ስለ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል ምን ያህል ያውቃሉ ?
የሻዳይ፣ አሸንድዬ እና ሶለል ባህል ዓመታዊ ክብረ በዓል በአማራ ክልል የሚከበር በዓል ነው።
በዋግ ሹሞች መዲና ሰቆጣና አካባቢዋ ሻደይ፣ በቆቦ አካባቢ ሶለል እና በላስታ እና በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች አሸንድዬ በሚል የሚከበረ የልጅ አገረዶች ጨዋታ በዓል ነው።
በዓላቱ አማራ ክልል ባለብዙ ዘርፍ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት መሆኑን ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባሕላዊ ትውፊቶች ያሉት፣ ሕዝቦች በመተሳሰብ በመፈቃቀር እና በአንድነት የሚኖሩበት መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።
የሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል በዓል የአዲስ አመት መምጣቱን ተከትሎ የሚከበር ብስራት ነው።
ልጃገረዶች ከክረምት መግባት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ውጣ ውረዶችን አልፈው ብሩህ ዘመን እየመጣ መሆኑን የሚያበስሩበት፣ እጮኛ የሚያጩበት፣ ከአቻዎቻቸው ጋር የሚጨፍሩበት እና የሚጫወቱበት ባሕላዊ ጨዋታ ነው።
በተጨማሪ እናቶች እና ህጻናት ያለ ልዩነት ሚሳተፉበትም ነው።
በዓላቱ በህዝባዊ አንድነት የሚያከብሩ፣ የመተሳሰብ፣ የፍቅር እና አብሮ የመኖር እሴትን ለትውልድ ማስተላለፊያ ጠንካራ ገመድ ናቸው።
ለውጭ ሀገራት ብርቅ በመሆኑም የገቢ ምንጭም ነው።
እነዚህ በዓላት በተለይም ባለፉት አመታት በአማራ ክልል በነበረው ጦርነት እና አለመረጋጋት እንዲሁም በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ኮቪድ-19 ምክንያት በሚፈለገው ልክ በተሟላ ሁኔታ አልተከበሩም።
ዘንድሮም በዓሉ በተቃረበበት ወቅት በክልሉ ሰላም ደፍርሶ ፣ ንፁሃን ተገድለው፣ በርካቶች ተጎድተው አጠቃላይ ቀውስ በመፈጠሩ እንዲሁም ክልሉ ባአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር በመውደቁ ድባቡ እንደከዚህ ቀደሙ የደመቀ አይደለም።
በነዚህ በዓላት በተለይ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት በርካታ ቱርስቶች ወደ ክልሉ ይጎርፉ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ ምክንያት እንቅስቃሴ ሁሉ ተዳክሞ ነበር ፤ ከወራት በፊት በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የቱሪስት እንቅስቃሴ ትንሽ የመነቃቃት ነገር ቢፈጠርም ዳግም በፀጥታ ችግር እና ጦርነት ወደ ክልሉ የሚደረግ የቱሪስት እንቅስቃሴ እጅግ ተዳክሟል።
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#BRICS በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የብሪክስ ቡድን መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ተዘግቧል። መሪዎቹ በዚህ ስብሰባቸው ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መላ ሳያበጁ እንደማይቀር እየተነገረ ነው። በስብሰባው…
#Update
በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የBRICS ቡድን መሪዎች ነገ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጉባኤያቸውን ይጀምራሉ።
ለዚሁ ጉባኤ የቻይና ፕሬዜዳንት ሺ ጂንፒንግ ፣ የብራዚል ፕሬዜዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ፣ እንዲሁም የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል።
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬድራ ሞዲ ወደ ደቡብ አፍሪካ እየተጓዙ እንደሚገኙ ታውቋል።
ከብሪክስ / BRICS አባል ሀገራት በተጨማሪ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በስብሰባው ላይ ለመካፈል ወደ ደቡብ አፍሪካ እያቀኑ ናቸው።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚኬል ሳማ ሉኮንዴ ትላንት ምሽት ደቡብ አፍሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።
የጎረቤት ሀገር ኤርትራ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ዛሬ ልዑካቸውን ይዘው ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸውን ከሀገሪቱ የኮሚኒኬሽን ቢሮ የወጣው መረጃ ያሳያል።
ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፤ በፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ ግብዣ በBRICS ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንዳቀኑ የተነገረ ሲሆን በልዑካቸው ውስጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌ ይገኙበታል።
በደቡብ አፍሪካ በሚደረገው የBRICS መሪዎች ጉባኤ ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መፍትሄ ሊያበጁ እንደሚችሉ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።
በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያል ተብሏል። ኢትዮጵያ ቡድኑን ለመቀላቀል ጥያቄ ካቀረቡ ሀገራት አንዷ መሆኑ ይታወቃል።

#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን #በውድድር መሆኑን አስታውቋል።
ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን " በልዩ " ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ መሆኑን አስመልክቶ ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 16፤ 2015 በዋናው ቅጥር ግቢ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር " ሁለት ዓመት ባልሞላ " ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን አስታውቀዋል።
መረጃው የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር እና የኢዜአ " ነው።

ዶ/ር አብርሃም በላይ ምን አሉ ?
የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በዛሬው እለት የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተረጋገጠ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተለልፈዋል።
በመልዕክታቸው ፤ " የአሸንዳ በዓል ለትግራይና ትግራዎት ልዩ ትርጉም ያለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላችን ነው። " ብለዋል።
" የዚህ አመት የአሸንዳ በዓል ህዝባችን ከደረሰበት ጉዳት ገና ባላገገመበት ፣ ጥያቄዎቹ በተሟላ መልኩ ባልተመለሱበት ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸውና መደበኛ አኗኗራቸው ባልተመለሱበት ፣ በቀጣዩ ጉዞው በግልፅና ተስፋ በሚሰጥ መልኩ የሚመራውን መሪ እንዲኖረው በሚጠይቅበት ፣ በአጠቃላይ ጥያቄዎቹ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ በአስቸኳይ እንዲመለሱለት በሚጠይቅበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ቀናት ተገቢ ትኩረት በመስጠት የምንሰራቸው ስራዎች አሉ ያሉት ዶ/ር ኣብርሃም ፤ " የተጀመረው ሰላም ዘላቂ ፍትህ እንዲያስገኝ በማሰብ መተግበር ከሚገባው በላይ ሳይተገበር የዘገየ በህዝባችን ላይ ከባድ ስቃይ በማድረስ ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት በመጠለያ ማእከላት የሚገኘው ህዝባችን ሰብአዊና ህገመንግስታዊ መብቱ በመሆኑ በተደራጀ መልክ ወደ ቄየውና መደበኛ አኗኗሩ እንዲመለስ በትኩረት እየሰራን ነው " ብለዋል።
የአከባቢው ነዋሪም አስተዳዳሪዎቹን ራሱ መርጦ የሚተዳድርበት ሁኔታ ይረጋገጣል ሲሉም አሳውቀዋል።
" በመጠለያ ማእከላት ውስጥ የሚገኝ ህዝባችን ተነግሮ የማያልቅ ለሰሚው ጀሮ የሚያሳምም ፤ ለተመልካች አይን ላለው በሚያስገርም ችግር ውስጥ ይገኛል " ያሉት ዶ/ር አርሃም ፤ " ይህንን ያስተዋሉ አገርንና ህዝባቸው የሚወዱ ወዴት ነው እያመራን ያለነው ? ህዝባችን መቼ ነው ወደ ቄየው የሚመለሰው ? የህዝባችን ስቃይና ሞት መቼ ነው የሚቆመው ? ህዝባችን የሚፈልገውን መሪ መቼ ነው የሚመርጠው ? የትግራይ ግዛት በተሟላ መልኩ መቼ ነው የሚመለሰው ? የሚሉ አሁናዊና ትክክኛ ተገቢ ጥያቄዎች መጠየቃቸው አላቆሙም። " ሲሉ ገልጸዋል።
በመልዕክታቸው ላይ " ለህዝባችንና ለወዳጆቻችን ግልፅ ማድረግ ያሉብን ጉዳዮች " ብለው ተከታዮቹን ዘርዝረዋል።
1. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በሚያከራክሩ የትግራይ ቦታዎች ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄ ካለው በህገ-መንግስት ብቻ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
2. በቅድሚያ የተፈናቀለው ህዝብ ድህንነቱና ሰላሙ በሚያረጋግጥ መንገድ ሙሉ በሙሉ ወደ ቄየው እንዲመለስ ሁሉም የሚመለከታቸው የሁለቱ ክልል አመራሮች ባሉበት የፌደራል መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ ወደ ተግባር ለመቀየር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
3. ህዝቡ በአጭር ጊዜ ወደ ቄየው ተመልሶ ህገ-መንግስታዊ መብቱ በሚያረጋግጥ መንገድ አስተዳደሩ ራሱ እንዲመሰርት ይደረጋል። በአከባቢዎቹ በነበረው ሁኔታ በመጠቀም ተፈጥሮ የቆየው አስተዳደር እንዲፈርስና ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች ውጭ የታጠቀ ሃይል አንዳይኖር ፣ ይህ እንዲፈፀም የፌደራል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፍነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ትእዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
4. ህዝባችን ዝግጁ ሲሆን ጥያቄዎቹ ያለ ማንም ተፅእኖ በህገ-መንግስቱ መሰረት በሪፈረንደም የሚፈልገውን እንዲወስን የሚያስችል ሁኔታ በሂደት እንዲረጋገጥ እንሰራለን ብለዋል።
5. ከዚህ ውጭ ከባለቤቱ በላይ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳ ፤ ከባለ ጉዳይ በላይ ጉዳይ አለኝ የሚል ፤ ከህግና ስርአት ውጭ በጉልበት ለመንቀሳቀስ የሚሰራ አካል ካለ የፌደራል መንግስት በጀመረው መንገድ ህግና ህገ-መንግስታዊ ሰርአቱ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ ገልጻዋል።
(ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል)

#ማስታወሻ ዛሬ በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ልጆች የሚካፈሉባቸው የፍፃሜ ውድድሮች ይደረጋሉ። ዛሬ የሚደረጉት ውድድሮች የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ እና የ3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ናቸው። ውድድሮቹ ምሽት 4:30 እና ምሽት 4:42 ላይ ነው የሚደረጉት። ሀገራችን የሚወክሉ አትሌቶች እነማን ናቸው ? - በ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ (አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ብርቄ ሀየሎም)…
#ኢትዮጵያ
አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና አትሌት ብርቄ ሀየሎም ሀገራችንን የወከሉበት ተጠባቂው የ1500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።
ድል ለሀገራችን !
@tikvahethiopia @tikvahethsport