#ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አስጠልላቸው የሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስደተኞች የዕርዳታ እህል በመቋረጡ፣ ሕይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑንና ለአገርም የደኅንነት ሥጋት መደቀኑ ተነገረ፡፡
ከጥቂት ወራት በፊት የዓለም የምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ ተፈጸመ ባሉት የዕርዳታ እህል ዝርፊያ ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ዕርዳታ ማቆማቸው ይታወሳል፡፡
የምግብ አቅርቦቱ እንደገና እንዲጀመር የኢትዮጵያ መንግሥት እየተነጋገርኩበት ነው ቢልም፣ ዕርዳታው እየቀረበ ባለመሆኑ በኢትዮጵያ የተጠለሉ የውጭ አገሮች ስደተኞች በምግብ ዕጦት እየሞቱና ሕመም ላይ መውደቃቸውን፣ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ምን አለ ?
- ኢትዮጵያ ስደተኞችን ተቀብላ ስታስተናግድ የዓለም አቀፉን ሕግ መሠረት በማድረግ ከለላና ጥበቃ የምታደርግ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለስደተኞች የሚቀርበው ዕርዳታ በመቆሙ ቀውስ ተፈጥሯል።
- በምግብ እጥረት ምክንያት የሚሞቱትና የሚታመሙት ወይም የሚቸገሩት ስደተኞች ብቻ ሳይሆኑ፣ ችግር ሲፈጠር በመሠረታዊነት የመጀመርያ ተጎጂ ሕፃናትና ሴቶች ናቸው።
- በመጠለያ ካምፕ የሚገኝን ሀብት አፈላልጎ ለመመገብ ጥረት በሚያደርግበት ወቅት፣ ስደተኞቹ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ግጭት ውስጥ ይገቡና ሰላማዊ የኑሮ ሁኔታን የሚያናጋ ነገር እየተፈጠረ ነው።
- በአሁኑ ወቅት ምግብ ነክ ድጋፎች እየቀረቡ ባለመሆናቸእ በቀጣይ አፋጣኝ ዕርምጃ ካልተወሰደ ችግሩ የከፋ ሊሆን ይቻላል። በሁሉም የአገሪቱ መጠለያ ካምፖች ችግሩ ተከቷል።
- በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ለመታደግ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ፤ በአጭር ጊዜ ዕርዳታው እንደገና ይጀመራል የሚል እምነት አለ።
በስደተኛ ቁጥር ፦
👉 በጋምቤላ ወደ 400,000
👉 በቦሎ መልካዲዳ በሶማሌ ክልል 200,000፣
👉 በቤኒሻንጉል አሶሳ ወደ 90,000፣
👉 በአፋር 68,000፣
👉 በሶማሌ ጅግጅጋ ወደ 50,000፣
👉 አማራ ክልል ባባት 25,000፣ መተማ ወደ 40,000፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ወደ 80,000 ስደኞች ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከ900,000 በላይ የሚሆኑት በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ናቸው።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ፣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ ለተረጂዎች እየቀረበ ባለመሆኑ ወደ 400,000 የሚጠጉ በጋምቤላ ክልል ውስጥ በካምፕ የሚገኙ ስደተኞች ሕይወት አደጋ ውስጥ መውደቁን ገልጾ አፋጣኝ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቋል፡፡
በጋምቤላ ክልል ከግንቦት 2015 ዓ.ም. ወር ጀምሮ ዕርዳታ ያላገኙ ስደተኞች (አብዛኞቹ ከደ/ሱዳን የተሰደዱ) በምግብ እጥረት የተነሳ በሚመጣ ረሃብ ለሞትና ለከፋ ሕመም እየተጋለጡ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ኮሚሽኑ ከስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ተቋም አገኘሁት ባለው መረጃ በምግብ እጥረት ምክንያት በጋምቤላ ብቻ 30 ሰዎች መሞታቸውን፣ 5 ዓመት ያልሞላቸው ሕፃናት ለከፋ ሕመም መጋለጣቸውን አስታውቋል፡፡
በተከሰተው የምግብ እጥረት የተነሳ ከስደተኞች መጠለያ ካምፕ ወጥተው ወደ ማኅበረሰቡ በሚገቡበት ወቅት ለሰላም ችግር መንስዔ መሆናቸው በኮሚሽኑ ሪፖርት የተገለጸ ሲሆን፣ ከመጠለያ ወጥተው በምግብ ስርቆት በመሰማራታቸውና ከቆሻሻ ላይ ምግብ ለማንሳት ሲጥሩ ሕይወታቸው ያለፉ መኖራቸውንም አስታውቋል፡፡
አሁን ላይ በርካታ ስደተኞች አደጋ ላይ በመሆናቸው የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትም ሆኑ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡ ኢሰመኮ አሳስቧል።
#ሪፖርተር
@tikvahethiopia

