TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፈረንሳይ iPhone 12ን አገደች።

ፈረንሳይ iPhone / አይፎን 12 ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ አዘዘች።

ትናንት መስከረም 1/2016 ዓ.ም. የሬዲዮ ሞገዶችን የሚቆጣጠረው አካል አይፎን 12 ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው ብሏል።

ተቋሙ ስልክ አምራቹ አፕል ችግሩን በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች በአስቸኳይ የማይቀርፍ ከሆነ በመላው አገሪቷ ተሽጠው የሚገኙ አይፎን 12 ስልኮችን ለመሰብሰብ እገደዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የፈረንሳዩ የሬዲዮ ሞገዶች ተቆጣጣሪ ድረጅት ይህን ይበል እንጂ የዓለም ጤና ድርጅት ስልኮች የሚያመነጩት የራዲዬሽን መጠን በሰው ልጆች ጤና ላይ እክል እንደሚፈጥር ምንም ማረጋገጫ የለም ብሏል።

አይፎን 12 ከ3 ዓመታት በፊት እአአ መስከረም 2020 ላይ ለገበያ የቀረበ ሲሆን በመላው ዓለም በከፍተኛ መጠን ከተሸጡ የአፕል ምርቶች መካከል አንዱ ነው።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተቋሙ ውሳኔ እንደማይስማማ ገልጿል።

አፕል ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ በራሱ ላብራቶሪ እና ገለልተኛ በሆነ ሦስተኛ ወገን ቤተ-ሙከራ የተገኙ ወጤቶች አይፎን 12 የሚያመነጨው ጨረራ በጤና ላይ ጉዳት እንደማያስከትል እና ከደረጃ በላይ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ማረጋገጫዎችን ለመንግሥታት ተቆጣጣሪዎች አቅርቤያለሁ ብሏል።

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምራቹ ጨምሮም አይፎን 12 የጨረራ መጠኑ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያስከትል በመላው ዓለም ባሉ ተቆጣጣሪዎች እውቅና ያለው ምርት ነው ሲል አሳውቋል።

የፈረንሳዩ የሬዲዮ ሞገዶች ተቆጣጣሪ ድርጅት አይፎን 12 በኪስ ውስጥ ሲቀመጥ በአውሮፓ ኅብረት በአንድ ኪሎ ግራም ውስጥ መኖር ከሚኖርበት ስፔስፊክ አብሶርፕሽን ሬት 5.74 ዋትስ በላይ ነው ሲል አሳውቋል።

በሌላ አይፎንን በሚመለከት መረጃ " አይፎን 15 " ለገበያ ቀርቧል።

አፕል አዲሱን ምርቱን ይፋ ያደረገው በዩኤስቢ ሲ ታይፕ ቻርጅ ማድረጊያ ነው። የአውሮፓ ሕብረት የአፕል ምርቶች ቻርጅ የሚደረጉበት ቀዳዳ መቀየር አለበት ማለቱን ተከትሎ አዲስ ገመድ ይዞ ብቅ ያለው።

አይፎን 15 እና 15 ፕላስ ምርቶች ስክሪናቸው የጠራ፣ ካሜራቸው የተሻሻለ ሲሆኑ አይፎን 15 ፕሮ እና ፕሮ ማክስ ደግሞ ከታይታኒየም የተሠራ ገላ ያላቸው በመሆናቸው ጥንካሬያቸው ከፍ ያለ ነው።

ፕሮ እና ፕሮ ማክስ ‘አክሽን በተን’ የተባለ አዲስ ቴክኖሎጂ ይዘዋል። ለወትሮው ስልክ ‘ሳይለንት’ ለማድረግ የሚረዳው ቴክኖሎጂ አሁን የተለያዩ ተግባራትን እንዲፈፅም ሆኖ ተሠርቷል።

ነገር ግን የቴክኖሎጂ አዋቂዎች አዲሶቹ የአፕል ምርቶች በጣም ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ አዲስ ነገር አልያዙም ብለዋል። በዚህም ምክንያት ተጠቃሚዎች ረብጣ ዶላር አውጥተው ይገዛሉ ወይ ? ብለው እንዲጠይቁ ሆነዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም አይፎን 15 ፕሮ ዋጋው 999 ፓውንድ ነው ፤ በአሜሪካ አይፎን 15 ፕሮ በ128 GB በ$999 ለገበያ የቀረበ ሲሆን አይፎን ፕሮማክስ በ256 GB በ$1199 ነው ለገበያ የቀረበው።

መረጀው ከቢቢሲ እና አፕል ሃብ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ደቡባዊ ዞን ከፍተኛ አመራር በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ። 

