TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል የትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ የፈተና ውጤትን በቀን 04/01/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይ (ከታች ባለው ሊንክ) በመግባት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ወደ ድረገፁ ሲገቡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

ተማሪዎች ሲስተሙን ለመጠቀም ፦ ይህን ሊንክ  https://sidama.ministry.et  በመጫን ፤ ፊት ለፊት በሚታየው  ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር በማስገባት ፤ " ውጤት ይመልከቱ " የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ፤ ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል። በተመሳሳይ በዛው ዕለት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ትምህርት ስርጭት ይጀምራል።

የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 እንደሚሰጥ የሚያሳየው የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር ከየካቲት 4 እስከ 8 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ወቅት እንደሆነ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር እንደሚያሳየው የካቲት 18 የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት የሚጀምር ሲሆን ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 23 የአጠቃላይ የትምህርት ማጠቃለያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል።

ከግንቦት 26 እስከ 30 የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 7 የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ የማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ጊዜ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።

የሁለተኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ወቅትም ከሰኔ 17 እስከ 21 ሲሆን ከሰኔ 24 - 28 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው ፈተና የማረም፣ ውጤር የሚጠናቀርበት ፣ እና የሚገለፅበት እንደሚሆን ካሌንደሩ ያሳያል።

ሰኔ 30 ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

* * * ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግ ማሳስቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
ይበልጥ ፈክታና ደምቃ እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ እንዲሁም የዳታ ጥቅሎቿ ላይ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም የሚያስጠቅም ስጦታን ይዛ የቀረበችውን ተናፋቂዋን አደይ አበባ የሞባይል ጥቅል በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በ*999# ለራስዎ ይግዙ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበረክቱ!

ወዳጅ ዘመድን የምታቀላቅል… አደይ አበባ ጥቅል

መልካም አዲስ ዓመት!!
ኢትዮ ቴሌኮም
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለ 50 ወለል ህንጻ ሊገነባ ነው። 

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ደቡብ ግሎባል ባንክ የተሰኘውን ስያሜውን እና የንግድ ምልክቱን ከቀየረ በኋላ ዋና መስሪያቤቱን በአዲስ አበባ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ባንኩ ለዋና መስሪያቤቱ ግንባታ ከ18 በላይ ድርጅቶችን የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ያወዳደረ ሲሆን የባንኩን የወደፊት መስሪያ ቤት ዲዛይን ኢላፕስ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ. ማህበር የሰራውን ዲዛይን አሸናፊ አድርጎ መርጧል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ፣ ለዋና መ/ቤት ግንባታ የሚሆን 5,500 ካሬ ቦታ መረከቡን የጠቆመው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፤ ዲዛይኑ ሁለት መንትያ ህንጻዎች ያሉት ብሏል።

በዚህም ትልቁ ህንጻ ከ50 ወለል በላይ ሕንጻ፣ ትንሹ ደግሞ ከ12 በላይ ፎቅ እንደሚኖረው የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተስፋዬ ቦሩ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ባንኩ አክሎም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቅርንጫፍን 152 መድረሱን ገልጾ በአዲሱ በጀት አመት የቅርንጫፎቹን ብዛት 185 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ግሎባል ባንክ 820 ሚሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከባንኩ ሰምቷል። ጠቅላላ የሀብት መጠኑም 20 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል።

Via @TikvahethMagazine
#ወባ

በቀድሞው ደቡብ ክልል ውስጥ በ2015 ዓ.ም ብቻ 447 ሺሕ ሰዎች በወባ መታመማቸው እና 24 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በቀድሞው ደቡብ ክልል የወባ በሽታ ማስወገድ ፕሮግራም አማካሪ አቶ ሔኖክ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " መረጃዎች እንደምያሳዩን በ2015 ዓ.ም 447 ሺሕ ሰዎች በወባ ታመዋል " ብለዋል።

