TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሊቢያ

በምስራቃዊ ሊቢያ የምትገኘውን " ዴርና " ከተማን በመታው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ምክንያት 2000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።

7000 ሰዎችም የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።

በቤንጋዚ የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ኃላፊ ካይስ ፋከሪ እንደተናገሩት " ዳንኤል " በተባለው አውሎ ንፋስ በዴርና ከተማ ባደረሰው ጥፋት ቢያንስ 150 ሰዎችን ሞተዋል።

በከተማዋ ሁለት ግድቦች መደርመሳቸውም ተነግሯል።

ከቀናት በፊት በሌላኛዋ የአፍሪካ ሀገር #ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ2000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia
አዲሱ ዓመት 2016 ፦

- ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤

- ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤

- ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤

- ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤

- ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤

- ወጥተን የማንቀርበት፤

- በአጠቃላይ ሀገራችን ከጫፍ እስከጫፍ ሰላም እና ተስፋ የሚነግስበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ ፣ የሚወዱትን ከአጠገባቸው የተነጠቁ ወገኖችን በማፅናናት ፣ የታመሙትን በመጠየቅ ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

መልካም አዲስ ዓመት !

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Tikvah Family

#ኢትዮጵያ2016

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ ዓመት 2016 ፦ - ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤ - ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤ - ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤ - ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤ - ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤…
#ኢትዮጵያ2016

ኢትዮጵያ ዛሬ አዲሱን 2016 ዓ/ም አንድ ብላ ጀምራለች።

ዓመቱ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የፍትህ ፣ ከችግሮቻችን የምንላቀቅበት እንዲሆን የመላ የኢትዮጵያውያን ምኞት ነው።

አሁንም በኢትዮጵያ የሚወዱትን የተነጠቁ፣ በግፍ ከቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ብርድ እና ፀሀይ የሚፈራረቅባቸው ፣ የነበራቸውን ንብረት እና ሃብት በጦርነት እና በግጭት አጥተው የሰው እጅ ጠባቂ የሆኑ ፣ በየወቅቱ በሚፈጠሩ ችግሮች ሰበብ በጅምላ ታስረው የሚገኙ፣ በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተሰቃዩ  ያሉ ወገኖች እጅግ በርካታ ናቸው።

አዲሱ ዓመት ፍትሕ እና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ፤ የተበደለ የሚካስበት ፤ የእርስ በእርስ መግባባት እውን የሚሆንበት ፤ የህዝብ ድምፅ የሚሰማበት ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ ላለው ኑሮ መረጋጋት የሚፈጠርበት እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል።

ይህን አዲስ ዓመት ያለፉ ችግሮቻችን ሁሉ የሚታረሙበት ፣ ለጥፋት የዳረጉን ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት፣ ለችግሮቻችን ሁሉ ተነጋግረን መፍትሄ የምናበጅበት፣ የተበደሉትን የምናፅናናበት፣ እንደ አንዲት የኢትዮጵያ ልጆች እርስ በእርስ ከጥላቻ ርቀን ለእድገታችን የምንሰራበት እንዲሆን እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባል።

ሁሌም አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር የሚነገር ምኞት እና የተስፋ ቃላት መሬት ላይ ካልዋለ ትርጉም አልባ ነውና ሁሉም ለሚናገረውና ለሚገባው ቃል መታመንና መፅናት አለበት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጳጉሜን 2 /ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠርተውት መንግስት ሳይፈቅድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማነሳሳትና በመሳተፍ ምክንያት በቁጥጥር ሰር ያዋላቸውን እፈታ መሆኑን ገልጿል። የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፤ " ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ጨምሮ የፓለቲካ ፓርቲ ሊቃነ መናብርትና ጋዜጠኛ ገና አልተፈቱም " ብለዋል። ከመቐለ ከተማ ፓሊስ የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው ፦…
#Mekelle

" በአምባገነን ስርአት ምክንያት መብታችን እንዲቀማ እንፈቅድም " - አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ

በትግራይ መቐለ ከተማ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜን 2/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሊካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያዘዘ በቁጥጥር ስር የነበሩ የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ ሊቃነመናብትና  ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ መለቀቃቸው ታውቋል።

የዓረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ/ር ደጀን መዝገበ ፣ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበርና ከፍተኛ አመራር አቶ ሃያሉ ጎዲፋይና አቶ ዓብለሎም ገ/ሚካኤል ፣ የብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ አስተባባሪዎች አቶ ኪዳነ አመነና ክብሮም በርሀ ጳጉሜን 6/2015 ዓ.ም ከተለቀቁት መካከል ናቸው።

እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ በተጠራበት ሮማናት አደባባይ ተገኝቶ በፓሊስ ተድብድቦ በቁጥጥር ስር የቆየው ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብም ተለቋል።

