#ETHIOPIA #USA
ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መካከል የስልክ ውይይት ተደረገ።
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር እንዳሳወቁት ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ ውይይት ወቅትም ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ ፣ የሰብአዊ ሁኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበት አሠራር ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪ አንተኒ ብሊንከን፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ " አሳስቦኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
በሁለቱ ክልሎቹ ያሉትን ችግሮች #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተውበታል።
እውነተኛ ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#ትኩረት
#ከዳሎቻ ወደ #ወራቤ ያለው መንገድ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
ከላይ በምስሉ ላይ የምትታየው እናት ምጥ ይዟት ከዳሎቻ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ብትላክም በመንገዱ ብልሽት ምክንያት አንቡላንሷ በጭቃ ተይዛ እናትም በጭቃ መሃል እንድትወልድ ተገዳለች።
ከዚህ ባለፈ ከዳሎቻ ወደ ወራቤ ሆስፒታል ሪፈር የተፃፈላት ህፃን በመንገዱ ብልሽት ምክንያት አንቡላንሱ መሃል መንገድ ደርሶ ማለፍ ባለመቻሉ የህፃኗ ህይወት ልያልፍ ችሏል።
መንገዱ ከዳሎቻ ከተማ ጫፍ እስከ ወራቤ ከተማ ጫፍ ቡታጅራ መውጫ የተዘረጋና ርቀቱም ከአስር ኪሎ ሜትር ያነሰ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሁናቴ ተበላሽቶ ይገኛል።
በተጨማሪም መንገዱ እጅግ በጣም ጠባብ ፣ በየቦታው የተቆፋፈረ፣ በክረምት ወራት ከባድ ጭቃ፣ በበጋ ጊዜያት አስቸጋሪ አቧራ ያሚበዛበት ሲሆን በተደጋጋሚ የሚጠቀሙት መንገደኞች ላይ ከፍተኛ የጤና መታወክም ሲያደርስ ቆይቷል።
ይህም መንገድ በክልል ገጠር መንገድ በኩል በጠጠር መንገድ ደረጃ ተሰርቶ እያገለገለ ቆይቶ በየ ጊዜው የተወሰነ ጥገና እየተደረገለት እስካሁን ቢደርስም አሁን ላይ የጉዳቱ መጠን እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ መድረሱ ከክረምቱ ወቅት ዝናብ ጋር ተዳምሮ የመስመሩን ጉዞ እጅግ ፈታኝ አድርጎታል።
ስለሆነም የሚመለከተው አካል የመንገዱን አሁናዊ ሁኔታ ተመልክቶ አፈጠኝ ምለሽ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
(ሰይፈዲን ሉንጫ ከወራቤ)

TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ " ጸሎተኛው ፣ ደጉ፣ ርህሩሁና ታጋሹ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል " ብሏል። ብፁዕነታቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሀሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንዳሉ ከዚህ ዓለም ድካም እንዳረፉ ተገልጿል። የብፁዕነታቸውን…
#Update
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም እና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሊቀጳጳስ ዕረፍትን በማስመልከት አባታዊ የሐዘን መልዕክት አስተላለፉ።
ቅዱስነታቸው " የትህትና፣ የጸሎት ሕይወት እና የመልካምነት ምሳሌ የነበሩት ብፁዕ አባ ሰላማ ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የሰማነው በታላቅ ሐዘን ነው። " ብለዋል።
" ያለንበትን ፈተና የበዛበት ዘመን በጸሎት የሚያሻግሩ አባቶችን ማጣት ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ቢሆንም በቅዱስ መጽሐፍ ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ መኖር የሚችል ማን ነው ? እንደተባለ ሰው በምድር ላይ የሚኖርበት ዘመን በእግዚአብሔር ዘንድ የተቆጠረ እና የተለካ በመሆኑ ብፁዕነታቸው ሃይማኖትን ጠብቀውና መልካሙን ገድል ፈጽመው ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር በክብር ተሸጋግረዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ብፁዕነታቸው በዕረፍተ ሥጋ ከእኛ በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ቢሰማንም በሰማይ የሚጠብቃቸውን ክብር እያሰብን እንጽናናለን " ብለዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ " የብፁዕነታቸውን ነፍስ በቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት አጠገብ ያሳርፍልን! ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውም መጽናናትን ያድልልን ! " ብለዋል።

አክረም አል አሩሲ አረፈ።
በሱዑዲ አረቢያ መካና አካባቢዉ በተለያዩ ሀገራዊና ማህበረሰባዊ አገልግሎቶች በተለይ ደግሞ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጎላ ድምፅ በመሆን በሙያዉ ግንባር ቀደም አስተዋጽዖ ሲያበረክት የቆየዉ ታዋቂዉ ኢትዮጵያዊ አክረም አል አሩሲ ማረፉን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጅዳ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት አሳውቋል።

