TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች በዌብሳይት eaes.et ላይ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በ6284 ፣ በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ ሬጅስትሬሽን ቁጥር በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።

ከዚህ ውጭ ውጤት መመልከቻ ምንም አይነት መንገድ የሌለ ሲሆን ውጤት ለማየት ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም።

በ2015 ብሄራዊ ፈተናውን የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ሲሆኑ 50 በመቶና በላይ አምጥተው ያለፉት 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

እነዚህ 27,267 ተማሪዎች በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ሲሆን ትምህርት ሚኒስቴር በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም እንዳለ አሳውቋል።

የሬሜዲያል መግቢያ መቁረጫ ነጥብ በቀጣይ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛው ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ሲሆን የአዲስ አበባ ልደታ ክሩዝ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት ያስመዘገበችው ፤ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከደብረ ማርቆስ አዲስ አለማየሁ ት/ቤት በሚማር ተማሪ ነው የተመዘገበው።

ማንኛውም በውጤት ላይ ቅሬታ ያለው ተፈታኝ ቅሬታውን በአካል መሄድ ሳይጠበቅበት በድረገፅ እስከ ጥቅምት 5/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ብቻ ማቅረብ ይችላል።

@TikvahUniversity @Tikvahethmagazine @tikvahethAFAANOROMOO @TikvahEthiopiaTigrigna @BirlikEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ምንም አይነት የሲስተም / ቴክኒካል ችግር የለም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ውጤት በዌብሳይት eaes.et ላይ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በ6284 ፣ በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ " ሬጅስትሬሽን ቁጥር " በማስገባት ማየት እንደሚቻል ተገልጿል።

ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ውጤት ለማየት መቸገራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

ይህ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን አነጋግሯል።

አገልግሎቱ ፤ በውጤት መመልከቻ አማራጮቹ ላይ ምንም አይነት ቴክኒካል / የሲስተም ችግር እንደሌለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" በአንድ ግዜ ተማሪዎችና ወላጆችን ጨምሮ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰው ውጤት ለማየት እየሞከረ ስለሆነ መጨናነቅ መፈጠሩን " ከፍተኛ የአገልግሎቱ አመራር ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች በትዕግስት በመሞከር ውጤታቸውን እንዲያዩ ኃላፊው መክረዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሀናን_ናጂ_አህመድ👏

በኢትዮጵያ 🇪🇹 ደረጃ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

ተማሪ ሀናን ናጂ ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን ገልጻለች።

በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች፡፡

የክሩዝ ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡

Credit - AMN

@tikvahethiopia
ከዘመኑ ጋር ራሱን እያዘመነ ደህንነቱን እያሻሻለ የመጣውን ቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ከ https://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ የክፍያ ዘይቤዎን ይቀይሩ !

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#አማራ

በአማራ ክልል ወቅታዊ የክልሉ የሰላም መደፍረስ በፈጠረው የመንገዶች መዘጋጋት እና መድኃኒቶች በቀላሉ ወደ ጤና ተቋማት መድረስ ባለመቻላቸው ህሙማን ተገቢውን ህክምና እያገኙ እንዳለሆነ የጤና ባለሙያዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

በደምና በኦክስጅን አቅርቦት ችግር ወላዶች ለሞት እየተዳረጉ እንደሆነም ተገልጧል።

ከሐምሌ 2015 ዓ/ም መጨረሻ ጀምሮ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት በርካታ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ሥራቸው ተስተጓጉሏል።

ችግር ካጋጣማቸው ተቋማት መካከል የፀጥታ ችግሮች ባሉባቸው የምዕራብ አማራ አካባቢ የጤና ተቋማት ይጠቀሳሉ።

ነዋሪዎች እና የጤና ባለሞያዎች ምን ይላሉ ?

