TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ጥልዬ ዛሬም ነገም እንወድሃለን የኢትዮጵያ ጀግና አትሌት ነህ፤ ሀቋ ግን የበሪሁ ስለሆነች ነው በሪሁን ያስሮጥነው " - ረ/ኮ ደራርቱ ቱሉ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በ5000 ሜትር ውድድር እንደማይሮጥ ከሰማ በኃላ ወደ ሀገሩ ኢትዮጵያ በተመለሰው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ጉዳይ ተጨማሪ አሰተያየቷን ለሪፖርተር ሰጥታለች።

ረ/ኮ ደራርቱ ፤ " ጥላሁን ኃይሌ ቢሮጥ ደስ ይለኝ ነበር አልሮጠም መሮጥ ያልቻለው ደግሞ ሀቁ የበሪሁ አርጋዊ ስለሆነ ነው " ብላለች።

" ከዚህ በፊት ኦሪጎን ላይ በሪሁ ጥሩ ስላልሮጠ እድል እንስጠው ብለን ለጥላሁን ሰጥተን ነበር ግን ፋይናል (ፍፃሜ) አልደረሰም ፤ አሁን ላይም በሪሁ አንደኛ ነው ከዛ ሀጎስ አለ፣ ዩሚፍ አለ ፣ ጥላሁን አራተኛ ነው ፤ አንደኛ በወርልድ ራንኪንግም በቅርቡም ተሸናንፈው ነው የመጡት " ስትል ደራርቱ አስረድታለች።

" እኛ አትሌቶቹ በደረጃቸው ነው ያስቀመጥናቸው ለበሪሁ ሀቁን ነው የሰጠነው እንጂ በሪሁን አቅርበን ጥላሁንን አርቀን አይደለም ፤ ሁለቱም ለኢትዮጵያ ነው የሚሮጡት ሁለቱም የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን " ስትል ገልጻለች።

" ጥላሁን ከመናደዱ የተነሳ ደራርቱ ናት ያስቀረችኝ ብሏል ያን ለምን አለ ብዬ አልቀየመውም ፤ አትሌት ነውና ጥሮ ነው እዚህ የደረሰው ለመሳተፍ ብዙ ውጣ ውረድ አለው እኔም ያለፍኩበት ስለሆነ ይገባኛል ግን ደግሞ ሀቁ የበሪሁ ነው " ብላለች።

ደራርቱ ፤ " እኛ ጥዋት እሱንም አሰልጣኙንም አግኝተን በአግባቡ ልንነግረው ነበር " ያለች ሲሆን ግን ቀድሞ ከዓለም አትሌቲክስ ፔጅ ላይ  ተመለከተ በዚህም በጣም ተበሳጨ ፣ተናደደ አለቀሰ፤ እኔም በዚህ በጣም አዝኛለሁ እንደ እናትም እንደ አመራርም " ብላለች።

" በተፈጠረው ሁኔታ እኔ ይቅርታ ብያለሁ " ያለችው ደራርቱ " ይቅርታ ስል ደግሞ ሀቁ አሁንም የበሪሁ ነው ጥላሁን ለመሮጥ ስለጓጓ እንጂ ሀቁ የበሪሁ ነው " ስትል ገልጻለች።

" ሶሻል ሚዲያ ላይ የሚታዩ አንዳንድ ነገሮች ፤ ' ሀገር ቢቀይር በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ ' እየተባለ ነው  " ያለችው የፌዴሬሽን ፕሬዜዳንቷ " ይህ ሀገር መቀየር ግን ቀላል አይደለም ይሄ ልጅ ሀገር ቀይሮ የሌላ ሀገር ዜግነት ወስዶ መቼ ነው ያንን ሀገር የሚወክለው ፤ መቼ ነው ወርልድ አትሌቲክስ ላይ የሚሳተፈው ያን ነገር ከግምት ውስጥ ማስገባት ይገባል። " ብላለች።

