TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በፀጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመፈተን መዘጋጀቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር መሰጠቱን አገልግሎቱ አስታውሷል፡፡ ይሁንና በጎንደርና በጋምቤላ…
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና #ውጤት በፀጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።
በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።
የእነዚህ ተፈታኞች እና የመጀመሪያው ዙር ፈተና ተፈታኞች ውጤት አንድ ላይ እንደሚገለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ከቀናት በፊት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መስከረም 2016 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ይፋ ለማድረግ እና ጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲጀመር እቅድ መያዙን መግለፃቸው ይታወሳል።
@tikvahethiopia

ያለሃሳብ እንደውል ፣ ኢንተርኔት እንጠቀም ፣ የፅሁፍ መልዕክት እንላክ! ዛሬውኑ *777# በመደወል የሳፋሪኮምን የድኅረ ክፍያ ኢንተርኔት ጥቅል እንግዛ !
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል።
ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል።
የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን አጠናቀው ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የማዕከል ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ ከመስከረም 7- 10/2016 ዓ.ም ከማዕከል የሚሰጠው ፈተና #በወረቀት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50 % በታች ሆኖ ወደከፍተኛ ትምህርት መግባት ያልቻሉ እና በአንጻራዊነት የተሻለ ውጤት የነበራቸው ወደ 200ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአንድ ሴሚስተር የማካካሻ ትምህርት መውሰዳቸው ይታወቃል።
የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና የሚሰጠው ተማሪዎቹ በተቋማት እና በማዕከል የሚሰጠውን ምዘና ወስደው በሚያስመዘግቡት ውጤት መሠረት ከ2016 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ጋር የከፍተኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ነው።
#MoE

#Mekelle
" መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ
" ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር
የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ በማስመልከት ዛሬ ጳጉሜን 3 ለክልሉ ሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ መንግስት ያልፈቀድው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል ብለዋል።
" ሁሉም ሰው ከህግ በታች እንጂ ከህግ በላይ አይደለም " ያሉት የፓሊስ አዛዡ " ፖሊስ መንግሥት ያልፈቀደውን ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብሎ ቢያስጠነቅቅም ፤ ለ20 ደቂቃ ያህል በአምቢተኝነት ከፓሊስ ጋር ለመጋጨት የሞከሩ ነበሩ " ብለዋል።
ፓሊስ ከጳጉሜን 1 /2015 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ በመንግስት ያልተፈቀደው ሰልፍ እንዳይቀሰቅሱና እንዳይመሩ ለተፎካካሪ ፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ምክር መሰጡትንና ፤ ምክሩ ችላ ብለው ከሰዓት በኋላ 10:30 አከባቢ አመራሮቹ ሰልፉ እንዲካሄድ የሚቀሰቅስ ወረቀት ሲለጥፉ እጅ በፈንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር ውለዋል ፤ በተጨማሪ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም ጠዋት ሰልፉ ለማስተባበርና ለመሳተፍ የተገኙ ቀሪ አመራሮች መያዛቸው ገልፀዋል።
ፓሊስ የተሰጠው ህግ የማስከበር ሃላፊነት መሰረት በማድረግ ግርግር ለመፍጠር የሞከሩ በደቂቃዎች በመቆጣጠር የመቐለ ከተማ እንቅስቃሴ ከወትሮ የተለየ የፀጥታ ስጋት እንዳይታይባት ማድረግ መቻሉንና ፤ ህዝቡ ያልተፈቀደውን ሰልፍ ለማደረግ የመኮሩ ጥቂቶች ሰርአት እንዲይዙ የማድረግ ሚናው በመወጣቱ አመስግነዋል።
የውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አለምሰገድ አረጋይ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለምልልስ በበኩላቸው " ፓሊስ ሰልፉ ለመታደም በመጡ ድብድባ ፤ ማንገላታትና ባጠቃላይ ኢ-ሰብአዊ የሆነ ግፍ ፈፅመዋል " ብለዋል።
" ፓሊስ 50 ሊቀመናብርትና የማእከላይ ኮሚቴ አመራሮች የሚገኙባቸው ከ150 በላይ ሰዎች አስረዋል " ያሉት አቶ አለምሰገድ ፤ የዓረና ሉአላውነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር ዓምዶም ገ/ስላሴ ፣ የባይቶና ግዚያዊ አስተዳዳሪ ኪዳነ አመነ ከታሳሪዎች መካከል ናቸው ብለዋል።
" ይህን መሰል አፈና ሊቆም የሚችለው ገዢው ፓርቲ ህወሓት ከስልጣኑ ሲነሳ ነው " ያሉት አመራሩ ህዝቡ ትግሉ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋል።
የግዚያው አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ለሚድያዎች በሰጡት ሰፊ ቃለመጠይቅ "... ሰልፍ ማድረግ መብት ነው : ቢሆንም በክልሉ ካለው ከባድ የፀጥታ ስጋት አንፃር ስልፉ ማካሄድ አስቸጋሪ ነው " ማለታቸው ይታወሳል።
መረጃውን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