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፈረስ ቤት ከተማ የሚገኙ አንድ ታካሚ ያጋጠማቸውን የመድኃኒት እጥረት ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል

" ኤሌክትሪክ አደጋ ደርሶብኝ ለመታከም ወደ ሆስፒታል ሄጀ ነበር፣ መድኃኒት በሀኪም ቤቱ ባለመኖሩ ከግል መድኃኒት ቤት መድኃኒት በ12 ሺህ ብር ገዝቻለሁ፣ በግል መድኃኒት ቤት ያሉ መድኃኒቶችም እያለቁ ነው። "

በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ሆስፒታል ባለሙያ ፦

" በመድኃኒትና በደም እጥረት ምክንት  ህሙማን  በተለይ እናቶች እየሞቱ ነው። የደምና የኦክስጅን እጥረት በከፋ ሁኔታ በሆስፒታሉ ይስተዋላል። "

የፍኖተሰላም ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ  አቶ ማናየ ጤናው ፦

" በደምና በኦክስጅን አቅርቦት እጥረት በቅርቡ ሁለት ወላዶች ሕይወታቸው አልፏል። "

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የየጁቤ ሆስፒታል ሐኪም፦

" በአካባቢ ከሚገኙ ወረዳዎች በመበደርና በትብብር በመውሰድ የመድኃኒት አገልግሎት ለታማሚዎች እያቀረብን ነበር። አሁን ግን ወረዳዎችም መድኃኒት በመጨረሳቸው ያን ማድረግ አልተቻለም። "

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የደብረማርቆስ ሆስፒታል ሐኪም ፦

" የመድኃኒትና የጀነሬተር እጥረቶች፣ እንዲሁም የመብራት መቆራረጥ በተለይ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ፈተና ሆኗል።

ያለ መድኃኒት በሆስፒታሉ ውስጥ መሥራት፣ ያለ ጥይት መሳሪያ ይዞ ጦርሜዳ እንደመዋል ነው። "

የደብረ ማርቆስ የደም ባንክ አስተባባሪ አቶ ከፋለ ገበየሁ ፦

" ወቅታዊ ሁኔታው ደም ለመሰብሰብ አላስቻለንም።

ደም ለመሰብሰብ ሁለት ዓይነት መንገዶች አሉ፤ አንዱ ጊዜያዊ ድንኳኖችን አቁሞ ከፈቃደኞች ደም መውሰድ ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ ወደ ደም ባንክ ማዕከሉ የሚመጡ በጎ ፈቃደኞችን መቀበል ነው። ይሁን እንጂ አሁን ያን ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም።

ናሙናዎችን ወደ ባሕር ዳር ለመውሰድም የመንገዶች በፀጥታ ሁኔታ መዘጋጋት ሌላው አስቸጋሪ ሁኔታ ነው። "

የመድኃኒት አቅርቦትን በተመለከተበኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምን ይላል ?

የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሳሉ ጫኔ ፦

" የፕሮግራም የሚባሉ መድኃኒቶች ከለጋሽ ድርጅቶች በእርዳታ የሚሰጡ ሲሆን በራሳችን መሥሪያ ቤት በግዥ የሚፈፀሙ ደግሞ አሉ፣ ሁለቱንም ለማጓጓዝ አውሮፕላን እንጠቀማለም ከዚያም መድኃኒቱ ባሕር ዳር ከደረሰ በኋላም አንፃራዋ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች መድኃኒቶቹ ይሰራጫሉ።

የመንገድና የፀጥታ ችግሮች እያሉም ሰሞኑነ የተወሰኑ መድኃኒቶችን ወደ ምሥራቅ ጎጃም ማድረስ ችለናል።

ወደ ምዕራብ ጎጃም አካባቢዎችም ለማድረስ ጥረት እየተደረገ ነው ሆኖም አሁንም የመንገዶች ሁኔታ አስቸጋሪ ነው። "

Credit - #ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#GAT

ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና (GAT) ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።

ይሁን እንጂ በመጀመሪያው ቀን የፈተና አሰጣጡ ላይ የተወሰነ የቴክኒካል ችግር አጋጥሞ እንደነበር ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተረድቷል።