ከነዳጅ ዋጋ 📈 ቤንዚን እና ናፍጣ ላይ በሊትር ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ። የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ገልጿል። ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል፡፡ በዚህም…
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።
በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
- ቤንዚን 👉 በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ነጭ ጋዝ 👉 በሊትር 76 ብር ከ75 ሳንቲም
- የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 70 ብር ከ83 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 61 ብር ከ83 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡
መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘ ነው።

#TPLF የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አካል የሆነው ፓለቲካዊ ውይይት በአስቸኳይ በተጠናከረ መልኩ እንዲጀመር ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት ጠየቀ። ድርጅቱ ለአንድ ሳምንት ያህል ዝግ ስብሰባ ሲያካሄድ ቆይቶ ትላንት ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። ህወሓት መስከረም 14 /2016 ዓ.ም አመሻሽ ባወጣው መግለጫ ፥ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ህዝቡ ከጥይት…
" ... የተካሄደው ጦርነት መነሻ ፓለቲካዊ በመሆኑ በፓለቲካዊ ውይይት መቋጫ ማግኘት እንዳለበት ተወስኗል " - ህወሓት
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማእከላይ ኮሚቴ ሰላማዊ ትግል አጠናክሮ በማስቀጠልና በፓርቲው ስትራቴጂክ አመራር የታየው ድክመት አስመልክቶ በጥልቅ መወያየቱ ገለፀ።
ይህን የለፀው የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ስብሰባ የአመራር ችግር በትኩረት መገምገሙንና በአስቸካይ ማሰተካከያ እንዲደረግ ወስኗል።
" ያካሄድኩት ግምገማ ውሱንና ያልተሟላ ነው " ያለው የድርጅቱ ሊቀመንበር መግለጫ የመስመር ፣ የፓሊሲና ስትራቴጂ ፣ የብሄራዊ መከታ ግምገማ ለማረድግ ወመሰኑ አመልክተዋል።
ሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግሉ በመምራት በኩል የተፈፀመ የአመራር ጉድለት መኖሩም መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።
ህወሓት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አካል ነው ፤ ከፌደራል መንግስት በመስማማት የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መስማማቱም ተወስቷል በመግለጫው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የሰጠው ቴክኒካዊ ውሳኔ ትክክል አይደለም ፤ ህጋዊ እውቅና ያለው የህወሓት ፓርቲ እውቅና መስጠትና መንሳት በፓለቲካ እንጂ በቴክኒካዊ ሂደት የሚፈፀም አይደለም ተብሏል።
የአገሪቱ ከፍተኛ ህግ አውጪ የሆነው የተወካዮች ምክር ቤት ከሽብር መዝገብ ነፃ ያለው የፓለቲካ ድርጅት ፣ በተወካዮች ምክር ቤት ህግ በተቋቋው የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የሚነሳበት ሁኔታ የለም ብሏል።
የተፈጠረው የሰላም ስምምነት ዘላቂ እንዲሆን የህወሓት አወንታዊ አስተዋፅኦ መዘንጋት የግዚያዊ አስተዳደሩ ስራ ማደናቀፍ ማለት ነው ያሉት ከፍተኛ አመራሮቹ በትግራይ የታየው የፍትህ ፣ የፀጥታና የሙስና ችግሮች የስትራቴጂክ አመራር መጓደል ማሳያ መሆናቸው ተገምግመዋል ብሏል።
በተፈፀሙት የሙስናና ሌሎች ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ከሁሉም በላይ ከላይ ወደ ታች የማጥራት ስራ እንዲጀመር መግባባት ተደርሷል ያለው መግለጫው " የግዚያዊ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫዎች የህወሓትና የትግራይ ህዝብ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ሲል " አክለዋል።
ደሞ ተከፍሎበት የተገኘው ሰላማዊ ትግል ከማስቀጠል ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ፤ ስለሆነም የተካሄደው ጦርነት መነሻ ፓለቲካዊ በመሆኑ በፓለቲካዊ ውይይት መቋጫ ማግኘት እንዳለበት ተወስኗል።
የግዚያዊ መንግስቱ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸውና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ " የትግሉ ሰማእታት የቤተሰቦቻቸው ብቻ ሳይሆኑ የሁላችን ናቸው " ያሉ ሲሆን የትግራይ ህዝብን ከጥፋት ለመከላከል ዋጋ የከፈሉ ናቸው ብለዋል።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመላ ክልሉ የሃዘን ቀን እንደሚታወጅ የመስቀል በአል ምክንያት በማድረግ በመቐለና በዓዲግራት ባስተላለፉት መልእክት ማስታወቃቸው መዘገባችን ይታወሳል።

