TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው መካከል የተወሰደ ፦

" እባካችሁ ንስሐ ገብተን በመስቀሉ ቃል ተቀራርበንና ተስማምተን ይቅር ተባብለን በአንድነት በእኩልነት በሰላምና በፍቅር እንኑር።

በምድራችን ፍትሕ ርትዕ ይንገሥ፥ ሰብአዊ መብት ይከበር፥ የተበደለ ይካስ ፥ እግዚአብሔር ይደመጥ መስቀል ማክበር ማለት ይህ ነው፡፡

ይህ ሲሆን ሀገር በመንፈሳዊና በቊሳዊ በረከት ትባረካለች፤ ትለማለችም፤ ታድግማለች፤ እግዚአብሔርም በተግባሩ ወይም በፍጥረቱ ይደሰታል፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

Grap. Tikvah Family

@tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ (ትግርኛ)👇
https://t.iss.one/+PNA7LEU9eBwzYzM0

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (አፋን ኦሮሞ) 👇
https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23

ጥቆማ >> BiRLiK (ቢርሊክ) - ETHIOPIA 👇
https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የ2016 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።

መልካም በዓል!
#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

" ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም "

ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት።

ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል።

ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን የሚገፈ አርሶና አርብቶ አደር አካባቢ ነው።

በወረዳው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብትም ይገኛል።

ጠቅላላ ካለው የእንስሳት ሀብት የዳልጋ ከብት 104,430፣ የጋማ ከብት 22,121 በግ እና ፍየል 465,428 ይገኙበታል።

ከዚህ ውስጥ ለድርቅ የተጋለጡ የዳልጋ ከብት 92,430፣ የጋማ ከብት 16,121፣ በግ እና ፍየል 396,760 ናቸው።

ወደአጎራባች ዞን የተሰደዱ የዳልጋ ከብት 20,328 ፣ በግ እና ፍየል 116,900 ሲሆኑ እስካሁን በድርቅ ምክንያት የሞተ የዳልጋ ከብት 1320 ፣ የጋማ ከብት 71 በግ እና ፍየል 2457 ናቸው።

በወረዳው ከ52 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን 46ሺ የሚሆነው አፋጣኝ እርዳታ ካለገኘ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል።

አቶ ሲሳይ፤ " ምንም እንኳን ድርቅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ለእንስሳት የሚሆን ሳር አይጠፋም ነበር። ዛሬ ግን የተቃጠለ መሬት ብቻ ነው የሚታየው፤ ለጥርስ ስጋ ማውጫ የሚሆን የሳር ስንጥር እንኳን አይታይም፤ የወረዳው ነዋሪዎች እንደነገሩን እንደ ወረዳችን እንዲህ አይነት ድርቅ አይተን አናውቅም፤ ሰባሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " በማለት የድርቁን አስከፊነት ገልጸዋል።

በወረዳው የአርሶ አደሩ ማሳ ርቃኑን ቀርቷል፣ እንስሳት ቆዳቸው ከስጋቸው መጣበቅ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸው በጣዕረሞት ላይ ናት፣  ህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን በርሀብ ተገርፈው ነፍሳቸው ከጉንጫቸው ተጣብቃ ይዛቸው ልትጠፋ አፋፍ ላይ ነች። ተሎ መድረስ ካልተቻለ አሳዛኝ ክስተት በሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ሊከሰት ይቻላል።

የአስተዳደሩ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ጉዞ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የብሄረሰቡ ከፍተኛ አመራሮችና አንዳንድ ግብረሰናይ ድርጅቶች በወረዳው ተገኝተው ቀበሌዎቹን ጎብኝተው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የቀበሌው ማህበረሰብ በውይይቱ ላይ " ከእግዚአብሄር በታች መንግስት ነበር ለሰው ልጅ ዋስትና፣ ዛሬ ግን መንግስትም ፊቱን አዞረብን " ብለዋል።

" በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችን አናገኛቸውም ፤ አሁንም ቢሆን አንዲት እንጀራ ለ10 ሰው ነው የምንሻማው፤ ከዛ ውጭ ግን ጨው በውሀ በጥብጠን ነው የምንጠጣው " ብለዋል።

እስካሁንም በወረዳው በርሀብ ምክኒያት የ2  ሰዎች ሂይወት አልፏል ሲሉ አሳውቀዋል።

እንስሳትን በተመለከተ " በወረዳችን ትንሽ እህል ካገኘን እንሰሳ ስለምናረባ ከብት እና ፍየሎቻችንን ሸጠን እህል ስለምንሸምት ብዙም አያሳስበንም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ለከብቶችም ሆነ ለፍየሎችና በጎች የሚሆን የሚጋጥ ሳር ስለሌለ ተስፋ አስቆርጦናል " ብለዋል።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ፤ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቃል ከመግባት የዘለለ በመንግስት በኩልም ምንም የቀረበ ነገር የለም።

ለክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ የችግሩን አሳሳቢነት ብንገልጽም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ብለዋል።

መረጃው ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ነው የደረሰን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ALERT🚨 " ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል። በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት። ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል። ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን…
#ALERT🚨

አንድ አንጀራ ለ10 ተሻምተው የሚበሉ ወገኖቻችን እንዳሉ እናውቅ ይሆን ?

