TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን #ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! #TikvahFamily @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ 1 ሺህ 498ኛው የመውሊድ በዓል አከባበር በታላቁ አንዋር መስጊድ እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች።
Photo Credit - ENA / DW
@tikvahethiopia
Photo Credit - ENA / DW
@tikvahethiopia
#ዓዲግራት
በደም አፋሳሹ ጦርነት የወደሙ ተፈጥራአዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ለማደስ በትኩረት እንደሚሰራ የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ አስታወቀ።
ዩኒሸርስቲው የህንን ያስታወቀው የዘንድሮው የመስቀል በዓል በማስመልከት ባከናወነው ዓለምአቀፍ ኮንፈረንስ ነው ።
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ፕረዚደንት ዶ/ር ዛይድ ነጋሽ በኮንፈረንሱ መክፈቻ እንዳሉት ፤ ባለፉት ሁለት የጦርነት አመታት በቅርሶች ላይ የውድመትና የስርቆት ተግባራት መፈፀማቸው በቱሪዝም ኢንዱስትሪው አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሯል።
ፕረዚደንቱ አክለው እንዳሉት በአከባቢው በሚገኙ የአርኪኦሎጂ ማእከላት የደረሰው ጉዳት ከባድ መሆኑና በተለይ የአክሱም ቅድመ ስልጣነ ማሳያ መሆናቸው በቁፋሮ የተረጋገጠላቸው መዛብርና መነበይቲ የተባሉ ቦታዎች ለኤርትራ ቅርብ በመሆናቸው ያሉበት ሁኔታና የደረሰባቸው ውድመት ምንያህል እንደሆነ ማጥናት አልተቻለም ብለዋል።
የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ዶ.ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር በኩላቸው የማንነት ምንጭ የሆኑት የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ የሁሉም ዜጋ ርብርብ ይጠብቃል ፤ በተለይ በክልሉ የሚገኙ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ያለውን እምቅ የቱሪዝም ፀጋ በማጥናትና በማስተዋወቅ ወደ ጥቅም እንዲለወጥ በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ የአርኪኢሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ሃይላይ አፅብሃ ደግሞ ዓለምአቀፍ የቅርሶች ጥበቃ ስምምነት በጦርነት ወቅትና በኃላ መነሻ ማድረግ በቱሪዝምና አርኪኦሎጂ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ የአገር ውስጥና የውጭ ሙሁራን ያጠኑት መለስተኛ ጥናት መቅረቡንና ዩኒቨርስቲው ጥናቱን መነሻ በማድረግ ጉዳት የደረሰባቸው ቅርሶች በመለየት የመልሶ ማልማት ስራ እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በትግራይ ደረጃ በዓዲግራት ዓጋመ የሚከበረው የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ በዓዲግራት የኒቨርስቲ አዘጋጅነት በተከናወነው የባህልና የቱሪዝም ዓለምአቀፍ ኮንፈረስ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ብቻ ከ120 በላይ በአገር ውስጥና በውጭ ቱሪስቶች ሊጎበኙ የሚችሉ ውቅር አብያተ ክርስትያን እንዳሉ ያመለክታል።
በዓለም የቅርስ ጥበቃ ድርጅት ማለትም ዩኔስኮ የተመዘገበው የውቕሮው አልነጃሺ መስጊድ ፤ የአክሱም ቅድመ ስልጣኔ መገኛ መሆኑ በዓለም አቀፍ የቁፋሮ ባለሙያዎች (አርኪኦሎጂስቶች ) የተረጋገጡ መዛብርና መነበይቲ የቁፋሮ ማእከላትም በአከባቢው ይገኛሉ።
የዘንድሮ የመስቀል በዓል" ለሰላም ለመልሶ ግንባታ ስነ-ልቦናዊ ማገገም " በሚል መሪ ቃል በትግራይ ደረጃ በመቐለና በዓዲግራት ከተሞች በልዩ ድምቀትና ትኩረት እየተከበረ ይገኛል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ከተማ ዘግቧል ።
ዓዲግራት ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ነች።

ፎቶ ፦ የመስቀል #ደመራ_በዓል በአዲስ አበባ መስቀል ዐደባባይ ፤ ብፁዓን አባቶች ፣ ምዕመናን ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ እየተከበረ የሚገኘውን የመስቀል ደመራ በዓል የሚያሳዩ ፎቶዎች / ቪድዮዎችን በ @tikvahethmagazine ላይ የምንስቀምጥ ይሆናል። የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን /…
ፎቶ ፦ የ2016 ዓ.ም በዓለ መስቀል ደመራ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ባማረ መልኩ ተከብሯል።
በተለያዩ ከተሞች የነበረውን የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ፎቶዎችን በ @tikvahethMagazine ላይ መመልከት ይችላሉ።