TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን ጠራ።

ዩኒቨርሲቲው የ2015 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ተማሪዎች ከመስከረም 3-6/2016 ዓ.ም ወደ ግቢ እንዲገቡ በዛሬው ዕለት ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

የተማሪዎች የምረቃ ጊዜ መስከረም 26 / 2016 ዓ.ም መሆኑንም አሳውቋል።

ምንጭ፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

@tikvahethiopia
የሰራዊቱ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በማዘጋጀት በአገልግሎት ላይ እያዋለ መሆኑን አሳውቋል።

ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ የቀየረ ሲሆን ከነሃሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሸከርካሪዎች ላይ በመለጠፍ አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ እንደሚደርስ ይፋ ሆናል።

የሰሌዳ / ታርጋ ቅያሪ የተደረገው በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሰሌዳዎች ከተቋሙ እውቅና ወጪ በሌሎች እጅ በመገኘቱ ነው ተብሏል።

በመሆንም እነዚህ ከተቋሙ እውቅና ውጭ በሌሎች እጅ የገቡ ሰሌዳዎች ለህገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ ሰሌዳው መቀሩን ሚኒስቴሩ አስረድቷል።

የተቀየሩት ሰሌዳዎች የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት #በኮድ ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል። #EPA

@tikvahethiopia
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopia
#itel_Mobile

የዘመነ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ብሎም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚደገፈው አዲሱ አይቴል S23+ ሞዴል አስደናቂ በሆነ መልኩ ማንኛውንም አይነት ፎቶ በየትኛውም ጊዜ ማንሳት የሚያስችል ብቃት ያለው ድንቅ ስልክ ሲሆን የፊትለፊት 32ሜጋ ፒክስል እና ዋናው የኃላ ካሜራ 50ሜጋ ፒክስል ካሜራ ያካተተ ነው ። itel S23+ የሚያስደንቁ ፎቶዎችን በዝቅተኛ ብርሀን ውስጥም ቢሆን በጥራት እና ቀለማትን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል አቅም አለው ።

አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us :  Facebook Instagram
#COOP

ቴሌግራም ለምን አይነት ጉዳዮች እየተጠቀሙ ነው?
ከወዳጆችዎ ጋር ለመጨዋወት፣ ፋይሎችን ለመላላክ፣ መረጃ ለማግኘት...?

ኮፕ ቻፓግራም @ChapagramBot ቀላል እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በቴሌግራም ገንዘብ መላክ፣ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገራት መቀበል እንዲሁም ክፍያ ክፍያ መፈፀም እንዳስቻለስ ያውቁ ኖሯል?
TIKVAH-ETHIOPIA
የታሰሩት የምክር ቤት አባላት የት ናቸው ? በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተያዙ የም/ቤት አባላት ታስረውበት ከነበረው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የማቆያ ቦታ እንደሌሉ እና ያሉበትን ቦታ ማወቅ እንዳልቻሉ ከጠበቆቻቸው አንዱ ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ…
#EHRC

አዋሽ አርባ ላይ ታስረው የሚገኙ አብዛኞቹ እስረኞች ለእስር የተዳረጉት #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 5 የኮሚሽኑ ባለሙያዎች የሚገኙበት ቡድን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በቁጥጥር ሥር ውለው አዋሽ አርባ አካባቢ በሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙትን ታሳሪዎች ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ጎብኝቷል።

እነዚህ ታሳሪዎች ፦
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣
- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣
- የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሳ ተሻገር፤
- ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ፣ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ፤
- የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ አቶ በለጠ ጌትነት፤
- በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በኃላፊነት ይሠሩ የነበሩት አቶ ከፋለ እሱባለውን ጨምሮ በአጠቃላይ 53 ወንድ እስረኞች ሲሆኑ ከአዲስ አበባ ከተማና ከአማራ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በተለያየ ጊዜ ተይዘው ከነሐሴ 15 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የሚገኝ ጊዜያዊ / መደበኛ ያልሆነ ማቆያ ጣቢያ የተወሰዱ ናቸው፡፡

ኮሚሽኑ በተለመደው አሠራሩ መሠረት ታሳሪዎቹን ለብቻቸው አነጋግሯል፣ ቦታውን ጎብኝቷል እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የፖሊስ ኃላፊዎች አነጋግሯል፡፡

የፖሊስ ኃላፊዎች ለኮሚሽኑ እንደገለጹት ፤ ታሳሪዎችን ወደዚህ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ማምጣት ያስፈለገው አዲስ አበባ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ላይ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ታሳሪዎች ምን አሉ ?

እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው #አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት ደግሞ #በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆነ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን አመልክተዋል።

ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ታሳሪዎቹ የአዋሽ አርባ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ያለው በመሆኑና ከአካባቢው የአየር ጠባይ እንዲሁም ቦታው የወታደራዊ ካምፕ እንጂ መደበኛ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ስፍራ ስላልሆነ ለጤንነታቸው፣ ለደኀንነታቸውና ለሕይወታቸው ሥጋት እንዳላቸው፣ አልባሳትን ጨምሮ ከቤተስብ የሚፈልጉትን አቅርቦት ለማግኘት እንዳልቻሉ፣ ከፊሎቹ በሥራቸውም ሆነ በግል ሕይወታቸው ፈጽሞ በፖለቲካ ነክ ጉዳይ ተሳትፎ እንደሌሉና እንዴት ለእስር እንደበቁ መገረማቸውንና መደንገጣቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተስብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ ተደርሷል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" የህዝብን ደህንነት መጠበቅ የመንግስት ዋነኛ ተግባር መሆኑ መዘንጋት የለበትም " - የትግራይ ዩኒቨርስቲዎች ምሁራን ማህበር

የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሁራን ማህበር ከቅርብ ግዚያት ወዲህ በክልሉ እየታዩ ያሉ የፀጥታ ስጋቶችና ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። 

ማህበሩ በመግለጫው እንዳለው ባለፉት ወራት በክልሉ የከተማና የገጠር አከባቢዎች ወንጀሎች እየተበራከቱ ሰዎች እየተገደሉ ፣ አካላቸው እየጎደለ ፣ እየታፈኑ  ፣ ንብረታቸው እየተዘረፉ ነው ፤ ለምሳሌ በኣሸንዳ ሳምንት ያጋጠሙ ሁለት ከፍተኛ ወንጀሎች ለበርካቶች የሞትን የመቁሰል አደጋ ምክንያት ሆነዋል ሲል ገልጿል።

በተለይም በእህታችን ዘውዱ ሃፍቱ ላይ ያጋጠመ ወንጀል የተለየ እጅግ ዘግናኝና አሰቃቂ የግድያ ተግባር ነው ያለው የማህበሩ መግለጫ " በዚህም በዓሉን ለማክበር ከሌላ አከባቢ ለመጣና ለነዋሪው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል " ብለዋል። 

የምሁራን ማህበሩ መግለጫ ወንጀሎች ፣ የሰላምና የድህንነት ስጋቶች እየቀነሱ ሳይሆን እየጨመሩ መሆናቸው ገልፆ ፤ የግዚያዊ መንግስቱ አስተዳደርና በየደረጃው ያሉት የመንግስት አካላት የህዝብ ደህንነት መጠበቅ ዋነኛና የቀን ተቀን ተግባራቸው መሆን መዘንጋት የለባቸውም ሲል አስገንዝቧል።

#ስለ_ዘውዱ_ሃፍቱ ፦ ነሃሴ 13/ 2015 መኪና በሚነዱ ማንነታቸው እስከ አሁን ባልታወቁ ሰዎች በመቐለ ፤ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ደስታ ሆቴል አከባቢ በአሰቃቂ ሁኔታ ለህልፈት የተዳረገች እንስት ስትሆን ፤ በወቅቱ አብራት የነበረች ሰምሃል የተባለች ጓደኛዋ በሁኔታው ደንግጣ ዓይደር ሆስፒታል ገብታለች።

የዘውዱ ገዳዮች እስከ አሁን በቁጥጥር ስር ባለመዋላቸው ህዝቡ በተለይ በውስጥና በውጭ የሚገኙ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎች ቁጣቸው በመግለፅ ላይ ናቸው። የከተማው ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ የምርመራው ስራ ስላልተጠናቀቀ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደሚቸገር አመልክቷል።

በሌላ መረጃ ፤ ነሃሴ 26 / 2015 ዓ.ም አመሻሽ 12:20  በመቐለ በተለምዶ " ዳያስፓራ " ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከባድ ወንጀል  ተፈፅሟል።

በአከባቢው የነበሩ የአይን እማኞች እንዳሉት የሰሌዳ ቁጥር " 02779 ኮድ 3 " ከሆነች መኪና በመውረድ በጉዞ ላይ የነበረ አንድ ወጣትን ለማጥቃት ሲጀምሩ ሰው ስለደረሰባቸው በያዙዋት መኪና ገጭተው አምልጠዋል። 

ይህንን መሰል የወንጀል ተግባሮች በመቐለ እና በሌሎች የክልሉ ከተሞች እየተባባሰ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ማሳያ ናቸው መባሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahFamilyMekelle
                          
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሁን ጊዜው ማርሻችንን ወደላቀ ስኬት የምንቀይርበት ነው!

#GearUp #FutherAheadTogether
በጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ የተፃፈው 'ስለእኛ ' የፋሽን ፣ የውበትና የአኗኗር ዘይቤ ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል።

መፅሀፉ በቤት ውስጥ ውበትን ለመንከባከብ የሚረዱ ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን የሚጠቁም ፣ - ተለዋዋጭ በሆነው የፋሽን አለም ለሁኔታዎች ካለን አመለካከት ፣ከቁመና ፣ ከእድሜና ከውሏችን ጋር የተጣጣመ የአለባበስ ስታይል /ዘይቤ እንዴት መምረጥ እንደምንችል በቀላል አቀራረብና በምስል የተደገፈ ገለፃ የሚሰጥ እንዲሁም በጤናማ የአ ኗኗር ዘይቤ ላይ ያተኮረ ነው።

መፅሀፉ በ206 ገፅ በቀለም ህትመት የቀረበ ሲሆን በጃፋር መፅህፍት ፣ በተመረጡ የወንዶችና ሴቶች ውበት መጠበቂያ ማእከላትና ቡቲኮች ገበያ ላይ ውሏል።

ጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ ከዚህ ቀደም በልጆች አስተዳደግ ላይ ያተኮረ መፅሀፍ ለአንባቢዎች አድርሳለች።
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተገናኝተው ተነጋገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር " መልካም የሥራ ግንኙነት ስለመፍጠር " መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት አሳውቋል። ውይይቱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ…
የሰራተኞች ጥያቄ ምንድነው ? ከሰሞኑን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይት ምን ጥያቃ ተነሳ ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?

(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ደሞዝ ተከፋዩ ሰራተኛ ችግር ላይ ነው ያለው። በተለይ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆነው ሰራተኛ እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ይገኛል።

ለኑሮ ውድነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ከሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የታየው የዋጋ ንረት፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያቶች ሲሆኑ #ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ጦርነቶች እና ግጭቶች ለኑሮ ውድነት አስተዋፅኦ አድርገዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ፦

- ሰራተኛው በጣም ችግር ላይ ስለሆነ  የስራ ግብር ይቀነስ።

- ዝቅተኛ ደመወዝ የሚከፈላቸው ጭራሽ መኖር ወደማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለደረሱ የገበያው ሁኔታ ታይቶ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ይወሰን።

- ለሁለት ዓመት የተቋረጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ተመልሶ እንደገና ስራ እንዲጀምር። ይህ ቦርድ ከመንግሥት 5 ከሠራተኛ 5 ፣ ከአሰሪ 5 የሚሳተፉበት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አፈፃፀምን እየተከታተለ አቅጣጫ የሚሰጥ ችግር ሲኖርም የሚፈታ ነው። ይህ ቦርድ ስራው በመቋረጡ የሠራተኞችን ጉዳይ ተጠያቂ የሚደረግበት ቦታ አልነበረም።

- 20/80 ተግባራዊ አልሆነም ተግባራዊ ይደረግ። ይህ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለሚቀጥሩት ሰራተኛ ይከፍላሉ ተብሎ የወጣ መመሪያ ነው። መመሪያው የሚለው ለሰራተኛው 80% ለአስተዳደራዊ ወጪ 20% ይውሰድ የሚልነው።

- በነፃ የመደራጀት እና የመደራደር መብት ይከበር። ሰራተኞች ለመደራጀት ሲሞክሩ / ሲደራጁ በአሰሪዎቻቸው እርምጃ ይወሰድባቸዋል ፣ እርምጃዎቹ ከቦታ ቦታ ማዘዋወር፣ ከድራ ዝቅ የማደረግ፣ ከስራ ማባረር ይጨምራሉ። ስለዚህ ህግ በሚፈቅደው የመደራጀት እና የመደራደር መብታቸው ይጠበቅ ይህጉ ይፈፀመ።

- በሀገሪቱ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሰራተኞች ላይም ጉዳት እያመጣ አንዳንድ ቦታዎች ሰራተኞች እንደሚታገቱ፣ እንደሚገደሉ፣ ስለሚታወቅ ያ ጉዳይ ተነስቶ መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምንድነው ?

