በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ዛሬ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፣ ሶዶ ወረዳ በአናቲ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 4 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው።
የሶዶ ወረዳ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ፍሰት ቁጥጥር ማስተባበሪያ በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12 ሰአት ላይ ነው አደጋው የደረሰው።
አደጋው የህዝብ ማመላለሻ FSR የሰሌዳ ቁጥር " ደቡብ 13955 " የሆነ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆሳዕና ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ የሰሌዳ ቁጥሩ " B-20669 " ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨቱ የተፈጠረ ነው።
በዚህም አደጋው የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
ፖሊስ አደጋው የተከሰተበት ሰአት የአየር ንብረቱ ጭጋጋማ እንዲሁም አደጋ የደረሰበት አካባቢ መንገዱ ብልሽት ያለበት መሆኑን ገልጿል።
ይህ ቦታ በየጊዜው አደጋ እንደሚደርስበትና በተደጋጋሚ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት የሚቀጥፍበት ፣ ንብረትም የሚወድመት መሆኑ ተጠቁሟል። በመሆኑም አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ፖሊስ ማሳሰቡን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።
በተያያዘ መረጃ ፤ በዚህ እጅግ አሳዛኝ የትራፊክ አደጋ ፤ የሆሳዕና ከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ ዮናስ ዱባለን ጨምሮ አብረዋቸው የነበሩ ሁለት ጓደኞቻቸው ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።
በዚህም የሆሳዕና ከተማ ምዕመናን መሪር ሀዘን ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia

This could be you 2024 😊😊. Embarking on a path of value-based and ethical entrepreneurship can be challenging. By joining the Jasiri Talent Investor, you gain access to invaluable support, resources, and networking opportunities that will help you succeed in your venture. The deadline for applications is rapidly approaching. Take the first step on your entrepreneurial journey with us at https://jasiri.org/application!
የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ይበልጥ አስተማማኝ የሚያደርጉ የደህንነት እና ሌሎች ማሻሻያዎች መተግበራችንን በደስታ እንገልጻለን!
መተግበሪያዎን ለማዘመን: https://onelink.to/fpgu4m
ለተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/3t6gCgD
ቴሌብር የዲጂታል ኢትዮጵያ አውታር!

በ " ናዝሬት ትምህርት ቤት " እና በ " አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን " መሃከል የተፈጠረው ምንድነው ?
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የናዝሬት ትምህርት ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መሃከል በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት የናዝሬት ት/ቤት መደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መጀመር አለመቻላቸው ተገለፀ።
በሁለቱ አካላት መሃከል የተፈጠረው ውዝግብ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳስተጓጎለው ወላጆች ለቲክቫህ ገልፀዋል።
ውዝግቡ እንዴት ሊፈጠር ቻለ ?
- ናዝሬት ትምህርት ቤት ባሳለፍነው 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቱ ከሚማሩ ተማሪዎች መሀከል 15 ተማሪዎች ውጤት አጭበርብረዋል በማለት በዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት ከትምህርት ገበታ አግዷቸዋል።
- ይህንን ተከትሎ በናዝሬት ትምህርት ቤት ልጆቻቸው የታገዱባቸው የተማሪ ወላጆች ለአራዳ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
- ቅሬታቸውን የሰማው የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፤ ልጆቻቸው የታገዱባቸውን ወላጆች እና ናዝሬት ትምህርት ቤትን በጋራ ለማነጋገር ጥሪ አድርጎ ነገር ግን የናዝሬት ትምህርት ቤት የቦርድ አባላት ጉዳዮን ቀርቦ ለማስረዳት እንዳልቻሉ በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።
- የናዝሬት ትምህርት ቤት በበኩሉ "ጉዳዩን ቀርቤ ለማስረዳት ሞክሬ ነበር ነገር ግን የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የታገዱት ተማሪዎች በምን ምክንያት እንደታገዱ ሳይረዳ ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንድንመልሳቸው ጫና እያደረገብን ነው" በማለት ለጽ/ቤቱ በፃፉት ደብዳቤ ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
- አለመግባባቱን ተከትሎ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ጉዳዮን የበላይ አካል ወደ ሆነው የአዲስ አበባ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የወሰደው ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታገዱ ተማሪዎች ወላጆችን እና ትምህርት ቤቱን በጋራ ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካ ገልጿል።
- ይህንን ተከትሎ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ቤቱን እውቅና ፈቃድ አግዶ የነበረ ሲሆን በነሃሴ 19 2015 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ "ትምህርት ቤቱ የታገዱ ተማሪዎችን ለመመለስ ተስማምቷል" በማለት የእውቅና ፈቃድ እገዳውን ማንሳቱን አሳውቋል።
- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የእውቅና ፈቃድ እገዳውን አንስቻለሁ በማለቱ ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እንደገና ከባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ ምዝገባ አቁሙ የሚል የቃል ትእዛዝ መምጣቱን በመስከረም 4 , 2016 ዓ.ም ለወላጆች በማሳወቅ ምዝገባ በይፋ ማቆሙን አሳውቋል።
በዛሬው እለት ወላጆች መደበኛው ትምህርት እንዲጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርበው መነጋገራቸው የተገለፀ ሲሆን ከወላጆች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ወንድወሰን ሙሉጌታ የታገዱት ተማሪዎች ተመልሰው እንዲመዘገቡና አዲስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተቋቁሞ ታግደው የነበሩት ተማሪዎች ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ እንደተወሰነ ከቲክቫህ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ አንስተዋል።
የወላጅ ኮሚቴው ከሚመለከተው አካል ጋር ከተነጋገረ በኋላ ፤ በነገው እለት የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚጀምር ሲገለፅ ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ/ም በይፋ ትምህርት እንደሚጀመር ትምህርት ቤቱ አሳውቋል።

