TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መንግሥትን እና ፓርቲን ለመለየት ወስኖ እየሰራ ነው ብለዋል። ይህን አዲስ ያሉትን የአሰራር ሂደት በ " ፀረ-ህወሓት " እንቅስቃሴ የፈረጁ የፓርቲው አመራሮች እንዳሉ ተናግረዋል። አንዳንድ…
#Update 

ዛሬ ጳጉሜን 2/2015 ዓ/ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ? 

የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ ጳጉሜን 2/ 2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:00 ሰአት ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ይካድበታል ተብሎ ጥሪ በተላለፈበት " ሮማናት አደባባይ " ተገኝቶ ያጠናቀረው መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሮማናት አደባባይና ወደ አደባባዩ መጋቢ በሆኑ መንገዶች  እንዲሁም ከክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች ወደ መቐለ ማለትም በሳምረ ፣ በኪሓ ፣ በተምቤንና በዓዲግራት በኩል ወደ ከተማዋ በሚያስገቡ የመኪና በሮች ከወትሮ የተለየ ጥብቅ ፍተሻ ነበር።

ሁለት ሰአት አከባቢ ሰልፉ ከጠሩት ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተወሰኑ በሮማናት አደባባይ የተገኙ ሲሆን ፤ በአደባባዩ የተገኙት የተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሰልፉ ለመሳተፍ የመጡ  ፣

1. ዓብለሎም መለስ
2. ተስፋሚካኤል ንጉስ
3. መሓሪ ዮሃንስ
4. ሃይለኣብ ሃይለስላሴ
5. ፍቕረ ኣሸብር
6. ንጉስ ኣረፈ
7. ሸዊት ውዳሴ
8. ሃፍቶም ኪዳነ ማርያም
9. ጌትነት ገብረእግዚኣብሄር
10. ጠዓመ ብርሃኑ
11. ካሕሳይ ሃይሉ (ገረብ ፃና)

ሰልፉ ለመሳተፍ ከመጡ ደግሞ  
1. ፀጋይ ገብረመድህን 

ሁሉም በፓሊስ መኪና ተወስደዋል።

ከተወሰዱ በኋላ የተወሰኑ ተሳታፊዎች መፈክር እያሰሙ ከአደባባዩ አንድ አቅጣጫ  ወደ  መሃል  ለመገባት ሲሞክሩ በፓሊስ ተባረዋል፤ የተወሰኑ ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

እስከ ረፋዱ 4:30 ሰልፉ ለመዘገብ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ፣ የአሜሪካ ድምፅ ( VOA) ፣ የጀርመን ድምፅ ( DW) እና ሎሎች ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች በሮማናት አደባባይ የተገኙ ሲሆን የክልሉ ሚድያዎች በቦታው አልነበሩም። 

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም መጪው አዲስ ዓመት 2016 ዓ.ም በማስመልከት ለሚድያዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ " ሰልፍ እንዳይካሄድ ተብሎ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ ነገ (ጳጉሜን 2/2015 ዓ.ም) ሰልፍ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ የለም " ማለታቸው ይታወሳል።

More - @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia                    
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀኑን ሙሉ ወይም ሳምንቱን ሙሉ በነፃ ከሳፋሪኮም ወደ ሳፋሪኮም ማውራት እንችላለን ፣ ከኛ የሚጠበቀው የሳፋሪኮም ቁጥራችን ላይ ከ5 ብር ጀምሮ ካርድ መሙላት ብቻ ነው።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
የ " ቶኪ በአ " በዓል ተከብሮ ዋለ።

" ቶኪ በአ " በዳውሮ ብሄረሰብ ዘንድ  ከጥንት ጀምሮ የክረምት ወራት ማብቂያና የፀደይ ወራት መግቢያ በአሮጌ ዓመት መጨረሻና አዲሱ ዓመት መግቢያ መካከል ባለው ጳጉሜ ወር የሚከበር በዓል ነው።

በዓሉ ህዝቡ በሠላም ላከረመው አምላክ ምስጋና የሚቀርብበትና መጪው ግዜ ከቤተሰብ እስከ ሀገር የሰላም ፣ የጤና፣ የጥጋብ እንድሆን በመመኘት፣ ችቦ በመለኮስ፣ ከየአይነቱ ቤት ያፈራው ምግብ ተዘጋጅቶ በታላቅ ደስታ የሚከበር በዓል ነው።

የዘንድሮው የ "ቶኪ በዓ" በዓል ዛሬ ጳጉሜን 2  በታርጫ ከተማ  ተከብሮ ውሏል።

" የጥንት አባቶች ጠብቀው ያቆዩልንን ባህል በመንከባከብና በማሳደግ ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ የሁላችንም ኃላፊነት " መሆኑ በበዓሉ አከባበር ላይ ተገልጿል።

መረጃው የዕድገቱ ነው (ከዳውሮ ታርጫ)።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#G20 አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት። የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል። ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት…
" አፍሪካ ሕብረት እንዲገኝ ጥሪ አልደረሰንም " - ኤባ ካሎንዶ

አዲሱ የቡድን 20 የበለጸጉ ሀገራት ዓባል ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የአፍሪካ ኅብረት ቡድኑ በሳምንቱ መጨረሻ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ እንዳልተጋበዘ ገልጿል።

ነገ ዓርብ እና ቅዳሜ በኒው ደሊ የሚካሄደውን ጉባኤ ያዘጋጀችው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ አፍሪካዊው ድርጅት ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ አድርገው ነበር።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ቃል አቀባይ የሆኑት ኤባ ካሎንዶ፣ ኅብረቱ በጉባኤው ላይ እንዲገኝ ጥሪ እንዳልደረሰው ትናንት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል።