" ከእነዚህ ውስጥ 24 ሰዎች ሞተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በበሽታው በቅርብ የተጠቁ ሰዎችን ሲያስረዱም፣ " በሁለት ወራት ውስጥ  የታመሙ ሰዎች ቁጥር ከ80 ሺሕ አልፏል። በሳምንት ከ9,000 እስከ 10,000 ሰዎች ይታመማሉ " ብለዋል።

" በሽታው በኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ " እንደሚስተዋል ያስረዱት አቶ ሔኖክ፣ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያሉ ችግሮች እየታዩ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የወባ ስርጭት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሔኖክ ፤ "በጉልህ ቀንሷል የሚያስብል ደረጃ ላይ አይደለም " ነው ያሉት።

አክለውም፣ " ከበፊት ካለው የመቀነስ ሁኔታ አሳይቷል። አስደሳች ግን አይደለም። ምናልባት የኬሚካል እርጭት በስፋት አካሂደን በጉልህ የሚቀንስበት ሁኔታ ይኖራል የሚል እምነት ይኖረናል " ብለዋል።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎችን ምጣኔ በተመለከተ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ አቶ ሔኖክ፣ " በቁጥራዊ ደረጃ ሲታይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 7,000፣ በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ2,000 እስከ 3,000 ሰዎች በሳምንት በወባ ምክንያት ይታመማሉ " ሲሉ
ተናግረዋል።

አማካሪው፣ " በእርግጥ የተለመዱ የወባ ወረርሽኝ ማስቆሚያ ዘዴዎች ወይም መፍትሄዎች ሲተገበሩ አልነበሩም " ብለው፣ " በፌደራል መንግሥት በኩል ነበር የሚቀርበው እነርሱም በሒደት እየሰሩ ነበር። አሁን ተሳክቶ የወባ አስተላላፊ ትንኝ ዕጭ መግደያ ኬሚካሎችን ተቀብለናል። አሁን ወደ እርጭት እየተገባ ያለበት ሁኔታ አለ " ሲሉ አስረድተዋል።

" በየሳምንቱ በአማካኝ ከ9,000 እስከ 10,000 ሰዎች ይታመማሉ። ባሳለፍናቸው ዘጠኝ ሳምንታት ውስጥ ከ80 ሺሕ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ታመዋል " ሲሉ አክለዋል።

" በ2015 ዓ.ም 24 ሰዎች ናቸው በወባ ምክንያት ሞተዋል " ያሉት አማካሪው፣ " አሁን አዲሱን ዓመት (2016) ከተቀበልን ጀምሮ በወባ ምክንያት የሞተ ሰው የለንም። የሚታመሙ ሰዎች ግን በርካታ ናቸው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ፣ "በተመሳሳይም በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው ዝናብ ከመዝነቡ ጋር ተያይዞ የወባ ወረርሽኝ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ተከስቷል" ብሏል።

የወባ ወረርሽኝ ተከስቷል የተባለው፣  " በጋሞ፣ ጌድዮ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና አሌ፣ አማሮ እና ቡርጂ  ወረዳዎች" በሚገኙበት ክልል ነው።

ኢሰመኮ ይህን ያለው መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው የመጀመሪያው የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዓመታዊ ሪፖርት ነው።

የወባ በሽታ ማስወገድ ፕሮግራም አማካሪ አቶ ሔኖክ በበኩላቸው የኢሰመኮን ሪፓርት በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ለረጅም ጊዜ ባለመዝነቡ የወባ በሽታ ተከስቷል መባሉ ትክክል መሆኑን ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ " የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት #ሀገር_አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11/2016 ዓ/ም ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ #የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር #አስረግጦ ተናግሯል ፤ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ/ም የትምህርት መስከረም 7/2016 ዓ/ም እንደሚጀምር ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#CBE

ነጋዴ ነዎት?

እንግዲያውስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርቻንት አፕ (Merchant APP) ተጠቅመው ክፍያዎትን ይቀበሉ።
==========

መርቻንት አፕ ነጋዴዎች ወይም የሽያጭ ባለሙያዎች ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡

መተግበሪያውን ከ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbebirr.merchantapp አውርደው በመጫን ባቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ይመዝገቡና መለያ ቁጥር (Till No.) ይውሰዱ ። ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር (Till No.) ወስደው ከሆነ በቀጥታ መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ፡፡

አጠቃቀሙ

1. መተግበሪያውን ከፍተው የደንበኛውን ስልክ ቁጥር በማስገባት ክፍያውን ያስጀምሩ፣

2. ገዥው የነጋዴውን መለያ ቁጥር (Till No.) እና የክፍያውን መጠን የያዘ መልእክት ስልኩ ላይ ይደርሰዋል። ትክክለኛነቱን አረጋግጦ የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) በማስገባት ክፍያውን ያከናውናል፡፡

3. የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል። አለቀ፡፡
#Update

ሪድም ዘ ጀኔሬሽን "Advocating Peace Through Art" በሚል ባዘጋጀው የቡድን ስዕል ውድድር ላይ ከተሳተፉ 13 ቡድኖች አሸናፊዎች ተለዩ።

በዚህም፦

-  " ስክነት " በሚል ርዕስ የተሳለው ሥዕል በዳኞች ምርጫ አሸናፊ ሆኗል።

-  " የሰጎን እንቁላል " በሚል ርዕስ የተሳለው ሥዕል ደግሞ በዳኞች በሁለተኛ ደረጃ የተመረጠ ሥዕል ሆኗል።

-  " ሰላምን በህብረት መጠበቅ " በሚል ርዕስ የተሳለው ሥዕል በዳኞች ምርጫ ሦስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

-  በማኅበራዊ ሚዲያ በነበረ ቅስቀሳ ደግሞ " ማኅቶት " በሚል ርዕስ የተሳለው ሥዕል ከፍተኛ ድምጽ ያገኘ በሚል ተመርጧል።

አሸናፊው ቡድን የ60 ሺ ብር ሽልማት ያገኘ ሲሆን ለሁለተኛ እንዲሁም ሦስተኛ ለወጣው ደግሞ የ40 ሺ እና የ20 እንደየቅደም ተከተላቸው አሸንፈዋል። ከፍተኛ የተመልካች ድምጽ ያገኘው ቡድን ደሞ የ10 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የሥዕሎቹን መልዕክት ያንብቡ https://telegra.ph/Peace-09-16

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

አባ ገዳዎች እና ሃዳ ሲንቄዎች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ብለዋል።

የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27/2016 ዓ.ም በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር ይፋ አድርገዋል።

የቱለማ አባገዳና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ፀሓፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ፤ " የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት እሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል " ሲሉ ገልጸዋል።

'' ኢሬቻ እርቅና ሰላም በመሆኑ የዘንድሮው ኢሬቻ በደስታ፣ በአንድነትና በፍቅር ይከበራል '' ብለዋል።

የሲኮ መንዶ አባገዳና የህብረቱ አባል አባ ገዳ አሊይ መሐመድ ሱሩር ፤ "  ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት በመሆን በዓሉን ማክበር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲዉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሃዳ ሲንቄ አፀዱ ቶላ በበኩላቸው ፤ '' ኢሬቻ ሰላም መሆኑንና የሰላም እናት መሆናችንን በአንድነት የምናሳይበት በዓል ነው '' ብለዋል።

'' ኢሬቻ የይቅርታ፣ የተጣለ የሚታረቅበት፣ የተለያዩ የሚገናኙበትና ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው '' ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም  " በዓሉ ያለምንም ችግር እንዲከበር፣ በሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር እንዲፀና ሃዳ ሲንቄዎች በትብብር ይሰራሉ  " ብለዋል።

ሃዳ ሲንቄ ጫሊ ቱምሳ ፤ " ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ መከበር አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ወጣቶችና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በዓሉ ያማረና የተሳካ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ኢዜአ / ፋይል

@tikvahethiopia