ችግሩ በተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የተከሰተ መሆኑ ተመልክተናል። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን በተሳካ መልኩ መስጠታቸውንም ሰምተናል።

የቴክኒክ ችግር ያጋጠማቸው ዩኒቨርሲቲዎች የዛሬውን ፈተና ወደ ረቡዕ እና ሐሙስ ማሸጋገራቸውን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ከመስከረም 23/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀናት የመለማመጃ ፈተና (Mock Exam) ሲሰጡ ቢቆዩም የዛሬው ቴክኒካል ችግር መከሰቱ አልቀረም።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ፈተና እስከ ጥቅምት 01/2016 ዓ.ም ይቆያል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል ፤ የሚያልፉ ተማሪዎችም በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለፁት ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ እንጥራለን  " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

" ፈተናው ዛሬ በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ተጀምሯል። " - የትግራይ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።

ፈተናው በክልሉ በሚገኙ አራቱ የፌደራል ዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ጊዜ በሰላማዊ ሁኔታ መሰጠት መጀመሩ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጠዋል።

በቢሮው የግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሰለሞን ገ/ታትዮስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦
- በራያ ዩኒቨርስቲ 1561
- በመቐለ ዪኒቨርስቲ 2280
- በዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 2382
- በኣክሱም ዩኒቨርስቲ 3291 በአጠቃላይ ከዘጠኝ ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ዛሬ ጀምረዋል።

ፈተናው ጥቅምት ሁለት ይጠናቀቃል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መስከረም 28 /2016 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ፤ የትግራይ ተፈታኞቹን ውጤት በአንድ ሳምንት ውስጥ ለማሳወቅ ይሰራል።

የሚያልፉ ተማሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ውጤታቸው ከተገለጸ ተማሪዎች ጋር አብረው ወደ ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ለማድረግ ጥረት ይደርጋል ብለዋል።

ፎቶ፦ TIGRAY TV

@tikvahethiopia
#Jasiri4Africa

Don't miss out! You have 7 days to submit your application for the Jasiri Talent Investor program. If you're considering applying, now is the time to go to jasiri.org/application and get your application in before the deadline. #Jasiri4Africa
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Update ከጥቅምት 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ተፈፃሚ የሚሆነው የትግራይ የሃዘን ቀን ማሰፈፀምያ መመሪያ ይፋ ሆነ። ከመስከረም 21/2016 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆንና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ፊርማ ያረፈበት 18 አንቀፆችን የያዘ የትግራይ የሃዘንና መርዶ " መመሪያ ቁጥር 022016 " ምን ይላል ?  የመርዶና የሃዘን ስነ-ሰርአቱ ጥቅምት 2…
#ትግራይ

" የሚቋረጥ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም ፤ ባንኮች ግን ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናሉ " - የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት

የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ም/ቤቱ በትግራይ ክልል ደረጃ የታወጀው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት አስመልክቶ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው የህክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት የማይቋረጥ ሲሆን የባንከ አገልግሎት ግን ጥቅምት 3 እና 5 /2016 ዓ.ም ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናል ብሏል።

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት ጥቅምት 2 አመሻሽ በይፋ በሚድያ ተነግሮ ከጥቅምት 3 አስከ 5 ባሉት ሶስት ቀናት በተመሳሳይ ሰአት በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ስር ባሉ ሁሉም የክልሉ አከባቢዎች በጥብቅ ድስፒሊን እንደሚተገበር ምክር ቤቱ አስታውቀዋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንትና የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ፤ * የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ ትግራዋይ ያለ ልዩነት ያስተሳሰረ የጋራ አጀንዳ ነው " ብለዋል።

ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በጊዚያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ስር ባሉት አከባቢዎች ተግባራዊ የሚሆነው የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ህዝቡ በቀበሌ ደረጃ በማሰባሰብ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሰርአቱ በጠበቀ መልኩ እንዲፈፀም የሚያስተባብሩ አራት ንኡሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ስራ ጀምረዋል ብለዋል።

