TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#VISA

Big congratulations to Kacha Digital Finance Service for being crowned the overall winner of the 2023 Ethiopian edition of the Visa Everywhere Initiative (VEI) innovation program and competition for start-ups and fintech companies. Kacha received a $25,000 USD monetary prize while Qena who finished in second place won $15,000 USD with Smile Pay, receiving $10,000 USD for clinching third place. We received over 170 applications for the 2nd VEI Ethiopia Edition and top 4 start-ups got a chance to present their solutions in the presence of esteemed judges, panelists, speakers and invited guests. 

#Everywhereinitiative
የሳፋሪኮም ማህበራዊ ሚዲያ ጥቅሎችን በመግዛት ከምንወዳቸው ጋር አብሮነታችንን እናጠናክር

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#ኮሌራ #አማራ_ክልል

በአማራ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የሱዳን ጦርነትን ሸሽተው አማራ ክልል የገቡ የሱዳን ዜጎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር /UNHCR/ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ በተቋቋመ የኩመር መጠለያ ጣቢያ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሠተና ዘጠኝ #ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሞቱ አሳውቋል።

395 ሰዎች ደግሞ እንደታመሙም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ማርጋሬት አትዬኖ ፤ በሱዳኑ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ብዛት፣ ከ35 ሺሕ በላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ከእኒዚም ውስጥ፣ 10 ሺሕ የሚደርሱት ፤ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በሚገኝ የኩመር መጠለያ ጣቢያ እንደተጠለሉ ሌሎቹ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሸርቆሌ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ፤ በአማራ ክልል ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ 6 ቀናት የኮሌራ በሽታ ክትባት መሰጠት ዘመቻ እንደተጀመረ ተጋጿል።

ክትባቱ እድሜያቸው አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች  ነው የሚሰጠው።

የክትባት ዘመቻው አስቻይ ሁኔታዎች አሉባቸው በተባሉት ባሕር ዳርና ጎንደር ከተማን ጨምሮ 9 ወረዳዎች ላይ ይሰጣል ፤ በዚህም ለ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ክትባቱን ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል።

አሁን ላይ በአማራ ክልል በ28 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።

በዚህም ከ3 ሺህ 8 መቶ በላይ ሰዎች በበሽታው የተጠቁ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።

በየቀኑ ከ15 እስከ 20 ሰዎች በአዲስ በበሽታው እየተጠቁ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።

(ስለ ኮሌራ መተላለፊና መከላከያ መንገዶች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
#ዓለምአቀፍ #ፖላንድ

በፖላንድ ፤ እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ #ኦዲት ሊደረግ ነው ተባለ።

በፖላንድ ለአፍሪካውያን በክፍያ ቪዛ እየተሰጠ ነው በሚል መንግሥት ላይ ጥያቄ ማስነሳቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የፖላንድ የላይኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቶማዝ ግሮዲዚ በአገሪቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ቪዛ የመስጠት አካሄድ ተባብሷል ብለዋል።

መንግሥት ስለ ጉዳዩ ምን መረጃ እንዳለው ይፋ እንዲያደርግም ጠይቀዋል። ነገሩ የአገሪቱን ስም እያጠለሸ ነው ብለዋል።

መንግሥት የተወሰነ መረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን ፤ እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ግን ስደተኞች እስከ 5,000 ዶላር እየከፈሉ የሥራ ቪዛ የማግኘት ሂደቱን ያፋጥናሉ ተብሏል።

እስካሁን ሰባት ሰዎች ላይ ክስ ቢመሠረትም ከመካከላቸው የመንግሥት ባለሥልጣን እንደሌለ ታውቋል።

የአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮር ዋውዚክ ፤ ባለፈው ሳምንት ክሶችን ተከትሎ ከሥራ ተነስተዋል። የፖላንድ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው የተባረሩት።

የሕግ ክፍሉ ዳይሬክተርም ተባረዋል።

እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ ኦዲት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል ፤ እስከ 250,000 ቪዛዎች ሕግ ሳይከተሉ ለእስያ እና አፍሪካ አመልካቾች ተሰጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት ግን ቁጥሩ በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠር ነው ሲል አስተባብሏል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶናልድ ተስክ ፤ " ከአፍሪካ ፖላንድ መምጣት የፈለገ ሁላ ከኤምባሲያችን ቪዛ ገዝቶ አገራችን በቀላሉ ይገባል " ብለዋል።

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ይህ ንግግር ቀውስ እንደሚያስከትል ገልጸው ችግሩ የተባለውን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" አገራችን ኃላፊነት የሚሰማት ዴሞክራሲያዊ አገር ሆና ሳለ የነጻውን ዓለም ደኅንነት አደጋ ውስጥ የምትከት ሆና እንድትታይ የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ በጥልቀት ሊብራራ ይገባል። ይህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ቅሌት ነው። ሙስና በመንግሥታችን ተንሰራፍቷል " ሲሉ የላይኛው ምክር ቤት አባል አሳስበዋል።