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዝቅተኛ ደመወዝ ወለል፣ ስራ ግብር ቅነሳ፣ ከአማካሪ ቦርድ ጋር በተያያዘ ሌሎችም ለተነሱ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

" ጥያቄዎቹ ትክክል አይደሉም " ፤ ወይም " አይፈፀሙም " የሚል ምላሽ አልተሰጠም። በጊዜ ሂደት ምላሽ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ምላሽ የሚሰጡት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በመሆኑ ይታያል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።

ወዲያው መፈፀም ያለበት የአማካሪ ቦርድ መቀጠል ላይ ቅድመ ሁኔታ የማያስፈልገው ስለሆነ እሱ እንዲቀጥል ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ሌሎችም ጥያቄዎች እንዲታዩ በሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)

@tikvahethiopia
" ቲክቶክ " ኪርጊስታን ውስጥ እንዲታገድ ተወሰነ።

ኪርጊስታን " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው በሚል ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስናለች።

ውሳኔውን ያሳለፈው የሀገሪቱ የባህል ፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ነው።

ሚኒስቴሩ ባደረገው ግምገማ መሰረት " ቲክቶክ " ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ መቆጣጠሪያ እንደሌለው ገልጿል።

በተጨማሪም መተግበሪያው ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደሌሉት ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት ይስባል እናም እነዚህን ክሊፖች ከተመለከቱ በኋላ አንዳንድ ሰዎች ለሕይወት አስጊ የሆኑ አደጋዎችን የሚያስከትሉ ቪዲዮዎችን ለመኮረጅ ይሞክራሉ ሲል አክሏል።

እንዲህ ያለው #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ የገለፀው ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ "ን ከሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ እንዲታገድ ወስኗል።

ቲክቶክ ለሀገሪቱ እገዳ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።

" ቲክቶክ " በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ ሀገራት የሚደረግበት እገዳ እና ገደብ እየጨመረ መሆኑ ተነግሯል።

" ቲክቶክ " ከዚህ ቀደም በምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር #ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ መቅረቡ ይታወሳል። በወቅቱም የፓርላማው አፈጉባኤ  " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦ ግጭቶችን በማባባስ፣  ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣ የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣ የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣ አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ተናግረው ነበር።

የእግዱ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ ግን የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ከ " ቲክቶክ " ስራ አስፈፃሚ ጋር በመነጋገር በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ስምምነት ላይ ሊደርሱ ችለዋል።

ከኬንያ በተጨማሪ ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፣ አሰቃቂ ቪድዮዎች ያለገደብ ይሰራጩበታል፣ ህዝቡንም አሳሳች መልዕክቶች ይዘዋወሩበታል በሚል እንዲታገድ መወሰኗ ይታወቃል።

የ " ቲክቶክ " መተግበሪያ በተለይ ፦

- ህፃናት ፣ ወጣቶች እንዲያዩትና እንዲሰሙት የማይመከሩ ቪድዮዎችን፤
- ልቅ የሆኑ የብልግና ስድቦችን ፤
- የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን፤
- ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን . . . የመሳሰሉትን በፍጥነት እንዲሁም እጅግ በቀላሉ ወደ ብዙሃን ያደርሳል ፤ ይህንን  የሚቆጣጠርበት ስርዓት የለውም በሚል ይተቻል።

መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላልና ማንኛውም ሰው የሚሰራው ቪድዮ በቀላሉ ለብዙሃን የሚደርስበት መንገድ ችግሩን እንዳባሰው የሚገልጹም አልጠፉም።

ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ " ቲክቶክ " በተለያዩ ሀገራት በርካታ ወጣቶች ተሠጥኦቸውን አውጥተው በቀላሉ ተደራሽ እንዳሆኑ ፣ በሚሰሯቸው ስራዎችም ክፍያዎችን እያገኙ እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲደግፉ ፣ ሀሳብ ያላቸውም ሀሳባቸውን በቀላሉ ለብዙሃን እንዲያደርሱ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው በሚል የሚያወድሱት አሉ።

@tikvahethiopia