በአዲስ ዓመት አብሳሪዋ አደይ አበባ የተሰየመችው ተናፋቂዋ አደይ አበባ የሞባይል ጥቅል ይበልጥ ፈክታና ደምቃ፤
ከወትሮው ለየት ብላ የዳታ ጥቅሎቿ ላይ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቴሌግራም የሚያስጠቅም ስጦታን ይዛ ቀረበች!!!
ከአይነተ ብዙ ሰፊው ገበታችን አደይ አበባ ጥቅልን በቴሌብር ሱፐርአፕ እና ማይ ኢትዮቴል እንዲሁም በ*999# ለራስዎ እየገዙ ለሚወዷቸው በስጦታ እያበረከቱ የበዓል መልካም ምኞትዎን ያድርሱ!
ወዳጅ ዘመድን የምታቀላቅል… አደይ አበባ ጥቅል
መልካም አዲስ ዓመት!!

#G20 አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት…
አፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 አባል ሆነ።
ቡድን 20 " ታሪካዊ ነው " በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ።
በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት ስብስብ የሆነው ቡድን ሃያ አባላት ውሳኔ ታሪካዊ ተሰኝቷል።
55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 (G20) አባል አገራትን ተቀላቅሏል።
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ ሞዲ የአፍሪካ ኅብረትን አዲስ የቡድን 20 ቋሚ አባል አድርገው ሲያስተዋውቁ አንደኛው ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው አፍሪካን በአንድ ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ማካተት ነው።
ሕንድ የቡድን 20 መሪነቷ የዓለምን ደቡባዊ አገራት ተሳትፎ ከማሳደግ ጋር የተያያዘ መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች። የዚህ ዕቅድ ትልቁ አካል ደግሞ የአፍሪካ ኅብረትን የቡድኑ አባል ማድረግ ነው።
ሞዲ የአፍሪካ ኅብረትን በቡድኑ መቀላቀል ሲገልጹ አጠገባቸው የነበሩ የአፍሪካ ተወካዮች ደስታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዚል አሶሚኒ በቡድን 20 የፓርላማ አባላት መቀመጫ እንዲወስዱም በሞዲ ተጋብዘዋል።
ሁለቱ መሪዎች ይህ ይፋ ከተደረገ በኋላ ተቃቅፈው ታይተዋል። ተወካዮቹ “ታሪክ ተሠርቷል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት በቡድን 20 መቀላቀል ቡድኑን የተሻለ አካታች እንደሚያደርገው ተገልጿል።
ሕንድ በጉባኤው እንዲነሳ ከምትፈልገው ርዕሰ ጉዳይ አንዱ የታዳጊ አገራት ምጣኔ ሀብት ነው።
በርካታ ታዳጊ አገራት ከቻይና፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የተበደሩትን ገንዘብ ለመክፈል ስለሚከብዳቸው ሕንድ ሃብታም አገራት እንዲያግዙ ትሻለች።
መረጃው የቢቢሲ ነው።
ቪድዮ ፦ የደ/አፍሪካ ፕሬዜዳንት ፅ/ቤት

#Mekelle " መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ " ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው…
#Tigray
" መሰረታዊ ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች መከበር አለባቸው " ሲል የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ትእዛዝ አውጥቷል።
ፍትሕ ቢሮ ፤ ለትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና ለትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፅፏል።
በፃፈው ደብዳቤም ፤ ሰብአዊና ህገ-መንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በዚህ ሳምንት ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ጋር ተያይዞ የፓርቲዎቹ መሪዎችና አባላት የሚገኙባቸው በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል ያለው ቢሮው በዚሁ ሂደት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች መሰረታዊ ሰብአዊ መብታቸው እየተከበረ አይደለም የሚል ስሞታ ቀርቦልናል ብሏል።
በመሆኑም ፦
1. በህጉ መሰረት በ48 ሰአታት ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ፤
2. ከቤተሰብም ሆነ ሌላ ጠያቂ እንዲገናኙና ምግብና ልብስ እንዲገባላቸው፤
3. የተጎዱ ህክምናና መድሃኒት እንደዲያገኙ፤
እንዲሁም ሌሎች ተዘማጅ መብቶቻቸው ሳይሸራረፉ ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲከበሩላቸው ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል።
ትእዛዙ በአግባቡ መፈፀሙን ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሚገኙባቸው ማረፍያ ማእከላት በአካል ተገኝቶ የሚያረጋግጥ የሰብአዊ መብት ክትትል ቡድን ከቢሮው የተመደበ መሆኑን አሳስውቋል።
መረጃው የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

" ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 የማካካሻ (Remedial) ትምህርት ፈተና ይሰጣል " - ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ሚኒስቴር የማካካሻ (ሬሜዲያል) ፈተና ከመስከረም 7 እስከ 10/ 2016 እንደሚሰጥ ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ አሳውቋል። ፈተናው በ30 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከናወን ይሆናል። የሚሰጠው ፈተና የማካካሻ ትምህርታቸውን…
#MoE
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርት ተከታታዮች ፈተና የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።
(ከላይ ያንብቡ)
@tikvahethiopia
የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ የማካካሻ (ሬሜዲያል) ትምህርት ተከታታዮች ፈተና የሚሰጥበትን አቅጣጫ አስቀምጧል።
(ከላይ ያንብቡ)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 አባል ሆነ። ቡድን 20 " ታሪካዊ ነው " በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና ከአዳጊ አገራት የላቀ የምጣኔ ኃብት ዕመርታ ያስመዘገቡት አገራት ስብስብ የሆነው ቡድን ሃያ አባላት ውሳኔ ታሪካዊ ተሰኝቷል። 55 አባላት ያሉት የአፍሪካ ኅብረት የቡድን 20 (G20) አባል አገራትን ተቀላቅሏል። የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ንሬንድራ…
#G20
አፍሪካ ህብረት " ቡድን 20 " ን በቋሚ አባልነት መቀለቀሉን ተከትሎ የቡድኑ ዝርዝር ይህን ይመስላል።
🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት
🌍 #አፍሪካ_ሕብረት

ከ5 ብር ጀምሮ ስንሞላ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ዕለታዊ እና ሳምንታዊ ጥሪ ማድረግ እንችላለን። ያለሃሳብ ከምንወዳቸው ጋር አብሮነታችንን እናጠንክር!
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
" አርሶ አደሩ መሬት የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው " ለማድረግ ማቀዱን ትንሣኤ 70 እንደርታ ፓርቲ ገለጸ።
የምሥረታ ጉባኤውን ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያካሄደው የ " ትንሣኤ 70 እንደርታ " ፓርቲ (ትሰእፓ) ሊቀ መንበር ሆነው የተሾሙት አቶ ከበደ አሰፋ ፤ " አርሶ አደሩ መሬቱን የመሸጥና የመለወጥ መብት እንዲኖረው ይደረጋል " ብለዋል።
ሊቀ መንበሩ፤ "መሬት የሕዝብ እንጂ የመንግሥት መሆን የለበትም " ያሉ ሲሆን፣ ትሰእፓ " በመሆኑም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሀብት በወጉና በሥርዓቱ እንዲሁም ሕዝብንና አገርን ጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፓሊሲ ያዘጋጃል " ሲሉ አስረድተዋል።
አቶ ከበደ አክለውም፣ "መንግሥት አርሶ አደሩን የማይረባ ዋጋ እየሰጠ በማፈናቀል፣ መንግሥት ራሱ መሬቱን በከፍተኛ ዋጋ በመሸጥ የሚነግድበት ሥርዓት መወገድ አለበት" ብለዋል።
" እስከ ዛሬ ድረስ 'መሬት የሕዝብም የመንግሥትም ነው' ተብሎ ግን መንግሥት በካሬ 40 ሺህ እና 50 ሺህ በሊዝ ስም የሚሽጥበት እውነታ ስለሆነ ያለው፣ መሸጥም ካለበት መንግሥት ሳይሆን ራሱ ሕብረተሰቡ ይሽጠው " ሲሉ ተናግረዋል።
ፓርቲው በተጨማሪም፣ "ታላላቅ ኢንዱስትሪዎች ሲቋቋሙ አገሬውን ተጠቃሚ በሚያደርግና በማያፈናቅል መንገድ፣ ለኢንቨስትመንት የሚውሉ ሰፋፊ መሬቶች አርሶ አደሩን በማማከር እና የልማቱን ባለድርሻ በማድረግ ይከናወናል " ብሏል።
በምስረታ ጉባኤው የታደሙ የፓርቲው ደጋፊዎች በበኩላቸው የፓርቲውን የእንደርታ ሕዝብ በሕወሓት አመራሮች ጫና፣ መገለል እንደተፈጸመበት በምሬት ተናግረዋል።
አክለውም ትሰእፓ ከሕወሓት ጋር ምንም አይነት ቁርኝት እንዳይኖረው ጠይቀዋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ከበደ በበኩላቸው ፓርቲው ከሕወሓት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደማይችል አስረድተዋል።
ትሰእፓ የምስረታ ጉባኤውን ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ/ም ያካሄደ ሲሆን፣ በጉባኤው የተሳተፉ አባላቱ የማዕከላዊ ኮሚቴዎች፣ የኦዲትና ሥራ አስፈጻሚዎችን መርጠዋል።
አቶ ከበደ አሰፋ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " 15 የማዕከላዊ ኮሚቴ፣ ሦስት የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን ተመርጠዋል። እኔ አቶ ከበደ አሰፋ ሊቀመንበር ሆኘ ተመርጫለሁ " ሲሉ አስረድተዋል።
አክለውም 15ቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቶችም ባከናወኑት ምርጫ 14 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቶችን መርጠዋል፤ አቶ ጊደና መድህን ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል" ብለዋል።
ትሰእፓ በትግራይ ክልል “የተንሰራፋውን ጭቆና እና የአንድ ፓርቲ ስርዓት” መታገል ዋነኛ አላማው መሆኑን አስታውቋል።
መረጃውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።