ኮሚቴዎች የሚድያና የማነሳሳት ፣ የመርዶ ፣ የህግና የፋይናንስ መሆናቸውን ያብራሩት የምክር ቤቱ ሰብሳቢ  ፤ ኮሚቴዎቹ የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ በተያዘለት እቅድ እንዲፈፀም ፣ ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ የሚጥስ ደግሞ ከገንዘብ እስከ የእስራት ቅጣት እንዲጣልበት ለመከታተል ሃላፊነት የተሰጣቸው እንደሆኑ ገልጸዋል።

በተያያዘ " የሰው ህይወት በማጥፋት ፣ ሴት ልጅ በመድፈርና ለጠላት ሚስጥር በመስጠት ወንጀል " ከሚጠየቁ ተብለው በእስራት ላይ ከሚገኙት ውጭ ያሉ የህግ ታራሚዎች በፀጥታ አስከባሪ በመታጀብ ቤታቸው ድረስ በመሄድ የቤተሰቦቻቸው መርዶ እንዲካፈሉ የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት መወሰኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።   

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ፊርማ ያረፈበት 18 አንቀፆች የያዘ የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ማስፈፀምያ  መመሪያ ቁጥር 022016 ከመስከረም 21/2016 ዓ..ም  ጀምሮ መተግበር ጀምረዋል።

መመሪያው " የሰማእታት አስከሬን ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ የሚከለክል " ሲሆን ፤ ይህንን መመሪያ የጣሰ ከብር 50 ሺህ እስከ ሶስት አመት አስራት እንደሚቀጣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።  

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የእስራኤልና ፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት በቀጣይ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ? ዋና ነጥቦች ፦ ▪️ሃማስ ፤ " ወራሪ " ናት በሚላት #እስራኤል ላይ  ወታደራዊ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመሩንይህ ኦፕሬሽንም #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ እንደሆነ ገልጿል። ▪️ እስራኤል ፤ " አሸባሪ " የምትለው የሃማስ ቡድን ጥቃት መክፈቱ ከባድ ስህተት መሆኑን በመግለፅ ለእያንዳንዱ ድርጊቱ…
#Update

የእስራኤል እና የፍልስጤም ሀማስ ጦርነት ዛሬም ለተከታታይ ቀን እጅግ ተባብሶ መቀጠሉን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።

የአሁኑ ጦርነት ከመቼውም የከፋ ነው ተብሏል።

ጦርነቱ እስካሁን የምን ያህል ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ ?

እስራኤል ፦ 1,200 ሰዎች ሞተዋል። 3,418 ተጎድተዋል።

ጋዛ ፦ 950 ፍልስጤማውያን ሞተዋል። 5,000 ተጎድተዋል።

በእስራኤል እና ጋዛ ድንበር ቅርብ ርቀት ላይ በነበረ አንድ የሙዚቃ ዝግጅ ላይ ሀማስ በፈፀመው ጥቃት የሞቱ ከ260 በላይ ሰዎች አክሬን መነሳቱ የተነገረ ሲሆን አሁንም ድረስ በሃማስ እጅ የሚገኙ ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች አሉ ሲል ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ከእስራኤል እና ፍልስጤማውን ባለፈ የአሜሪካን ጨምሮ እስራኤል ውስጥ የነበሩ የሌሎች ሀገራት ዜጎች በሃማስ ጥቃት መገደላቸው ተነግሯል።

2 ሚሊዮን ህዝብ ባለበት በጋዛ ሰርጥ ውሃ፣ ምግብ፣ነዳጅ የለም ተብሏል። ሰዎች መሄጃ አጥተው ተቀምጠዋል።

ሃማስ በእስራኤል ላይ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ጀመርኩ ካለ በኃላ እስራኤል በተለይ በአየር እየወሰደችው ባለው አፀፋ በጋዛ የሚገኙ ህንፃዎች፣ ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።

