#G20
አፍሪካ ህብረት G20ን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የ " አፍሪካ ህብረት " የቡድን 20 አባል እንዲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ ማቅረባቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
በሚቀጥለው ወር በሕንድ ፤ ኒው ዴሊ የቡድኑ መሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል።
ሞዲ ለአፍሪካ ህብረት ጥሪውን ያቀረቡት " ቢ20 የተሰኘው በቢዝነስ ፎረም እና የመስከረም ወሩ ጉባዔ መዳረሻ መድረክ ላይ ማደረጉት ንግግር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ የዓለም አቀፉ የአቅርቦት ሰንሰለት ችግሮችን ለመቅረፍ ሀገራቸውን እንደመፍትሔ አቅርበዋል።
የ20 ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ስሪት የሆነው ቡድን 19 አገሮችን እና የአውሮፓ ህብረትን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ፣85 በመቶውን ዓለም አቀፉ ጥቅል የሀገራት ምርት መጠን እና ከዓለም ህዝብ መካከል ደግሞ ሁለት ሶስተኛውን ይሸፍናል።
ይሁንና ከአፍሪካ የህብረቱ ብቸኛ አባል ደቡብ አፍሪካ ናት።
በታህሳስ ወር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ህብረት የቡድን 20 ሀገራት G20 ቡድንን በቋሚ አባልነት እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ ተናግረው ነበር።
በዛሬው ዕለት የወቅቱ የቡድኑ ጉባዔ አስተናጋጅ ሀገር ሕንድ መሪ ሞዲ ባለፈው አመት በአጠቃላይ 3 ትሪሊዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያስመዘገበው ፓን- አፍሪካዊ ህብረት በቡድኑ አባልነት እንዲካተት ጥሪ አቅርበዋል።
" ቋሚ አባልነት በመስጠት ራዕይ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት ግብዣ አቅርበናል " ሲሉ ተናግረዋል ።
መቀመጫውን በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት 55 አባላት ያሉት ሲሆን በወታደራዊ አስተዳደር ስር የሚገኙ አምስት ሀገራት ግን በአሁኑ ጊዜ ከአባልነት ታግደዋል ሲል ቪኦኤ በዘገባው አስታውሷል።
የቡድን 20 አባላት እነማን ናቸው ?
🇦🇷 አርጀንቲና
🇧🇷 ብራዚል
🇨🇦 ካናዳ
🇨🇳 ቻይና
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇩🇪 ጀርመን
🇮🇳 ህንድ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇮🇹 ጣልያን
🇯🇵 ጃፓን
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇲🇽 ሜክሲኮ
🇷🇺 ሩስያ
🇸🇦 ሱዑዲ አረቢያ
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇹🇷 ቱርክ
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇺🇸 አሜሪካ
🇪🇺 አውሮፓ ሕብረት ናቸው።
@tikvahethiopia

#Update
በቡዳፔስት ሲደረግ የነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሚደረጉ ውድድሮች ፍፃሜውን ያገኛል።
በዛሬው የፍፃሜ መርሃ ግብር ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትካፈልበት የ5000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦
- በአትሌት በሪሁ አረጋዊ
- በአትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ
- በአትሌት ሀጎስ ገብረሕይወት ተወክላለች።
መልካም ዕድል !

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኢትዮጵያ በ5000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ድል አልቀናትም።
ዩሚፍ 5ኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ፤ ሀጎስ 6ኛ ፤ በሪሁ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ወርቁን ኖርዌይ ስትወስድ ፤ ስፔን ብር ፤ ኬንያ ደግሞ ነሃስ አግኝታለች።
@tikvahethiopia
ዩሚፍ 5ኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ፤ ሀጎስ 6ኛ ፤ በሪሁ 8ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ወርቁን ኖርዌይ ስትወስድ ፤ ስፔን ብር ፤ ኬንያ ደግሞ ነሃስ አግኝታለች።
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች።
በውድድሩ ሀገራችን ፦
- በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ
- በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ
- በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች።
መልካም ዕድል !
@tikvahethiopia
ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች።
በውድድሩ ሀገራችን ፦
- በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ
- በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ
- በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች።
መልካም ዕድል !
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጨረሻዋ ውድድር የሆነውን የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ውድድር ማድረግ ጀምራለች። በውድድሩ ሀገራችን ፦ - በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ - በአትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ - በአትሌት ሎሜ ሙለታ ተወክላለች። መልካም ዕድል ! @tikvahethiopia
#ተጠናቋል
በዚህም ድል አልቀናንም !
በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ ድል አልቀናትም።
ዘርፌ ወንድማገኝ 4ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።
ሎሜ ሙለታ 12ኛ ፣ ሲምቦ አለማየሁ 13ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ሀገራችን በሀንጋሪ፣ ቡዳፔስት ስታካሂድ የነበረውን ውድድሮች ሁሉ #አጠናቃለች።
ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም 6ኛ ደረጃ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ኬንያን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች። ኢትዮጵያ 2 የወርቅ፣ 4 የብር እና 3 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ነው ያገኘችው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዋና ገፅ / @tikvahethiopia ስፖርት በተለይ አትሌቲክስ #ሀገራዊ ስሜትን ፣ አብሮነትን ፣ አንድነትን ያጠነክራል የሚል እምነት ስላለው የሀገራችን ልጆች የተካፈሉባቸውን ውድድሮች ሁሉ #ከስፍራው ከፎቶ ጋር ሲያደርስ ቆይቷል።
ስፖርታዊ መረጃዎችን በ @tikvahethsport መከታተል ትችላላችሁ።
#TikvahFamily

ፖለቲካዊ ጉዳዮችንና ተያያዥ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገው የሚከሰቱ ቀውሶች ብዙ ዋጋ እያስከፈሉ ነው፡፡
ለተከታታይ ዓመታት በየምክንያቱ የተፈጠሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች፣ እንዲሁም የለየለት ጦርነቶች በሕይወትና በንብረት ላይ ያደረሱት ውድመት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የማይሻሩ ጠባሳዎችንም አኑረዋል፡፡
ያለመረጋጋቶቹ የፈጠሯቸው አያሌ ጥፋቶች አገራዊ ኢኮኖሚው ላይም ያሳረፈው ተፅዕኖ በቀላሉ ሊጠገን የማይችል ስብራት ከማድረሱም በላይ፣ የአገር ዕድገት ወደኋላ እንዲጎተት አድርጓል፡፡
ከአንደኛው ችግር ወጣን ስንል ሌላ ችግር እየተተካ ስናስተናግደው የቆየነው ትርምስ ዛሬም መቋጫ ያልተገኘለት በመሆኑ፣ አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያለማቋረጥ የቀጠሉ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች የአገሪቱን ሀብት እየበላ ነው፡፡
ለልማት መዋል የሚችል ገንዘብ እየታጠፈ በየጊዘው የሚፈጠሩ ቀውሶች ማብረጃ ሲሆን ቆይቷል፡፡
ባለፉት ዓመታት አገራችን ያጋጠማትን ተደራራቢ ችግሮች ለመወጣት የወጣውን ወጪ ቤት ይቁጠረው እንጂ፣ መልሰን ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመግባትም የሚጠይቀን ድካምና ወጪ አገሪቱ መሸከም ከምትችለው በላይ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡
በተከታታይ የተከሰቱና እየተፈጠሩ ያሉት ቀውሶች መነሻቸው ምንም ይሁን ምን፣ እንደ አገር እያስከፈለ ያለው ዋጋ ነገም ላለመቀጠሉ እርግጠኞች አይደለንም፡፡
ማንኛውም ግጭትና ቀውስ ከሚያስከትላቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች ውስጥ በግብይት ሥርዓት ውስጥ እያስከተለ ያለውን ችግር ብቻ ነጥለን እንኳን ብናይ ጉዳቱ እያንዳንዱን ዜጋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ዋጋ አስከፍሎታል፡፡
ያንብቡ ፡ https://telegra.ph/Reporter-08-28
(ሪፖርተር ጋዜጣ)

Telegraph
Reporter
መንግሥት ሰላም በሌለበት የዋጋ ንረትን ማርገብ እንደማይቻል ይገንዘብ ! ፖለቲካዊ ጉዳዮችንና ተያያዥ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገው የሚከሰቱ ቀውሶች ብዙ ዋጋ እያስከፈሉ ነው፡፡ ለተከታታይ ዓመታት በየምክንያቱ የተፈጠሩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች፣ እንዲሁም የለየለት ጦርነቶች በሕይወትና በንብረት ላይ ያደረሱት ውድመት እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ የማይሻሩ ጠባሳዎችንም አኑረዋል፡፡ ያለመረጋጋቶቹ የፈጠሯቸው አያሌ ጥፋቶች…
በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል ለምን ተቋረጠ ?
የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከነሃሴ 21 /2015 ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ በመላ ትግራይ መቋረጡ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት ትግራይ ቅርንጫፍ በተገኘው መረጃ መሰረት አገልግሎቱ የተቋረጠው በመኾኒ ባጋጠመ የመስመር መቋረጥ ነው።
ችግሩን ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ለመፍታት አስቀደመው ወደ ተላኩ ባለሙያዎች ተጨማሪ የሰው ኃይል መላኩን በኢትዮጵያ መብራት ኃይል አገልግሎት የትግራይ ቅርንጫፍ የኦፕሬሽን ትራንስሚሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገ/እግዚአብሄር ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

#AddisAbaba " የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተን ለማደር ተቸግረናል " - ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከጤፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተው ለማደር መቸገራቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። ለሪፖርተር ጋዜጣ ቃላቸውን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎች ፤ ሰሞኑን የአንድ እንጀራ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት 17 ብር ወደ 22 እና 24 ብር ከፍ በማለቱ፣ ገዝተው ለመጠቀም ተቸግረዋል፡፡ እንጀራን…
የዳቦ እና እንጀራ ዋጋ ስንት ገባ ?
በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች (የመኖሪያ መንደሮች) የአንድ ትንሹ ዳቦ ዋጋ ከወራት በፊት ከነበረበት 4 እና 5 ብር አሁን ላይ 9 -10 ብር መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
የዳቦ ዋጋ ባለፈው ዓመት 5 ብር በገባበት ወቅት ብዙ ሲባል የነበረ ሲሆን በተወሰኑ ወራት ልዩነት እጥፍ በሚያስብል ደረጃ እንደጨመረ አመልክተዋል።
ሁሉም ነገር የአንድ ሰሞን የማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ይሆንና መፍትሄ ሳይሰጠው በዛው ይቀጥላል ፤ የኑሮው ጫና እጅግ እየከበደ ነው ብለዋል።
መፍትሄው ግራ የሚያጋባ ነው ያሉት አስተያየታቸውን የላኩ የቤተሰባችን አባላት ፤ የአንድ ዳቦ ዋጋ ቀስበቀስ እየጨመረ መጥቶ ወደ 10 ብር ተጠግቷል ፤ ከዚህ ቀደም ጨመረ ተብሎ ለተነሳው ሮሮ መፍትሄ ሳይሰጥ #እንድንለማመደው ተደረገ አሁንስ እንዲሁ ይቀጥላል ? ሲሉ ጠይቀዋል።
ከሰሞኑን ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከጤፍ ዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ የእንጀራ ዋጋ በመጨመሩ በልተው ለማደር መቸገራቸውን መገለፃቸው ይታወሳል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ፤ ሰሞኑን የአንድ እንጀራ ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት 17 ብር ወደ 22 እና 24 ብር ከፍ በማለቱ፣ ገዝተው ለመጠቀም መቸገራቸውን ገልጸው እንደነበር አይዘነጋም።

የዳቦ እና እንጀራ ዋጋ ስንት ገባ ? በአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች (የመኖሪያ መንደሮች) የአንድ ትንሹ ዳቦ ዋጋ ከወራት በፊት ከነበረበት 4 እና 5 ብር አሁን ላይ 9 -10 ብር መድረሱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። የዳቦ ዋጋ ባለፈው ዓመት 5 ብር በገባበት ወቅት ብዙ ሲባል የነበረ ሲሆን በተወሰኑ ወራት ልዩነት እጥፍ በሚያስብል ደረጃ እንደጨመረ አመልክተዋል። ሁሉም ነገር የአንድ…
" ኑሮውን አልቻለነውም "
እጅግ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በየአካባቢያቸው የዳቦና የእንጀራ ዋጋ አሁን ላይ የደረሰበትን ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች አንድ ትንሽ ተብሎ የሚታሰበው ዳቦ ከ5 ብር - 9 ብር ድረስ እንደየአካባቢው የሚሸጥ ሲሆን እንጀራ ከ15-20 ብር ድረስ ይሸጣል ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው ቀጠናዎች ዋጋው እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ኑሮው እጅግ መክበዱን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ተማፅነዋል።