የዓረና ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት እሳቸው ጨምሮ 150 የሰልፉ ተሳታፊዎች መታሰራቸው ፤ ዓርብ ጳጉሜ 3 /2015 ዓ.ም 6 የአራት ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች  ፍርድ ቤት ቀርበው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ቢወሰንም ፤ ፓሊስ ፍቃደኛ ባለመሆኑ እስከ ጳጉሜን 6 /2015 ዓ.ም መታሰራቸው ገልፀዋል።       

" ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ ፤ ግርፋትና እስራቱ ፣ አልፎም ከፍርድ ቤትና ዳኛ በላይ መሆን የመሰለ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው የተፈፀመው " ያሉት አቶ ዓንዶም ፤ " በአምባገነን ስርአት ምክንያት መብታችን እንዲቀማ እንፈቅድም  ፤ መብታችን መስዋእትነት ጭምር በመከፈል እናረጋግጣለን ፤ ቀጣይ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሌሎች ፓለቲካዊ እንቀስቃሴዎች በማካሄድ ህዝቡ የዴሞክራሲያዊ መብት ባለቤት እስኪሆን ድረስ እንታገላለን  " ብለዋል። 

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲካሄድ አልፈቀድኩም ካለው የጳጉሜን 2 ቱ ሰልፍ ጋር በተሳሰረ ከተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር የታሰሩት 49 እንደሆኑ የጠቀሱት የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ፤ ባልተፈቀደው ሰልፍ የተፈጠረው ግርግር ፓሊስ በ20 ደቂቃ በማይሞላ ግዜ  እንደተቆጣጠረው መግለፃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።  

More - @tikvahethiopiaTigrigna
                          
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በሊቢያ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 5000 ሺህ ሳይጠጋ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

10 ሺህ ሰዎችም ያሉበት አይታወቅም ተብሏል።

የሊቢያ ቀይ ጨረቃ እስካሁን ባለው 2,084 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በሊቢያ የሚገኘው ቀይ መስቀል በበኩሉ የገቡበት የማይታወቁ ሰዎች 10 ሺህ ደርሰዋል ሲል አሳውቋል።

መቀመጫውን በ ' ምስራቃዊ ሊቢያ ' ያደረገው አስተዳደር በአደጋው 5000 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ገልጿል።

100 ሺህ ነዋሪ ባላት ደርና ከተማ ውስጥ የነበሩ ሁለት ግድቦች እና አራት ድልድዮች ከተደረመሱ በኋላ በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በውሃ ተውጣለች ብሏል።

" የሰዎች አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

የከተማዋ ሩብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷልም ብሏል።

በከተማይቱ የሞቱ ሰዎች በጅምላ እየተቀበሩ እንደሆነ ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ

የአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከግራር የጠቢባን መናኸርያ እንዲሁም ከUSAID ጋር በመተባበር የዘወትሯ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል። ይህ አውደርዕይ በሚካኤል ጸጋዬ ዋና አዘጋጅነት የቀረበ ነው።

የመጀመርያ ዙር ቆይታውን በባህርዳር፣ ሁለተኛ ማረፊያውን ድሬዳዋን ያደረገው አውደርዕዩ በብዙዎች ተወዳጅነትን አትርፏል። በቀጣይ ጉዞውን ወደ ሀዋሳ የሚያደርግ ይሆናል።

ከመስከረም 3 - 7/2016 በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል በ15 የፎቶግራፍ ባለሙያዎች የተዘጋጁት የፎቶግራፍ ስብስቦች የሚቀርቡ ሲሆን ከአውደርዕዩ ባለፈ ነጻ የፎቶግራፍ ስልጠናን ጨምሮ የጥይቄና መልስ ግዜዎች ከፎቶግራፍ ባለሙያዎቹ ጋር ተዘጋጅተዋል።

በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! የአንድነታችንን ውበት በጋራ እናድንቅ!
የቅመም ናና ስማርት ስልክን በሚገርም ዋጋ! ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች ጎራ ብለን የጉግል መተግበሪያዎች ያሉትን የቅመም ናና ስልክ እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ ለመተግበር መወሰኑን ገልጿል።

የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ጥቅም ላይ መዋሉ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት መለየት የሚያስችል ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል ብሏል።

ይህም ዲጂታል መታወቂያ በሁሉም የትምህርት ተቋማት አበይት የማንነት ማረጋገጫ ስርዓት ሆኖ እንዲያገለግል የሚያስችል እንዲሁም የአሰራር ድግግሞሽን በመቀነስ እና በተማሪዎች የትምህርት ሰነዶች መካከል አንድነት እና ቅንጅትን የሚያጠናክር ነው ሲል ገልጿል።

ከዚህም ባለፈ  የግል መረጃን የማስቀመጥ እና የመጠቀም ደህንነትን በእጅጉ እንዲጨምር  የውሂብ ጥበቃን እንዲረጋገጥ  ፣ ማንኛውም አይነት ጥሰቶችን ለመቀነስን ያግዛል ብሏል።

የብሔራዊ መታወቂያ መርሃ ግብር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋራ ባደረገው ስምምነት እስከ አሁን 640 ሺህ ተማሪዎች ብሔራዊ መለያ ቁጥር ማግኘታቸው ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethiopia