተዋል እኮ ለምን ? " ሲል ጠይቋል። 

ከመኾኒ ራያ ወደ መቐለ ለመጓዝ ከሌሊቱ 10:00 የተነሳው አቶ ሃፍሩ ኪሮስ ደግሞ 200 ብር ይከፈልበት የነበረው 600 ብር እንዲከፍል መጠየቁ ተናግሯል።

ወዲ ተካ የተባለው ሓውዜን ከተማ ነዋሪ ደግሞ በመንገድ ትራንስፓርት ሰራተኞች ፣ በትራፊክ ፓሊስና በፀጥታ አካላት መካከል ያለው ያለመናበብ ችግር አሽከርካሪዎች በህገወጥ እንዲሰሩ በር በመክፋቱ ተጓዦች ለከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና እንግልት መጋለጣቸው በማህበራዊ የትስስር ሚድያ ሃሳቡ አጋርቷል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአሽከርካሪዎችና ረዳቶች ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ፣ የትራንስፓርት ፍሰቱ ነጠላ በመሆኑ ማለት ሄደው ተመላሽ ተጓዥ ስለማይገኝ በቆየው ታሪፍ ማገልገል እንደሚያከስራቸው  ይናገራሉ።

የመንገድ ትራንሰፓርትና የትራፊክ ፓሊስ አባላት በሰጡት አስተያየት ድግሞ አሽከርካሪዎቹ ህዝቡ በየአከባቢው የመርዶ ስነ-ሰርአቱ እንዲሳተፍ የሚያደርገው ከቦታ ወደ ቦታ የመጓጓዝ ሁኔታ ከአደጋ የፀዳ እንዲሆን ትርፍ ከመጫንና በፍጥነት ከማሸከርከር እንዲቆጠቡ ከፍተኛ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ላይ መሆናቸው ያስረዳሉ።

ሰራተኞቹና ትራፊክ ፓሊስ አባላቱ አክለው እንዳሉት ፣ ባለው ወደ አንድ አቅጣጫ ያተኮረ የትራስፓርት ፍሰት አሽከርካሪዎች ለኪሳራ እንዳይጋለጡ ከነበረው ዋጋ  እስከ 10 በመቶ ጭማሪ በማድረግ እንዲያገለግሉ መፈቀዱንና ከመነሃሪያ ውጭ ያለ መውጫ ፍቃድ የሚጭኑና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ እየተቀጡ መሆናቸው የትራንስፓርት ህጉ እንዲከበር ተጓዦችና አሸከርካሪዎች ተባባሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።  

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል ፤ የሚያልፉ ተማሪዎችም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለፁት ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ እንጥራለን  " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ " ፈተናው ዛሬ በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ተጀምሯል። " - የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።…
#Update

በትግራይ ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተጠናቀቀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል አገራዊ ፈተና በተረጋጋ እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።

በተመሳሳይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮው ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ መጠናቀቁ አሳውቋን።

የቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ ፤ አገር አቀፍ ፈተናው በተያዘለት ዕቅድ እንዲጠናቀቅ ያደረጋችሁ ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤቶች እና ዩንቨርሲቲዎች ያላችሁ ተቋሞች፣ የትምህርት ኣመራሮች እና መምህራን፤ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያላችሁ የፀጥታ እና ደህንንት ተቋሞች እና ኣመራሮች፤ ከተለያዩ ኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች የተውጣጣችሁ ፈታኞች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን "  ብለዋል።

ኃላፊው " ፈተናው በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ  ተፈታኝ  ተማሪዎቻችን ከናንተ የሚጠበቀው ሁሉ ስለደረጋችሁ ለናንተም የላቀ ምስጋና ይገባችኋል " ሲሉ አክለዋል። 

ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ/ም  ለአራት ተከታታይ ቀናት በትግራይ ክልል ሲሰጥ የቆየውን የ12 ክፍል አገራዊ ፈተና ከ9,000 በላይ ተማሪዎች መፈተናቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያሳያል።

ብሔራዊ ፈተናው የተሰጠው በመቐላ፣ አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ውጤቱን ባጠረ ጊዜ ለማሳወቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
" የቀድሞ ተዋጊዎችን ለማቋቋም ከ800 ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ያስፈልጋል " - የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን

የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

የኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽንና ዓለም አቀፍ ትብብር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሉልሰገድ በላይነህ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰቡ ለማቀላቀልና ለማቋቋም ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ብለዋል።

ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉት የቀድሞ ተዋጊዎች በጦርነት ቀጠና ውስጥ በመቆየታቸው የሚነሱት ከምንም ስለሆነ፣ የሚጠብቁት ነገር ስላላቸው ይህ የገንዘብ መጠን ላይበቃ እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል።

ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉት የቀድሞ ተዋጊዎች ፦
- በሥራ ላይ የነበሩ የዩንቨርሲቲ መምህራን፣
- ተማሪዎች
- አርሶ አደሮች፣
- የመንግሥት ሠራተኞች እና ሌሎች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካላት መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ልኡልሰገድ ፤ " ገንዘቡን የመንግሥት በጀት አይችለውም በአጭር ጊዜ ውስጥ መሠራት ያለበት ሥለሆነም ዓለም አቀፍ ርብርብ ይጠይቃል " ነው ያሉት።

ከ200 ሺሕ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ወደ ማኅበረሰቡ አቀላቅሎ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲገቡ ማድረግ ይቻል ዘንድ በጋራ ለመስራት የብሄራዊ ኮሚሽንና በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዥራ ሆቴል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።

የገንዘብ ሥምምነቱ ኮሚሽኑና በምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም ባደረጉት ተከታታይ ውይይቶች መሠረት ሁለቱ ተቋማት በመካከላቸው የትብብር ግንኙነት በመፍጠር ውጤታማ የተሃድሶ ሥራ ለመስራትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ  ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተነግሯል።

ይሁን እንጅ ከሚያስፈልገው ገንዘብ እስካሁን ምን ያህል ድጋፍ እንደሚያደርግ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት የተገባ ቃል እንደሌለ አቶ ሉልሰገድ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉት የጸጥታ ችግሮች ሥራውን ለማስኬድ እንቅፋት እንዳይሆኑ ትኩረት መሰጠት እንዳለበትም በመርሀ ግብሩ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ  ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 በአንቀጽ 85 መሰረት የተቋቋመ ገለልተኛ ተቋም ሲሆን፣ ሕጋዊ ዕውቅና ያገኙትን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ በመወከል በኢትዮጵያ ውስጥ ዘርፉን በመወከል እንዲንቀሳቀስ በአዋጁ ኃላፊነት ተሰጥቶታል ተብሏል።

በአሁኑ ወቅትም ከ4700 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የምክር ቤቱ አባላት እንዳሉም በጋዜጣዊ መግለጫው ተመላክቷል።

መረጃው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
Success begins with the right mindset! 💡 Join Jasiri Talent Investor Programme - Cohort 5 and cultivate the entrepreneurial mindset needed to overcome challenges and seize opportunities. Surround yourself with a community that believes in your potential. Apply now at https://jasiri.org/application and embark on a journey of growth and success!
🎤 አዲስ አበባ
የዘመናችን የመጨረሻውን የ5G ኔትወርክ በአዲሱ የ5G ጥቅል ለመጠቀም ዝግጁ!!!?🏃‍♂️🏃‍♀️

ወርሃዊ የ5G ጥቅሎችን ከ10%_ተጨማሪ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም በ*999# በመግዛት የአዲሱን ትውልድ ኔትወርክ ያጣጥሙ!

በአዲስ አበባ የ5G አገልግሎት የሚያስጠቅም ስልክ ያላቸውን ደንበኞቻችንን አገልግሎት ወደ 5G አሳድገናል ::

ለዝርዝር መረጃው: https://bit.ly/3RQ2McR

#አዲስ_ዓመት_አዲስ_ፍጥነት_ምቾት_እና_አኗኗር #5G
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD: ይህን የ4 ደቂቃ መረጃ ዳሰሳ ጥናት በመሙላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የምንሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ መመርያ ያግዙ።
👉 https://09u34jhg43098.typeform.com/to/nToapX9c

(የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል)
TIKVAH-ETHIOPIA
በቅበት ጉዳይ ምን ተባለ ? በስልጤ ዞን፣ ቅበት ከተማ ለተፈጠረው ችግር ፣ የዞኑ እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት፣ አስቸኳይ መፍትሄ ሊያበጁለት እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ችግሩን አስመልክቶ፣ ከዞንም ሆነ ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች…
#ቅበት

ከአንድ ወር በፊት በቅበት ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታታ ስምምነት ላይ መደረሱን ከስልጤ ዞን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከዞን አስተዳደር በተገኘው መረጃ ፤ ስምምነት ላይ የተደረሰው የቅበት ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ተባብረ ባዘጋጁት ውይይት ነው።