" እድል ስጡት የሚሉ አስተያየቶችም ሲሰጡ ነበር ፤ እድል እንሰጠዋለን እሱን የሚያስሮጠው ውጤቱ ነው እንጂ የደራርቱን ፍቃድ ሆነ የሌላ ሰው ፍቃድ አይፈልግም ፤ ስለዚህ ማንም ሰው በችሎታውና በሰዓቱ ነው እየተመረጠ ያለው ነገም እንደዛው ነው የሚሆነው ዛሬ ይሄን ተናገረ ተብሎ ደራርቱ እዛ ጋር ተፅእኖ የምታደርግበት ምክንያት የለም ፤ ስብዕናዬም አይደለም ፤ ወደፊትም አላደርግም " ስትል አስገዝባለች።

አትሌቱን የሌላ ሀገር ዜጋ ይሁን እያሉ የሚመክሩ ሰዎች " እኛ ኢትዮጵያውያን አይደለንም ወይ ? እንደ ዜጋ ለምን አናስብም ? ይሄ ነገር ሌላ ጊዜ ባይደገም ጥሩ ይመስለኛል ለአትሌቱም መታሰብ አለበት ዛሬ እንደሄደ አይደለም ዜግነት ውስዶ ለዛ ሀገር የሚሮጠው ያም አብሮ መታሰብ አለበት እንጂ እንዲሁ ሀገር ስለቀየረ ብቻ ዛሬ ቀይሮ ነገ ይሮጣል ማለት አይደለም ፤ መቼ እዛ ሀገር ሄዶ ዜግነት ቀይሮ መቼ ነው የሚሮጠው የሚለውን ማሰብ ያስፈልጋል ስትል ገልጻለች።

ረ/ኮ ደራርቱ ፤ " ጥልዬ ዛሬም ነገም እንወድሃለን የኢትዮጵያ ጅግና አትሌት ነህ ሀቋ ግን የበሪሁ ስለሆነች ነው በሪሁን ያስሮጥነው " ስትል ተናግራለች።

@tikvahethiopia
#Oromia

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የኦሮሚያ ክልል የ2015 የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ከክልሉ የትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም  ስማቸውን እና የID. ቁጥራቸውን በማስገባት ዉጤታችሁን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አሳውቋል።

Website:- https://oromia.ministry.et/#/result

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
#ዘይት

የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት 88.1 ቶን ወይም 4,405 ካርቶን ባላ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ  የሱፍ ዘይት  ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል በአዳማ መገቢያና መውጫ ኬላ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳወቀ።

በአዳማ መገቢያ መውጫ ኬላ በኩል በቀን 15/12/2015 በተደረገ ቁጥጥር 88.1 ቶን ወይም 4405 ካርቶን ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ የሱፍ ዘይት ፦

- የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት ይህም ማለት (የተመረተበት በቀን 04/05/22 የሚያበቃበት ጊዜ ደግሞ በቀን 04/05/2023)፤
- በባለስልጣን መ/ቤቱ ያልተመዘገበ፤
- ከስሪት ሀገሩ የጤና ሰርተፍኬት ያልተያያዘ፤
- የምርቱ ገላጭ በድጋሚ የተጻፈ (relabeled ) የተደረገ፤
- የምርት መለያ ቁጥር (batch number ) የሌለው፤
- በምርት ማሸጊያው ላይ ምርቱ መያዝ ያለበትን ንጥረ ነገር አለመገጹ የተረጋገጠ ነው ተብሏል።

በተደረገው ፍተሻ የተገኙትን ጉድለቶች መሰረት በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ጥቅም ላይ እንዳይውል በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ ላይ ይህ ዜጎች ጋር ቢደረስ የጤና ጉዳት የሚያስከትል ዘይት ማን ሊያስገባው እንደነበር / ይዞት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብ ይኖር እንደሆነ የገለፀው ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ማንኛውንም ምርት ስትገዙ እባክችሁ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት መሆን አለመሆኑን አጣሩ።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ከሚጠበቁበት ውድድሮች አንዱ የሆነው የሴቶች ማራቶን ውድድር በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ውድድር በዓለም ሻምፒዮናዋ ጎይተይቶም ገብረስላሴ ፣ ፀሀይ ገመቹ ፣ አማኔ በሪሶ እና ያለምዘርፍ የኋላው ተወክላለች።