መስራት፣ ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ ገበያ እና ተባባሪ አጋሮቹ መካከል ባለው ስምምነት የተደራጀ ሲሆን ለመስራት የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማመልከቻዎች መከፈቱን ያስታውቃል። መርሃ ግብሩ በመላው ኢትዮጵያ 100 ሁለገብ የጊግ ስራዎች እና ፕሮፌሽናል የገበያ ቦታዎችን ይደግፋል።
መስራት ለሥራ ፈጣሪዎች ብጁ የምርት ስም ያለው የገበያ ቦታ ቴክኖሎጂን በማቅረብ፣ የብቃት ማጣሪያ አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት፣ የምስክር ወረቀቶችን በመሸለም እና የጊግ ሠራተኞችን ለሥራ በማቅረብ ለእነዚህ ሥራ ፈጣሪዎች የሚያስፈልጋችውን ድጋፍ ይሰጣል።
ድጋፋችን የንግድ ልማትን፣ የፋይናንስ አቅርቦትን እና የገበያ ትስስርን ያካትታል። በተጨማሪም፣ ለጊግ ኢኮኖሚ እና ለጊግ ሰራተኞች ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና መመሪያ ልማት እናበረታታለን እና ከህዝብ ሴክተር ተዋናዮች ጋር አንድ ላይ እንሰራለን።
ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች፡ በእዚህ ያመልክቱ
https://mesirat.org/apply
የማመልከቻ ገደብ፡ መስከረም 19, 2016 ሲሆን ለማንኛዉም አይነት ጥያቄዎች [email protected] ላይ ማቅረብ ይቻላል።

#አማራ
ከፊታችን ያሉት ሃማኖታዊ በዓላት በአደባባይ እንዲከበሩ ተፈቀደ።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በአማራ ክልል ለመውሊድ ፣ ደመራ እና መስቀል በዓላት መሰባሰብን ፈቀደ።
ዕዙ ፤ መስከረም 16 እና 17 /2016 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ እየሰራሁ ነው ብሏል።
ምንም እንኳን የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ቢከለከሉም መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀዱን ገልጿል።
ዕዙ ፤ እነዚህ መሰባሰቦች ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ የሚውሉ እንደሆነ አሳውቋል።
የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ገልጿል።
በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር #ግዴታ እንደተጣለ አሳውቋል።
በአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ ከክልሉ አስተዳደር አቅም በላይ በመሆኑ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተቀመጡ ክልከላዎች አንዱ ደግሞ " መሰባሰብ " ነው። ከቀናት በኃላ በሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት ላይ ስነሥርዓቶቹ ተከናውነው እስኪያልቁ መሰባሰብ መፈቀዱ ይፋ ተደርጓል።

#ትግራይ
በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የዛፍ አምበጣ መንጋ የታየ ሲሆን ይኸው መንጋ በዛፍና በደረሱ እህሎች ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የክልሉ እርሻና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።
የአምበጣ መንጋው ጉዳት ያደረሰባቸው የዞኑ ወረዳዎች ታሕታይ ኣድያቦ ፣ አስገደና ማእኸላይ ኣድያቦ የተባሉ ናቸው።
የአንበጣ መንጋው ከመስከረም 2/2016 ዓ.ም ጀምሮ መታየቱ የገለፀው ቢሮው ፤ በ471 ሄክታር መሬት በተካሄደው የኬሚካል መርጨት ስራ 17 በመቶ መከላከል መቻሉ በቢሮው የተባዮች መከላከል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መለስ ኣባዲ ገልፀዋል።
አሁን በክልሉ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን የተከሰተው የዛፍ አንበጣ መንጋ ወረራ ሙሉ በሙሉ ለመከላከል የሚያስችል የኬሚካል መርጫ መሳርያ እጥረት መኖሩንና አርሶ አደሩ በተቻለው ሁሉ በመጠቀም የመከላከል ስራው አጠናክሮ እንዲቀጥል ባለሙያው አሳስበዋል።
በዞኑ ማእኸላይ አድያቦ ወረዳ ደግሞ በ8 ቀበሌ ገበሬ ማህበራት 1950 ሄክታር አዝርእት የሸፈነ የበቆሎ ተባይ መታየቱ ተገልፀዋል።
በተያያዘ ዜና በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ ዓዘቦ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ወረራ በሁለት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት መታየቱንና በባለሙያዎችና በህዝቡ የተቀናጀ ተሳትፎ የመከላከለ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከክልሉ የእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