በዚሁ ውይይት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላት ተከስቶ የነበረው አለመግባባት ሀይማኖታዊ መሰረት ያልነበረውና በግለሰቦች ችግር የተፈጠረ ነበር ብለዋል።

ለአለመግባባቱ መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን ከስር መሰረቱ መፍታት የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱ ሲሆን ሚዛናቸውን የሳቱ ትችቶችና ማህበረሰቡን በጠቅላላ የመፈረጅ አዝማሚያዎች ተገቢ እንዳልነበሩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፤ በማናቸውም በኩል ያሉ ወንጀለኞች በአግባቡ እንዲጠየቁና በተለያየ መልኩ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ በጋራ መስራት ይገባል ብሏል።

በዚሁ መድረክ የተፈናቀሉ ዜጎች ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲመለሱ የሚያስችል መግባባት ላይ ተደርሷል።

የግጭት መባባስ መንስኤ የሆኑ ጥፋተኞች፣ ዜጎችን ያፈናቀሉና ንብረት ያወደሙ ሰዎች በሕግ ተጠያቂ ይደረጋሉ ተሽሏል።

የወደሙ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይገነባሉ ተብሏል። የቤቶችን ግንባታም በአንድ ሳምንት ጊዜ አጠናቅቆ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አለመግባባቱን በዘላቁነት ለመፍታት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ከአንድ ወር በፊት በቅበት በተፈጠረው ችግር የሰው ህይወ መጥፋቱ ንብረት መውደሙ፣ ዜጎችን ከቄያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ሲፌፓ

ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

አሁን ሀገር ካለችበት ሁኔታና ከተደቀነባት ፈተና ችግር አንፃር የተወሰኑ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥሮ ሀገራዊ ምክክር ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ገልጿል።

ፓርቲው ፤ በየአከባቢው የሚደረጉ ጦርነቶችና ግጭቶች ቆመው ችግሮች በምክክርና በውይይት ብቻ መፈታት እንዳለበት አቋም መያዙን አሳውቋል።

ለዚህም የራሱን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጿል።

በተጨማሪ የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት በመወከል በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፍ ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ የለም ያለው ሲፌፓ " በምክክር ሂደቱ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የህዝቡን ፍላጎት ማንፀባረቅ እንዳለብን አምንናል " ሲል አሳውቋል።

በመሆኑንም ፓርቲው በምክክር ሂደት ላይ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሀገር ድረስ በበቂ ሁኔታ መሳተፍ የሚችልበት አግባብና በተለያዩ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመነጋገር መስከረም 29/01/2016 ከኮሚሽኑ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዉ አቶ ገነነ ሀሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት መረጃ እንደገለጹት ስምምነቱ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍና የንግግርና የዉይይት መድረክ በመክፈት ክልላዊም ሆነ ሀገራዊ ክፍተቶችን ለማስተካከል እንደሚረዳ አመልክተዋል።

ስምምነቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል በሚያደርገዉ የዉይይት  መድረክ የበኩሉን ለማበርከት በወረዳ በዞን እንዲሁም ክልል ደረጃ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንዲጠናከር ይደረጋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከታች ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ይጠናከራል አለ።

አገልግሎቱ ፤ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ለመቅረፍ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንደሚጠናከር ይደረጋል ብሏል።

" ለውጤት መቀነስ አንዱ ምክንያት ተማሪዎች በታችኞቹ የትምህርት ደረጃዎች በተገቢው ፈተና እየወሰዱ አለመምጣታቸው ነው " የሚለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ይህም ተማሪዎች በየደረጃው ማወቅ ያለባቸውን እንዳያውቁ አድርጓል " ብሏል።

ይህ ሁኔታ በስተመጨረሻ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ ማድረጉን አመልክቷል።

ችግሩን ለመቅረፍ ተማሪዎች በተገቢው ምዘና እንዲያልፉ እንደሚደረግ ያሳወቀው አገልግሎቱ ይህንም ለመተግበር በ8ኛ ክፍል የሚሰጠውን ፈተና ከማጠናከር ባለፈ በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ምዘና ለማጠናከር ይሰራል ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉን አቀፍ የማሻሻል ስራዎች እንደሚያስፈልግ እና እንደሚሰራ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል "

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ​​ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።

የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
ብርቱ አጋር!!
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123