ከአዲስ አበባ የተለዩ አካባቢዎች በመጡት መልዕክቶች ምንም እንኳን እንደየአካባቢው ቢለያይም አንድ እንጀራ ያውም ስስ እንጀራ ከ20-25 አንዳዴም ደህና እንጀራ ከሆነ እስከ 27 ብር እንደሚሸጥ ጠቁመዋል።
ዳቦም በተመሳሳይ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ላይ እስከ 10 ብር (ትንሽ የሚባለው) የሚሸጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።
የዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን ጣራቱና መጠኑም መቀነሱን ሳይናገሩ አላለፉም።
አንድ በአዲስ አበባ በግል ስራ የምትተዳደር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " ጮኸን ጮኸን ደክሞናል ፤ መፍትሄ የሚሰጠንም አጥተናል። እኔ የማገኘው ገንዘብ ደህና ኑሮ ሊያኖረኝ ቀርቶ በልቶ ለማደርም ስለማይበቃ ከቤተሰቦቼ ጭምር ይላክልኛል " ብላለች።
አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " በጣም ከባድ ነው ፤ እኔ ነጋዴ ነኝ እገዛለሁ አትርፌ እሸጣለሁ ነገር ግን ማህበረሰቡ ያሳዝነኛል፤ በተለይ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኛ እንዴት ከ3000 ባነሰ ደመወዝ እንደሚኖሩ ሳስብ እገረማለሁ፤ ዱቄት 1200 ብር በላይ ጨምሯል፤ ዳቦ 10 ብር ነው፤ እንጀራም 20 ብር ነው ብቻ ይከብዳል፤ በጣም የማዝነው ደግሞ ጊዜው ላለው በመሆኑ ነው፤ መናገር የምፈልገው ነገር በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ከድሃ ጎሮሮ ላይ ቀምተው ሀብታም ለመባል የሚፈልጉትን ነው ሁሉም ሟች ነው ይህን እወቁት " ሲል ሀሳቡን ገልጿል።
ሌላ ነዋሪ እሱ ባለበት አካባቢ የእንጀራ ዋጋ የቤት የሚባለው 27 ብር እንደሚሸጥ የሱቅ ተብሎ ደግሞ የሚሸጠው 24 ብር መሆኑን ጠቁሞ ገዝቶ መግባት እንደከበደው ጠቁሟል።
አንዲት የቤተሰባችን አባል፤ እኛ ስቃይ ላይ ነን ዋጋውን ብንናገር ከወሬ የዘለለ መፍትሄ የለም ስትል ገልጻለች።
ሌላ ነዋሪ፤ ዛሬ ዳቦ መግዣ የሚባለው ከአንድ አመት በፊት የእንጀራ ዋጋ ነበር፤ በጣም ከባድ ነው ሲጨምርም መጠነኛ ቢሆን ጥሩ ግን ሁሉም ነገር እጥፍ በሚባል ሁኔታ ነው እየጨመረ ያለው ብሏል።
አንድ የቤተሰባችን አባል ደግሞ፤ " ነገሩ በሶሻል ሚዲያ እየተወራ ስለሆነ ነው በሁሉም አካባቢ ዋጋዉ የጨመረው " ብለዋል።
" ለምን ዋጋ ጨመራቹ ሲባሉ ሚዲያ ያለቸው
ናቸው ነገሩ እያባባሱት ያሉት በቀናት ልዩነት
ከ15 ብር ወደ 17 ብር ከዛ ወደ 20 ብር፤ ዛሬ ደግሞ 22 ገባ የሚለው የሶሻል ሚድያ ወሬ ይሰሙና እንጀራ 22 ብር ገባ ማለታቸው የማይቀር ነው " ሲሉ ገልጻዋል።
" መልስ ሊሰጠው ካልተቻለ በሶሻል ሚዲያ ላይ ባይነገር ይሻላል " ብለዋል።
በርከት ያሉ የቤተሰባችን አባላት የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ተደርጎ ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ግጭት እና ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በሙሉ ኃይል ወደ ምርት ካልተገባ ፤ ዜጎችም ደህንነታቸው ተጠብቆ በሀገራቸው እንደልብ ቀንና ማታ እየተጓዙ ያለስጋት ካልሰሩ ያለው ሁኔታዎች ከዚህ እንዳይከፋ እንደሚያሳስባቸው ገልጻዋል።
ህዝባችን ያለበት ጫና ይመለከተናል የሚሉ አካላትም ቀስ በቀስ እየጨመረ እና ዜጎችም በማይችለው አቅማቸው እንዲለማመዱት እየተደረገ ያለው በተለይ በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየውን ከፍተኛ ጭማሪ እንዲቆጣጠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Addis Lissan Hamle 29-2015 ZM (1).pdf
" ውል ማዋዋል የምንጀምረው ረቡዕ ነው "
የ5ኛዉ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ግልጽ ጨረታ አሸናፊዎችን ውል ማዋዋል የሚጀመረው ከረቡዕ 24/12/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።
አሸናፊዎች ይህ ተረድተው ለመዋዋል የሚጠበቅባቸውን ሰነድ አሟልተው እንዲቀርቡ ማሳስቢያ ተላልፏል።
ለዉል ሲኬድ ምን ማሟላት ይገባል ?
1ኛ. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ሁለት ኮፒ
2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN /
3ኛ. የጋብቻ ሁኔታን የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውን እና ሁለት ኮፒ
4ኛ. አራት/4/ ጉርድ ፎቶ
5ኛ. የዉጭ ሀገር ዜግነት ያለዉ ከሆነ ካለበት ሀገር የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚሰጥ መታወቂያ እና ሙሉ የቤቱን ዋጋ 100% መክፈል ይጠበቅበታል፡፡