የመውሊድ በዓል ረቡዕ ይከበራል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 1498ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰዓወ) የመውሊድ በዓል የፊታችን ረቡዕ መስከረም 16 ቀን 2016 ዓ.ም በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር አሳውቋል።
ለበዓሉ አከባበር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከታላቁ አንዋር መስጂድ ጋር በቅንጅት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።
በዓሉ ረቡዕ ከጠዋት አንስቶ እስከ ቀን 7:00 ሰዓት ድረስ በታላቁ አንዋር መስጂድ እንደሚከበር ተመላክቷል።

" የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ አይቻልም "- አዲስ አበባ ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ #ኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።
ፖሊስ ምን አለ ?
- ህብረተሰቡ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የተከለከሉ ነገሮችን በፍጹም መያዝ አይገባውም። ለሚኖሩ ፍተሻዎችም መተባበር አለበት።
- በየአካባቢው በሚደመሩ ደመራዎች አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
- ከዚህ በፊት ደመራ ተደምሮባቸው የማያውቁ ቦታዎች #የጸብ_መነሻ እንዳይሆኑ የድሮዎቹን መጠቀም ይገባል።
- ርችት መተኮስ በፍጹም ክልል ነው። ክልከላው የተደረገው ርችትን ሽፋን በማድረግ ህገወጦች ህገወጥ የጦር መሳሪያቸውን የሚሞክሩበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ ሆነ ተቋም በህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድበታል።

" በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው " - ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሊቀመንበሩ ዶ/ር ጫኔ ከበደ ትላንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንደዋሉ አሳወቀ።
ፓርቲው ዶ/ር ጫኔ ፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው ብሏል።
በምን ምክንያት እንደተያዙም እስከዚህ ሰዓት ድረስ ማወቅ አልተቻለም ሲልም አክሏል።
ኢዜማ " ይህን መሰል ህግ እና ሥርዓት ያልተከተለ እርምጃ በፅኑ እናወግዛለን " ያለ ሲሆን ጉዳዩን በጥንቃቄ እና በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ አሳውቋል።
የፓርቲያው ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን እያንዳንዱን ሂደትም እየተከታተለ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ብስክሌት፣ የባለ አራት እግር እና ባለሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ ምሽት 12 ሰዓት አንስቶ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ተጣለ።
የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ለሞተር ብስክሌተኞች፣ የባለ አራት እግርና ባለሶስት እግር ባጃጅ አሽከርካሪዎች በሙሉ ባሰራጨው መልዕክት ከዛሬ መስከረም 14/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ማክሰኞ መስከረም 29/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 12:00 ድረስ ሞተር ብስክሌትን፣ የባለ አራት እግርና የባለሶስት እግር ባጃጅ ማሽከርከር ፍጹም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።
ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ነው ተብሏል።
ቢሮው ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ብሏል።
ይህንን በሚተላለፉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል ሲል አሳስቧል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያለው ነገር የለም።
ባለፈው ዓመት ሃምሌ ወር መጨረሻ ላይ ምክንያቱ በግልፅ ባልተነገረበት ሁኔታ የ " ሞተር ብስክሌት " ማሽከርከር ታግዶ ነሐሴ 15/2015 ዓ.ም ላይ እገዳው መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም።

#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ
በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic

#FireAlert - አዲስ አበባ ለቡ ጀርባ ትራኮን 75 የሚባለው አካባቢ በሚገኝ አንድ እየተሰራ ባለ የትራኮን ሪል ስቴት ህንፃ የእሳት አደጋ መነሳቱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
እሳቱን ለመቆጣጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።
በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምንም እንኳን የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች በስፍራው ቢገኙም እሳቱ እስካሁን እንዳልቆመ አስረድተዋል።
ቪድዮ - Al3X (Tikvah Family)