#EHPA
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ልኮልናል።
በዚሁ መግለጫው በቅርቡ በአማራ ክልል በተከሰተዉ ግጭትና አለመረጋጋት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል እንዳስከተለ አሳውቋል።
ማህበሩ ፤ አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ አገልግሎት አለመስጠት እና ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ ለወታደራዊ እንቅስቃሴ አገልግሎት ሲዉሉ ተስተዉሏል፡ ብሏል።
" አሁንም ወደ ጤና ተቋም አገልግሎት ያልተመለሱ ብዙ አንቡላንሶች እንዳሉ አረጋግጠናል " ሲል ገልጿል።
በአጠቃላይ በሀገሪቱ ያሉ ችግሮች ህብረተሰብን ፤ የጤናውን ዘርፍ ፤ ሀገርንም በከፍተኛ ደረጃ እየጎዱ መሆኑ አስገንዝቧል።
በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ፦
- እየተካሄደ ያለው ግጭት ባስቸኳይ እንዲቆምና ሰላማዊ ድርድር እንዲያደርጉ የሰላም ጥሪ አቅርቧል።
- በጦርነቱ ወቅት አንቡላንሶችን ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ መጠቀም እንዲቆም አና አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የህይወት አድን ስራቸዉን መስራት ሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር አሳስቧል።
- በትግራይ አፋርና አማራ ክልል በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸዉ ጤና ተቋማት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መልሶ የማቋቋም እና በሙሉ አቅማቸዉ ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ማድረግ ቀዳሚ የመንግስት ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብሏል።
ማህበሩ ከዚህ በተጨማሪ በመግለጫው ፤ የጤና ባለሙያዎች ኑሮአቸውን ለመምራት የሚያስችል #ደሞዝም ሆነ #ጥቅማጥቅሞች ተነፍገዉ አየኖሩ ይገኛሉ ብሏል።
" በተደጋጋሚ ችግሩን ለመንግስት አካላት ብናቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠም " ሲል ገልጿል።
ማህበሩ በቀን 30/06/2015 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ ቤት እስከ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ለሌሎች የሃገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት የጤና ባለሙያዎችን ደሞዝና የመብት ጥያቄዎችን ቢያቀርብም ምንም አይነት ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ ጤና ባለሙያዎች ለከፋ የኑሮ ቀዉስ መዳረጋቸውን አመልክቷል።
በመሆኑንም የጤና ባለሙያዎች የሚያነሷቸዉ የመብት ጥያቄዎች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ማህበሩ ጠይቋል።
(ከማህበሩ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

#ALERT🚨 አንድ አንጀራ ለ10 ተሻምተው የሚበሉ ወገኖቻችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን ? በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከፍተኛ ድርቅ ተመቷል። ነዋሪው ችግር ላይ ወድቋል። ሰው በረሃብ #ሞቷል ፣ እንስሳት ሞተዋል ፣ ተሰደዋል። ወገኖቻችን በቂ ምግብ አጥተው 1 እንጀራ ለአስር እየተሻሙ እየበሉ ነው። ካዛ ውጭ ጨው በውሃ በጥብጠው ነው የሚጠጡት። " በዚህ ሳምንት…
#Update
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በተለይም ሰሀላ ሰየምት ወረዳ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የወረርሽኝ ኬዞች እንዳሉ የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ ኪዳት እድል (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ኪዳት (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ " ከድርቁ ጋር በተያያዘ መንገድ በእርግጥ አንድ አንድ የተቅማጥ ኬዞች አሉ " ብለዋል።
አክለውም ፤ " ነገር ግን ኬዙ አተት ወይም ኮሌራ ነዉ ብለን ለይተን ያስቀመጥነው ነገር የለም ከዚህ በኋላ ግን ከፍተኛ የሆነ ስጋት ነዉ ያለን በተቅማጥ በኩል የሚከሰት ወረርሽኝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።
" ከድርቁ ጋር በተያያዘ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ሊጨምሩ ይችላሉ " ያሉት ኪዳት (ዶ/)፣ " ከምግብ እጥረቱ ጋር ተያይዞ በተለይ ከ 5 ዓመት በታች ባሉ ህፃናት የሳንባ በሽታ፣ ተቅማጥ እና ተያያዥ የሆኑ ለሞት የሚያደርሱ በሽታዎች ይከሰታሉ " ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
" እንዲሁም ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ ተቅማጥ፣ ውሃ ወለድ የሆኑ በሽታዎች ይከሰታሉ " ያሉት ኃላፊው፣ " ከእንስሳት ጋር ተያይዞም የእንስሳት በሽታዎች ይከሰታሉ እነዚህ እንግዲህ ተያያዥ ችግሮች ናቸው " ብለዋል።
" በወረርሽኝ መልክ ይከሰታሉ ብለን ከምናሰገባቸው በሽታዎች መካከል አንደኛው ወባ ሲሆን በተጨማሪም አተት የሚባለው በሽታ በተለምዶ ኮሌራ ድርቅ በተከሰተበት ወረዳ መከሰቱ የማይቀር ነው። እንዲያውም ቁጥር አንድ ይከሰታል ብለን ከምናስባቸዉ ወረዳዎች ሰሀላ ሰየምት ዋነኛው ነው " ሲሉ አክለዋል።
የጤና መምሪያ ኃላፊው፣ " እንደ ጤና ድርቅ ሲኖር የሚከሰቱ ብዙ ችግሮች አሉ ፊት ለፊት ያለው የረሀብ ችግር ነውና በተለይ አጥቢና ነፍሰጡር እናቶች ከ 5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት በጤና ጉዳይ ግንባር ቀደም ተጠቂ ናቸው ስለዚህ እሱ በጣም ትልቅ ችግር ስለሆነ የምግብ እጥረት ልየታ እያሰራን ነው " ብለዋል።