አንድ የፍልስጤም ጋዜጠኛ ከዚህ ቀደም 6 ጊዜ ያህል በጋዛ የተካሄደ ጦርነት መዘገቡን ገልጾ ይኸኛው እጅግ በጣም የከፋውና ፍፁም ደም አፋሳሽ እንዲሁም ምንም ህግ የሌለበት ነው ብሏል።

እስራኤል በሃማስ ጥቃት ህፃናት እና ሴቶች ሳይቀሩ መገደላቸውን የገለፀች ሲሆን ሃማስ በተመሳሳይ እስራኤል በምትፈፅመው ድብደባ በርካታ ህፃናት እና ሴቶች መገደላቸውን ገልጿል።

ሀገራት በጦርነቱ የተለያየ አቋም ይዘዋል። አሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ሃማስን " አሸባሪ " ሲሉ አውግዘው ከእስራኤል ጎን መቆማቸውን ገልጸዋል። አሜሪካ ከድጋፍ ቃል በዘለለ ወታደራዊ ድጋፍም እያደረገች ነው።

ኢራን " እየሩሳሌም እና ፍልስጤም " ነፃ እንዲወጡ ከፍልስጤም ተዋጊዎች ጎን መሆኗን አስረግጣ ተናግራለች። እንደ ሩስያ እና ቻይና ያሉ ኃያላን ሀገራን ጦርነቱ እንዲበርድ ተኩስ እንዲቆም የሚል አቋም ይዘዋል። ቱርክ ይህ አስከፊ ጦርነት ይበርድ ዘንድ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አደርጋለሁ ብላለች።

ሌላው የእስራኤል ጎረቤት ከሆኑት ሌባኖስ (ሂዝቦላህ ቡድን) እንዲሁም ከሶሪያ አቅጣጫ እስራኤል ላይ መሳሪያ የተወረወረ ሲሆን ይህ ጦርነቱን ይበልጥ አስፋፍቶ ሌሎች ሀገራትም ገብተውበት የከፋ ሁኔታ እንዳይፈጠር አስግቷል።

ያም ሆነ ይህ ጦርነቱ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ እርስ በእርስ ከሚፋለሙት የታጠቁ ኃይላት ባለፈ እጅግ  በርካታ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን እያረገፈ ይገኛል።

ምንም እንኳን ጦርነቱ መካከለኛው ምስራቅ ቢገኝም ዳፋው ለዓለም እንዳይተርፍ ይሰጋል። ከወዲሁ ነዳጅ ዋጋው እየናረ ነው።

ተጫማሪ መረጃዎችን በ @BirlikEthiopia ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ። በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ማድረጉ ተዘግቧል። የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4 % በላይ መጨመሩ ተነግሯል። ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ እያሳየ መጥቶ ነበር። ነገር ግን ቅዳሜ በሃማስ እና እስራኤል መካከል…
#ነዳጅ

በመካከለኛው ምሥራቅ በእስራኤልና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ መፍጠር የጀመረው የዋጋ ጭማሪ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ የበለጠ ሰማይ ሊነካ ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ የነዳጅ ዋጋን ወደ ተጠቃሚው ለማስተላለፍ በወሰነው መሠረት እስሁን ድረስ በአማካይ ከአሥር በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረገ የመጣ በመሆኑ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊፈጥር የሚችለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ከማስተላለፍ ሊቆጠብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክኤ መክረዋል።

የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክሌ ምን አሉ ?

" በመካከለኛው ምሥራቅ የሚከሰት ጦርነትና አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።

በቀዳሚነትም የዓለም የነዳጅ አቅርቦትና ገበያ የሚታወክ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የሚከሰት ከሆነ አሉታዊ ተፅዕኖው ለኢትዮጵያም የሚተርፍ እና የሚያሰጋ ነው።

የዓለም የነዳጅ ምርትና ገበያ ሰላምን ይፈልጋል። እንዲህ ያሉ ትልልቅ ጦርነቶች በተለይ አገሮች በፖለቲካ አመለካከታቸው ወገንተኝነታቸውን በግልጽ በሚያሳዩበት ወቅት የነዳጅ ግብይት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

