TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

እጅግ ተጠባቂው የ5000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ተጀመረ።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በውድድሩ ፦
- በጉዳፍ ፀጋይ፣
- በእጅጋየሁ ታዬ፣
- በመዲና ኢሳ፣
- በፍሬወይኒ ኃይሉ ተወክላለች።

በዚሁ ፤ የ5000 ሜትር ውድድር ላይ የኔዘርላንዷ ሯጭ ሲፋን ሀሰን ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

ድል ለሀገራችን አትሌቶች !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሴቶች 5000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር ሊጠናቀቀ 3 ዙር ብቻ ቀርቶታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመጨረሻው ዙር።
#Update

የሀገራችን ልጆች በውድድሩ ብርቱ ትግል ቢያደርጉም ድል አልቀናቸውም።

የ5000ሜ የሴቶች ፍፃሜ ውድድር #በኬንያ አትሌት ኪፕዬጎን የበላይነት ተጠናቋል።

ሁለተኛ ሲፋን ሀሰን ወጥታለች።

ሶስተኛ እና አራተኛ ኬንያ አትሌቶች ሲሆኑ ፤ አምስት ፣ ስድስት ፣ ሰባት የኢትዮጵያ አትሌቶች ወጥተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሀገራችን ልጆች በውድድሩ ብርቱ ትግል ቢያደርጉም ድል አልቀናቸውም። የ5000ሜ የሴቶች ፍፃሜ ውድድር #በኬንያ አትሌት ኪፕዬጎን የበላይነት ተጠናቋል። ሁለተኛ ሲፋን ሀሰን ወጥታለች። ሶስተኛ እና አራተኛ ኬንያ አትሌቶች ሲሆኑ ፤ አምስት ፣ ስድስት ፣ ሰባት የኢትዮጵያ አትሌቶች ወጥተዋል። @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በሴቶች 5000ሜ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን ስንተኛ ደረጃ ይዘው ጨረሱ ?

5ኛ ደረጃ - እጅጋየሁ ታዬ
6ኛ ደረጃ - መዲና ኢሳ
7ኛ ደረጃ - ፍሬወይኒ ሀይሉ

የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ጉዳፍ ፀጋይ 13ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። 

የሀገራችን ልጆች ምንም እንኳን ድል ባይቀናቸውም በውድድሩ ላይ ለሀገራቸው ውጤት ለማምጣት ላደረጉት ጥረት ምስጋና ይገባቸዋል።

@tikvahethiopia    
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በሴቶች 5000ሜ ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን ስንተኛ ደረጃ ይዘው ጨረሱ ? 5ኛ ደረጃ - እጅጋየሁ ታዬ 6ኛ ደረጃ - መዲና ኢሳ 7ኛ ደረጃ - ፍሬወይኒ ሀይሉ የ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ጉዳፍ ፀጋይ 13ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።  የሀገራችን ልጆች ምንም እንኳን ድል ባይቀናቸውም በውድድሩ ላይ ለሀገራቸው ውጤት ለማምጣት ላደረጉት ጥረት ምስጋና ይገባቸዋል። @t…
#ኢትዮጵያ

በ5000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ 13ኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ዛሬ ከነጉዳቷ ወደ ውድድር የገባች ሲሆን የተሻለ መተጋገዝ ቢደረግ ኖሮ ጥሩ ውጤት ይገኝ እንደነበር ከሩጫው መጠናቀቅ በኃላ ለ " ልዩ ስፖርት " ድረገፅ በሰጠችው አጭር ቃለምልልስ ገልጻለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፦

" ትንሽ እግሬ ተልጦ ነበር ፤ ሁለት ቀን ልምምድ አልሰራሁም እዚህ ሙቀትም ስለነበር ፤ እግሬ ተልጦ ነው ወደዛሬው ውድድር የገባሁት።

ይህም ቢሆን ግን እኔ ነኝ የመራሁት ዙሩን ማለት ይቻላል። የተነጋገርነው ነገር በየ600 ለመተጋገዝ ነው ግን ሁሉንም እኔ ስለመራሁት ፊት ተሁኖ ስቆይ መቋቋም ስለማይቻል እሱ ጋር ነው ያጠፋሁት እንጂ ጠብቄ ብሄድ ኖሮ የተሻለ ውጤት ይመጣ ነበር።

የነበረብኝ ጉዳት ስሜት አለው በእርግጥ ግን እራሴን ጠብቄ መሀል ሆኜ ብሄድ ኖሮ ጥሩ ነገር ይኖር ነበር።

ውድድሩ ተይዞ ነበር ፤ #እለፉ_እያልኳቸው ነበር ልጆቹን ግን ሊያግዙኝ አልቻሉም። "

ፎቶ፦ @tikvahethsport (Hungary, Budpest)

@tikvahethiopia
#SifanHassen

ብርቱና ጠንካራዋ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቡዳፔስት በምን ያህል ርቀቶች ተካፈለች ? ምን ውጤት አስመዘገበች ?

አትሌት ሲፋን ሀሰን ፦

🇳🇱 1,500 ሜትር ማጣርያ
🇳🇱 10,000 ሜትር ፍፃሜ
🇳🇱 1,500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ
🇳🇱 1,500 ሜትር ፍፃሜ
🇳🇱 5,000 ሜትር ማጣሪያ
🇳🇱 5,000 ሜትር ፍፃሜ ሮጣለች።

አትሌቷ በድምሩ በሁሉም ውድድር 24,500 ሜትር ሮጣለች።

ከተሳተፈችባቸው ውድድሮች በ1,500 ሜትር የነሃስ እንዲሁም በ5,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። በ10000 ሜትር ፍፃሜ ውድድሩን ለመጨረስ ጥቂት ሲቀራት ወድቃ ድል ሳይቀናት ቀርቷል።

ሲፋን ከዚህ በፊት በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ1,500 ሜትር ፣ 5,000 ሜትር እና 10,000 ሜትር ርቀቶች ላይ በመሮጥ ሁለት ወርቅ እና አንድ ነሀስ አሳክታ ነበር።

በርካቶች የአትሌት ሲፋን ሀሰን ብርታ እና ጥንካሬን ፣ ለማሸነፍ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት እና ጥረት እያወደሱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

የወንዶች ማራቶን ውድድር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታምራት ቶላ ፣ ፀጋዬ ጌታቸው ፣ ልዑል ገ/ስላሴ እና ሚልኬሳ መንገሻ ተወክላለች።

ከሀገራችን አትሌቶች አሁን ላይ ወደፊት መውጣት የቻለው አትሌት ልዑል ገብረስላሴ ብቻ ሲሆን ከኡጋንዳ አትሌት ጋር ባለድል ለመሆን እየተፋለም ነው።

ታምራት ቶላ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

1 ሰዓት ከ53 ደቂቃ መሮጥ ችለዋል።

@tikvahethsport