የፍትሕ ሚኒስተሩ ዚግኒው ዚዎብሮ ፤ ይህ አባባል የተጋነነ ነው ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ይህ ጉዳይ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያ በቀጣዩ የፓርላማ ምርጫ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መገለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የሲዳማ ክልል የትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ የፈተና ውጤትን በቀን 04/01/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይ (ከታች ባለው ሊንክ) በመግባት ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ወደ ድረገፁ ሲገቡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

ተማሪዎች ሲስተሙን ለመጠቀም ፦ ይህን ሊንክ  https://sidama.ministry.et  በመጫን ፤ ፊት ለፊት በሚታየው  ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር በማስገባት ፤ " ውጤት ይመልከቱ " የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ፤ ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል። በተመሳሳይ በዛው ዕለት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ትምህርት ስርጭት ይጀምራል።

የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 እንደሚሰጥ የሚያሳየው የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር ከየካቲት 4 እስከ 8 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ወቅት እንደሆነ ገልጿል።

የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር እንደሚያሳየው የካቲት 18 የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት የሚጀምር ሲሆን ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 23 የአጠቃላይ የትምህርት ማጠቃለያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል።

ከግንቦት 26 እስከ 30 የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 7 የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ የማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ጊዜ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።

የሁለተኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ወቅትም ከሰኔ 17 እስከ 21 ሲሆን ከሰኔ 24 - 28 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው ፈተና የማረም፣ ውጤር የሚጠናቀርበት ፣ እና የሚገለፅበት እንደሚሆን ካሌንደሩ ያሳያል።

ሰኔ 30 ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

* * * ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግ ማሳስቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
ይበልጥ ፈክታና ደምቃ እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ እንዲሁም የዳታ ጥቅሎቿ ላይ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም የሚያስጠቅም ስጦታን ይዛ የቀረበችውን ተናፋቂዋን አደይ አበባ የሞባይል ጥቅል በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በ*999# ለራስዎ ይግዙ ለሚወዷቸው በስጦታ ያበረክቱ!

ወዳጅ ዘመድን የምታቀላቅል… አደይ አበባ ጥቅል

መልካም አዲስ ዓመት!!
ኢትዮ ቴሌኮም
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባለ 50 ወለል ህንጻ ሊገነባ ነው። 

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ደቡብ ግሎባል ባንክ የተሰኘውን ስያሜውን እና የንግድ ምልክቱን ከቀየረ በኋላ ዋና መስሪያቤቱን በአዲስ አበባ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ባንኩ ለዋና መስሪያቤቱ ግንባታ ከ18 በላይ ድርጅቶችን የአርኪቴክቸራል ዲዛይን ያወዳደረ ሲሆን የባንኩን የወደፊት መስሪያ ቤት ዲዛይን ኢላፕስ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ. ማህበር የሰራውን ዲዛይን አሸናፊ አድርጎ መርጧል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ፣ ለዋና መ/ቤት ግንባታ የሚሆን 5,500 ካሬ ቦታ መረከቡን የጠቆመው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ፤ ዲዛይኑ ሁለት መንትያ ህንጻዎች ያሉት ብሏል።

በዚህም ትልቁ ህንጻ ከ50 ወለል በላይ ሕንጻ፣ ትንሹ ደግሞ ከ12 በላይ ፎቅ እንደሚኖረው የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተስፋዬ ቦሩ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ባንኩ አክሎም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቅርንጫፍን 152 መድረሱን ገልጾ በአዲሱ በጀት አመት የቅርንጫፎቹን ብዛት 185 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

በተጠናቀቀው በጀት አመት ግሎባል ባንክ 820 ሚሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከባንኩ ሰምቷል። ጠቅላላ የሀብት መጠኑም 20 ቢሊዮን ብር መድረሱን ገልጿል።

Via @TikvahethMagazine
#ወባ

በቀድሞው ደቡብ ክልል ውስጥ በ2015 ዓ.ም ብቻ 447 ሺሕ ሰዎች በወባ መታመማቸው እና 24 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በቀድሞው ደቡብ ክልል የወባ በሽታ ማስወገድ ፕሮግራም አማካሪ አቶ ሔኖክ በቀለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " መረጃዎች እንደምያሳዩን በ2015 ዓ.ም 447 ሺሕ ሰዎች በወባ ታመዋል " ብለዋል።

" ከእነዚህ ውስጥ 24 ሰዎች ሞተዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በበሽታው በቅርብ የተጠቁ ሰዎችን ሲያስረዱም፣ " በሁለት ወራት ውስጥ  የታመሙ ሰዎች ቁጥር ከ80 ሺሕ አልፏል። በሳምንት ከ9,000 እስከ 10,000 ሰዎች ይታመማሉ " ብለዋል።