ከፍተኛ አመራሩ አቶ ሳምሶን ተፈሪ  በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት መስከረም 1/2016 ዓ.ም ምሽት 3:30 መሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ጠቅሰዋል።

አቶ ሳምሶን ተፈሪ ከጥቅምት 21 / 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመታት የማይጨው ከተማ ከንቲባ በመሆን አገልግለዋል። 

በተተኮሰባቸው ጥይት በሞት እስከተለዩበት ቀንና ሰአት ድረስ ደግሞ የትግራይ ደቡባዊ ዞን የማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ በመሆን ያገለገሉት አቶ ሳምሶን ፤ ቀደም ሲል በክልሉ የተለያዩ የመንግስት የስራ እርከኖች መስራታቸው የምንጮቻችን መረጃ ያስረዳል ።

አቶ ሳምሶን ተፈሪ በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብ ይህንን ዘገባ እስከተጠናቀረበት ግዜ ድረስ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።

በትግራይ ከተሞች ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እንደሚታይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሚመለከታቸው አካላት ጠቅሶ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።  
                          
@tikvahethiopia
#Jasri

Attention to all aspiring candidates in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹:

The Jasiri team will be hosting an information session on their telegram channel on Thursday,14th September at 6pm EAT to offer more insights into the Jasiri Talent Investor program and address any questions you might have.

Please follow Jasiri on their telegram channel(Jasiri4Africa) and rsvp for the info session on this link: https://bit.ly/3PuCNpx
Feel free to spread the word – tell a friend 🇪🇹 to tell a friend🇪🇹!

Please join us on telegram 👉https://t.iss.one/jasiri4ethiopia

#Jasiri4Africa
TIKVAH-ETHIOPIA
በቅበት የሆነው ምንድነው ? በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በስልጤ ዞን ውስጥ " ቅበት ከተማ " የሰው ህይወትን የቀጠፈ አለመረጋጋት መከሰቱን ለማውቅ ተችሏል። ጉዳዩን በተመለከተ ምን ተባለ ? የእስልምና ጉዳዮች  ላይ  ትኩረት አድርገው የሚሰሩ የሚዲያ ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ የችግሩ መነሻ " ተደርጓል በተባለ መተት / ድግምት ምክንያት የልጆች ጤና እየታወከ ፣ ከትምህርት ገበታቸውም እንዲርቁ እየሆነ…
በቅበት ጉዳይ ምን ተባለ ?

በስልጤ ዞን፣ ቅበት ከተማ ለተፈጠረው ችግር ፣ የዞኑ እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት፣ አስቸኳይ መፍትሄ ሊያበጁለት እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ችግሩን አስመልክቶ፣ ከዞንም ሆነ ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለጠቅላይ ም/ቤቱ በይፋ የቀረበ አቤቱታ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በተቻለ መጠን የተከሰተው ችግር እዚያው በክልሉና በዞኑ እንዲፈታ እንሻለን ብለዋል።

" ሥራ ወዳዱና ጠንካራው የስልጢ ማኅበረሰብ እየተፈተነ መሆኑ ይገባናል " ያሉት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም " ጉዳዩን እየተከታተልን ነው፤ ይሁን እንጂ የተፈጠረው ችግር ከክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ም/ቤትና የሃይማኖት ጉባዔ አቅም በላይ አይሆንም ብለን እናምናለን " ብለዋል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በመጠቀም፣ ሕዝብን ወደስሜታዊነት ለመግፋት የሚደረግ እኩይ ጥረት አለ ያሉት  ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም " እኛ ሃይማኖታችንም፣ ተግባራችንም የሰላም መንገድ ነው " ብለዋል።

" መስጂድ መደፈሩን እና በመስጂድ ላይ መተኮሱን ሰምተናል " ያሉት የም/ቤቱ ፕሬዜዳንት፤ "ሕግ ሊከበር ይገባል። በሃይማኖት ተቋም ወንጀል አይሠራም፤ ለሁላችንም የሚበጀን ለችግሮች ሰላማዊ መፍትኄ መሻት ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰጠችው መግለጫ፤ በስልጤ ዞን ባሉ #ኦርቶዶክሳውያን ላይ ግፍና መከራ እየደረሰ መሆኑን አስገንዝባ ሁኔታው የሃይማኖት ግጭት እንዳያመጣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና የእምነቱ አባቶች በጥንቃቄ እንዲያዩት አሳስባለች።

ቤተክርስቲያኗ በቅበት ከተማ በ " ጽንፈኛ ኃይሎች " በተቀነባብሯል ባለችው ሴራ በቤተ ክርስቲያንና በኦርቶዶክሳውያን ላይ መከራና እንግልት ደርሷል ብላለች።