Photo
" እውነቱን ለመናገር ነዋሪዎቹ እርቧቸዋል። እያለቀሱ ነው የተናገሩት። ድረሱልን እያሉ ነው " - አቶ ምሕረት መላኩ
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የአማራ ክልል መንግሥት ድርቅ በተከሰተባቸው ቦታዎች የዕለት ድጋፍ ለማድረስ ቢስማማም በጸጥታ ችግር መድረስ እንዳልቻለ ገልጸዋል።
ኃላፊው ከ1.2 ሚሊዮን በላይ እንስሳት ወደ አጎራባች ወረዳዎች ለመፈናቀል እንደተገደዱ በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ሂደው ማረጋገጣቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በቦታው ገብተው ድጋፍ በማድረግ ችግሩን እንስኪጋሩ ድረስ የክልሉ መንግሥት የዕለት ምግብ አቀርባለሁ ብሎ ውሳኔ አሳልፏል " ያሉት አቶ ምህረት፣ " ነገር ግን ሰሞኑን በጎንደር መስመር የጸጥታ ችግር ስለነበረ የትራንስፓርት ተጫራቾቹ ችግር አለ #አንሄድም አሉኝ ነው ያለው " ብለዋል።
" መስከረም 18 እና ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም አንጻራዊ ሰላም ከሆነ ምግብ ይዘው እንዲገቡ ነው የተግባባነው " ሲሉ አክለዋል።
እስካሁን የተገኘ ድጋፍ እንዳለና እንደሌለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄም፣ " የሕጻናት አድን ድርጅት (ሴቭዘቺልድረን) 475 ቤት መሪዎች ለእያንዳንዳቸው 21,000 ብር ድጋፍ አደርጋለሁ ብሎ ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም የተጠቃሚ ልየታ ሊጀመር ነው " ብለዋል።
አክለውም፣ " ቅድመ ዝግጅት ነውና እያደረግን ያለነው ወደ ሕዝቡ በተጨባጭ የገባ ድጋፍ ይለም " ነው ያሉት።
ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄም፣ " ነዋሪዎቹ እውነቱን ለመናገር እርቧቸዋል። እያለቀሱ ነው የተናገሩት። ድረሱልን እያሉ ነው " ሲሉ ድርቅ በተከሰተበት አካባቢ በአካል ተገኝተው ያረጋገጡትን አስረድተዋል።
" እንስሳትንም ለማየት ሞክረን ነበር" ያሉት አቶ ምህረት የጋማ ከብቶች፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየሎችን ጨምሮ 1.2 ሚላዮን እንስሳት ሳር ወዳለባቸው አጎራባች ቦታዎች መፈናቀላቸውን ገልጸዋል።
አክለውም ፣ " ተከዜን ተሻግሮ በሚገኙ የሰሀላ ሰየምት 13 ቀበሌዎች ከአንዱም ቀበሌ ለእንስሳት የሚሆን መኖ አላገኘነም። የእንስሳት ሞት ቁጥርም እየጨመረ ነው" ብለዋል።
ቀይ መስቀል በአካባቢው ላይ ገብቶ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥያቄ እንዳቀረቡም አቶ ምህረት ገልጸዋል።