በተለይ አሁን በተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ ባለፀጎች ለአንደኛው ወገን የሚያደላ የፖለቲካ አቋም ለመያዝ ከተገደዱ ይህንን የፖለቲካ አቋማቸውን የሚገልጹት የነዳጅ ምርትና አቅርቦታቸውን በመገደብ እንደሚሆን ቀደም ሲል የነበራቸውን ተሞክሮ ያሳያል።

ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በነዚሁ ወገኖች መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት ነዳጅ አምራች አገሮች በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል ጎራ ለይተው በመሠለፋቸው በዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዕክል ፈጥረው ነበር።

አሁንም እነዚሁ ተመሳሳይ አገሮች የሚፋለሙበት ጦርነት በመከሰቱ በነዳጅ ሀብት የታደሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በዋናነትም፣ ኢራንና ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮች አንደኛውን ተፋላሚ ወገን ደግፈው ምዕራባዊያኑ ደግሞ ሌላኛውን ወገን ደግፈው የሚቆሙ ከሆነ የዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦትን ሊያስተጓጉልና ዋጋውም ጣሪያ ሊነካ ይችላል።

ይህ ሁኔታ ከተከሰተ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ትልቅ ፈተና ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት ቀስ በቀስ የሚያደርገውን የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሠረት ያደረገ ወርኃዊ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ ቆም ብሎ ሊፈትሸው ይገባል።

ያልጠበቀውን ጦርነት ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳለ ኅብረተሰቡ ላይ መጫን የሚያዋጣ አይደለም።

መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት በገበያ ዋጋ እየሠራ ቢሆንም እንዲህ ባሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖው ግልጽ ከመሆኑ አንፃር በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየው የዋጋ ንረት ጦርነቱ ሊያስከትል የሚችለውን የዋጋ ጭማሪ ኅብረተሰቡ ላይ እንዲጫን ማድረግ ተገቢ አይሆንም።

ይህ ካልሆነ ግን የዋጋ ንረቱን በማባባስ ማኅበረሰብን ብሎም ኢኮኖሚውን ይጎዳል።

በሌላ በኩል ግን የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ከተፋላሚ አገሮች ባሻገር አገሮችን ጎራ ለይተው ወገንተኝነታቸውን እየገለጹ መሆን ምናልባት ትላልቆቹ የነዳጅ አቅራቢዎች ነዳጅ ባያቀርቡ ዓለም ላይ ችግር እንዳይኖር በተቃራኒ ያሉ አገሮች ተጨማሪ ነዳጅ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት ሊሞክሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አለ። ይህ ሊሆን የሚችለበት ዕድል ጠባብ ቢሆንም አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ሲታይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው አይቀመስም ብዙ አገሮችን ተጎጂ ያደርጋቸዋል፡፡

በተለይ ከፍተኛ የገቢ ንግድ ያለቸው አገሮች የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትልባቸው ይችላል። ስለዚህ በተለይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖ በማሰብ መንግሥትም ጊዜውን የዋጀ አሠራር ያስፈልገዋል።

በአጠቃላይ ግን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዓለም አቀፉን ኢኮኖሚ ይፈትናል፡፡

ጦርነቱ ዛሬ ያቆማል ቢባል እንኳን በብዙ መልኩ ተፅዕኖው ቀላል አይሆንም። በተለይ ዕቃን የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ዘርፎች በሚፈጠርባቸው ሥጋት እንቅስቃሴያቸው ይገደባል፡፡ ከዚህም ሌላ መንቀሳቀስ ከቻሉም ከፍተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን የሚጠይቁ መሆኑንና ተያያዥ ጉዳዮች የአቅርቦት ዋጋን ስለሚያስወድዱ የጦርነቱ ግልጽ የሆነ ተፅዕኖ አለው። "

(ከሪፖርተር የተወሰደ)

@tikvahethiopia