በዚህም ምዕመናን ለረጅም ዓመታት ያፈሩት ንብረት ከመውደሙ በላይ ከቀያቸው ተፈናቅለው በቡታጅራ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከ1 ሺህ በላይ ቁጥር ያላቸው አማኞች ተጠልለው ይገኛሉ ብላለች።

እንዲህ ያለው መከራ ምዕመናን ላይ እየደረሰ ባለባት ወቅት የአካባቢው አንዳንድ የመንግሥት ጸጥታ አካላትና መሪዎች ተበባሪነት በሚመስል መልኩ ድርጊቱን በዝምታ ማለፋቸውና ጥፋቱንም አለመከላከላቸው እጅግ እንዳሳዘናት ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።

የተፈጠረው ችግር ገዝፎ  የሃይማኖት ግጭት እንዳይፈጥር የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና የእምነቱ (እስልምና) አባቶች በጥንቃቄ ተመልክተው ሊያስተካክሉት ይገባል ብላለች።

ቤተክርስቲያኗ ችግሮችን በሰላምና በውይይት የመፍታት ልምድ ሊጠናከር እንደሚገባ አስገንዝባ፤ ችግሮችን በግፍ ማሰር፣ መግደልና ማፈናቀል ለመፍታት መሞከር ዘለቄታዊ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ቋሚ ችግር ይፈጥራል ብላለች።

ከቅበት ሁኔታ ጋር በተያያዘ ከእስልምና ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አባል ጋር ውይይት ስለመደረጉም አመልክታለች።

ከሰሞኑን በቅበት ከተማ የሰውን ህይወት የቀጠፈ፣ ንብረት ያወደመ የፀጥታ ችግር ተከስቶ እንደነበር ይታወሳል።

የችግሩ መነሻ " በመተት/ ድግምት ምክንያት የልጆች ጤና እየታወከ፣ ከትምህርት ገበታቸውም እንዲርቁ እየሆነ ነው " የሚል ነበር 👉 t.iss.one/tikvahethiopia/81294

@tikvahethiopia
#Amhara

በአማራ ክልል የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ጥሪ ቀረበ።

ከ300 በላይ የሚሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አባል የሆኑበት የ #KeepItOn ጥምረት እንዲሁም 48 ድርጅቶች በፈረሙት ጥሪ በአማራ ክልል የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ጥያቄ ቀርቧል።

ከ105 ሀገራት የተወጣጡት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የተሳተፉት ፈራሚዎቹ፤ በአማራ ክልል በግጭት ምክንያት የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲጀመር ነው ለመንግስት ጥሪ ያቀረቡት።

"አክሰስ ናው" በመባል የሚታወቀው የዜጎች ሲቪል መብት ተከራካሪ ድርጅት ከሌሎች የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጋር በመሆን በጉዳዩ ላይ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ተሟጋቾቹ በጥምረት ባወጡት የጋራ የአቋም መግለጫ በግጭት ወቅት የኢንተርኔት የአገልግሎትን ማቋረጥ ዜጎች አስፈላጊ መረጃን እንዳያገኙ በማድረግ የመረጃ ፍሰትን የሚገድብ እንደሆነ አሳውቀዋል።

መግለጫው በአማራ ክልል ግጭቱ ከተጀመረበት ከነሀሴ ወር አንስቶ የኢንተርኔት አገልግሎት እንደተቋረጠ ተገልጿል።

የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋት የዜጎችን መብት መጣስ እንደሆነ የገለፁት ተሟጋቾቹ  በግጭት ወቅት የመረጃ ፍሰትን ለማደላደልና የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መንግስት ከምንግዜውም በላይ ቁርጠኛ አቋም መያዝ እንዳለበት አሳስበዋል።

https://www.accessnow.org/press-release/open-statement-internet-shutdown-amhara/

Via @TikvahethMagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ለግብፅ መግለጫ ምን ምላሽ ተሰጠ ?

" ግብፆቹ ስለ4ኛው ሙሌት በደንብ ያውቃሉ ፤ ምንም የተጣሰ መርህ የለም " - ኢ/ር ጌዲዮን አስፋው

ከሰሞኑን ኢትዮጵያ 4ኛውን ዙር የአባይ ግድብ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ ካሳወቀች በኃላ ግብፅ ሙሌቱ ህገወጥ እንደሆነና እ.ኤ.አ. በ2015 በሱዳን፣ በግብፅና በኢትዮጵያ የተፈረመውን የመርህ ስምምነት  የጣሰ ነው በሚል ቁጣ አዘል መግለጫ አውጥታ ነበር።

ለዚህ ግብፅ መግለጫ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎችና ባለስልጣናት " ምንም የተጣሰ ነገር የለም ፤  መግለጫዋ ለሀገር ውስጥ የሚዲያ ፍጆታ የሚውል ነው " ብለውታል።

የኢትዮጵያ የግድቡ ተደራዳሪ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ምን አሉ ?

" ምንም የተጣሰ ነገር የለም፡፡ ግብፆች ያወጡት ነገር ትክክል አይደለም፡፡ የመርህ ስምምነቱ አልተጣሰም፡፡

በመርህ ስምምነቱ መሠረት የወጣ የሙሌት ሠንጠረዥ አለ፣ በእሱ መሠረት ነው አሁን የሞላነው፡፡

አሁን በቅርቡ የተጀመረው ድርድር የአገሮቹ መሪዎች በሰጡት መመርያ መሠረት የተጀመረና የተካሄደ ነው።

የሦስትዮሽ ድርድር ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረው ከቆመበት መቀጠል እንጂ፣ አዲስ ድርድር አይደለም።

አራተኛው ሙሌት በቅርቡ ከተጀመረው ድርድር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡

ግብፆቹ ስለአራተኛው ሙሌት በደንብ ያውቃሉ፡፡ በተስማማነው መሠረት ነው የተሞላው። "

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምን አሉ ?

" ሙሌቱ በሌሎች የተፋሰሱ አገሮች ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ የለውም።

የእነሱ የሚዲያ እንካ ሰላንቲያ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የቀጠለ ነው፡፡

አሁን ያወጡት መግለጫም የተለመደ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ፍጆታ ነው፣ ለውስጥ ፍጆታ የሚጠቀሙበት ነው፡፡

እኛ የእነሱ የሚዲያ እንካ ሰላንቲያ ውስጥ መግባት አንፈልግም፡፡

ይኼ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያከብረው ፕሮጀክት ነው፡፡ ግድቡ የትብብር እንጂ የፉክክር ምንጭ መሆን የለበትም። "

Credit - #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ርዕደ መሬቱ በተከሰተባቸው አከባቢዎች እስከ አሁን ያጋጠመ አደጋ የለም " - አስተዳዳሪዎች ከባድ ርእደ መሬት በኤርትራ ፣ ሱዳን እንዲሁም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ማጋጠሙ የሚያመላክቱ መረጃዎች ወጥተዋል። ሃምሌ 25 /2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:15 ገደማ በእንዳስላሰ ሽረ ፣ ሰለኽለኻ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ውቕሮ ፣ ሓውዜንና አከባቢው ፣ ኣፅቢ ፣ መቐለና ሌሎች አከባቢዎች ከባድና ቀላል…
#Earthquake

ትግራይ ድረስ ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

ከአንድ ሰዓት በፊት በሬክተር ስኬል 5.0  የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከኤርትራ፣ አስመራ በ59 ኪሎሜትር ርቀት መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጡን የሚመለከት ዝርዝር መረጃዎች በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የመሬት መንቀጥቀጡን በተመለከተ አንድ ኤርትራዊ ፤ " ከደቂቃዎች በፊት እናቴን በስልክ እያነጋገርኳት ነበር (አዲ ቀይኺ) በድንገት ግን ቤት የነበሩ ህፃናት ሲጯጯሁ ሰማሁ ፤ በሁኔታው ተደናግጬ እናቴን ምን እንደተፈጠረ ጠየኳት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደሆነ ነገረችኝ " ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በትግራይ ክልል መቐለ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምሽት 2:52 ደቂቃ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት እንደተሰማቸው ጠቁመዋል።

በሽረ ፣ ዓዲግራት ፣ ኣክሱም እንዲሁም ዓድዋና ሌሎች አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የተሰማቸው እንዳሉ የትግራይ ቤተሰቦቻችን ገልጻዋል።

ሃምሌ 25 /2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:15 ገደማ ዋና መነሻው (Epicenter) ከምፅዋ ወደብ በ43 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሆነ ከባድና 5.6 ሬክተር ስኬል የሚለካ የመሬት መቀጥቀጥ ተከስቶ ፤ በእንዳስላሰ ሽረ ፣ ሰለኽለኻ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ውቕሮ ፣ ሓውዜንና አከባቢው ፣ ኣፅቢ ፣ መቐለና ሌሎች አከባቢዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት እንደተሰማ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
በሳፋሪኮም ዕለታዊ የዩቲዩብ ጥቅሎች አዳዲስ ዕውቀቶችን እናግኝ፤ ቢዝነሳችንን እናሳድግ!