19 ሀገራትን እና የአውሮፓ ኅብረትን በዓባልነት ያቀፈው ስብስብ፣ 85 በመቶ የዓለምን የሀገር ውስጥ ምርት እና ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሶስተኛውን ይይዛል።

ደቡብ አፍሪካ ከአህጉሪቱ ብቸኛዋ የቡድኑ ዓባል ነች፡፡

“የአፍሪካ ኅብረትን የጋበዝነው ወደፊት ቋሚ ዓባል እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ነው” ሲሉ ሞዲ ከ 10 ቀናት በፊት ተናግረው ነበር።

“የአፍሪካ ኅብረትን በቋሚ ዓባልነት ሞቅ አድርገን ለመቀበል እንጠብቃለን” ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው ታህሳስ ተናግረው ነበር፡፡

የቡድን 20 አባላት እነማን ናቸው ?

🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት ናቸው።

#ኤኤፍፒ #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

ዕቁብ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ!
ከፍተኛ የተቀማጭ ወለድ እና የብድር አማራጮች የሚያገኙበት፡፡

ለበለጠ መረጃ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡ https://www.bankofabyssinia.com/saving-account/

#Equb #BankofAbyssinia  #BankingService  #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#iPhone #Apple

የአፕል የገበያ ድርሻ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በ200 ቢሊዮን ዶላር ቀነሰ።

ከሰሞኑን የቻይና መንግሥት የአፕል ምርት የሆነውን #አይፎንን ማገዱ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

እገዳው ምናልባት ከደህንነት ጋር ሊያይዝ ይችላል ተብሏል።

ይህን እገዳ ተከትሎ የአፕል የገበያ ድርሻ ለ2 ተከታታይ ቀናት ቅናሽ ማሳየቱ ተነግሯል።

የድርጅቱ የድርሻ ገበያ ከ6 በመቶ በላይ የቀነሰ ሲሆን ይህም ማለት በ200 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት ሁለት ቀናት ቀንሷል።

ቻይና የአፕል ምርቶች ሦስተኛዋ ትልቁ ገበያ ስትሆን ከዓመታዊ ገቢው 18% የሚገኘውም ከቻይና ገበያ ነው።

ግዙፉ የአፕል ምርቶች አምራች የሆነው ፎክስኮን በርካታ የአፕል ምርቶችን የሚሠራው በቻይና ነው።

ዋል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው የማዕከላዊ ቻይና መንግሥት ሠራተኞች አይፎን ለሥራ እንዳይጠቀሙና መ/ቤት ይዘውም እንዳይሄዱ ታግደዋል።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ዕገዳው በመንግሥት የሚተዳደሩ ተቋሞችን እንዲሁም መንግሥት የሚደግፋቸውን ተቋሞችም ይጨምራል።

ስለዘገባዎቹ ከቻይና መንግሥት የተሰጠ ምላሽ የለም።

ይህ በቻይና መንግሥት ይፋ የተደረገው ዕገዳ የተጣለው አይፎን 15 ከመውጣቱ ከ5 ቀናት በፊት ነው።

አፕል የዓለም ትልቁ የስቶክ ገበያ ያለው ሲሆን፣ ገበያው ወደ 2.8 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ2016

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሰት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ለመላው ምዕመናን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህም መልዕክታቸው ላይ ፤ " አሁን #አገራችን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪና አሳሳቢ ሆኖ እናየዋለን፡፡ " ብለዋል።

" ምክንያቱም አገራችን በፈጠራት ፈጣሪዋ ምንም ሳታጣና ሳይጎድላት እኛ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠርነው ምድራውያን ሰዎች እርስ በርሳችን በመገፋፋትና በመጋጨት ያለማቋረጥ መጠፋፋትንና መገዳደልን የምናስተናግድ ሆነናል፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሁሉም መስክ በአስተዋይነትና በጥበብ ነባራዊውን የጥፋት ሁኔታ ከባለፈው የስቃይ ጊዜ በመማር የሁሉንም የአገሪቱ ሕዝቦች ድምጽ በመስማት የወንድማማቾችን ግጭት በሕዝቦች ውይይት፣ በዕርቅና በሰላም ብሎም በእውነትና በመቻቻል መንፈስ ነገሮችን በማሰከንና የአብሮነትና የሰላም ጉዞ በእዲስ ዓመት እንዲመጣልን አጥብቀን እንመኛለን ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ፤ " ዜጎች በሰላምና በደስታ በልማትና በሥራ እንዲተጉና እንዲሳተፉ ታዳጊዎች ልጆቻችንም በተስፋና በፍቅር የሚያድጉባት አገር እንድትኖረን መልካም መሠረት ለመጣል እንድንተጋ ሁሉንም በእጽንዖት እንጠይቃለን " ብለዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

" 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል " -የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተገልጋዮች ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ነው አለ።

ይህን ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ " የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር " መሆኑን ገልጸዋል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርም ለቅሬታዎቹ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።

ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቀጥታ (online Visa) አገልግሎት ይጀመራል ብለዋል።

የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈበት ሰው ዘወትር #ቅዳሜ ቀን እየመጣ መስተናገድ ይችላልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች ፣ እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ተቋም ውስጥ አለ ባለው ሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት በርካታ ዜጎች ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል። ፓስፖርት ለማግኘትም ያለው የጊዜ ርዝመት እና እንግልት እጅግ በርካቶችን ያማረረ ነው።

@tikvahethiopia