TIKVAH-ETHIOPIA
" ክትትል እየተደረገ ነው ፤ በወረርሽኝ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች አሉ " - ወ/ሮ ሰላማዊት ግርማቸው (በኢሰመኮ የሰሜንና ማዕከላዊ ሪጅን የክትትልና ምርመራ ዳይሬክተር) በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በማቆያና በፓሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች እንዳሉና በእነዚህ ወገኖች የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ላይ ክትትል እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።…
#አማራ_ክልል
ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ #አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ #አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ_ክልል ከትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ #አሳሳቢነታቸው የቀጠለ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
#አማራ
በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ውስጥ ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውንና የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ጎዳና ላይ የነበሩ ሰዎች ማቆያ መገኘቱ ይፋ ተደርጓል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የታሰሩ ሰዎችም የተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው እንዲረጋገጥ ተጠይቋል።
ኮሚሽኑ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል።
ኮሚሽኑ ፦
- ከነዋሪዎች፣
- ከተጎጂዎች፣
- ከተጎጂ ቤተሰቦች
- ከዐይን ምስክሮች ባሰባሰባቸው መረጃዎች መሠረት የትጥቅ ግጭቱ ወደ ክልሉ ልዩ ልዩ ወረዳዎች መስፋፋቱን ተረድቷል" ሲል የጠቀሰው መግለጫው፣ "በነዋሪዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳትም ተባብሶ ቀጥሏል" ብሏል።
" ለምሳሌ ከነሐሴ 19 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በተለይም ፦
- በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ፣
- በሰሜን ጎጃም ዞን አዴትና መራዊ፣
- በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር፣
- በማእከላዊ ጎንደር ዞን ደልጊ፣
- በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ፣ ሸዋ ሮቢት እና አንጾኪያ ከተሞች እና በአካባቢዎቻቸው በሚገኙ አንዳንድ የገጠር ቀበሌዎች በግጭቱ ዐውድ በርካታ ሲቪል ሰዎች መሞታቸውን " አስታውቋል።
ኢሰመኮ አክሎ፣ " ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውን እና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው ለመረዳት ተችሏል " ብሏል።
ኮሚሽኑ በመግለጫው፣ " በተኩስ ልውውጦች ወይም በከባድ መሣሪያ ተኩስ ከሚሞቱ ሰዎች መካከል በመንገድና በእርሻ ሥራ ላይ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ የነበሩ ሰዎች ጭምር የሚገኙ መሆኑን ቤተሰቦች እና የዐይን ምስክሮች ያስረዳሉ " ሲል አስገንዝቧል።
" በዚሁ የግጭቱ ዐውድ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከሕግ/ፍርድ ውጭ የተፈጸሙ ግድያዎች (extrajudicial killings) እጅግ አሳሳቢ ነው "ም ብሏል።
" ለምሳሌ ከሐምሌ 24 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ በተለይም ፦
- በአዴት፣
- በደብረማረቆስ፣
- በደብረ ታቦር፣
- በጅጋ፣
- በለሚ፣
- በማጀቴ፣
- በመራዊ፣
- በመርጦ ለማርያምና ሸዋ ሮቢት ከተሞች ተስፋፍተው በተፈጸሙ ከሕግ/ፍርድ ውጪ የሆኑ #ግድያዎች ሰለባ " የሆኑ ሰዎች እንዳሉ መግለጫው ያስረዳል።
ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች " በተፈጸመ ከሕግ አግባብ ውጭ ከሆኑ ሰዎች መካከል ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ የተያዙ ሰዎች፣ በግጭቱ ወቅት መንገድ ላይ የተገኙ እና ያልታጠቁ ሰዎች፣ ' የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል አምጡ ' በሚል የተያዙ ሰዎች፣ የሰዓት እላፊ ገደቦችን ተላልፈው የተገኙ ሲቪል ሰዎችና በቁጥጥር ስር የዋሉ የታጣቂው ቡድን (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚታወቀው) አባላት የሚገኙበት ሲሆን፤ በኮሚሽኑ እና በአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርዱ አማካኝነት የተሟላ ምርመራ ሊደረግበት የሚያስፈልግ ነው " ይላል መግለጫው።
" ከዚህ በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ኮማንድ ፖስት በይፋ ካሳወቃቸው እስሮችና ቦታዎች ውጪ በተለይ በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐውዱ የተስፋፋና የዘፈቀደ እስር የተፈጸመ "ም ተመላክቷል።
ኮሚሽኑ ይህን ሲያብራራም፣ "ለምሳሌ በአማራ ክልል ፦
- በባሕር ዳር፣
- በደብረ ታቦር፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በፍኖተ ሰላም፣
- በጎንደር፣
- በላሊበላ፣
- በመካነሰላም፣
- በቆቦ እና በሸዋ ሮቢት ከተሞች፤ በኦሮሚያ ክልል በተለይ #በሸገር ከተማ እና #በአዲስ_አበባ ከተማ የተፈጸሙ የዘፈቀደ እስሮች ይገኙበታል " ሲል አክሏል።
" ከእነዚህ ታሳሪዎች ውስጥ በደቡብ ክልል ፖሊስ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ (በተለምዶ አቦስቶ በመባል የሚታወቀው ቦታ) የነበሩ ታሳሪዎችን ጨምሮ ከተለያየ ጊዜ መጠን በኋላ የተለቀቁ መኖራቸውን ማወቅ የተቻለ ቢሆንም፤ በአንጻሩ ገና ቁጥራቸው በትክክል ያልታወቀ ሰዎች ይህ መግለጫ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በእስር ላይ ይገኛሉ " ነው ያለው።
እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ፣ " በመንግሥት የጸጥታ አካላት የሚታሰሩ ሰዎች በአብዛኛው ' ለታጣቂ ቡድኑ ድጋፍ ታደርጋላችሁ ' እና/ወይም 'የጦር መሣሪያ ደብቃችኋል ' በሚል ምክንያት ነው " ብሏል።
አክሎም ፣ " በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ገላን ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲዳ አዋሽ ወረዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ውስጥ ተይዘው የነበሩ " ሰዎች ማረጋገጡን አስታውቋል።
" ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊትና በኋላም ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ሕፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ውሏቸውን ጎዳና ያደረጉ ነዋሪዎች ከጎዳና ላይ ተነስተው እንዲቆዩ የሚደረግበት ቦታ መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ፤ በቅርቡ ወደ ማእከሉ ከተወሰዱት ውስጥ 29 ሰዎች በመታወቂያ ካርዳቸው ተለይተው እንዲለቀቁ መደረጉን " አትቷል።
አክሎም ፤ " የተወሰኑት ደግሞ በመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም ወደየመጡበት አካባቢዎች እንዲመለሱ የተደረገ መሆኑን፣ በጣቢያው ውስጥ ተከስቶ የነበረው ተላላፊ በሽታ በቁጥጥር ስር የዋለ መሆኑን ኮሚሽኑ በክትትሉ ተመልክቷል " ብሏል።
ኮሚሽኑ በመጨረሻም የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ጨምሮ ፤ " በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት የታሰሩ ሰዎችም የተጠረጠሩበት ወንጀል ምርመራ በአስቸኳይ በማጠናቀቅ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው እንዲረጋገጥ " ሲል ጠይቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያዘጋጀው #ከኢሰመኮ በተላከለት መግለጫ ነው።