ዛሬውኑ ወደ *777# በመደወል ጥቅሎችን እንግዛ!

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#CBE
ስጦታ ይቀበሉ!
=======
እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም
• የውጭ አገር ገንዘብ በባንካችን ሲመነዝሩ
• በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ ከባንካችን ሲቀበሉ
• እንዲሁም
• በባንካችን የSWIFT አድራሻ (CBETETAA)
• በ EthioDirect እና
• በ CashGo ሲላክልዎ
የሞባይል ስልክ የአየር ሰዓት ስጦታ ያገኛሉ!

መልካም አዲስ ዓመት!
" የዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቅበላ በአብዛኛው ከትኩረት መስክ ጋር የተናበበ ይደረጋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በዚህ ዓመት ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡበት የትኩረት መስክና ተልዕኮ የዝግጅት ስራ ቅድሚያ የሚሰጡ መሆኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ በ10 ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ትኩረት መስክና ተልዕኮ እንዲሸጋገሩ የትግበራ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ የመጀመሪያው ምዕራፍ ስራ መጀመሩን አመልክቷል።

ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ቅድሚያ ለተልዕኮና ለትኩረት መስካቸው እንዲሰጡ በዚህ ሂደት ውስጥ ያልገባ የትምህርት ተቋም ካለም ማስተካከያ እንደሚደረግበት ተመላክቷል።

በ2016 ዓ.ም የትኛውም የትምህርት ተቋም አዲስ የትምህርት ፕሮግራም እንደማይከፍት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ የትምህርት መስክ ይዘጋ ተብሎ የተወሰነበት የትምህርት ዓይነት እንደሌለ የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ ነገር ግን ተማሪዎች ሲመደቡ የማይፈልጉት የትምህርት ፕሮግራም ካለ ሊታጠፍ እንደሚችል አሳውቋል።

ይህ ማለት ግን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አይሰጥም ማለት እንዳልሆኑ ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቅበላም በአብዛኛው ከትኩረት መስክ ጋር የተናበበ የሚደረግ ሲሆን በዚህም ዩኒቨርሲቲዎች በየደረጃው ወደ ተመደቡበት የተልዕኮ መስክ የሚሸጋገሩ ይሆናል ተብሏል።

መረጃው ከኢዜአ ነው።

@tikvahethiopia
በአዲስ አበባ የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሒደት መስከረም 07/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

በአዲስ አበባ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን የሚያስተምሩ ከ2,200 በላይ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ከመዲናዋ የትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።

በሌላ በኩል በኦሮሚያ ክልል ' ኪድ -ኢንተርፕረነርሺፕ ' የተሰኘ ከቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ጀምሮ ህጻናትን በክህሎት ለማነጽ የተዘጋጀ መጽሐፍና ' በርኖታ ሰፉ ' የተሰኘ ከ1ኛ ክፍል እስከ 6ኛ ክፍል የሚሰጥ የግብረ ገብ ትምህርት መፅሃፍ ተመርቋል።

በዚህም ፤ ' ኪድ-ኢንተርፕርነርሺፕ ' እና ' በርኖታ ሰፉ / የግብረ ገብ ትምህርት ' ይሰጣል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሊቢያ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 5000 ሺህ ሳይጠጋ እንደማይቀር እየተነገረ ነው። 10 ሺህ ሰዎችም ያሉበት አይታወቅም ተብሏል። የሊቢያ ቀይ ጨረቃ እስካሁን ባለው 2,084 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል። በሊቢያ የሚገኘው ቀይ መስቀል በበኩሉ የገቡበት የማይታወቁ ሰዎች 10 ሺህ ደርሰዋል ሲል አሳውቋል። መቀመጫውን በ ' ምስራቃዊ ሊቢያ ' ያደረገው አስተዳደር…
#Update

" ዳንኤል " የተባለው አውሎ ንፋስ በፈጠረው ከባድ ጎርፍ በሊቢያ የሞቱ ሰዎች 20 ሺህ ገደማ ሊደርሱ እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል።

በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ እስካሁን ያሉበት አልታወቀም።

ደርና የተባለችው ከተማ ትልቁ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን አብዛኛው የከተማዋ ክፍል በውሃ ተወስዷል።

በሌላ በኩል ፤ አርብ በሞሮኮ በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች 3000 ገደማ መድረሳቸው የተነገረ ሲሆን አሁንም ድረስ በህይወት ያሉ ሰዎች ካሉ በሚል ፍለጋ እየተደረገ ነው። በአደጋው ሰዎችን በህይወት የማግኘቱ ነገር እጅግ የመነመነ ነው ተብሏል።

በአደጋው ከ5,530 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

@tikvahethiopia