" በዓመት 44,000 በላይ የሚሆኑ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " - ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ
በኢትዮጵያ የካንሠር በሽታ #የከፋ_ደረጃ ላይ እየደረሰ በመሆኑ ማኅበረሰቡ ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ አሳስቧል።
የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " በእኛ አገር ሕሙማን ራሳቸውን ስለሚደብቁና ታክሞ መዳን አይቻልም ስለሚባል በሽታው በጣም እየከፋ ነው " ብለዋል።
ማኅበረሰቡ ወደ ሕክምና ተቋም በወቅቱ በመምጣት ከሕመሙ መዳን እንደሚችል ሊያውቅና ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባም ተጠይቋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ " በአሜሪካን አገር ግን ወደ 15 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ታክመው ድነው ሕይወታቸውን እየመሩ ነው " በማለት ከበሽታው መዳን እንደሚቻል አስረድተዋል።
አክለውም፣ " በኢትዮጵያ ሕሙማን ወደ ሕክምና ተቋም አለመምጣታቸውና ታክሞ መዳን እይቻልም የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ በመኖሩ ወደ 75 በመቶ የሚሆኑት ሕሙማን ሕይወታቸው ያልፋል " ነው ያሉት።
የድርጅቱ ሜዲካል ዳይሬክተር ናትናኤል አለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ባለፉት ዓመታት ውስጥ የካንሠር ሕሙማን ወደ ሕክምና የመምጣት ቁጥራቸው የመጨመር ሁኔታ ይታያል " ብለዋል።
አክለውም፣ " በየዓመቱ ከ60,000 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሠር በሽታ ይያዛሉ። ከእነዚህ ውስጥ 44,000 በላይ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸውን ያጣሉ " ነው ያሉት።
"ከካንሠር ሕመም መዳን ይቻላል ተገቢዉን ምርመራ እና ህክምና በተገቢዉ ጊዜ በማድረግ መዳን ይቻላል" ያሉት ናትናኤል (ዶ/ር)፣ የካንሠር ሕሙማን ሕይወታቸው የሚያልፍበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ " ሕሙማን ወደ ሕክምና ማዕከል የሚመጡት የሕመም ደረጃቸው ከፍ ካለ፣ ሥር ከሰደደ፣ መዳን የሚቻልበት ደረጃ ካለፈ በኋላ ነው " ብለዋል።
በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ያለበት ምክንያት ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ናትናኤል (ዶ/ር)፦
- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ መስፋፋት፣ በቂ ያልሆነ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤ መቀየር
- የሲጋራ፣ ሽሻ አጫሾች መበራከት የአልኮል መጠቀም
- ለተለያዩ ኬሚካሎች መጋለጥ
-ከተለያዩ ኢንᎊክሽኖች ጋር የሚያያዙ የካንሰር አይነቶች መበራከት
- በወቅቱ ሕክምና ሳያገኙ የኖሩ ሰዎች አሁን አሁን ወደ ሕክምና እየመጡ በመሆኑና ሌሎች መሰል ምክንያቶችን ጠቅሰዋል።
ወደ ሕክምና የሚመጡት 70 በመቶ የሚሆኑት የካንሠር ሕሙማን የህመሙ ደረጃ ከፍ ካለ እና ስር ከሰደደ መሆኑን ተናግረዋል። ለህሙማን ሁለንተናዊ የሆነ እንክብካቤ እና ድጋፍ ሁሉም ካለዉ ቀንሶ እንዲያደርግ፣ ማህበረሰቡም በካንሰር ላለመያዝ አጋላጮቹን መከላከል እና ቅድመ ምርመራ ላይ እንዲያተኩር አሳስበዋል።
ድርጅቱ የ20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በዛሬው ዕለት በማሪዮት ሆቴል ያከበረ ሲሆን፣ ድርጅቱ እስካሁን ከ3,000 ሺሕ በላይ የካንሠር ሕሙማን እንዳከመ፣ በአሁኑ ወቅት ከ150 በላይ ሕክምና የሚጠባበቁ እንዳሉ ተነግሯል።
መረጃው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።