" በክልሌ ውስጥ ምንም አይነት የማቆያ ካምፕ የለም " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት " በክልሌ ውስጥ ምንም አይነት የማቆያ ካምፕ የለም " አለ።
የክልሉ መንግሥት ይህንን ያለው ዛሬ ምሽት " የሀሰት መረጃ " በሚል በተረጋገገጠ የኮሚኒኬሽን ቢሮ የማህበራዊ ትስስር ገፁ በኩል ባወጣው አጭር የፅሁፍ መግለጫ ነው።
በዚህም ፅሁፉ ፤ " ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት #በሸገር እና #ፊቼ ከተሞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የማያውቃቸው የማቆያ ካምፕ እንዳለ ተደርጎ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ህዝብን የሚያደናግር ሃሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
ነገር ግን " በተጠቀሱ ከተሞችም ሆነ አጠቃላይ በክልላችን ምንም ዓይነት የማቆያ ካምፕ የለም " ሲል የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

ቪድዮ ፦ በአሜሪካ ፤ የፍሎሪዳ ግዛት አቃቤ ህግ በደህንነት ካሜራ የተቀረፀ ቪድዮ አሰራጭቷል።
በዚሁ በደህንነት ካሜራ በተቀረፀው ቪድዮ ፤ በማያሚ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የደህንነት / ፍተሻ ሰራተኞች ከመንገደኞች ሻንጣ #ሲሰርቁ ያሳያል።
በመቶዎች የሚቆጠር ዶላሮችን ወደ ኪሳቸው ያስገቡ 2 የደህንነት / ፍተሻ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

#VISA
Big congratulations to Kacha Digital Finance Service for being crowned the overall winner of the 2023 Ethiopian edition of the Visa Everywhere Initiative (VEI) innovation program and competition for start-ups and fintech companies. Kacha received a $25,000 USD monetary prize while Qena who finished in second place won $15,000 USD with Smile Pay, receiving $10,000 USD for clinching third place. We received over 170 applications for the 2nd VEI Ethiopia Edition and top 4 start-ups got a chance to present their solutions in the presence of esteemed judges, panelists, speakers and invited guests.
#Everywhereinitiative

#ኮሌራ #አማራ_ክልል
በአማራ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ ሳቢያ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ የሱዳን ጦርነትን ሸሽተው አማራ ክልል የገቡ የሱዳን ዜጎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር /UNHCR/ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፤ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ በተቋቋመ የኩመር መጠለያ ጣቢያ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሠተና ዘጠኝ #ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሞቱ አሳውቋል።
395 ሰዎች ደግሞ እንደታመሙም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ ማርጋሬት አትዬኖ ፤ በሱዳኑ ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ብዛት፣ ከ35 ሺሕ በላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
ከእኒዚም ውስጥ፣ 10 ሺሕ የሚደርሱት ፤ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በሚገኝ የኩመር መጠለያ ጣቢያ እንደተጠለሉ ሌሎቹ ደግሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሸርቆሌ መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ፤ በአማራ ክልል ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ 6 ቀናት የኮሌራ በሽታ ክትባት መሰጠት ዘመቻ እንደተጀመረ ተጋጿል።
ክትባቱ እድሜያቸው አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ነው የሚሰጠው።
የክትባት ዘመቻው አስቻይ ሁኔታዎች አሉባቸው በተባሉት ባሕር ዳርና ጎንደር ከተማን ጨምሮ 9 ወረዳዎች ላይ ይሰጣል ፤ በዚህም ለ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ክትባቱን ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል።
አሁን ላይ በአማራ ክልል በ28 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳውቋል።
በዚህም ከ3 ሺህ 8 መቶ በላይ ሰዎች በበሽታው የተጠቁ ሲሆን ከ70 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል።
በየቀኑ ከ15 እስከ 20 ሰዎች በአዲስ በበሽታው እየተጠቁ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ጠቁሟል።
(ስለ ኮሌራ መተላለፊና መከላከያ መንገዶች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖርዎት ከላይ የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ)