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከፍተኛ ድርቅ ተመቷል።

ነዋሪው ችግር ላይ ወድቋል።

ሰው በረሃብ #ሞቷል ፣ እንስሳት ሞተዋል ፣ ተሰደዋል።

ወገኖቻችን በቂ ምግብ አጥተው 1 እንጀራ ለአስር እየተሻሙ እየበሉ ነው። ካዛ ውጭ ጨው በውሃ በጥብጠው ነው የሚጠጡት።

" በዚህ ሳምንት የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችንን አናገኛቸውም " ብለዋል።

የግብረሰናይ ድርጅቶች ቃል መግባት እንጂ ጠብ የሚል ነገር አላደረጉም። መንግሥትም ለገዛ ዜጎቹ እየደረሰ አይደለም።

ከፈጣሪ በታች ለህዝቡ ዋስትና ነው የሚባለው መንግሥት ፊቱን እንዳዞረባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ሁኔታው ከሰባ ሰባቱም የከፋ ነው።

via @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
" 7 ስድተኞች ህይወታቸው አልፏል ፤ 9 ተጎድተዋል " - IOM

ታንዛኒያ ውስጥ በደረሰ አደጋ ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በተባበሩት ታንዛኒያ ሪፐብሊክ ፤ ኒጆምቤ ክልል በደረሰ የመኪና አደጋ ስደተኞች ላይ የሞት እና አካል ጉዳት መድረሱን ባወጣው መግለጫ አሳውዋል።

ድርጅቱ አደጋው እንደደረሰ የታመነው እኤአ መስከረም 14 መሆኑን አመልክቷል። #ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብለው የታሰቡ 29 ስደተኞችን የጫነ መኪና ወደ ዛምቢያ ድንበር ቱንዱማ በመጓዝ ላይ እያለ አደጋው መድረሱን ገልጿል።

በአደጋው 7 ስደተኞች እንደሞቱና 9ኙ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጿል። 13 ስድተኞች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ብሏል።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዚህ አሰቃቂ አደጋ ለተጎዱት ሁሉ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

ሰራተኞቹ በታንዛኒያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች ጋር በመሆን በቦታው ተገኝተው ስለሁኔታው የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና በተቻለ መጠን ድጋፍ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም በውጭ ጉዳይ በኩል ጉዳዩን በተመለከተ የሚወጣ መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እንልካለን።

@tikvahethiopia
#HaileCoffee

በብራይተን ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የቀድሞ የእንግሊዝ አትሌቶች በኢትዮጵያዊው ጀግና አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስም " ሀይሌ ኮፊ " የተሰኘ ቡና #ለሯጮች መሸጥ መጀመራቸው ተገልጿል።

" ሀይሌ ኮፊ " የሚል ስያሜን ያገኘው ይህ ቡና በቀድሞ የእንግሊዝ የማራቶን ሯጭ ሪቻርድ ኔርኩር ሀሳብ አመንጪነት ለገበያ መቅረቡ ታውቋል።

ሪቻርድ ኔርኩር ዘጠኝ አመታትን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በቆየበት ወቅት ከኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ሀይሌ ጋር በነበረው ቅርበት ይህ የቢዝነስ ሀሳብ ሊመጣለት እንደቻለ ተገልጿል።

" ቡና በኢትዮጵያውያን ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው " ያለው ኔርኩር ሀይሌ በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ያለውን ስም በመጠቀም ቡናን ለሚያዘወትሩ አትሌቶች " ሀይሌ ኮፊን " እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ለሽያጭ የሚቀረበው " ሀይሌ ኮፊ " ምርት " Premium Ethiopian Coffee " የሚል መገለጫ እንደሚኖረው ታውቋል።

" በሀይሌ ኮፊ " ሶስት የተለያዩ የቡና አይነትን ለሯጮች እንደሚቀርብ ሲገለፅ Champion’s Choice  ፣ Emperor's Delight እና Haile Blend እንደሚሰኙ ተገልጿል።

ሀይሌ ኮፊ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ለተጠቃሚዎች ለሽያጭ መቅረቡ ተዘግቧል።

Via @tikvahethsport