" በሽታው በኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ " እንደሚስተዋል ያስረዱት አቶ ሔኖክ፣ በእነዚህ አካባቢዎች ሰፋ ያሉ ችግሮች እየታዩ ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የወባ ስርጭት በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ከቲክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሔኖክ ፤ "በጉልህ ቀንሷል የሚያስብል ደረጃ ላይ አይደለም " ነው ያሉት።

አክለውም፣ " ከበፊት ካለው የመቀነስ ሁኔታ አሳይቷል። አስደሳች ግን አይደለም። ምናልባት የኬሚካል እርጭት በስፋት አካሂደን በጉልህ የሚቀንስበት ሁኔታ ይኖራል የሚል እምነት ይኖረናል " ብለዋል።

በበሽታው የሚጠቁ ሰዎችን ምጣኔ በተመለከተ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ አቶ ሔኖክ፣ " በቁጥራዊ ደረጃ ሲታይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 7,000፣ በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ2,000 እስከ 3,000 ሰዎች በሳምንት በወባ ምክንያት ይታመማሉ " ሲሉ
ተናግረዋል።

አማካሪው፣ " በእርግጥ የተለመዱ የወባ ወረርሽኝ ማስቆሚያ ዘዴዎች ወይም መፍትሄዎች ሲተገበሩ አልነበሩም " ብለው፣ " በፌደራል መንግሥት በኩል ነበር የሚቀርበው እነርሱም በሒደት እየሰሩ ነበር። አሁን ተሳክቶ የወባ አስተላላፊ ትንኝ ዕጭ መግደያ ኬሚካሎችን ተቀብለናል። አሁን ወደ እርጭት እየተገባ ያለበት ሁኔታ አለ " ሲሉ አስረድተዋል።

" በየሳምንቱ በአማካኝ ከ9,000 እስከ 10,000 ሰዎች ይታመማሉ። ባሳለፍናቸው ዘጠኝ ሳምንታት ውስጥ ከ80 ሺሕ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ታመዋል " ሲሉ አክለዋል።

" በ2015 ዓ.ም 24 ሰዎች ናቸው በወባ ምክንያት ሞተዋል " ያሉት አማካሪው፣ " አሁን አዲሱን ዓመት (2016) ከተቀበልን ጀምሮ በወባ ምክንያት የሞተ ሰው የለንም። የሚታመሙ ሰዎች ግን በርካታ ናቸው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ፣ "በተመሳሳይም በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው ዝናብ ከመዝነቡ ጋር ተያይዞ የወባ ወረርሽኝ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ተከስቷል" ብሏል።

የወባ ወረርሽኝ ተከስቷል የተባለው፣  " በጋሞ፣ ጌድዮ፣ ጎፋ፣ ኮንሶ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች እና አሌ፣ አማሮ እና ቡርጂ  ወረዳዎች" በሚገኙበት ክልል ነው።

ኢሰመኮ ይህን ያለው መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው የመጀመሪያው የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዓመታዊ ሪፖርት ነው።

የወባ በሽታ ማስወገድ ፕሮግራም አማካሪ አቶ ሔኖክ በበኩላቸው የኢሰመኮን ሪፓርት በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ለረጅም ጊዜ ባለመዝነቡ የወባ በሽታ ተከስቷል መባሉ ትክክል መሆኑን ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 7 ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት የፊታችን ሰኞ መስከረም 7 /01/2016 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ተቋማት እንደሚጀምር አስታወቀ።

ቢሮው ይህን ያሳወቀው የትምህርት ሚኒስቴር የ2016 ዓ/ም የትምህርት ካላንደርን ለህዝብ ካሰራጨ በኃላ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው አጭር መልዕክት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ፤ " የ2016 የትምህርት ዘመን ትምህርት መስከረም 14 /1/2016 ዓ.ም እንደሚጀመር በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #የተሳሳተ ነው " ብሏል።

ቢሮው በየትኞቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ እንደተሰራጨ በግልፅ አላሰፈረም።

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ይፋ ባደረገው የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት #ሀገር_አቀፍ የትምህርት ካላንደር መሰረት ከመስረም 7 እስከ 11/2016 ዓ/ም ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።

መስከረም 14 ደግሞ የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ካላንደሩ ላይ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ #የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ ይደረግ ብሏል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከዚህ ቀደም ይፋ ባደረገው መሰረት የ2016 ዓ/ም ትምህርት ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም ተቋም እንደሚጀምር #አስረግጦ ተናግሯል ፤ መላው የትምህርት ማህበረሰብ ይህን እንዲያውቀው ብሏል።

ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2016 ዓ/ም የትምህርት መስከረም 7/2016 ዓ/ም እንደሚጀምር ማሳወቁን መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia