TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር አብርሃም በላይ ምን አሉ ?

የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በዛሬው እለት የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተረጋገጠ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተለልፈዋል።

በመልዕክታቸው ፤ " የአሸንዳ በዓል ለትግራይና ትግራዎት  ልዩ ትርጉም ያለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላችን ነው። " ብለዋል።

" የዚህ አመት የአሸንዳ በዓል ህዝባችን ከደረሰበት ጉዳት ገና ባላገገመበት ፣ ጥያቄዎቹ በተሟላ መልኩ ባልተመለሱበት ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸውና መደበኛ አኗኗራቸው ባልተመለሱበት ፣ በቀጣዩ ጉዞው በግልፅና ተስፋ በሚሰጥ መልኩ የሚመራውን መሪ እንዲኖረው በሚጠይቅበት ፣ በአጠቃላይ ጥያቄዎቹ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ በአስቸኳይ እንዲመለሱለት በሚጠይቅበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት ቀናት ተገቢ ትኩረት በመስጠት የምንሰራቸው ስራዎች አሉ ያሉት ዶ/ር ኣብርሃም ፤ " የተጀመረው ሰላም ዘላቂ ፍትህ እንዲያስገኝ በማሰብ መተግበር ከሚገባው በላይ ሳይተገበር የዘገየ በህዝባችን ላይ ከባድ ስቃይ በማድረስ ላይ ያለውን ችግር  ለመፍታት በመጠለያ ማእከላት የሚገኘው ህዝባችን ሰብአዊና ህገመንግስታዊ መብቱ በመሆኑ በተደራጀ መልክ ወደ ቄየውና መደበኛ አኗኗሩ እንዲመለስ በትኩረት እየሰራን ነው " ብለዋል።

የአከባቢው ነዋሪም አስተዳዳሪዎቹን ራሱ መርጦ የሚተዳድርበት ሁኔታ ይረጋገጣል ሲሉም አሳውቀዋል።

" በመጠለያ ማእከላት ውስጥ የሚገኝ ህዝባችን ተነግሮ የማያልቅ ለሰሚው ጀሮ የሚያሳምም ፤ ለተመልካች አይን ላለው በሚያስገርም ችግር ውስጥ ይገኛል " ያሉት ዶ/ር አርሃም ፤ " ይህንን ያስተዋሉ አገርንና ህዝባቸው የሚወዱ ወዴት ነው እያመራን ያለነው ? ህዝባችን መቼ ነው ወደ ቄየው የሚመለሰው ? የህዝባችን ስቃይና ሞት መቼ ነው የሚቆመው ? ህዝባችን የሚፈልገውን መሪ መቼ ነው የሚመርጠው ? የትግራይ ግዛት በተሟላ መልኩ መቼ ነው የሚመለሰው ? የሚሉ አሁናዊና ትክክኛ ተገቢ ጥያቄዎች መጠየቃቸው አላቆሙም። " ሲሉ ገልጸዋል።

በመልዕክታቸው ላይ " ለህዝባችንና ለወዳጆቻችን ግልፅ ማድረግ ያሉብን ጉዳዮች " ብለው ተከታዮቹን ዘርዝረዋል።

1. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በሚያከራክሩ የትግራይ ቦታዎች ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄ ካለው በህገ-መንግስት ብቻ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

2. በቅድሚያ የተፈናቀለው ህዝብ ድህንነቱና ሰላሙ በሚያረጋግጥ መንገድ ሙሉ በሙሉ ወደ ቄየው እንዲመለስ ሁሉም የሚመለከታቸው የሁለቱ ክልል አመራሮች ባሉበት የፌደራል መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ ወደ ተግባር ለመቀየር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

3. ህዝቡ በአጭር ጊዜ ወደ ቄየው ተመልሶ ህገ-መንግስታዊ መብቱ በሚያረጋግጥ መንገድ አስተዳደሩ ራሱ እንዲመሰርት ይደረጋል። በአከባቢዎቹ በነበረው ሁኔታ በመጠቀም ተፈጥሮ የቆየው አስተዳደር እንዲፈርስና ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች ውጭ የታጠቀ ሃይል አንዳይኖር ፣ ይህ እንዲፈፀም የፌደራል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፍነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ትእዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

4. ህዝባችን ዝግጁ ሲሆን ጥያቄዎቹ ያለ ማንም ተፅእኖ በህገ-መንግስቱ መሰረት በሪፈረንደም የሚፈልገውን እንዲወስን የሚያስችል ሁኔታ በሂደት እንዲረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል።

5. ከዚህ ውጭ ከባለቤቱ በላይ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳ ፤ ከባለ ጉዳይ በላይ ጉዳይ አለኝ የሚል ፤ ከህግና ስርአት ውጭ በጉልበት ለመንቀሳቀስ የሚሰራ አካል ካለ የፌደራል መንግስት በጀመረው መንገድ ህግና ህገ-መንግስታዊ ሰርአቱ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ ገልጻዋል።

(ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ብር አገኘች !
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ብር አገኘች !
#ኢትዮጵያ

ድርቤ ወልተጂ በ1500 ሜትር ፍፃሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ኬንያዊቷ በአንደኝነት አጠናቃለች።

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

እንኳን ደስ አለን !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ድርቤ ወልተጂ በ1500 ሜትር ፍፃሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። ኬንያዊቷ በአንደኝነት አጠናቃለች። በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ኔዘርላንዳዊ የሆነችው ሲፋን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። እንኳን ደስ አለን ! @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪኳ 100ኛውን ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።

ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ 100ኛ የሆነውን ሜዳሊያ አትሌት ድርቤ ወልተጂ አማካኝነት ማግኘት ችላለች።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ ዛሬ ምሽት በተካሄደው የ1500 ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር በሁለተኛ ደረጃ በማጠናቀቅ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ከዚህ ቀደም በነበሩት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድሮች ኢትዮጵያ 95 ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ አማካኝነት ማግኘት ችላ ነበር።

አሁን እየተደረገ በሚገኘው የቡዳፔሽቱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስካሁን ባለው 1 ወርቅ፣ 2 ብር፣ 2 ነሐስ ማግኘት ችላለች።

via @tikvahethsport 
የመጨረሻው ዙር ተደወለ።

@tikvahethiopia
ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ አስገኘ።
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳሊያ አስገኘ።
#ኢትዮጵያ

በ3000 ሜትር መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለሀገሩ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በውድድሩ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው ከነበሩት አትሌቶች መካከል ሞሮኳዊው ኤል ባካሊ ወርቁን ወስዷል።

@tikvahethiopia