TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ

በሚቀጥለው ሳምንት በመላ ትግራይ ክልል #የሃዘን ቀን ይታወጃል።

ይህንን ያስታወቁት የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ  ዛሬ የመስቀል በዓል በማስመልከት በመቐለ ከተማ ለህዝብ ባስተላለፉት መልእክት ነው።

የዘንድሮ የመስቀል በዓል ከቄየው ተፈናቅሎ በስደት በረሃብና ጥማት ከሚሰቃይ ህዝባችን በመሆን የምናከብረው መሆናችን መዘንጋት የለብንም ያሉት ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ "  ይህንን አንፃራዊ ሰላም እንዲገኝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰማእታት መክፈላችን መዘንጋት የለብንም " ብለዋል።

" ለህዝብ ህልውና የተሰውና አካላቸው የጎደሉ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው ሁሌም ሊዘከሩና ሊከበሩ ይገባል የመሰቀል በዓል ስናከብርም ብሄራዊ የሃዘን ቀን ለማዋጅ በተዘጋጀንበት ወቅት መሆኑ በማወቅ ከሰማእታት ቤተሰቦችና ለኛ ሲሉ አካላቸው የጎደሉ በቀጣይነት ለማከበር  ቃል በመግባት ሊሆን ይገባዋል " ብለዋል አቶ ጌታቸው።    

" ሰማእታት ስናስታውስና አካላቸው የጎደሉና ቤተሰቦቻቸው ስናከብር መስዋእት የከፈሉባቸውና አካላቸው የጎደሉባቸው ሜዳና ተራራ እንዲሁም የወደሙ መሰረተ ልማቶች በተደራጀና በተናበበ መልኩ በእልህና በቁጭት በማልማት ሊሆን ይገባል " ያሉት ፕረዚደንቱ " ግዚያዊ አስተዳደሩ በተገቢ የመምራት ሚናው ይወጣል " ብለዋል።  

የተጀመረው የሰላም ስምምነት ከማፅናት ጎን ለጎን ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዲመለሱ ፣ በሃይል የተያዙ መሬቶች ወደ ባለቤታቸው እንዲመለሱ የምናደርገው ሰላማዊና ፓለቲካዊ ትግል በመደገፍ በኩል ህዝቡ የበኩሉ እንዲወጣ አቶ ጌታቸው ረዳ ጥሪ ማቅረባቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የትግራይ ቴሌቪዥን በዋቢነት በመጥቀስ ዘግቧል። 
  
@tikvahethiopia
#መልዕክት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው መካከል የተወሰደ ፦

" እባካችሁ ንስሐ ገብተን በመስቀሉ ቃል ተቀራርበንና ተስማምተን ይቅር ተባብለን በአንድነት በእኩልነት በሰላምና በፍቅር እንኑር።

በምድራችን ፍትሕ ርትዕ ይንገሥ፥ ሰብአዊ መብት ይከበር፥ የተበደለ ይካስ ፥ እግዚአብሔር ይደመጥ መስቀል ማክበር ማለት ይህ ነው፡፡

ይህ ሲሆን ሀገር በመንፈሳዊና በቊሳዊ በረከት ትባረካለች፤ ትለማለችም፤ ታድግማለች፤ እግዚአብሔርም በተግባሩ ወይም በፍጥረቱ ይደሰታል፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

Grap. Tikvah Family

@tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ (ትግርኛ)👇
https://t.iss.one/+PNA7LEU9eBwzYzM0

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (አፋን ኦሮሞ) 👇
https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23

ጥቆማ >> BiRLiK (ቢርሊክ) - ETHIOPIA 👇
https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የ2016 ዓ/ም የመስቀል በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን ለምታከብሩ ቤተሰቦቻችን በሙሉ በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ እንዲሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

በዓሉን ስናከብር በሀዘን ውስጥ ያሉትን ፣ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንን እያሰብን ፣ ለሀገራችን እና ለሀገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ፍፁም ሰላምን እንዲሰጠን ፈጣሪን እየተማፀንን እንዲሆን አደራ እንላለን።

መልካም በዓል!
#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

" ሰባ ሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም "

ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ በከባድ ድርቅ መመታቱ ተገልጿል።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ስር ያለው ሰሀላ ሰዬምት ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉት።