#ዓለምአቀፍ #ፖላንድ
በፖላንድ ፤ እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ #ኦዲት ሊደረግ ነው ተባለ።
በፖላንድ ለአፍሪካውያን በክፍያ ቪዛ እየተሰጠ ነው በሚል መንግሥት ላይ ጥያቄ ማስነሳቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
የፖላንድ የላይኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቶማዝ ግሮዲዚ በአገሪቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ቪዛ የመስጠት አካሄድ ተባብሷል ብለዋል።
መንግሥት ስለ ጉዳዩ ምን መረጃ እንዳለው ይፋ እንዲያደርግም ጠይቀዋል። ነገሩ የአገሪቱን ስም እያጠለሸ ነው ብለዋል።
መንግሥት የተወሰነ መረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን ፤ እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ግን ስደተኞች እስከ 5,000 ዶላር እየከፈሉ የሥራ ቪዛ የማግኘት ሂደቱን ያፋጥናሉ ተብሏል።
እስካሁን ሰባት ሰዎች ላይ ክስ ቢመሠረትም ከመካከላቸው የመንግሥት ባለሥልጣን እንደሌለ ታውቋል።
የአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮር ዋውዚክ ፤ ባለፈው ሳምንት ክሶችን ተከትሎ ከሥራ ተነስተዋል። የፖላንድ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው የተባረሩት።
የሕግ ክፍሉ ዳይሬክተርም ተባረዋል።
እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ ኦዲት እንደሚደረግ ተገልጿል።
ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል ፤ እስከ 250,000 ቪዛዎች ሕግ ሳይከተሉ ለእስያ እና አፍሪካ አመልካቾች ተሰጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።
መንግሥት ግን ቁጥሩ በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠር ነው ሲል አስተባብሏል።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶናልድ ተስክ ፤ " ከአፍሪካ ፖላንድ መምጣት የፈለገ ሁላ ከኤምባሲያችን ቪዛ ገዝቶ አገራችን በቀላሉ ይገባል " ብለዋል።
የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ይህ ንግግር ቀውስ እንደሚያስከትል ገልጸው ችግሩ የተባለውን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል።
" አገራችን ኃላፊነት የሚሰማት ዴሞክራሲያዊ አገር ሆና ሳለ የነጻውን ዓለም ደኅንነት አደጋ ውስጥ የምትከት ሆና እንድትታይ የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ በጥልቀት ሊብራራ ይገባል። ይህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ቅሌት ነው። ሙስና በመንግሥታችን ተንሰራፍቷል " ሲሉ የላይኛው ምክር ቤት አባል አሳስበዋል።
የፍትሕ ሚኒስተሩ ዚግኒው ዚዎብሮ ፤ ይህ አባባል የተጋነነ ነው ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
ይህ ጉዳይ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያ በቀጣዩ የፓርላማ ምርጫ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መገለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

#ሲዳማ
የሲዳማ ክልል የትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ የፈተና ውጤትን በቀን 04/01/2016 ዓ.ም ይፋ አድርጓል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን በኦንላይ (ከታች ባለው ሊንክ) በመግባት ማየት ይችላሉ ተብሏል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ወደ ድረገፁ ሲገቡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
ተማሪዎች ሲስተሙን ለመጠቀም ፦ ይህን ሊንክ https://sidama.ministry.et በመጫን ፤ ፊት ለፊት በሚታየው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር በማስገባት ፤ " ውጤት ይመልከቱ " የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል።

#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የአጠቃላይ ትምህርት የ2016 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚመራበት ሀገር አቀፍ የትምህርት ካላንደር ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት ፤ ከመስረም 7 እስከ 11 ድረስ የትምህርት ሳምንት ሆኖ ይከበራል ብሏል።
መስከረም 14 የአንደኛ ሴሚስተር መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት እንደሚጀምር አሳውቋል። በተመሳሳይ በዛው ዕለት የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ትምህርት ስርጭት ይጀምራል።
የ1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከጥር 27 እስከ የካቲት 1 እንደሚሰጥ የሚያሳየው የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር ከየካቲት 4 እስከ 8 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው የተማሪዎች ፈተና የሚታረምበት ውጤት የሚጠናቀርበትና የሚገለፅበት ወቅት እንደሆነ ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር እንደሚያሳየው የካቲት 18 የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርት መደበኛ የክፍል ውስጥ ትምህርት የሚጀምር ሲሆን ከግንቦት 12 እስከ ግንቦት 23 የአጠቃላይ የትምህርት ማጠቃለያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና ይሰጣል።
ከግንቦት 26 እስከ 30 የ6ኛ ክፍል አንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ከሰኔ 3 እስከ 7 የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ የማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ጊዜ እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።
የሁለተኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ወቅትም ከሰኔ 17 እስከ 21 ሲሆን ከሰኔ 24 - 28 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ዝግ ሆነው ፈተና የማረም፣ ውጤር የሚጠናቀርበት ፣ እና የሚገለፅበት እንደሚሆን ካሌንደሩ ያሳያል።
ሰኔ 30 ወላጆች እና የትምህርት ማህበረሰቡ በተገኙበት የአመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።
* * * ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ክልሎች በብሔራዊ ፈተናና በተለያዩ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታዎች መነሻ የተወሰኑ የቀናት ለውጦች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ታሳቢ እንደሚደረግ ማሳስቢያ ሰጥቷል።