" ጉዳዩ ሳይከር ትኩረት ይሰጠው "
በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ወሰን አካባቢ የፀጥታ ችግር እንዳለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።
በዚህ የፀጥታ ችግር ሳቢያ ከሀረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ማስተጓጎል እንደተፈጠረ አመልክተዋል።
በአካባቢው የሚገኝ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ባቢሌ ዳከተ አካባቢ ግጭት መኖሩን ጠቁሞ በዚህም መንገድ መዘጋቱን አሳውቋል።
በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ጉዳት መድረሱን የጠቆመው የቤተሰባችን አባል አሁንም ችግሩ እንዳለ ጠቁመዋል።
ሌላ የቤተሰባችን አባል ፤ ከአዲስ አበባ ወደ ጅግጅጋ መስመር " ባቢሌ " አካባቢ ወይም በሁለቱ ክልሎች ወሰን መንገድ ላይ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አልፏል ብለዋል።
" ልዩ ኮሌጅ " ተብሎ የሚጠራበት ስፍራ ትናንት በፀጥታ ችግር አንድ ሰው እንደሞተ በአይናችን አይተናል ሶስት ሰው ቆስሎ ሆስፒታል ገብተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።
ዛሬ የተረጋጋ ቢሆንም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል ጉዳዩ ሳይከር የምመለከተው የፌዴራል አካል እልባት ቢሰጠው መልካም ነው ሲሉ አሳስበዋል።
በግጭቱ ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ ከትላንት አንስቶ መንገደኞች ከፍተኛ እግልት እንደገጠማቸውም ይኸው ቤተሰባችን ገልጿል።
" በበዓል ምክንያት ከስራ ወጥተን የምመለስበት ሰዓት ላይ እንዲህ አይነት ነገር መፈጠሩ በማህበረሰቡ ላይ ትልቅ ችግር እና በባቢሌ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል " ሲሉ ገልጿል።
ሌላው የቤተሰባችን አባል ፤ ባቢሌ መውጫ እና በባንባስ መካከል በተለምዶ " ዳከታ " እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።
ሁኔታው የነዋሪዎችን ደህንነት አደጋ ላይ እንደጣለው ጠቁመዋል። ግጭቱ ዛሬም ቀጥሎ እንደዋለ ገልጸዋል።
ችግሩ በሁለቱ ክልሎች መካከል የፍተሻ ቦታ ላይ #ከወሰን ጋር በተገናኘ የተፈጠረ እንደሆነ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ጥረት ቢያዳርግም አልተሳካም።

ዋትስ አፕ አዲሱን የቻናል ሥርዓቱን ጀመረ።
በ " ሜታ " ባለቤትነት ስር የሚገኘው ዋትስ አፕ የመልክእት መተግበርያ የቻናል ሥርዓትና ሌሎች አዳዲስ ማዘመኛዎችን ከ150 በላይ ሀገራት አስተዋውቋል።
ዋትስ አፕ ቻናል መመስረትና ማስተዳደር የሚያስችለውን አገልግሎት በሲንጋፖር እና ኮሎምቢያ ቢጀምርም ከዛሬ ሴፕቴምበር 19 ጀምሮ ስርጭቱን ወደቀሩት የዓለም ሀገራት አስፋፍቷል።
አዲስ ያስተዋወቀው ይህ ማዘመኛ ከ #ቴሌግራም ጋር ይበልጥ እንደሚያመሳስላቸው እየተነገረ ይገኛል።
በቀጣይም ዋትስ አፕ በሚደረጉለት አዳዲስ ማሻሻያዎች እንደ ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ቻናሎች መመስረትና ማስተዳደር እንዲሁም መልእክቶችን ከቻናሎች ወደ ግላዊ ማህደራቸው ማውረድ የሚያስችላቸውን ባህሪያት አካትቶ ብቅ ብሏል።
Follow the TIKVAH-ETHIOPIA channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Va9S9ChCXC3OmB1b7R2U

📣 Visit Oromia Hackathon 2023 ይቀላቀሉ !
ከመስከረም 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም የኦሮሚያን ይጎብኙ ሐካቶን ውድድር በአዲስ አበባ ይከናወናል።
ለመመዝገብ 👇https://forms.gle/AZcTaDhMfX257iWx8
የኦሮሚያ ቱሪዝም የወደፊት ርዕይን እንቃኛለን! 🏞🗺
በኹነቱ የሚጠበቁ፦
✨ የፈጠራ ቴክኖሎጂ መፍትሔዎች
✨ አነቃቂ ንግግሮች
✨ የትስስር ዕድሎች
✨ ሽልማቶችና ስጦታዎች
🔔ቀኑን ይመዝግቡ! እንዳያመልጥዎ!

" በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ ተጋልጧል " - ጃን አሞራ ወረዳ
በሰሜን ጎንደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ሰዎች እና እንስሳት እየሞቱ ነው ተባለ።
በሰሜን ጎንደር ዞን በምትገኘው ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ 13 ቀበሌዎች በክረምት ወራት ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ ህብረተሰቡ ለሞት እና ረሐብ መጋለጣቸውን የወረዳው ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸጋው ተሰማ ገልፀዋል ።
አስተዳዳሪው አክለውም በድርቁ ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች ፣6500 የጋማ ከብቶች እና 400 ዶሮዎች መሞታቸውን ገልጸው 1400 ሰዎች በድርቁ ምክንያት አካባቢውን ጥለው መሰደዳቸውን እና አሁንም ከ 58 ሺ በላይ ሰዎች የከፋ ረሃብ ላይ መውደቃቸውን አክለዋል።
ጃን አሞራ ወረዳ ውስጥ 38 ቀበሌዎች የሚገኙ ሲሆን በውስጡ ከ 230ሺ በላይ ህዝብ የሚኖር ሲሆን ከ 38 ቀበሌዎች ውስጥ በ13 ቀበሌዎች ውስጥ በክረምቱ ምንም አይነት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት ረሐብ እና ድርቅ መከሰቱ ነው የተገለጸው።
በዚህም ምክንያት ድርቁን ተከትሎ የተለያዩ ወረርሽኞች መከሰታቸውን እና በአተት ምክንያት ብቻ 6 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል።
ላለፉት ዓመታትም በወረዳው ድርቅ መከሰቱን የገለፁት አስተዳዳሪው የአሁኑ ግን ከዚህ በፊቱ የከፋ መሆኑን እና መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ዘገባው የሸገር ራድዮ ነው።
@TikvahethMagazine

" በድርቅ ምክንያት ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - ነዋሪዎች
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አፅቢ ወረዳ ባጋጠመው የድርቅ አደጋ ከ100,000 በላይ ነዋሪዎች ለአደጋ መጋለጣቸውን ተገለፀ።
በወረዳው የሚገኙትን ዘጠኝ ቀበሌዎች ለድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን ተገልጿል።
የአከባቢው ነዋሪዎች በክረምቱ በቂ ዝናብ መዝነብ ባለመቻሉ ከፍተኛ ድርቅ አደጋ መከሰቱን ገልፀዋል።
በዚህም በተለይም እንስሳት እየሞቱ መሆናቸውን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
" ምንም እንኳ አንዴ ሁለቴ በዘነበው ዝናብ አርሶ አደሩ ሰብል ለመዝራት ጥረት አድርጎ ቢሆንም ዝናቡ በመቋረጡ የተዘራው አዝርእት የእንስሳት ቀለብ እንዲሆን ተደርጓል " ብለዋ ነዋሪዎቹ።
በዚህም ነዋሪዎቹም ሆነ እንስሳቱ ለከፍተኛ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና የከፋ እልቂት እንዳይከሰት ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ተናግረዋል።
በመሆኑም የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፣ ፌደራል መንግስት ሆነ ለጋሽ ድርጅቶች እና በውጭ ሃገራት የሚገኙ የአፅቢ ወረዳ ተወላጆች እና ወዳጆች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ተማፅነዋል።
የወረዳዋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መዝገበ ግርማይ በበኩላቸው በክረምቱ ወቅት በወረዳዋ በሚገኙ 12 ቀበሌዎች 8445 ሄክታር መሬት በተለያዩ አዝርእቶች ተሸፍኖ የነበረ ቢሆንም ባጋጠመው የዝናብ እጥረት ምክንያት በዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ የሚገኘውን 7310 ሄክታር ታራሽ መሬት በከባድ ድርቅ መመታቱን ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት ከመቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች እና ከሁለት መቶ ሺህ በላይ እንስሳት ለምግብ እና ወሃ እጥረት ተጋልጠው በአደጋ ውስጥ በመሆናቸው የሚመለከተው ሁሉ ህይወት የማዳን ስራዎች እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበዋል ሲል ባልደረባችን መዝገበ ጎይቶኦም ዘግቧል።
ዘገባው የድምጺ ወያነ ነው።