ወረዳው የ2015/2016 የምርት ዘመን #ድርቅ ክፉኛ መትቶታል።

ወረዳው በከፊል አርብቶ አድር የሚታወቅ ሲሆን ከማሳው በሚያገኛት ጥቂት ኩንታል እህል በይበልጥ ለገለባው ዋጋ ሰጥቶ በእንሰሳቱ ኑሮውን የሚገፈ አርሶና አርብቶ አደር አካባቢ ነው።

በወረዳው ከፍተኛ የእንስሳት ሀብትም ይገኛል።

ጠቅላላ ካለው የእንስሳት ሀብት የዳልጋ ከብት 104,430፣ የጋማ ከብት 22,121 በግ እና ፍየል 465,428 ይገኙበታል።

ከዚህ ውስጥ ለድርቅ የተጋለጡ የዳልጋ ከብት 92,430፣ የጋማ ከብት 16,121፣ በግ እና ፍየል 396,760 ናቸው።

ወደአጎራባች ዞን የተሰደዱ የዳልጋ ከብት 20,328 ፣ በግ እና ፍየል 116,900 ሲሆኑ እስካሁን በድርቅ ምክንያት የሞተ የዳልጋ ከብት 1320 ፣ የጋማ ከብት 71 በግ እና ፍየል 2457 ናቸው።

በወረዳው ከ52 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርበት ሲሆን 46ሺ የሚሆነው አፋጣኝ እርዳታ ካለገኘ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ብሩ ተናግረዋል።

አቶ ሲሳይ፤ " ምንም እንኳን ድርቅ ቢሆንም ከዚህ በፊት ለእንስሳት የሚሆን ሳር አይጠፋም ነበር። ዛሬ ግን የተቃጠለ መሬት ብቻ ነው የሚታየው፤ ለጥርስ ስጋ ማውጫ የሚሆን የሳር ስንጥር እንኳን አይታይም፤ የወረዳው ነዋሪዎች እንደነገሩን እንደ ወረዳችን እንዲህ አይነት ድርቅ አይተን አናውቅም፤ ሰባሰባት እንኳን አንዲህ አልነበረም " በማለት የድርቁን አስከፊነት ገልጸዋል።

በወረዳው የአርሶ አደሩ ማሳ ርቃኑን ቀርቷል፣ እንስሳት ቆዳቸው ከስጋቸው መጣበቅ ብቻ ሳይሆን ነፍሳቸው በጣዕረሞት ላይ ናት፣  ህጻናት፣ እናቶችና አረጋውያን በርሀብ ተገርፈው ነፍሳቸው ከጉንጫቸው ተጣብቃ ይዛቸው ልትጠፋ አፋፍ ላይ ነች። ተሎ መድረስ ካልተቻለ አሳዛኝ ክስተት በሰሀላ ሰዬምት ወረዳ ሊከሰት ይቻላል።

የአስተዳደሩ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ጉዞ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን የብሄረሰቡ ከፍተኛ አመራሮችና አንዳንድ ግብረሰናይ ድርጅቶች በወረዳው ተገኝተው ቀበሌዎቹን ጎብኝተው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የቀበሌው ማህበረሰብ በውይይቱ ላይ " ከእግዚአብሄር በታች መንግስት ነበር ለሰው ልጅ ዋስትና፣ ዛሬ ግን መንግስትም ፊቱን አዞረብን " ብለዋል።

" በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚበላ ካልቀረበ ልጆቻችን አናገኛቸውም ፤ አሁንም ቢሆን አንዲት እንጀራ ለ10 ሰው ነው የምንሻማው፤ ከዛ ውጭ ግን ጨው በውሀ በጥብጠን ነው የምንጠጣው " ብለዋል።

እስካሁንም በወረዳው በርሀብ ምክኒያት የ2  ሰዎች ሂይወት አልፏል ሲሉ አሳውቀዋል።

እንስሳትን በተመለከተ " በወረዳችን ትንሽ እህል ካገኘን እንሰሳ ስለምናረባ ከብት እና ፍየሎቻችንን ሸጠን እህል ስለምንሸምት ብዙም አያሳስበንም ነበር፤ ዘንድሮ ግን ለከብቶችም ሆነ ለፍየሎችና በጎች የሚሆን የሚጋጥ ሳር ስለሌለ ተስፋ አስቆርጦናል " ብለዋል።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ፤ የተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ቃል ከመግባት የዘለለ በመንግስት በኩልም ምንም የቀረበ ነገር የለም።

ለክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሪፖርት ከማድረግ ባለፈ የችግሩን አሳሳቢነት ብንገልጽም እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ብለዋል።

መረጃው ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ነው የደረሰን።

@tikvahethiopia