ሁሉም አትሌቶቻችን ከፊት መስመር ከሚገኙት መካከል ናቸው። ጥሩ መቁመናም ላይ ናቸው።

የውድድሩን መረጃዎች በ @tikvahethsport በኩል ይከታተሉ።

ፎቶ፦ Tikvah Ethiopia Sport (Hungary , Budapest)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የሴቶች ማራቶት ሊጠናቀቅ ጥቂት ኪሎሜትር ቀርቶታል።

በውድድሩ ብርቱ ሆነው ወደፊት እገሰሱ ያሉት 3 አትሌቶች ሲሆኑ 3ቱም የሀገራችን ልጆች ናቸው።

በከፍተኛ ጥንካሬ ወደፊት እየመጣች የነበረችው ፀሀይ ገመቹ ውድድሩን አቋርጣለች። ውድድሩን ከማቋረጧ በፊት የህመም ስሜት ተሰምቷት ነበር።

ፀሀይ ውድድሩን እስክታቋርጥ ድረስ በቡድን ስራ ከ3ቱ የሀገሯ ልጆች ጋር ከፍተኛ ስራ ሰርታለች።

የኢትዮጵያ ልጆች በጥሩ የቡድን ስራ ከፊት ሆነው እየተፈራረቁ ውድድሩን እያስኬዱ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቀ 6 ኪሎሜትር ብቻ ቀርቷል። ፉክክሩ የሶስቱ ኢትዮጵያውያን ሆኗል። 🇪🇹 አማኔ በሪሶ 🇪🇹 ያለምዘርፍ የኋላው 🇪🇹 ጎተይቶም ገብረስላሴ አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢትዮጵያ በጀግና ሴት አትሌቶቿ ወርቅ ፣ ብር፣ ነሃስ ማግኘቷ የማይቀር ነው። @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቅ ጥቂት ኪሎሜትር ብቻ ቀርቷል። አንደኛ ደረጃ የያዘችው አትሌት 40 ኪሎ ሜትር አጠናቃለች።

ውድድሩን አማኔ በሪሶ እየመራች ሲሆን ጎተይቶም ገብረስላሴ ሁለተኛ ነች።

1. አማኔ በሪሶ
2. ጎተይቶም ገብረስላሴ

ያለምዘርፍ የኃላው በሞሮኮ አትሌት ተቀድማ 4ኛ ደረጃ ላይ ሆናለች።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

አማኔ በሪሶ #ወርቅ አመጣች ❤️

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር አመጣች❤️

@tikvahethiopia
ያለምዘርፍ የኃላው እስከመጨረሻዎቹ ኪሎሜትሮች ከመሪዎች ተርታ ሆና ብትመጣም 5ኛ ደረጃ ወጥታለች።

ያለምዘርፍ በከፍተኛ ድካምና ህመም ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው።

ያለምዘርፍን የቀደሟት የሞሮኮ እና የእስራኤል አትሌቶች ናቸው።

ፀሀይ ገመቹ ውድድሩን ብታቋርጥም ያበረከተችው የቡድን ስራ የሚይኮራ ነው።

#ጀግኖች

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ያለምዘርፍ የኃላው እስከመጨረሻዎቹ ኪሎሜትሮች ከመሪዎች ተርታ ሆና ብትመጣም 5ኛ ደረጃ ወጥታለች። ያለምዘርፍ በከፍተኛ ድካምና ህመም ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው። ያለምዘርፍን የቀደሟት የሞሮኮ እና የእስራኤል አትሌቶች ናቸው። ፀሀይ ገመቹ ውድድሩን ብታቋርጥም ያበረከተችው የቡድን ስራ የሚይኮራ ነው። #ጀግኖች @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ጀግናዋ አትሌት አማኔ በሪሶ #ወርቅ ፤ ጀግናዋ አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር ለሀገራቸው አስገኝተዋል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኃላ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የተወሰዱ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ።

https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

ፎቶ፦ Tikvah Ethiopia Sport (Hungary , Budapest)

@tikvahethiopia